የሚሰኩ መጋጠሚያዎች

የሚሰኩ መጋጠሚያዎች በቤት-ዕቃ መቃን ስራ ውስጥ ለመዋቅር እና ክብደት ተሸካሚ መገጣጠሚያዎች እና ለክፍል አካላት አቀማመጥ ማስተካከያነት በስፋት ያገለግላሉ፡፡ በመሰኪያ የተሰሩ መገጣጠሚያዎች ለወጪ፣ጉብጠታዊ መቆረጥ እና ጥምዛዜ ኃይል የተጋለጡ ናቸው፡፡ ቢሆንም፤ በመገጣጠሚያዎች ላይ ጥቅም ላይ የሚውሉ የሚሰኩ መጋጠሚያዎች ለወጪ እና ጥምዛዜ ኃይል የተጋለጡ ናቸው፡፡ከዚህ በታች ባሉት ክፍሎች፤ ከብዛት ጋር የተያያዘ መረጃ ከወጪ እና ከመቀርጠፍ የመቋቋም ብርታት ጋር በተያያዘ መልኩ ይቀርባል፡፡

የአሰራር ልምምድ

በድንገት የሚነሱ ግፊቶች (የወጪ ኃይል) የመቋቋም ችሎታ ተነባበሮ በተሰራው ጣውላ እና የቤት-ዕቃው በተሰራበት የመገጣጠም ሁኔታ እና በመገጣጠሚያዎቹ ጥራት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ መሰኪያዎች ቀጥ ባለ ቅንጣት የተሰሩ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡  ጆሜትሪቸውም ክብ ከመሆን ይልቅ ሞላላ ቅርፅ ያለው ነው፡፡ ከፍተኛ እና ዝቅተኛ የክበብ አጋማሽ መስመራቸውን ለመለካት ማይክሮ ሜትር መጠቀም የግድ ይሆናል፡፡ ጥሩ የሚባለውን መሰኪያ ለመጠቀም ከተለያዩ አምራቾች ናሙና ወስዶ ማወዳደር ይመከራል፡፡ ድፍን የእንጨቱ መቆረጥን የመቋቋም አቅም ትርጉም ባለው ሁኔታ የመሰኪያውን የወጪ ኃይል የመቋቋም አቅም ይጨምራል፡፡ ከዚህም በመነሳት መሰኪያዎችን ከምንጠቀመው ጣውላ ወይም በአንድ ከተዘጋጀ ሰሌዳ ጋር እንዲጣጣም አድርጎ ከፍተኛ የሆነ መቆረጥን የመቋቋም አቅም ካላቸው የእንጨት አይነቶች ጋር በመጠቀም ጠንቃቃነት እና አርቆ አሳቢነትን አካቶ ማዘጋጀት ይቻላል፡፡

ምንም አይነት ክፍተት የሌለው መጋጠሚያ አመቺ እና ስኬታማ ቢሆንም ለመገጣጠም ባለው ውስብስብነት የተነሳ እምብዛም ጥቅም ላይ ሲውል አይታይም፡፡ በዚህ ውስጥ ሊኖር የሚችለውን ለመቀበል የሚቻል እጅግ ጥቂት ልዩነት በሙከራ እና ስህተት ሂደት ማግኘት ይቻላል፡፡ የዋናው አካል አሰራር  የተሸነሸኑ እና የተከፋፈሉ አካላትን ማካተት በጠርዝ መጋጠሚያዎች ላይ የሚኖረውን ክፍተት ይገድባል፡፡  ከፍተኛ የሆነ ውስጣዊ ትስስር ጥንካሬ ያላቸውን ቁሶች መጠቀም ይህን ችግር ለመፍታት ያግዛል፡፡ በመሰኪያ መገጣጠሚያ ስራ ላይ ጥቅም ላይ የሚውለው ማጣበቂያ መገጣጠሙ ላይ ደካማ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡ የፖሊቪንዪል ማጣበቂያን በተመለከተ ጠጣር ይዞታው በጨመረ ቁጥር መጋጠሚያውም በዚያው መጠን ይጠነክራል፡፡ ይህም ማለት ስድሳ በመቶ ጠጣር የሆነው የፖሊቪንዪል ማጣበቂያ አርባ በመቶ ጠጣር ካለው የፖሊቪንዪል ማጣበቂያ የበለጠ የማጣበቅ አቅም ይኖረዋል፡፡ ለማጣበቅ ከተጠቀምንበት የማጣበቂያ አይነት ይልቅም የማጣበቂያው ብዛት እና ስርጭት ይበልጥ አስፈላጊነት አለው፡፡ የሚሰኩ መጋጠሚያዎች ማጣበቂያን መሰረት ያደረጉ መጋጠሚያዎች ናቸው፡፡ ይህም ማለት ለጥንካሬያቸው በማጣበቂያው ላይ ይተማመናሉ፡፡ ከፍተኛ ለሆነ ጥንካሬ እና ዘላቂነት የመሰኪያው ቀዳዳዎች ግድግዳ በሚገባ በማጣበቂያው መሸፈናቸውን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡ ሌሎች ልምምዶች ደካማ ወደሆነ መጋጠሚያ የሚያመሩ ይሆናሉ፡፡ ጥንካሬውና ጤናማነቱ ቀጣይነት ያለው መቃን ለማዘጋጀት እንደዚህ ያለውን የማጣበቅ ልምምድ መከተል ያስፈልጋል፡፡ በጠርዞች አካባቢ ትርፍ ማጣበቂያን መጠቀም ይበልጥ የተሻለ ውጤትን ለማግኘት ይረዳል፡፡ ይህ ትርፍ ማጣበቂያ አካባቢው ላይ ባለው ንብርብር፤ መሰረታዊ ቁሱን በማጉላት ያገለግላል፡፡ በተጨማሪም ትርፍ የሆነ ማጣበቂያን መጠቀም ቁሱን በሚገባ ስለሚጠግን በዚህ መሰረታዊ ቁስ ጠርዝ አካባቢ ያሉትን ስንጥቆችን ለማከም ይረዳል፡፡

ጎናዊ የመያዝ አቅም

በእነዚህ አይነት መቃኖች ላይ የሚያርፈው ሸክም ከባድ በመሆኑ ከጥድ የተሰሩ እና የተዋቀረ ማረፊያ ሰሌዳ ያላቸው የሚሰኩ መገጣጠሚያዎች ጎናዊ ጥንካሬ ትኩረት ሊሰጠው እና ከግምት ሊገባ የሚገባው ነው፡፡ እነዚህ መጋጠሚያዎችም ከአግድም ሰሌዳ ላይ እንደ ጉቶ የሚሆኑ ወደ ፊት ወጥተው የሚታዩ መጋጠሚያዎች፣ ከላይ ከሚለብስ ሰሌዳ ላይ የሚንጠለጠሉ መልሶ መግጠሚያዎች፣ከሰሌዳ ላይ ወደ ሀዲድ መጋጠሚያ ከዚሁ በመቀጠልም ወደ ፊት እና ወደ ኃላ ካሉ ቋሚ መጋጠሚያዎች ላይ የሚሰኩ ናቸው፡፡  በብልሃት ሲታይ ተሰኪዎችን ከውስጣዊ ትስስር፣ ከሀዲድ ስፋት፣ ከሀዲድ አቀማማጥ (ጠርዝ ወይም ጠፍጣፋ ገፅ) እና ከመሳሰሉት ጋር የሚያያዝ በመሆኑ ከእነዚህ ጋር በማነፃፀር የሚገባውን አይነት መርጦ መጠቀም ይቻላል፡፡

የተሰኪዎች ጎናዊ የመያዝ አቅም የተውጣጣባቸው መለኪያዎች እጅግ የሚቀያየሩ እና ከላይ ከተዘረዘሩት ጋር የግድ የተዛመዱ ናቸው፡፡ እንደ ውጤትም  ጥንካሬያቸውን ለመለካት የተሰሩ አልነበሩም በመሆኑም የጎናዊ የመሸከም አቅምን በተመለከተ በቂ መረጃ ይሰጣል፡፡ በዚህም የጎናዊ ክብደቶችን የመቃን መጋጠሚያ በሚገባ ለማዘጋጀት ያግዛል፡፡

ሁለት አይነት ጎናዊ የመያዝ አቅሞች ከግምት ውስጥ መግባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጎናዊ ጠርዝ የመሸከም አቅም እና ጎናዊ የፊት ገፅን የመሸከም አቅም ናቸው፡፡ ከጥድ እና ከተለያዩ ሰሌዳዎች  የተዘጋጁ ጎናዊ ገፆች እና ጠርዞች የመሸከም አቅማቸውም እንደዚያው ይለያያል፡፡ በአጠቃላይ ጎናዊ ጥንካሬያቸው በጥራት ሙከራ የሚረጋገጥ ካልሆነ በቀር ጥሩ የንድፍ ልምምድ መጋጠሚያዎች ሊኖራቸው ከሚገባው ጥንካሬ እጅግ ጥቂቱን ያህል ሊኖራቸው እንደሚገባ ይገለፃል፡፡

የመጋጠሚያዎችን ጎናዊ ገፅ ሸክም የመቋቋም አቅም ንድፍ መግለጫ እንዲሆን የላይኛው ሀዲድ ከጀርባው ቋሚ ጋር የሚኖረውን ግፊት መገመት የሚረዳ ነው፡፡ አለም አቀፋዊ መመሪያዎች 70 ኪሎግራም ያህል የጀርባ መቃን ሸክም ላለበት የዚህን ሶስት እጥፍ ያክል በሚሆን ሸክም ተፈትሾ ማለፍ ይኖርበታል፡፡

በአንዳንድ አጋጣሚዎች መጋጠሚያዎች በአንዳንድ ሰሌዳዎች ላይ አጥጋቢ ውጤት ሊሰጡ በሌሎች ሰሌዳዎች ላይ ግን ይህን አጥጋቢ ውጤት ላናገኝ እንችላለን፡፡ ጥሩ የንድፍ ሂደቶች በዚሁ ምክንያት መጋጠሚያዎች ጥንካሬያቸውን ለመጨመር ሲባል ከሌሎች ማጥበቂያዎች ወይም መገንቢያዎች ጋር ተደባልቀው ሊሰሩ ይገባል፡፡

ጥምዞሽ

የሚሰኩ መጋጠሚያዎች ጥምዞሽን የመቋቋም አቅም ሌላው በጥድ እና ተዋቅረው በተሰሩ ሰሌዳዎች የተሰሩ የቤት-ዕቃዎችን መቃን ንድፍ ስራ ላይ ትኩረት ሊሰጠው የሚያስፈልግ ጉዳይ ነው፡፡ በተለይም የሶፋ መቃን የመቀመጫው ክፍል ላይ የሚገኙ ሀዲዶች ለጥምዞሽ ግፊት የተጋለጡ ይሆናሉ፡፡ ለምሳሌ የፊት ገፃቸው ቀጥተኛ በሆኑ ሶፋዎች የጎን ሀዲዶች መሰረታዊ ለሆኑ የጥምዞሽ ግፊቶች የተጋለጡ ይሆናሉ፡፡ ወደውስጥ እና ወደውጪ የሚገፉ ግፊቶች በጎናዊ ሀዲዶች መደገፊያ በእጀታው የላይኛው ብቻ ሳይሆን በጎናዊ ሀዲዶች ላይ ግፊትን ያሳድራሉ፡፡ እግሮች ከጎናዊ ሀዲዶች ጋር ተገጣጥመው በሚሰሩበት ጊዜ፤ሶፋዎች ከአንድ ቦታ ወደሌላ ወደ ጎን አቅጣጫ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ጥምዝ ግፊቶች በሀዲዶች ላይ ይተገበራሉ፡፡

Pin It on Pinterest

Share This