በዚህ ፅሁፍ ዉስጥ ክፍላችንን በጥሩ ሁኔታ ዲዛይን ለማድረግ የሚረዱን ከጥቃቅን እስከ ዋና ዋና ሃሳቦች እናያለን።

ክፍላችንን ዲዛይን የማድረግ እቅድ

ክፍላችንን ዲዛይን ለማድረግ ስናስብ በመጀመሪያ ክፍሉን ለምን አገልግሎት እንደምንጠቀመው ግልፅ የሆነ እቅድ ማስቀመጥ። ከዚህ በታች በክፍላችን አይነት ላይ ተመስርተን እንዴት ክፍላችንን ዲዛይን ማድረግ እንዳለብን እናያለን።  

እቅድ 

ክፍላችንን ዲዛይን ከማድረጋችን በፊት ክፍላችንን እንዴት እንደምንጠቀመው ማሰብ ይህም ማለት ያለን ቦታ ታሳቢ ማድረግ እንዲሁም ምን ያህል ሰው ክፍሉን እንደሚጠቅምበት ግንዛቤ ዉስጥ ማስገባት አስፈላጊ ነው።

መንደፍ

በተለምዶ ለቤታችን ይሆናሉ የምንላቸውን ፈርኒቸሮ ከመግዛታችን በፊት በወረቀት ላይ የቤታችን ዲዛይን መንደፍ አልያም በወለል ንድፍ (ፍሎር ፕላን) መተግበሪያን ተጠቅመን የክፍላችችን ዲዛይን በቀላሉ መንደፍ እንችላለን። ስለዚህ ፈርኒቸሮቻችንን ከመግዛታችን በፊት ቀደም ሲል ካስቀመጥናቸው ንድፎች ጋር ተስማሚ መሆናቸውን ማረጋገጥ።

                             የሳሎን ዲዛይን

ሶፍ አቀማመጥ

ሶፋችን ከክፍሉ ረዥም ግድግዳ ፊት ለፊት ማስቀመጥ ምክንያቱም ሶፋችንን አጭር እርዝማኔ ካለው ግድግዳ ፊት ለፊት ማስቀመጥ የክፍላችንን ዉበት ያሳጣል።

ወንበር

ወንበራችን በክፍላችንን ዉስጥ ከቴሌቪዥናችን ፊት ለፊት ቢሆን ይመከራል። እንዲሁም የወገብ ህመም ላለባቸው ሰዎች ምቹ  እና ክፍታ ያለው ወንበር ማካተት እና አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ማድረግ።

በቂ የመንቀሳቀሻ ቦታ መስጠት

በምንጥቀምባቸው ፈርኒቸሮ መካከል በቂ የሆነ የመንቀሳቀሻ ቦታ መተው ቢያንስ በቁሶቹ መካከል ያለውን ቦታ ሶስት ኢንች ማድረግ ተገቢ ነው።

ተፈጥሮአዊ ነገሮችን መጠቀም

በሳሎናችን ዉስጥ ተፈጥሮአዊ ነገሮችን መጠቀም ክፍላችንን የበለጠ ውበት እንዲኖረው ያደርጋል።

                          የመመገቢያ ክፍል እና የኩሽና ዲዛይን

ምንም እንኳን የመመገቢያ ክፍልን ዲዛይን ማድረግ እንደሌሎቹ ክፍሎች ከባድ ባይሆንም ጥንቃቄ ማድረግ ግን ተገቢ ነው።

የመመገቢያ ጠረጴዛ

የመመገቢያ ጠረጴዛችንን ከመመገቢያ ክፍላችን ኮሪደር ፊት ለፊት ማድረግ እንዲሁም ከጠረጴዛችን ጫፍ እስከ ክፍሉ ግድግዳ ለተጠቃሚው በቂ ቦታ ለመስጠት ጠረጴዛችንን ከክፍላችን መሃከለኛ ቦታ ላይ ማስቀምጥ።በጠረጴዛችን ዙሪያ የሚቀመጡትን ወንበሮች በመካከላቸው ያላቸው እርቀት ከሰላሳ እስከ ሰላሳ ስድስት ኢንች ማድረግ።

                                  የመኝታ ክፍል ዲዛይን

ብዙ ቁጥር የሚይዙት የዓለማችን ሰዎች አንድ ሶስተኛ እድሜያቸውን የሚያሳልፉት በእንቅልፍ ነው። ጥሩ የሆነ የመኝታ ክፍል ዲዛይን ደግሞ ይህን ያህል የእንቅልፍ ጊዜ በሃሴት እንድናሳልፍ ይረዳናል።

አልጋ

መኝታ ቤት ክፍላችንን ዲዛይን የምናረግበት መንገድ እንደ አልጋችን ቅርፅ እና እንደ መኝታ ቤት ክፍላችን የመስኮት እና የበር አቀማመጥ ይወሰናል፤አልጋችንን ከመኝታ ቤታችን በር ጎን ለጎን ማድረግ ይመከራል።

የወለሉ ቦታ

በመኝታ ክፍላችን ዉስጥ ሁለት አልጋ ካለን፣ በመካከላቸው ያለውን እርቀት ቢያንስ አስራ ስምንት ኢንች ቢበዛ ደግሞ ሃያ አራት ኢንች አራርቆ ማስቀመጥ።እንዲሁም አልጋችን ከግድግዳችን ጋር ያለውን እርቀት ቢያንስ ሰላሳ ኢንች ማድረግ ተግቢ ነው።

የልብስ መደርደሪያ

የልብስ መደርደሪያች ከሌሎች በክፍሉ ዉስጥ ካሉት የፈርኒቸር ዉጤቶች በሰላሳ ስድስት ኢንች እርቀት ላይ ማስቀመጥ።

                                የመስሪያ ቤት ዲዛይን

እለት ከእለት በመስሪያ ቤት በምንሰራቸው ስራዎች ውጤታማ ለመሆን ጥሩ የሚባል የመስሪያ ቤት ዲዛይን ሊኖረን ይገባል። ከዚህ በታች ደግሞ መስሪያ ቦታችን ዲዛይን ለማድረግ የሚረድኑን አንኳር ነጥቦች ቀርበዋል።

የመስሪያ ቤት ጠረጴዛ

የመስሪያ ቤታችንን ጠረጴዛ ከመቀመጫ ወንበራችን ጋር የተመጣጠነ ማድረግ እንዲሁም ብዙውን ሰዓታችንን በመስሪያ ቦታችን ስለምናሳልፍ ለጤናች ምቹ የሆነው ወንበር መምረጥ ተገቢ ነው ። ይህም ማለት በተደጋጋሚ ወይም አልፎ አልፎ በሚከሰት ህመም የሚሠቃዩ ሰዎች ለጤናቸው ምቹ በሆነ ወንበር ላይ እንዲቀመጡ ይመከራል ፡፡

በመስሪያ ቦታችን  ውስጥ ስራችንን ቀኑን ሙሉ ተቀምጠን የእለት ተእለት ስራችን መስራት የተለምደ ነዉ ፡፡ የጤና ችግር  ያለብን ሰዎች ወንበር ላይ ከመቀመጥ ውጭ ሌላ አማራጭ ከሌለን ህመሙ እየባሰብን ይሄዳል ፤ በምንሰራው ስራም ላይ ምቾት አይሰማንም፡፡ በሰውነት አካላችን ላይ ጭንቀትን የሚቀንስ የቢሮ መቀመጫ መጠቀም  የበለጠ ደስተኞች እና ዉጤታማዎች እንድንሆን ይረዳናል።

የግድግዳ ቀለም

ለመስሪያ ቤታችን ግድግዳ የምንቀባውን ቀለም በተቻለ መጠን ገለልተኛ እና ለእይታ የሚመች ቀለም ማድረግ ። አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በጣም ነጭ ወይም አመዳማ ቀለሞች የህሊና መነቃቃትን በመፍጠር ያለንን ትኩረትን ያሻሽላሉ።

የክፍሉ መስኮት

የመስሪያ ክፍላችንን መስኮት ከጠረጴዛችን ፊት ለፊት አለማድረግ። ነገር ግን ከክፍላችን ደብዛዛ ግድግዳ ፊት ለፊት ማድረግ ይመክራል።

  የጠባብ ክፍሎች ዲዛይን

የእድ ጥበብ ውጤት መጠቀም

የእደ ጥበብ ዉጤቶችን መጠቀም በተለይም በግድግዳ የሚሳሉ የጥበብ ስራዎችን በጠባብ ክፍሎች ውስጥ መጠቀም ለክፍሉ በሚፈጥሩት ዉበት ምክንያት ክፍላችን ሰፊ እንደሆነ ይሰማናል።

መደርደሪያዎችን መጠቀም

በመጠናቸው ትንንሽ የሆኑ የፈርኒቸር ዉጤቶች አንድ ላይ በመደርደሪያ ሰብስቦ ማስቀመጥ ተገቢ ነው።

በመስታወት ማሳመር

በጠባብ ክፍል ዉስጥ ተገቢው አይነት መስታወት መጠቀም ዉበት ለመጠበቅ ከማገዝ ባሻገር በቂ እና ክፍት ቦታ እንዳለን እናስባለን።

ክፍላችንን እንዴት እናሳምር

 • ክፍላችንን ታሪክን፣ ቅርስ እንዲሁም ባህል የሚያሳይ ማድረግ
  • ቀለል ያለ እና ብርሃናማ ማድረግ
  • ቀለል ያሉ የእንጨት ፈርኒቸሮች ወይም ቁሶችን መጠቀም
  • እጽዋቶችን ማካተት
  • ዉብ ቀለሞችን መጠቀም

            የፈርኒቸር ዘይቤዎች

ለክፍላችን የምንመርጣቸው የፈርኒቸር አይነቶች ወይም ዘይቤዎች ለክፍላችን ጉልህ ሚና አላቸው። ከእነዚህም ውስጥ ጠቃሚ የሚባሉት የፈርኒቸር ዘይቤዎች፡-

 • በተጠቃሚው መሰረት መምረጥ ይህም ማለት ፈርኒቸራችንን ለህፃናት፣ ለጎልማሳ፣ ለሽማግሌዎች ወይስ ለአካል ጉዳተኞች ነው የምንጠቀመው የሚለውን ለይቶ ማወቅ
 • በእጅ የተሰሩ የእደ ጥበብ ውጤቶችን መጠቀም
 • ሶፋዎች፣ አግዳሚ የእንጨት ወንበሮች እና ነጠላ ወንበሮች እንደ አስፈላጊነታቸው መጠቀም
 • ከብረት ወይም ከቆዳ እና ከብርጭቆ የሚሰሩ ፈርኒቸሮችን መጠቀም

Pin It on Pinterest

Share This