የቤት-ዕቃ ማምረቻ ኩባንያ የቤት-ዕቃን ለማምረት እና ለመሸጥ የሚንቀሳቀስ ተቋም ነው፡፡ በዋናነትም አላማው የደንበኞችን ፍላጎት ማሟላት እና ትርፍ ማስገኘት ነው፡፡ ይህንንም ለማሳካት የቤት-ዕቃው ከተመረተበት ወጪ በሚበልጥ ዋጋ መሸጥ ይኖርበታል፡፡ ደካማ የማምረት አቅም ያላቸው ድርጅቶች ጠንካራ የሽያጭ ክፍል ስላላቸው ብቻ የተሻለ ሽያጭ ሲኖራቸው ብቁ የማምረት አቅም እና ጠንካራ የሽያጭ ክፍል በአንድ ላይ ያካተቱ የቤት-ዕቃ አምራቾች አስተማማኝ የሽያጭ ፍሰት ይኖራቸዋል፡፡

የማምረቻ ክፍሎች

የሳንቃ ቦታ እና ማድረቂያ

የዚህ ጥቅሙ በዋናነት ለጥሬ-ዕቃ ማከማቻነት ነው፡፡ ጣውላ ለቤት-ዕቃ መስሪያነት ጥቅም ላይ ከመዋሉ በፊት መድረቅ ስላለበት ጭምርም ጣውላውን በአየር ለማድረቅም እንጠቀምበታለን፡፡ ለተወሰኑ ዝርያዎች በማሞቂያ የማድረቅ ሂደት በጣውላው ላይ ችግር የሚያመጣ ስለሚሆን የማድረቂያ ቦታው ዋነኛ አገልግሎት በአየር ማድረቅ ይሆናል፡፡

ሸካራ ጫፍ

ይህ የደረቁትን የጣውላ ሰሌዳዎች ወደ ተወሰነ ልኬት ያላቸው ትናንሽ የእንጨት ቁርጥራጮች ይለውጣል፡፡ አንዳንዴ እነዚህ ቁርጥራጮች የአራት ማዕዘን ቅርፅ ሲኖራቸው በማሽኑ ክፍል ውስጥ ሀዲድን ወይም መደገፊያ ቋሚን ለመስራት ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ በሌላ ጊዜም በዘፈቀደ ልኬት ቆራርጦ አንድ ላይ በማጣበቅ የበር እና የግድግዳ ማስዋቢያን ለመስራት ይጠቅማሉ፡፡

ፎርማይካ እና  ሳንቃ ማምረቻ ክፍሎች

በዚህ ክፍል ፎርማይካዎች በተለያየ መጠን ይቆረጣሉ፣ በስላች ይቆረጣሉ ወይም እርስበርስ ይጣበቁና ሳንቃ ይሰራባቸዋል፡፡ ከፎርማይካዎች በተጨማሪ የሳንቃ ክፍል የጣውላ ሰሌዳ እና  ለውስጣዊ ንብሮች የሚያስፈልግ ጠንካራ ሰሌዳ ለመስራት ይጠቅማል፡፡ ለውጫዊ ንብሮች የተለያዩ ፕላስቲኮችም ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ ስያሜያቸውም የፊት ፎርማይካ ይባላል፡፡

የማሽን የመጨረሻ ስራ ክፍል

የመጨረሻ ማሽን ክፍሉ ሻካራ ጫፍ ባለው ማሽን ከሚሰራው ክፍል አራት ማዕዘን ቅርፅ ያላቸው ቁርጥራጮችን እና ክፍልፋዮችን ይጠቀማል፡፡ እነዚህ ምርቶች ለቤት-ዕቃዎች ክፍል በሚያስፈልግ ትክክለኛ ልኬት ይዘጋጃሉ፡፡ እነዚህም ክንዋኔዎች ማቀድን ወይም ትክክለኛ ውፍረቱንና ቅርፁን እንዲይዝ ማድረግ እነዲሁም የሚሰካ ከሆነም በአግባቡ እንዲሰካካ ማድረግ እና ሌሎችም ብዙ ስራዎችን መስራት ነው፡፡ አንዳንዴም አንድ ክፍል ለብቻው በሶስት የተለያዩ ስራዎች በሚሰሩ ማሽኖች ሊሰራ ሲያልፍም አስከ አሰራ አምስት አይነት የተለያዩ ስራዎች የሚሰሩ ማሽኖችን ሊጠቀም ይችላል፡፡ በተለይም የተለምዶ አገልግሎትን የሚሰጡ የቤት-ዕቃዎች በሚሰሩበት የመጨረሻ መልክ መስጫ ማሽን፤ ክፍሉ ትልቁ ክፍል ሲሆን ከፍተኛ ገንዘብ ስራ ላይ እንዲውል ማድረግንም ይጠይቃል፡፡

የማለስለሻ ክፍል

የማለስለሻ ማሽን የጣውላ ሰሌዳን ውፍረት እኩል እንዲሆን ለማድረግ ወይም ወደ ሌላ አይነት ልኬት ለመቁረጥ ስራ ላይ ይውላል፡፡ በዚህ መንገድ ስናየው ማለስለሻ የተለየ የመስሪያ ማሽን አይነት ነው፡፡ የማለስለስ ዋና ጥቅሙ የእንጨቱን ገፅ ለመጨረሻ የምርት ደረጃ ማብቃት ነው፡፡ ተሰርቶ ያለቀን የቤት-ዕቃ ከመገጣጠም ክፍሎቹን ለብቻ አድርጎ ማለስለስ ቀላል ስለሆነ የማለስለሻ ክፍሉ የሳጥን መስሪያ ክፍሉን ቀድሞ ይገኛል፡፡ብዙውን ጊዜ የማለስለሻ ክፍሉ የቤት-ዕቃን የመጨረሻ ደረጃ ስራ መስሪያ ማሽን ክፍል ውስጥ ይገኛል፡፡

የማከማቻ ክፍሎች

የአዘቦት መጠቀሚያ የሆኑ የቤት-እቃዎችን ማምረቻ ፋብሪካ ውስጥ ባሉ ማከማቻዎች ውስጥ በማሽን ተቀናብረው ፣ በማለስለሻም ገፃቸው ተስተካክሎ ለመገጣጠም ዝግጁ የሆኑ የቤት-እቃዎች የሚቀመጡባቸው ክፍሎች ናቸው፡፡

የስፌት ክፍል

የስፌት ክፍል እንደ ስፌት ፋብሪካ ያለ ነው፡፡ ምንም እንኳን አብዛኛውን ጊዜ የስፌት ማሽኑ ኦፕሬተር አንድ የተወሰነ የስፌት አይነት ብቻ የሚሰፋ ቢሆንም ልዩ የሆኑ የስፌት ማሽኖች ፍራሽን ለመጠረዝ ፣ ለመቀጣጠል እና በቻርኔላ ለመዝጋት ስራ ላይ ይውላሉ፡፡ ስራዎችን በተለያዩ የስፌት ቦታዎች ላይ በፍጥነት መፈፀም ተለቅ ያለ ተግዳሮት ሲሆን አንዳንድ ኩባንያዎች አመላላሽ ማሽን ይጠቀማሉ፡፡

ምቾት ባላቸው ጨርቃጨርቆች የተሸፈነ የቤት-እቃን መደገፍ ተከታታይ የሆነ የመሸፈን ሂደትን ለማስኬድ የሚሆን መሰረትን ይሰጣል፡፡ ይህም ማያያዣንና ሌሎች ቁሳቁስን ያካትታል፡፡

የጨርቅ እና ምቾት ያላቸው ቁሶች መሸፈኛ ክፍል

ይህ ማምረቻ ክፍል ጥራዞችን  ከመደገፊያ ክፍል ፣ ሽፋኖችን ከስፌት ክፍል ፣ የስፖንጅ ፍራሽ ፣ ጥጥ እና ሌሎች ቁሳቁስን ከማከማቻ ክፍል ይቀበላል፡፡ እነዚህ ቁሳቁሶችም ሽፋን የተበጀላቸውን የቤት-እቃዎች ለመስራት ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ ብዙውን ጊዜ በጨርቅ እና ምቾት ባላቸው ነገሮች የመሸፈን ስራ በሶስት የተለያዩ ክፍሎች ተከፍሎ ይታያል፡፡ እነዚህም

  • ውስጠኛ ሽፋን መስጠት
  • ውጫዊ ሽፋን መስጠት
  • ትራስ (መከዳ) ማዘጋጀት

Pin It on Pinterest

Share This