ሚዲያ በአስራ ሶስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንደተጀመረ ይነገራል። በሚዲያ ክፍል ብዙን ጊዜ የትዳር አጋሮች ፣ ቤተሰቦች እንዲሁም ወዳጆ በአንድ ላይ ሆነው ፊልሞችን፣ድራማዎች እያዩ፤ የሚዝናኑበት፣ ትምህርት የሚያገኙበት ነው። ታዲያ በሚዲያ ክፍል ዉስጥ ረዘም ያለ ሰአት የምናሳልፍ ከሆነ ፤ ሚዲያ ክፍላችን ምቾት እንዲሰጠን ምን መሆን አለበት ? የሚለውን ሃሳብ እንቃኝ።  

የሚዲያ ክፍል የግድ የብቻው በአንድ አዳራሽ ዉስጥ መሆን የለበትም። የሚዲያ ክፍልን እራሱን ችሎ ከሚሰራው ክፍል በተጨማሪ  በቤታችን ዉስጥም ማካተት እንችላለን።

የሚዲያ ክፍል ዲዛይን በምናደርግበት ጊዜ በመጀመሪያ ሊታሰብባቸው ከሚገቡ መሰረታዊ ነገሮች መካከል አንዱ ወንበር ነው።

 በሚዲያ  ክፍል ውስጥ የሚኖረን ወንበር የእንግዶቻችንን ቀልብ የሚስቡ መሆን አለባቸው። ከቤተሰቦቻችን እንዲሁም ከወዳቾቻችን ጋር  በሚዲያ ክፍል ውስጥ ብዙ ሰአትን እናሳልፋለን ፣ ስለዚህ ወንበሮቻችንን በቂ እና ምቹ  ማድረግ አለበን ፡፡

የሚዲያ ክፍል ወንበሮች ስናስብ ፤ ወዳጆች በአንድ ላይ መቀመጥ የሚችሉበት ወጥ ረዥም ወንበርን ጨምሮ እስከ ነጠላ ወንበሮች ማካተት እንችላለን።

ለሚዲያ ክፍሎቻችን ወንበር በምንመርጥበት ጊዜ ትኩረት መስጠት ያለበን ዋና ዋና ነጥቦች፦

የክፍሉ ስፋት ወይም መጠን

የሚዲያ ክፍላችን ስፋት እና ጥበት፤ መርጠን የምንገዛቸውን ወንበሮች ለመወሰን ከፍተኛ ሚና አላቸው። ጠባብ ክፍሎች የፈለግነው አይነት እንዳንገዛ ሊያስገድዱን ይችላሉ። እንዲሁም ወንበራችን  ከቴሌቪዥኑ ስክሪን ያለዉን እርቀት መመጥን ያስፈልጋል።ምክንያቱም በቴሌቭዥናችን እና በስክሪኑ መካከል ያለው እርቀት ትንሽ ከሆነ ቴሌቪዥኑ የሚለቀው ጨረር አይናችንን ይጎዳናል።

ወንበሩን የሚጠቀሙት ሰዎች ብዛት

የሚዲያ ወንበር በምንገዛበት ጊዜ ሌላ ግንዛቤ ዉስጥ የምናስገባው ነገር ወንበሩ ምን ያህል ሰዎች እንዲይዝልን እንፈልጋለን የሚለው ጥያቄ ነው? ብቻችንን ነው የምንኖረው? ብዙ ቤተሰብ አለን? ብዙ ጊዜ ብዙዎች የሚገኙበትን  ግብዣዎችን እናዘጋጃለን?  ወይስ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን አብረዉን የሚመለከቱ ብዙ ጓደኞች አሉን?

ለሚዲያ ቤት ወንበሮች ተጨማሪ ገጽታዎች

የሚዲያ ቤት መቀመጫ በአሁኑ ጊዜ ሚዲያችን የበለጠ ምቹ የሚያደርጉ ሰፋ ያሉ ተጨማሪ ባህሪያትን ይዘው መጠዋል። ከእነዚህ ምሳሌዎች አንዱ የርቀት መቆጣጠሪያውን ወይም ሪሞት ለማስቀመጥ ፣ እንዲሁም መጠጥ እና ምግብ ለማስቀመጥ ይረዳናል  ፡፡ በወንበራች ላይ ሆነን ቲቪያችን እያየን ቻርጅ ማድረግ እንድንችል ፖርት አብሮ ማካተት ይቻላል።

መብራት

የመገናኛ ብዙሃን ክፍል መብራት ዋና ተግባር ድባብን መፍጠር ነው ፣  ስለዚህ መብራቶቹ ለተመልካች በጣምም የሚያንጸባርቁ ወይም በጣምም ደብዛዛ የሆኑ መሆን የለባቸውም። የሚንጠለጠሉ መብራቶች ሁልጊዜ ማለት ይቻላል በቴሌቪዥን ማያ ገጽ  ወይም ስክሪን ላይ ያንፀባርቃሉ ፣ ወይም  ትክክለኛውን ምስል ያበላሻሉ ፡፡ የሚዲያ ክፍላችንን የመብራት  አጠቃቀም በተቻለ መጠን ከክፍሉ ዲዛይን ጋር የተቀናጀ ማድረግ ጥሩ ነው።

የመብራት አገጣጠማችንን መሰረት አድርገን ስናይ ሶስት አይነት የመብራት አገጣጠም ዘዴዎች አሉ።

የግድግዳ መብራት

 የግድግዳ መብራት መጠቀም በጨለማ ክፍል ዉስጥ በቂ ብርሃን እንድናገኝ እና የፈለግነውን ስራ በአግባቡ እንድንከዉን ያስችሉናል። ነግር ግን በጣም ትልቅ ቅርፅ ላላቸው ስክሪን ወይም ለቴሌቪዥን ገፅ የግድግዳ መብራቶች ሊረብሹ ወይም ለእይታ የሚፈለገውን ምስል በአግባቡ እንዳናይ ያደርጉናል።

የጣራ መብራት

 በጣም ያልደበዘዙ ነገር ግን በተወሰነ ደረጃ ደብዘዝ ያሉ የጣራ መብራቶች ለሚዲያ ክፍል ዉበት ይሰጣሉ። እነዚህ የጣራ መብራቶች በምናየው ምስል ወይም ቪድዮ ላይ ምንም አይነት ተጽንኦ አያሳድሩም።

የወለል መብራት

የወለል መብራቶች በሚዲያ ክፍሉ ሌሎች መብራቶች ተጽንኦ ሳይገደቡ ታዳሚዉን የሚጓዝበት ቦታ ለማሳየት ምቹ ናቸው።

ባርን ማካተት

በሚዲያ ክፍላችን ውስጥ አነስተኛ የቤት ዉስጥ ባር በማካተት የተሟላ የመዝናኛ   ክፍል መፍጠር ይቻላል። በሚያምር የሚዲያ ክፍል በጎን በኩል ውብ ፣ አስደናቂ እና በደንብ የተሟላ ባርን ማካተት ይቻላል ፡፡ የባሩ ድምቀት ለክፍሉ ብሩህነትን እና ማራኪነትን ይሰጣል።

ብሩህ የፀሃይ ብርሃን

 አብዛኛዎቹ የሚዲያ ክፍሎች ዲዛይኖች ጨለማ እና ድራማዊ ቢሆኑም የፀሃይ ብርሃን  በመስታወት ጣራ ለክፍሉ ድምቀትን ለመስጠት  ይረዳናል ፡፡ ብርሃን የሚያስገቡ የጣራ ክፍል ከጠቅላላው የጣሪያ ክፍል ግማሹን ይሸፍናሉ ፣ ይህም በቤት ውስጥ ሆነን ከቤት ውጭ እንዳለን እንዲሰማን ያደርገናል ፡፡

ወለሉን እንደ መቀመጫ መጠቀም

ጃፓኖች የሚዲያ ክፍሎችን ዲዛይን በመንደፍ በኩል ስመጥር ናቸው።

 ይህም የሚዲያ ክፍል  ዲዛይን ፅንሰ ሃሳብ የግድግዳን ንፁህነት ፣ የክፍሉን ብዙ ጠቀሜታ ሰጭነት እና ተግባራዊነትን እንዲሁም የገለልተኛ ቀለሞችን አጠቃቀም ባህሪ አካቷል ፡፡ የክፍሉ የትኩረት ነጥብ ወይም ዋና ቦታ ለክፍሉ እንደ መቀመጫነት የሚያገለግለው የወለል ንጣፍ ነው ፡፡ ምንጣፉን ከጎኑ የሚሸፍኑ ትራሶች  ጀርባችንን ለማስደገፍ ያገለግላሉ ፡፡

የሚዲያ ክፍላችንን ለማዘምን ዋና ዋና ነጥቦች፦

  • ዉብ እና ማራኪ የቀለም ዲዛይን እና  ስእሎች
  • ለስላሳ የሆኑ የፈርኒቸር ዉጤቶች
  • ከግድግዳ ጋር ነጥረው የሚመለሱትን ድምጾች  የሚያመጣጥን ቴክኖሎጂ
  • የክፍሉን ሙቀት የሚያመጣጥን ቬንቲሌተር

ለበለጠ ምቾት

የቤት ሚዲያ ክፍል የሲኒማ ቤት መቀመጫዎች ከሚሰጡት አገልግሎት ጋር  ሲነፃፀር የቤት ሚዲያ ወንበር የበለጠ ምቾት ይሰጣል ፡፡ በአካባቢያችን ወደ  አሉት ሲኒማ ቤቶች ጎራ ብንል ምቹ ያልሆኑ እና የተሰሩበት ቁሶች በአግባቡ ጥናት ያልተካሄደባቸው ናቸው ፡፡

ክፍላችንን እንዴት አድርገን ወደ ሚዲያ ክፍል እንቀይር

የምንቀይረውን ክፍል መምረጥ

ለሚዲያ የምንመርጠውን ክፍል በተቻለ መልኩ አራት ማአዘን ቅርፅ ያለዉን ማድረግ። እንዲሁም ትንሽ በር እና መስኮት ያለውን ክፍል መምረጥ። እንዲሁም የሚዲያ ክፍላችንን ከልጆች ክፍል ጎን አለማድረግ ምክንያቱም ደግሞ ከክፍሉ የሚወጣው ድምፅ ህፃናትን ሊረብሽ ስለሚችል ነው። 

ክፍሉን ማጽዳት

ለሚዲያ ክፍል የማይፈለጉትን ነገሮች ከክፍሉ ማፅዳት

ዲመር ማብሪያ እና ማጥፊያ መጫን

ፊልም እና ጌም በምንጫወትበት ጊዜ ዲመር ማብሪያ እና ማጥፊያ ዝቅተኛ ሃይል ያለው መብራት  እንድንጠቀም ያስችለናል። በጨለማ ክፍል ዉስጥ ፊልም በምናይበት ጊዜ የስክሪኑ ሙሉ ጨረር አይናችን ላይ ያርፋል። ስለዚህ ትንሽ ብርሃን ያለው መብራት መጠቀም አይናችን ላይ የሚያርፈውን የጨረር መጠን ይቀንሳል።

ኦዲዮ ቪዥዋል መሳሪያዎችን መጠቀም

በቻልንው መጠን ቴሌቭዥናችንን ከምንቀመጥበት ወንበር ፊት ለፊት ማስቀመጥ። እንዲሁም የኦዲዮ ቪዥዋል መሳሪያዎች ቴሌቭዥናችንን በምናስቀምጥበት ቲቪ ስታንድ መደርደሪያ ዉስጥ ማስቀመጥ።

ወንበራችንን ማስቀመጥ

የሚዲያ ወንበራች ከቴሌቪዥናችን ስፋት በሁለት እጥፍ ቴሌቪዥችን ካለበት ቦታ እርቀት ላይ ቢሆን ይመረጣል።

መጋረጃ መጠቀም

 የፀሃይ ብርሃን የሚዲያ ክፍላችንን የሚረብሽ ከሆነ መጋረጃ መጠቀም ተገቢ ነው።

Pin It on Pinterest

Share This