ንድፍ

ንደፍ ማለት የአንድን ቁስ መልክ እና አሰራር እንዲሁም ጠቀሜታ ከመገንባቱ ወይም ከመሰራቱ በፊት አስቀድሞ የሚደረግ ዝግጅት ወይም ሥዕላዊ ቀድሞ ማሳያ ነው፡፡ ይህ አይነቱን ቀድሞ የሚደረግ ዝግጅትለውበት መጨመሪያነት የሚሆን እንደ ሀረግ የተያያዘ ነው ተብሎም የሚታወቅ የሰው ልጆች የአዕምሮ እና የእጅ ስራ ውጤት ነው፡፡   ወይም ሥዕላዊ ማሳያ የማዘጋጀት ጥበብ እና አላማእቅድ ወይም ውጥንን መሰረት አድርጎ የቤት-ዕቃን ንድፍ በማውጣት ውስጥ የቤት-ዕቃን ለማዘጋጀት የሚጨበጡ እና የማይጨበጡ ሁኔታዎችን አዋህዶ የመጠቀም ዕውቀት እና ችሎታ ያስፈልጋል፡፡

ተጨባጮቹም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው

 • ቁሶች
 • የፍብረካ ሂደቶች
 • የተፈጥሮ ችሎታ

ተጨባጭ ያልሆኑትም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው

 • ፅንሰ ሃሳብ እና ታሪክ
 • ስነ-ምቾት እና ተቀራራቢነት
 • ስለ ሰውልጆች አካል እና የሰው ልጅ ሁኔታ በቂ የሆነ ዕውቀት
 • የንድፍ ሂደቱ
 • የመሸጥ ጥበብ እና  የማዘጋጀት ዘዴ
 • በሙያው የሰለጠነ ልምምድ

ንድፍ አውጪዎች ወደፊት ያለውን በፊት ካለው ስኬት እና ውድቀት፣ ሂደት እና የሌሎች ከፍተኛ ተስፋ ጋር እያዛመዱ በጊዜው ካለው ሁኔታ ጋር ያላቸውን መረዳት እና አስፈላጊ በሆኑ መሳሪያዎች ሁሉ መታገዝ መገንባት ይችላሉ፡፡ ባለፉ ጎዜያት የተሰሩ ንድፎችን እና ፍብረካዎችን በጥንቃቄ ማየት አስፈላጊ ነው፡፡ ፈጠራ የተሞላበት አጠቃቀም፣ ለመጠቀም የተሰጡ ቁሶችን፣ መገጣጠሚያዎችን እና ስነውበትን በአንድ ላይ አዋቅሮ መጠቀም ወደ አዲስ የቤት-ዕቃ ንድፍ መንፈስን ያነሳሳል፤ ይጠቁማልም፡፡

የቤት-ዕቃ ንድፍ አወጣጥ ሙሉበሙሉ ተቀባይነቱ እና ማስደነቁ ቀጣይነት እንዲኖረው በልምምድ መገኘት ይኖርበታል፡፡ ይሁንና በአንዳንድ ሁኔታ ውስጥ ሊጠና ፣ ለመማር እና ለማስተማር ይቻላል፡፡ ይህ የእውቀት አካል ለህዝብ በመጻሕፍት ፣ በመጽሔቶች ፣ በሙዚየሞች ውስጥ ፣ በማሳያ ሰገነቶች እና በድረ-ገፆች ላይ ክፍት እና በቀላሉ ሊገኝም የሚችል ሆኖ ይገኛል፡፡

የጥናት ዘዴዎች ሰፊ ከሆነው የቤት-ዕቃዎች ንድፍ አወጣጥ ዕውቀት ውስጥ በአንድ ሰው የግል ምርመራ ላይ ትኩረት የሚያደርጉ ናቸው፡፡ መረጃን በመሰብሰብ ፣ በማደራጀት እና በመመርመር ፈጠራ የተሞላበት ስራን ለመስራት የሚሆን መድረክ ማዘጋጀት ይቻላል፡፡ ጥናት እና ምርምር አሳቦችን ለማሳየት እና በቤት-ዕቃዎች ንድፍ አወጣጥ ውስጥ አንድ የተወሰነ ዕውቀትን ይበልጥ ግልፅ እንዲሆኑ በማድረግ ያግዛል፡፡ ንድፍ አውጪዎችን እና ፈብራኪዎችን ከቁሳዊ ባህሪያት ፣ የፍብረካ ሂደቶች ፣ የመሸጥ ስልት እና ቀልጣፋ የንግድ ስራ ሙያዊ የማቀድ ስራ እንዲረዱ እና በተረዱት መጠንም ለተሻለ ለውጥ እንዲተጉ ያደርጋል፡፡ 

ለሰው ልጆች የሚሆን ተስማሚ ስራን ለመስራት ሰዎች ካጠኗቸው ሰፊ ጥናቶች ለመረዳት እንደሚቻለው የጥናት አካባቢዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማካተት ይኖርባቸዋል፡፡

 • የሰዎች የመረዳት ችሎታና የባሕርይ ጥናት
 • ሕብረተሰባዊ ምርመራ
 • የሰዎች የጥራት ልኬት

ጭብጥ ዕይታ

ካርታ ፣ መስመር ቀመር ፣ ቬነን ዲያግራም እና ቻርቶች የቤት-ዕቃን ንድፍ ጥናት በሥዕላዊ መግለጫ ለማሳየት የሚጠቅሙ የተለመዱ ዘዴዎች ናቸው፡፡ በቅርብ ጊዜዎች የጭብጥ ዕይታዎች በተለያዩ አቅጣጫዎች መዳበርን አሳይቷል፡፡ እነዚህም

 • በተግባር ባልታየ ባልተፈተነ ሃሳብ
 • በአሰራር ጥበብ
 • አዲስ በሆኑ የሙያዊ ስልጣኔ አካባቢዎች

አንድ ግለሰብ ከቤት-ዕቃ ንድፍ ጋር በተያያዘ መልኩ የተዋቀረን መረጃ እንዴት ሊያየው ወይም እንደ መሪ ካርታ ሊጠቀመው እነደሚችል ስናመዛዝን፤ የማጣበቂያዎችን አንፃራዊ የማጣበቅ አቅም ወይም የቤት-ዕቃዎቹን ለማምረት የሚያስፈልገውን አጠቃላይ ወጪ ለመወዳደር እነደሚችል ለማየት እንችላለን፡፡ ምንም እንኳን በአሰራር መንገዱ የቤት-ዕቃን ንድፍ ማውጣት መሰብሰብ ፣ ማደራጀት ፣ መረጃን ማቀናበር የሚያካትት ሲሆን በአብዛኛው ሊሰበሰብ ፣ በቅደም ተከተል ሊቀመጥ ፣ በመስተፃምር ሊቀመጥ እና በተለያዩ ንድፋዊ ብልሃቶች ሊቀርቡ ይችላሉ፡፡ እነዚህም ብልሃቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው፡፡

 • ቬነን ዲያግራም
 • የመግለጫ ገበታ
 • ባለሁለት እና ባለ አራት ምህዋር
 • በመጀመሪያ ፊደል ቅደም ተከተል በማስቀመጥ

ቬነን ዲያግራም

ቬነን ዲያግራም በታህታይ ስብስብ መካከል ያለውን ተዛምዶ በተራ  የተቀራረቡ ከርባዊ ቅርፆች ተጠቅሞ ይገልፃል፡፡ ይህ መግለጫ ለታህታይ ስብስብ መዋቅር በመጠን ፣ በአቀማመጥ ፣ በከርባዊ ቅርፆች ጠፈራዊ ዝምድና መዋቅርን ወስኖ ይሰራል፡፡

ባለሁለት እና ባለ አራት ምህዋር

በመጠንም ሆነ በአይነት ያለውን ዝምድና በአጠቃላይ ወይም በተለየ ዝምድና የሚያሳይ ነው፡፡ ለዚህም ባለሁለት እና ባለ አራት ምህዋር ምሳሌ ሊሆን የሚችል ቁጥርና ውድ የሚባሉ የቤት-ዕቃዎቸች ክምችት አሉት፡፡

በመጀመሪያ ፊደል ቅደም ተከተል በማስቀመጥ

ይህም የአንድ የእውቀት ቃላት ወይም የድርጊት ስሞች ስብስብ ነው፡፡ የቤት-ዕቃ ንድፍ ስነ-ስርአት ከዚህ በታች ከተዘረዘሩትም ተጨማሪ ርእሶችን ያካትታል

 • ሙያዊ
 • ገላጭ
 • ሂደት
 • ህብረተሰባዊ ጥቅም
 • በተግባር ያልታየ እና ያልተፈተነ

Pin It on Pinterest

Share This