እንጨቶች ግብአትን በሚጠቀም የምርት ሂደት ውስጥ አልፈው ወደ ምርትነት የሚለወጡ ቁሶች ናቸው፡፡ ለማከማቸት ፣ ለማጓጓዝ ፣ ለማከም እና በመጨረሻም ለማስወገድ የሚያስወጡት ወጪም ከፍ ያለ በመሆኑ አደጋ እንዲጨምር እና የአምራቹ ምስል ጉዳት እንዲጨምርም ያደርጋል፡፡ ለረጅም ጊዜም አካባቢያዊ ወጪና ኪሳራ ሆነው እንዲቆዩ ያደርጋል፡፡ ከእንጨት የተሰሩ የቤት-ዕቃዎች በምርት ሂደቱ ውስጥ ከፍ ያለ  መጠን እና አይነቶች ይሰበሰባሉ፡፡

አይነቶች

እንደ ፋብሪካዎቹ የመሰንጠቂያ መኪና ፣ ከሳንቃ መፍጫ ፣ በእንጨት ከሚሰሩ የቤት-ዕቃዎች ማምረቻ ፋብሪካ የሚወጣው እንጨት የሚለያይ ሆኖ ሊገኝ ይችላል፡፡ ከእነዚህ ሁሉ የተወሰኑት ተመሳሳይነት ያላቸው ሲሆኑ የተወሰኑትም የተለያዩ ናቸው፡፡ በመሆኑም እንደየማምረቻ ፋብሪካዎቹ አይነቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፡፡

ከእንጨት መሰንጠቂያ የሚወጡ

ሀ. ጠፍጣፋ ቅርፅ ያለው

ለ. የተዘረዘረ የእንጨት ቅንጣት

ሐ. ቀጭን ሰሌዳዎች

መ. ከመጋዝ (መሰንጠቂያ) የሚወጣ ብናኝ

ሠ. የእንጨት ፍቅፋቂዎች

ረ. የተሸራረፈ እንጨት

ከተነባበረ ሳንቃ መሰንጠቂያ የሚወጡ

ሀ. ከሰንሰለታዊ መጋዝ የሚወጡ ብናኞች

ለ. ግንድ መቁረጫ

ሐ. የተላጠ ውስጣዊ ቡጥ

መ. ከአረንጓዴ ፎርማይካ ወይም ኮምፔንሳቶ መቁረጫ

ሠ. ከደረቀ ፎርማይካ ወይም ኮምፔንሳቶ መቁረጫ

ረ. የተነባበሩ ሳንቃ ጫፎች

ሰ. የእንጨት ቅርፊቶች

ከእንጨት የተሰሩ የቤት-ዕቃዎች

ሀ. የእንጨት ፍቅፋቂዎች

ለ. ቀጭን ሰሌዳዎች

ሐ. ቅርፊቶች

ሠ. የእንጨት ውስጥ ቡጦች

ረ. ከመጋዝ ወይም ከመሰንጠቂያ የሚወጡ ብናኞች

ሰ. ከስፓንድሬል የሚወጡ ብናኞች

ሸ. ጥቃቅን የሆኑ ሰሌዳዎች

ቅርፊቶች፡ መጠንን እና ዝርያን ላይ ተመስርቶ ከአስር በመቶ እስከ ሃያሁለት በመቶ አጠቃላይ የግንድ ይዘትን ያጠቃልላል፡፡ እንደ ማገዶ ወይም ከእንጨት ዝግጅት በፊት ካልተወገደ ከፍተኛ የሆነ የቆሻሻ ማስወገድ ችግርን ሊያመጣ ይችላል፡፡

ከፍ ያሉ እንጨቶች፡ እንደ ጠፍጣፋ መሸፈኛ ጣራ ፣ ጠርዞች ፣ የኮምፔንሳቶ ቁራጮች ፣ የእንጨት መሰንጠቂያ እና ሰሌዳዎች ቁራጭ ሲሆኑ እንደ ቤት-ዕቃን ውስጣዊ ክፍል መስሪያነት አንዳንዴም የውጪኛውን ክፍል መስሪያ መሆን ይችላሉ፡፡

ከመጋዝ (መሰንጠቂያ) የሚወጣ ብናኝ፡

ሜካኒካላዊ የእንጨት ማቀነባበሪያ ውጤት ሲሆን እጅግ ትንሽ የሆነ የቅንጣት መጠን ያለው በመሆኑ እንደ ምርጥ የውስጥ እቃ መስሪያነት የማገልገል ትኩረት የማግኘት እድሉ ጠባብ ነው፡፡

ጠፍጣፋ ፍቅፋቂዎች፡

ጣውላን ፣ የተነባበረ ሳንቃን እና ቅንጣት የሆነ እንጨትን ከሰሌዳ ለማንሳት በሚደረግ የመጨረሻ ደረጃ የማለስለስ ሂደት የሚፈጠሩ ናቸው፡፡ ለቺፕ ዉድ መስሪያነት እና በተለይም ለጡብ መጥበሻነት እና ማድረቂያነት እጅግ ከፍ ያለ ተመራጭነት አላቸው፡፡

 የዝግጅት ምክንያቶች

በየቤት-ዕቃ መስሪያ ተቋማት በተለያየ ምክንያት ይፈጠራሉ፡፡ ከእነዚህ ምክንያቶች አንዳንዶቹ ሊቀነሱ የሚችሉ ሲሆኑ ሌሎቹ ለማስቀረት የማይቻሉ ናቸው፡፡ ምክንያቶቹም ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፡፡

  1. የተበላሹ ጥሬ-ዕቃዎች
  2. የሰራተኞች ብቃት ማነስ
  3. የማሽነሪዎች ስህተት
  4. የንድፍ ብቁነት ማነስ
  5. ስህተት የበዛበት የማምረት ሂደት
  6. ሊወገዱ የማይችሉ ምክንያቶች

የተበላሹ ጥሬ-ዕቃዎች

የተበላሹ ጥሬ-ዕቃዎች አነስተኛ የጥራት ደረጃ፣ አነስተኛ የሆነ የእቃዎች ጥራት ስሚሰጡ ለእንጨት መባከን ይዳርጋሉ፡፡ በተጨማሪም ብዛት ካላቸው የተበላሹ የቤት-ዕቃዎች እጅግ አነስተኛ ክፍሎች ለምርት ሂደት የሚገቡ ሲሆን የተቀሩትም እንደተወጋጅ ተረፈምርትነት ያገለግላሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የተወሰኑት የእንጨት ብልሽቶች ከውጤታቸው እና መፍትሄያቸው ጋር ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፡፡

የእንጨት ብልሽት          ባህርይ          ውጤት መፍትሄ
ሰማያዊ ውጥረት  ሰማያዊ እና ግራጫ ቀለም በቤት-ዕቃው ቀለም ተደርቦ ወይም ቀይሮ መውጣት  -የእንጨት ቀለም መበላሸት    -ከእይታ እንዲርቅ ማድረግ                                                    
ምልክቶች ወይም ስንጥቆች-በሰሌዳው መጨረሻ ላይ ጀምሮ እስከ እንጨቱ  ቅንጣት የሚዘልቅ ስብራት    -የሰሌዳው ጥንካሬ እና መልክ ላይ   ተፅዕኖ ያሳድራል      ዙሪያው መስራት
የሞተ ወይም የላላ -የጠቆረና በአብዛኛው የላላ የእንጨቱ መልክ መበላሸት፣   -የእንጨቱ መልክ ሲለወጥ፣ ሲወድቅ፣ ጥንካሬውንም ያጣል    በዙሪያው  መስራት

Pin It on Pinterest

Share This