ጠባብ የሚባል የመኝታ ክፍል ካለን እና እንዴት አድርገን ይህንን ጠባብ የመኝታ ክፍል ወደ ምቹ እና  ባለ ብዙ ጠቀሜታ ሰጪ ክፍል እንቀይራለን የሚለውን ሃሳብ እናያለን። ከዚህ በታች የምንገልጣቸውን አጋዥ ሃሳቦችን በመጠቀም ጠባብ ክፍላችንን ምቹ እና በቂ ማድረግ እንችላለን።

ምንም እንኳን በመኝታ ክፍላችን ዉስጥ ያለን ቦታ ጠባብ ቢሆንም እንዴት ያለንን ቦታ እንደምንጠቀምበት በማጤን ክፍላችንን በአግባቡ መጠቀም እንችላለን።

የክፍሉን ዲዛይን ማሳመር

መጀመሪያ አልጋችንን ከክፍሉ መሃል ቦታ ላይ ማድረግ ፣ ብዙ ጊዜ አልጋችንን መሃከል ላይ ስናደርግ ከክፍሉ በር ፊት ለፊት መሆን አለበት።አልጋችንን ከክፍል መሃል ላይ ማድረጋችን ክፍሉ የተመጣጠነ ቅርጽ እንዲኖረው ያደርጋል። ይህም ማለት ከአልጋው ዉጪ ሌላ ትርፍ ቦታ ይኖረናል ማለት ነው።

ጠረጴዛዎችን ማስወገድ

በመኝታ ክፍላችን ወስጥ በቂ ቦታ ስለሌለን በክፍላችን ዉስጥ የሚገኙትን ጠረጴዛዎች ማስወገድ እና አልጋችንን ወደ አንዱ ገፅ ግድግዳ ማስጠጋት የክፍሉን ቦታ በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። በክፋላችን ዉስጥ ጠረጴዛዎችን ከመጠቀም ይልቅ ከአልጋችን ላይ ሸልፍ ወይም መደርደሪያ መስራት እንችላለን።

የልብስ መደርደሪያ

ክፍላችን ጠባብ በሚሆንበት ጊዜ የክፍላችንን ቦታ ወደ ጎን ከመጠቀም ይልቅ ወደ ላይ ከፍታን መጠቀምን ይመከራል። ለምሳሌ የልብስ ቁም ሳጣንን በመጠቀም ልብስ ከማስቀመጥ ባሻገር ቴሌቭዥናችንን ማስቀመጥ እንችላለን።

ብርድ ልብስ

የብርድ ልብሳችንን ቀለም ከክፍላችን ቀለም ጋር ማጣጣም ከቻልን  ለክፍላችን ልዩ ዉበትን ይሰጣል።

የተፈጥሮ ብርሃንን መጠቀም

የተፈጥሮ ብርሃንን በመጠቀም ክፍላችንን ዉብ እና ማራኪ ማድረግ ይቻላል። ደብዛዛ የግድግዳ ቀለሞችን ለክፍላችን ብንጠቀም ክፍላች የበለጠ ብርሃን እንዲያገኝ ይረዱታል። ክፍላችን በቀጥታ ብርሃን ማግኘት የማይችል ከሆነ የመኝታ ቤት መስታወት በመጠቀም ክፍላችን ብርሃን እንዲያገኝ ማድረግ እንችላለን።

የኮርሳችንን ቀለም ማሳመር

ኮርኒሳችንን የሚያመር ቀለም መቀባት፣ የተጠቃሚውን እይታ እንዲሰብ ማድረግ  እንዲሁም መስኮታችንን ከኮርኒሳችን ዝቅ ብሎ እንዲኖር ማድረግ  ክፍላችን የበለጠ ዉብ ያደርገዋል።  

መብራት እና መስታወት

ለክፍላችን የምንጠቀመውን መብራት ስንመርጥ ጭንቀትን የሚስብ እንዳይሆን መጠንቀቅ አለብን።  ከክፍላች ጥበት የተነሳ በጣም ደማቅ ብርሃን ያለው መብራት የምንጠቀም ከሆነ ፣ የሚለቀቀው ጨረር ሙሉ በሙሉ እኛ ላይ ስለሚያርፍ በአይናችን እና በቆዳችን ላይ ጉዳት ያደርሳል።

እንዲሁም ለመኝታ ክፍላችን ዉበት ከሚሰጡን ቁሶች መካከል አንዱ መስታወት ነው። መስታውትን በመኝታ ክፍላችን ዉስጥ ማካተት ዉበታችንን እንድንጠብቅ ይረዳናል።

የጥበብ ስራዎችን ማካተት

በየቀኑ ወደ ምኝታ ክፍላችን ጎራ ስንል የምንመለከታቸው እና ለራሳችን ሃሴት የሚሰጡን የኪነ ጥበብ ስራዎችን በጠባቧ የመኝታ ክፍላችን ዉስጥ ብናካትት ክፍላችንን የበለጠ ሳቢ ማድረግ እንችላለን። በመኝታ ክፍላች ውስጥ የምናካትታቸው የጥበብ ስራዎች ግድግዳ ላይ የሚሰቀሉ ቢሆን ይመረጣል ምክንያቱ ደግሞ የክፍላችንን ቦታ በአግባቡ ለመጠቀም  ስለሚረዱን ነው።

የዕቃ ማጠራቀሚያ መጠቀም

ጠባብ የሆነች መኝታ ክፍል ለማደራጀት የዕቃ ማጠራቀሚያ ጠቃሚ ቁስ ነው። ይህም ማለት እንደ መደርደሪያ እና ሳጥን ሆኖ በአንድ ላይ ሁለት ጥቅም የሚሰጥን ቁስ መጠቀም ወይም በአልጋ ዉስጥ ሊገባ የሚችል የዕቃ መያዣ መጠቀም የክፍላችንን ቦታ በአግባቡ እንድንጠቀም ያግዘናል።

የማያስፈልጉንን ቁሳቁሶች ማውጣት

በመኝታ ክፍላችን ዉስጥ የማያስፈልጉንን ቁሶች ከክፍሉ ማውጣት ተገቢ ነው ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች ከክፍሉ ማውጣት ክፍላችንን ንፅሁ ከማድረግ ባሻገር ውብ አየር እንድናገኝ ይረዳናል።

የግድግዳ ቀለም

እንደ ነጭ ፣ ክሬም ወይም  እንደ አመዳማ ያሉ ቀለል ያሉ ገለልተኛ ቀለሞች ቀለል ያለ ዉበት ለመኝታ ክፍላችን   ይሰጣሉ፡፡ የበለጠ ቀለማዊ እይታን ከመረጡ ግን እንደሰማያዊ ፣ ሀምራዊ ፣ ሚንት ፣  እና ጠቆር ያለ ቢጫ  ቀለሞች ይመረጣሉ።

የመኝታ ክፍላችን የሚመከሩ የፈርኒቸር መጠን

ምንም እንኳን የመኝታ ክፍላችን ጠባብ ቢሆን ልናካትታቸው የምንችላቸውን ቁሶች እና ምን ያህል መጠን መሆን እንዳለባቸው እናያለን።

የአልጋ መጠን

በእርግጥ የአልጋችን ቅርፅ ከዘይቤ ዘይቤ ቢለያይም ብዙን ጊዜ ትልቅ ቅርፅ ላላቸው አልጋዎች ስልሳ ኢንች በ በሰማንያ ኢንች እና ሰባ ስድሥት ኢንች በ ሰማንያ ኢንች ቅርጽ ይመከራል። ነገር ግን ለዩኒቨርሲት እና ለግል አልጋዎች የአልጋው ቁመት ከአምስት ኢንች እስከ አስር ኢንች እና የአልጋ እርዝመት ደግሞ ከአስር ኢንች እስከ ሃያ ኢንች እንዲሆን ይመከራል።

መደርደሪያ

ከሞላ ጎደል እያንዳንዱ መኝታ ቤት እንደ ካልሲዎች ፣ የውስጥ ሱሪ ፣ ጌጣጌጥ እና የግል ዕቃዎች ያሉ አስፈላጊ ነገሮችዎን ለማከማቸት ቁም ሳጥኖችን  ያካትታል ፡፡

መደበኛ እና የተለመደ የመኝታ ቤት መደርደሪያ አርባ ኢንች እርዝማኔ፣ አስር ኢንች ደግሞ ቁመት ሲኖረው እንዲሁም ሃያ ኢንች ስፋት ይኖረዋል።

ክፍላችን በጣም ጠባብ ከሆነ ደግሞ ሰላሳ ኢንች እርዝማኔ፣ አስራ ሰባት ኢንች ስፋት እና ስልሳ ኢንች ቁመት እንዲኖረው ይመከራል። ይህም ማለት ከመደበኛ መደርደሪያ በሶስት ኢንች ስፋት አንሶ እና በአምሳ ኢንች ቁመት ጨምሮ ማለት ነው።

 ትንሽ ጠረጴዛ

ጠረጴዛ በመኝታ ቤት ክፍል ውስጥ አስፈላጊ ቁስ ነው ።  ስልክዎን ፣ ተወዳጅ የምሽት መፃህፍቶች እና የማንቂያ ሰዓትን ለማስቀመጥ እንጠቀምበታለን ፡፡ የመኝታ ክፍል ጠረጴዛዎች  ብዙውን ጊዜ አራት ማዕዘን እና ጥንድ ሆነው ይመጣሉ ፤ ሁሉቱንም በአልጋችን በጎን በኩል እናስቀምጣቸዋለን ፡፡ አማካኝ የመኝታ ክፍል ጠረጴዛ   ሃያ ኢንች ስፋት እና  ሃያ ኢንች  ጥልቀት ወይም ቁመት ይለካል ፡፡ እንዲሁም ከአልጋችን ጋር ተመሳሳይ ቁመት ቢኖራቸው ይመረጣል ምክንያቱም ቀላል ቁሶችን ለማስቀመጥ ስለሚረዳን።

የሚዲያ ማከማቻ ክፍል እና የመጽሐፍ መደርደሪያ

የሚዲያ ማከማቻ ቁስ ፤ በዋና መኝታ ክፍሎች ውስጥ የጋራ መገልገያ ፣ እንደ ቴሌቪዥን ፣ ዲቪዲ ወይም ብሉ-ሬይ ማጫወቻ እና የድምፅ ማጫወቻ መሳሪያዎችን  በአንድ ላይ ይይዝልናል ፡፡ የሚዲያ ማከማቻ  ቁስን ከመኝታ ቤታች ክፍል ዉስጥ ዋና ቦታ ላይ ማስቀመጥ የለብንም  ፡፡  ይልቁንም  ሚዲያዎን ለማደራጀት እና  ከቁሱ ዉጭ ያሉ ገመድ እና ሃርድዌሮችን ለመቀነስ ሊያገለግል ይገባል ፡፡ የመኝታ ክፍላችን የሚዲያ ማከማቻ ሰላሳ ኢንች ርዝመት እና ሰላሳ ኢንች ስፋት ቢኖረው ይመረጣል። አልጋ ላይ በምንተኛበት ጊዜ ቴሌቪዥኑ ከእኛ ፊት ለፊት መሆን ስለሚኖርበት የማከማቻ ቁሱ ቁመት በአልጋው ፍሬም ቁመት መሰረት  መወሰን አለበት ፡፡

ምቹ ፍራሾች

ምንም እንኳን ዛሬ ጊዜ ፍራሾች ውድ ቢሆኑም ፣ የሰው ልጆች በሕይወታቸው በግምት ከአንድ አራተኛ  እስከ አንድ ሶስተኛ እድሚያቸውን የሚያሳልፉት  በምኝታ ስለሆነ ፣ ምቹ እንቅልፍ ማሳለፍ ተገቢ ነው ለዚህ ደግሞ በምቹ ፍራሾች መተኛት ተገቢ ነው  ፡፡ እንቅልፍ ለአካላዊም ሆነ ለአእምሮ ጤንነት ጠቃሚ የሆነ ሂደት ነው፡፡ እንዲሁም ብዙን ጊዜ ከአጭር ትራሶች ይልቅ ረዥም ትራሶች ተመራጭ  እና ምቾት ሰጪ ናቸው።

የመጽሐፍ መደርደሪያ መጠን

የመጸሃፍት መደርደሪያችን ቁመት ለማወቅ፣ አልጋውን ከሚጠቀሙት ሰዎች መካከል በጣም ረዥም የሆነው ወይም የሆነችውን ሰው መምረጥ እና   እነሱን አልጋ ላይ አስቀምጦ፣ ከአናታቸው ፀጉር በላይ ወደ ላይ ስድስት ኢንች መጨመር። እንዲሁም በቂ ቦታ በክፍላችን ዉስጥ  ስለማይኖረን የመፀሃፍ መደርደሪያችንን ባለ ቦታ ላይ ተመስርተን መስራት።

ወደ ላይ ቦታን መጠቀም

በመኝታ ክፍላች ውስጥ አብዛኛውን የወለል ቦታ የሚወስዱብንን ቁሶች የክፍሉን የከፍታ ቦታ እንዲይዙ ማድረግ  ይቻላል። አጭር እና ሰፊ የሆነ የመፅሃፍት መደርደሪያም ሆነ የልብስ ቁም ሳጥን ከመጠቀም ይልቅ ፣ ያን ያህል የወለል ቦታን የማይወስድ ረጅምና ጠባብ ስፋት  ያለው መደርደሪያ መምረጥ እንችላለን ፡፡ የመጽሐፍ መደርደሪያ ማከል በማንፈልግበት ጊዜ በግድግዳ ላይ የሚሰሩ መደርደሪያዎች በመጠቀም መፅሃፍታችንን ልናስቀምጥ እንችላለን ፡፡ በመኝታ ክፍላችን  ውስጥ በቂ ክፍተትን ለማግኘት ከአልጋችን ጋር የተሰራ  መደርደረያ በመጠቀም ፤ ስልካችንን ፣ የማንቂያ ሰዓትን እና ሌሎች  ቁሶች ለማስቀመጥ ይጠቅመናል፡፡

Pin It on Pinterest

Share This