ዛሬ የምንጠቀማቸው የምግብ ማብሰያ ክፍሎች የኤሌክትሪክ ምድጃን፣ማቀዝቀዣዎችን ወይም ፍሪጆችን እንዲሁም የምግብ ማብሰያ ክፍል መደርደሪያዎችን ዘመኑ በሚመጥን ዲዛይን አካተው ይዘዋል።በዋናነት የምግብ ማብሰያችንን ምግብን ለማብሰል፣ የኩሽና እቃዎችን ለመያዝ፣ እንዲሁም የምግብ ማብሰያ እቃዎችን ለማፅዳት እንጠቀምበታለን።የምግብ ማብሰያችንን ለመዝናኛ  እና እንደ ቁርስ ያሉ ቀላል ምግቦችን ለመመገብ እንጠቀምበታለን።

በሬስቶራንቶች፣ በካፍቴሪያዎች፣በሆቴሎች፣በሆስፒታሎች፣ በትምህርት ቤቶች በአጠቃላይ በስራ ቦታዎች የሚሰሩ የምግብ ማብሰያ ክፍሎች ከመኖሪያ ቤት የምግብ ማብሰያ ክፍሎች ይልቅ ሰፊ እና ብዙ ቁሶችን እና ትልልቅ ቁሶችን  መያዝ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

በዓለማችን ላይ በአደጉት አገራት በጤና ደንቦች ላይ ተመስርቶ የምግብ ማብሰያ ክፍሎች ለጤና ችግር ማጋለጣቸውን እና አለማጋለጣቸውን በየወቅቱ የሚገመግም ቡድን አለ። ቡድኑ የምግብ ማብሰያ ክፍሉ ተገቢዉን ጥንቃቄ እና ንፅህና አሟልቶ ካልተገኘ አገልግሎት መስጠቱ እንዲቆም ይደረጋል። በአገራችን ኢትዮጵያ  የማብሰያ ቦታችንን በአግባቡ ስናፀዳ እራሱ አይታይም።

የምግብ ማብሰያ ክፍልን በታሪክ ስንቃኝ ባህላዊ ምድጃን እናስባለን። በአለማችን ደረጃ፣ ከአስራ ስምንተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ በፊት ምግብን ለማብሰል እንጨትን እና የድንጋይ ምድጃን ይጠቀሙ ነበር።ይህም የምግብ አበሳሰል ስርአት በሃገራችን በገጠራማው ክፍል እስከ ዛሬ ድረስ የተለመድ ነው።

በሃገረ ግሪክ ከአስራ ስምንተኛው መቶ ክፍለ  ዘመን በፊት በኢኮኖሚ የደከሙ ሰዎች የምግብ ማብሰያ ክፍላቸውን አንድ ላይ ከሳሎናቸው ጋር ሲሰሩ፤ በአንፃሩ ደግሞ ባለፀጋ የሚባሉት ሰዎች ደግሞ የምግብ ማብሰያ ክፍላቸውን ከሻወር ቤት ጎን ለጎን ይሰራሉ፣ ምክንያታቸው እና የሚገርመው ደግሞ የምግብ ማብሰያ ክፍሉን ሙቀት እና የሻወር ቤቱን ቅዝቃዜ ለማመጣጠን ነበር።

እንዲሁም ከምግብ ማብሰያ ክፍሉ ጎን ላይ ምግብን ለማስቀመጥ የሚሆን ክፍል ይጠቀሙ ነበር።በሮማን ግዛት ዉስጥ ይኖሩ የነበሩ ማህበረሰቦችም የግል የሆነ የምግብ ማብሰያ ክፍል አልነበራቸው።ሮማውያን ምግብ በግል ከማብሰል ይልቅ በቡድን በትልቅ አዳራሽ ውስጥ ማብሰልን ይመርጡ እንደነበር ታሪክ ያስረዳል።

ከክፍሉ በሚወጣው ጭስ ላለመረበሽ እና ለጤናቸው ስጋት ላለመሆን ባለ ሃብት የነበሩ ሮማውያን ከቤታቸው ጎን  የምግብ ማብሰያቸውን ክፍል ይሰሩ ነበር ።  እንዲሁም የምግብ ማብሰያቸውን ምድጃ ከክፍሉ መሃከል ላይ ያደርጉ ነበር።በደንብ በአለም ላይ የታወቀው የመጀመሪያው ምድጃ ከሶስተኛ እስከ ስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወይም ኮፉን እየተባለ በሚጠራው ጊዜ በጃፓን እንደተሰራ ይነገራል።በወቅቱ ይህ ምድጃ ካማዶ የሚል ስያሜ ሲያገኝ የተሰራውም ከሸክላ እና   ከአርማታ እንደተሰራ ይነግራል።

በእንጨት እና በከሰል ግለው ወይም ተሟሽተዉ የሚሰሩት እነዚህ ጥንታዊ ምድጃዎች ከፊት እና ከላይ  የማብሰያ እቃን ለማንጠልጠል ቀዳዳ ነበራቸው።እንደ ሩዝ ያሉ ቀላል ምግቦች ለማብሰል ተመራጭ የሆነው ካማዶ ምድጃ ዘመን ተሻጋሪ ሆኖ ለትውልድ አገልግሏል።በአውሮፓ እስከ መካከለኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ የምግብ ማብሰያ ክፍላቸው  ጨለማ፣ጪሳማ እና የሚረብሽ ክፍል ነበር፣ በዚህ ምክንያት የምግብ ማብሰያ ክፍላቸውን ጪሳማው ክፍል ብለው ይጠሩታል።አሜሪካውያን በእንግሊዝያውን ቅኝ ግዛት በወደቁበት ጊዜ፣ የምግብ ማብሰያ ክፍላቸው ለብቻው ከመመገቢያ ክፍላቸው ጎን ላይ ይሰሩ ነበር።

የቴክኖሎጅ እድገት እና የምግብ ማብሰያ ክፍል ታሪክ

በኢንዱስትሪያሊዝም ጊዜ የቴክኖሎጅ እድገት በምግብ ማብሰያ ክፍል ዲዛይን ላይ ይህ ነው የማይባል ከፍተኛ የሆነ ተፅእኖ አሳድሩል። እሳትን አፍኖ የሚይዝ የብረት ምድጃ በወቅቱ ተመራጭ ምድጃ ነበር።በ1740 ቀድም ብሎ ዲዛይን የተደረገዉ እና ሙከራ ላይ ውሎ የነበረው የፍራንክሊን ምድጃ እና የምግብ ማብሰያ ክፍል ረዘም ላለ ጊዜ ሳያገለግል ከጥቅም ውጭ ሆኗል።

በ1800 በቤንጃሚን ቶምሰን በሃገር እንግሊዝ ዲዛይን የተደረገው ራምፎርድ ምድጃ፤ ቀደምት ከነበሩት ምድጃዎች ምግብ ለማብሰል የተሻሉ ነበሩ።ራምፎርድ ምድጃ አንድ የእሳት ማቀጣጠያ የነበረው ሲሆን አንዱ የእሳት ማቀጣጠያ በብዙ ድስቶች ማብሰል እንድንችል ያግዝ ነበር።

ምግብን በጋዝ እና በኤሌክትሪክ የማብሰል ልማድ በሃያኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንደተጀመረ መዛግብት ይናገራሉ።እንዲሁም በዚሁ ክፍለ ዘመን የምግብ ማብሰያ ክፍል ፕሮፌዥናልዝም በሚል መርህ መሰረት የምግብ ማብሰያ ዲዛይን ፅንሰ ሃሳብ ተጀመረ።

የእንጀራ ድንጋይ በፍራንክፈርት ውስጥ በማርጋሬት ሽቴ-ሊሆትዝኪ የተቀየሰ የምግብ ማብሰያ ክፍል ነበር ፡፡ የወንዶች ደመወዝ ብዙውን ጊዜ በቂ ስላልነበረ  ሴቶች በቤተሰብ ውስጥ ህልውናን ለማረጋገጥ በፋብሪካዎች ውስጥ በተደጋጋሚ ይሠሩ ነበር ፡፡በ 1926 የተሠራው ይህ የምግብ ማብሰያ ክፍል 1.9 ሜትር በ 3.4 ሜትር ( በመደበኛ ስሌት 6 ጫማ ከ2 ኢንች እና 11 ጫማ ከ2 ኢንች ) ይለካል።ይህ የምግብ ማብሰያ ክፍል የተገነባው ለሁለት ዓላማዎች ነበር።  አንደኛ የምግብ ማብሰያ ሰዓትን ለመቀነስ እና ለብቻ የሚሰሩ የምግብ ማብሰያ ቤቶችን የመገንቢያ ወጪን ለመቀነስ  ነበር፡፡

ዘመናዊ የምግብ ማብሰያ ክፍሎች

በአንፃሩ ደግሞ ዛሬ የሚገነቡት የምግብ ማብሰያ ክፍሎች በቀላሉ ለማጽዳት ይመች ዘንድ ወለላቸው ሴራሚክ ሲሆን ፣ የእቃ መደርደሪያ፣ ዘመናዊ ምድጃ፣ ማቀዝቀዣ እና ሌሎችንም አካቶ ይዛዋል።በሆቴሎች ፣ በሆስፒታሎች ፣ በትምህርት እና በሥራ ቦታ ተቋማት ፣ በሠራዊት ሰፈሮች እና በመሳሰሉት ተቋማት ውስጥ የሚገኙት ምግብ ቤት እና የመመገቢያ ማእድ ቤቶች በአጠቃላይ (ባደጉ ሀገሮች) ለህዝብ ጤና ህጎች ተገዢ ናቸው ፡፡

በየጊዜው በሕዝብ ጤና ጥበቃ ባለሥልጣኖች ቁጥጥር ይደረግባቸዋል እንዲሁም በሕግ የተደነገጉትን የንፅህና አጠባበቅ መስፈርቶች ካላሟሉ ለመዝጋት ይገደዳሉ ፡፡ካንቴንስ ማእድ ቤቶች (እና የቤተመንግስት ማእድ ቤቶች) ብዙውን ጊዜ በመጀመሪያ አዲስ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ የዋሉባቸው ቦታዎች ነበሩ ፡፡ ለምሳሌ ፣ የቤንጃሚን ቶምፕሰን ‹የኃይል ቆጣቢ ምድጃ› በ 19 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ሙሉ ድስቶችን ለማሞቅ አንድ የእሳት ምድጃን ይጠቀም ነበር።

የምግብ ማብሰያ እና የመመገቢያ ክፍል ጠረጴዛዎች 

የመመገቢያ ወይም የምግብ ማብሰያ ክፍል ጠረጴዛ ሁሉም የቤተሰብ አባላት ምግብ ለመመገብ  የሚሰባሰብበት አስፈላጊ ክፍል ነው ፡፡  የመመገቢያ ክፍል ጠረጴዛዎች ከእንጨት  ጠረጴዛዎች እስከ ዘመናዊ እስከሆኑት የመስታወት እና የብረት ጠረጴዛዎች ድረስ  የተለያየ ስሪት እና  የአሰራር ዘይቤ ሲኖራቸው በአንፃሩም  ክብ ጠረጴዛ ለአንድ ትልቅ  የመመገቢያ ክፍል ተመራጭ እና ተስማሚ ነው ፡፡

አነስተኛ ጠረጴዛዎች በተለይም ውስን ቦታ ሲኖርዎት እና አብዛኛውን ጊዜ አንድ ወይም ሁለት ሰዎች ብቻ  የሚጠቀሙበት ከሆነ ተመራጭ ናቸው።የምግብ ማብሰያ ክፍል በጣም ጥቅም ላይ ከሚውሉት የቤቱ ክፍል አንዱ ስለሆነ ሁሉም ሰው ተግቢውን አይነት ክፍል ሊኖረው  ይገባል ፣ ክፍሉ ማራኪ እና ሳቢ ከሆነ በክፍሉ ውስጥ የምናሳልፈው ጊዜ  ጥሩ ይሆናል ፡፡በምግብ ማብሰያ ክፍላችን ውስጥ ከምንጠቀማቸው የፈርኒቸር ውጤቶች  በተጨማሪ ዘመናዊ  የሆነ እና የተዋቀረ የክፍል ዲዛይን ያስፈልገናል ፡፡

ክፍሉን ንፁህ እና ለእይታ ቀላል ማድረግ

የምግብ ማብሰያ ክፍላችንን በየጊዜው የማናጸዳው ከሆነ ለበሽታ የመጋለጥ አድላችን በጣም ክፍ ያለ ነው፤ምክንያቱም የምግብ ማብሰያ ክፍላችን በየእለቱ ምግብ ለማብሰል ስለምንጠቀምበት ክፍሉ የተለያዩ እንደ ባክተሪያ እና ፈንገስ ያሉ በሽታ አምጭ ህዋሳት የመሳብ አቅሙ ከፍተኛ ይሆናል።እንዲሁም የምግብ ማብሰያ ክፍላችን ለእይታ ቀላል ማድረግ አለብን ይህም ማለት ለኩሽና ቤት የሚሆኑ መደርደሪያዎችን በመጠቀም የምንጠቀምባቸውን እቃዎች መሸከፍ ተገቢ ነው።

መስታዎቶችን መጠቀም

የምግብ ማብሰያ ክፍላችን በጣም ጠባብ ከሆነብን የክፍላችንን መስኮት ሰፊ እና ሙሉ በሙሉ መስታወት ማድረግ ክፍሉ ሰፊ እንደሆነ ይሰማናል።

ውብ ቀለሞችን መጠቀም

የክፍሉን ቀለም በውስጡ ከያዛቸው ቁሶች ጋር ተመሳሳይ ቀለም መጠቀም ለእይታ ጥሩ ነው።

Pin It on Pinterest