ምቾት ለማግኘት፣ ረዘም ላለ ጊዜ ለመጠቀም እና ውበት ለመጨመር ውድ ዋጋ አውጥተን ለቤታችንም ሆነ ለስራ ቦታችንን ከምንገዛቸው እቃዎች መካከል  አንዱ እና ዋነኛው ሶፋ ነው።ታዲያ ዉድ ዋጋ አውጥተን ከገዛን ላይቀር ጥራት ያለው ሶፋ እንዴት እንግዛ ለምትሉ ደንበኞቻችን ከዚህ በታች የተወሰኑ ምክሮች እንለግሳችሁ።

የሶፋ አጠቃቀማችን?

የምንፈልገውን ሶፋ በትክክል ለመወሰን እንዲረዳን የሚቀጥሉትን ጥያቄዎች እራሳችንን መጠየቅ ምርጫችንን ያቀልልናል፡፡ የኑሮ ሁኔታችንን ማሰብ ፣ ሶፋችንን የት እንደሚቀመጥ ማወቅ እና ብዙ ጊዜ ማን እንደሚጠቀምበት መለየት፡፡

-ሶፋችንን የት ነው የምናስቀምጠው በመደበኛ ሳሎን ውስጥ ለመዝናናት ወይስ ከቴሌቪዥኑ ፊት ለፊት ?

-ሶፋችችን ጠንካራ እና በከፍተኛ ድጋፍ የተሰራ እና ምቾት የሚሰጥ ነው ?

ምን ዓይነት ሶፋ ይፈልጋሉ?

ይህ ባለን የቦታ መጠን ፣ ምን ያህል ሰው እንዲይዝልን በምንፈልገው ልክ እና ከመቀመጫነት አልፎ ለመኝታ አገልግሎት ለመጠቀም በምናስበው ፍላጎታችን  ላይ የተመሠረተ ይሆናል ፡፡የዛሬዎቹ ሶፋዎች በአጠቃላይ የሚከተሉትን ዓይነቶች ናቸው።ባህላዊ ሶፋ – የእነዚህ ሶፋዎች እርዝማኔ ከሰባ ሁለት እስከ ዘጠና  ኢንች የሚደርሱ ሲሆኑ ከ ሶስት  እስከ አራት ሰዎች የመያዝ አቅም አላቸው ።

ሴክሽናል ሶፋ – የ ኤል ወይም የ ዩ ውቅር ሶፋዎችን  ለመፍጠር የተለያዩ የነጠላ ሶፋዎች ቅንጅት ውጤት ነው፡፡

ቅርፁን መቀየር የሚችል ሶፋ –  ምናልባት ሶፋች ላይ መተኛት በፈለግን ጊዜ  ወደ ምንፈልገው አይነት ቅርፅ መቀየር እንችላለን።

የጥንዶች ሶፋ – እነዚህ ሶፋዎች ደግሞ ከአርባ ስምንት  እስከ ሰባ ሁለት ኢንች እርዝመት ሲኖራቸው ሁለት ሰዎችን የመያዝ አቅም አላቸው።

የአፓርትመንት ሶፋ – በአጠቃላይ በርዝመት እና ሰው በመያዝ አቅማቸው የአፓርትመንት ሶፋዎች በጥንዶች  ወንበር እና በመደበኛ ሶፋ  መካከል የሚገኙ ናቸው።

ባለ አራት መቀመጫ ሶፋ – የመደበኛ ሶፋ  አዲስ ስሪት  ሲሆን፣ ከመደበኛ ሶፋ ጋር ተመሳሳይ ጥልቀት እና ቁመት አለው።

ሶፋች ስንት ሰዎች እንዲይዝልን ነው የምንፈልገው ?

ስንት ሰዎችን  እንደሚይዝልን ብቻ ሳይሆን እንዴት እንደምንጠቀምበት ከግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል ፡፡ አንድ ሰው መተኛት እና ሌላኛው መቀመጥ የሚወድ ከሆነ ይህን ፍላጎት ማሟላት መቻሉን  ማረጋገጥ ፡፡ልጆች ወይም የቤት እንስሳት ካለን ደግሞ እድፍ መቋቋም የሚችል የጨርቅ ወይም የቆዳ  ሶፋዎችን ብንገዛ ይመከራል።

የወለል ቦታ

ሶፋችንን ለማስቀመጥ የምንፈልግበትን ቦታ ከወሰን በኋላ ሶፋዎቹን ለማስቀመጥ ያሰብንበትን ቦታ በደንብ መለካት፡፡ ብዙ ነገሮች ሶፋችንን ለማስቀመጥ ካሰብንበት ቦታ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ ፡፡ ለምሳሌ:

-የግድግዳው ርዝመት

-የበር እና መስኮቶች አሰራር

-የመዝናኛ ክፍል

-መብራት እና

-የኤሌክትሪክ ሃይል ምንጮች

በእነዚህ ምክንያቶች ሶፋችንን ካስቀመጥን በኋላ ቦታ ከምንቀያይር መጀመሪያ በደንብ ማሰብ ተገቢ ነው።

የግል ሁኔታ

ዕድሜ- አንዳንድ በእድሜ ገፋ ያሉ ሰዎች በተወሰኑ የሶፋ ዓይነቶች ላይ ቁጭ ብለው መነሳት ይከብዳቸው ይሆናል ፡፡፡ በልዩ ሁኔታ ለተጎዱት ወይም ለአዛውንቶች እነሱን ያገናዘቡ ዓይነት ሶፋዎች ጥሩ ናቸው ፡፡

ንፅህና-ሌሎች ከጤና ጋር ተያያዥነት ያላቸው ተግዳሮቶች ላይኖራቸው ይችላል ነገር ግን በቀላሉ ሊጸዳ የሚችል ወይም ከባድ ጥገና የማይፈልግ ሶፋ ይፈልጉ ይሆናል ፡፡ ለምሳሌ ፣ አንዳንድ ሰዎች ወለሉን በቀላሉ ለማፅዳት ይፈልጉ ይሆናል ፡፡

ቁሳቁስ

ለመግዛት ከመወሰናችን በፊት አንድ ሶፋ የተሰራበትን ቁሳቁስ ማወቅ ያስፈልጋል ፡፡ እነዚህን ሁለት ምክንያቶች እናንሳ።

ክፈፍ እና ማጠፊያ: – ሶፋችን ጥሩ ክፈፍ እና በቂ ማጠፊያ ያለው መሆኑን መረዳት።እንዲሁም ተቀምጠን ስንነሳ በደንብ የማያስፈነጥረን ከሆነ ሶፋውን ለረዥም ጊዜ መጠቀም እንችላለን ማለት ነው ፡፡

ጨርቃጨርቅ: – እንዲሁም የምንመርጠው የሶፋችን ልብስ ቆሻሻን መቋቋም የሚችል ቢሆን ይመረጣል።

ዓይነት እና ዘይቤ

 ስለ ምናስቀምጥበት ቦታ እና  ስለ ተሰራበት ቁሳቁስ ዝርዝር ጉዳዮች ካረጋገጥን በኋላ ስለ ሶፋችን አይነት እና ዘይቤ ማሰብ ተገቢ ነው ፡፡ በቤታችን ውስጥ  ካሉ የጌጣጌጥ አይነቶች ጋር   የሶፋችንን ቀለም ማመጣጠን መቻል አስፈላጊ ተግባር ነው።

በአጠቃላይ ሶፋ ስንገዛ ተጽእኖ የሚያሳድሩ ምክንያቶች

  • ዋጋ
  • ዘይቤ ወይም ስታይል
  • ዘላቂነት
  • የቁሳቁስ ጥራት
  • ሜካኒካሎች
  • ፈጠራዎች
  • ወደ ሚፈለጉበት ቅርፅ የመቀየር ባህሪ
  • የጥገና መስፈርቶች
  • ከሽያጭ በኋላ ያለው ዋስትና እንዲሁም
  • የምርት ስም (ብራንድ)

የሶፋው ጥራት

ለረዥም ጊዜ መቆየት የሚችል እና ጥራት ያለው ሶፋ ያስፈልጋል። ጥራት ያለው ሶፋ ለመግዛት ደግሞ ስሪቱን በደንብ ማጤን ያስፈልጋል።

ክፈፍ

እንደ ዋርካ እና ጥድ ያሉ የተፈጥሮ እንጨቶች ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ናቸው ፡፡  በተፈጥሮ  ዝቅተኛ የሆነ እፍግታ ያላቸው ወይም መጠነ ቁሳቸው ከይዘታቸው አንፃር ዝቅተኛ የሆኑ እንጨቶች ዝቅተኛ ጥራት አላቸው፡፡

ከፍተኛ ጥራት ያለው ክፈፍ ወይም ፍሬም መኖሩ  ከጊዜ በኋላ ከመጣል ወይም ከጥቅም ውጪ ከመሆን  ይልቅ እንደገና የማደስ ወይም እንደገና የመሸጥ ዕድሉ ከፍተኛ ይሆናል  ማለት ነው።

የሶፋ መገጣጠሚያዎች

ለማደስ ምቹ የሆኑ እና ጠንካራ የእንጨት ምርቶች እና የብረት ማጠፊያዎች መጠቀም ጥሩ ነው ፡፡ እንዲሁም በአካል ሄደን የምንገዛ ከሆነ ሶፋው ስለተሰራበት ቁሳቁስ ባለሞያዎችን መጠየቅም የተገባ ነው።

የተሰራበት ስፖንጅ(ፎም)

ከፍተኛ ጥራት ያለው ፖሊዩረቴን ስፖንጅ ብዙ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን ስሪቱ ደግሞ ጥቅጥቅ ያለ መሆን አለበት ወይም የስፖንጁ መጠነ ቁስ ከ ስፖንጁ ይዘት የበለጠ መሆን አለበት ወይም  በቶሎ እንዳይበላሽ በጣም ጠንካራ መሆን አለበት።

አንዳንዴ ከፍተኛ እፍግታ ያለው ፎም ለስላሳ ፣ ጠንካራ እና  የመጭመቅ ባህሪ ሊኖረው ይችላል።

ዋስትና

ብዙ ጊዜ በጣም ጥራት ያላቸው ሶፋዎች በቂ የሆነ ዋስትና አላቸው።

የሶፋ ስፕሪንግ

የእንጨት ፍሬም አንድ የሶፋ የጀርባ አጥንት ከሆነ ፣ በላዩ ላይ የተዘረጉ ስፕሪንጎች እንደ መቀመጫ  ጅማቶች ሆነው ያገለግላሉ ፣ ስፕሪንጎች የሶፋችንን መዋቅር ይጠብቃሉ። እንዲሁም ስፖንጆቹ እንዳይጨመቁ ከማድረጋቸው ባለፈ ምቾትን ይሰጣሉ።

ጠንካራ ስፕሪንጎች በመካከለኛ ደረጃ ሶፋዎች ውስጥ በጣም የተለመዱ ናቸው ፡፡ ጠንካራ ስፕሪንጎች ቀጥ ያሉ የ “S“ ቅርጽ ያላቸው ጠመዝማዛዎች በተከታታይ መስመር ላይ ተጣጥፈው በከባድ መለኪያ የብረት ሽቦዎች የተሠሩ ናቸው ፡፡ አግድም የብረት ማሰሪያ ዘንጎች የሶፋችንን ስፕሪንግ ያጠናክራሉ ፣ በተለይም ደግሞ  የስፕሪንጉን መርገብ እና ማሽቆለቆልን ይከላከላሉ።

የሶፋ  እግሮች

ከብረት የተሰሩ የሶፋ እግሮች ለክፍላችን ዉበት የሚሰጡ ይመስለናል በእርግጥም ዉበት ሊሰጡ ይችላሉ።ነገር ግን  የምንመርጣቸውን የሶፋ እግሮች ከቤታችን ወለል ከተሰራበት ቁስ ጋር አብረው ይሄዳሉ ወይ የሚለው ነው? ብዙን ጊዜ ከእንጨት የሚሰሩ የሶፋ እግሮች ሶፋው የሚያርፍበትን ወለል አይጎዱም ስለዚህ ከብረት ከሚሰሩ እግሮች ከእንጨት የሚሰሩ እግሮች ተመራጭ ናቸው።

Pin It on Pinterest

Share This