የነዋሪዎች አማካይ እድሜ በመጨመሩ ምክንያት አካባቢያዊ እርዳታ የተሞላበት የኑሮ ሁኔታ በእጅጉ አስፈላጊ እየሆነ መጥቷል፡፡ አለም አቀፋዊ ንድፍ በ1980ዎቹ የቤት-ዕቃ እድሜያቸው የገፉ እና አካል ጉዳተኛዎችን ጨምሮ ለሁሉም ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ ተደርገው ንድፍ እንዲወጣላቸው ታስቦ በአሜሪካ አርኪቴክቶች የተጀመረ ነው፡፡

አለም አቀፋዊ ንድፍ ህዝብ ለሚበዛባቸው ቦታዎችም ሆነ ለኢንዱስትሪያዊ ድርጅቶች የሚያስፈልጉ ናቸው፡፡ አለም አቀፋዊ ንድፍ ጥብቅ የሆነ ህግ እና መስፈርትን የሚያሟላ ሳይሆን ዋና ግቡ ጥቅምን እና በተለያየ ሁኔታ ውስጥ ውጤትን ማምጣት መቻል ነው፡፡ በተጨማሪም አለም አቀፋዊ ንድፍ የግለሰብ ድርጅቶችን አስፈላጊነት የሚገድብ፤ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ግን የሚፈቅድ ነው፡፡ የአለም አቀፋዊ ንድፍ ፍልስፍና ከንድፍ ሙያ በተለየ በእነዚህ ቁልፍ መስፈርቶች ላይ ይመሰረታል፡፡

ተገቢነት ያለው አጠቃቀም፡- የንድፍ ውጤቶች በተለያየ ክህሎት በሰዎች ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ይገመታል

ተለማጭነት ያለው ጥቅም፡- የተቻለውን ያህል ንድፉ የተለያዩ ተጠቃሚዎችን ምርጫ ከግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡ ለምሳሌ፡ የአጠቃቀም ዘዴዎችን መምረጥ እና ለግለሰብ ተጠቃሚዎች የተለያየ የመጠቀሚያ ፍጥነትን እንደአስፈላጊነቱ ማስተካከል

ቀላል እና በተፈጥሮው አስተዋይነት ያለው፡- ይህን እቃ መጠቀም ትላልቅ የሚባሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሊያጋጥሙት አይገባም፡፡ ይህም ማለት የዚህ ዕቃ አጠቃቀም መስፈርቶች የተጠቃሚውን ልምድ እና ክህሎት በማይመለከት ሁኔታ ለመረዳት የሚቻሉ መሆን አለባቸው፡፡

በጉልህ የሚታይ መረጃ፡- ጉልህ የሆኑ ችሎታዎች ሳያስፈልጉ ለመጠቀም የሚያስችሉ ወሳኝ የሆነ መረጃን ለተጠቃሚው ማድረስ፡፡

ስህተትን መታገስ፡- ድንገተኛ እና ጤናማ ያልሆኑ እንቅስቃሴዎችን መቀነስ (ስህተትን ቀድሞ የሚያሳውቅ ማስጠንቀቂያ፣ከመጥፋት በፊት ደህንነትን መጠበቅ)፡፡  

አነስተኛ አካላዊ ጥረት፡- እንደ ድግግሞሽ ያላቸውን እንቅስቃሴዎችን የንድፍ ውጤቶቹን ለመጠቀም የሚያስፈልገውን አካላዊ ጥረት መቀነስ፡፡

ለመጠቀም የሚሆንና ዘዴኛ የሆነ መጠንና ስፍራ፡- የተጠቃሚውን እንቅስቃሴ እና አቋም ሳይመለከት፤ ለመቅረብ እና ለመቆጣጠር ንድፍ የወጣለት ቁስ ትክክለኛውን መጠን እና አስፈላጊ የሆነውን ስፍራ ይይዛል ተብሎ ይታሰባል፡፡

አለም አቀፋዊ የንድፍ ደንቦችን የመተግበር አላማው የተጠቃሚውን ፍላጎት ለማሟላት የሚያስፈልጉ የተሻሉ መፍትሄዎችን ለማግኘት እና እነዚህኑ የተጠቃሚውን ፍላጎቶች የአካል ብቃት፣ ችሎታ እና እውቀትን ላይ ትኩረት ባላደረገ መልኩ ለማሟላት ነው፡፡

በመሰረቱ፤ አለም አቀፋዊ ንድፍ ህዝባዊ ስፍራዎችን ልዩ ልዩ ጉድለት ካለባቸው ሰዎች ፍላጎት ጋር ከማላመድ ባለፈ፤ እነዚህ የአካል ጉዳት ያለባቸው ሰዎች የመለየት፣ ወደ ጎን የመገፋት እና መጥፎ ስም የመሰጠት ሁኔታዎችን በማስቀረት ሰብአዊ መብቶችን ተግባር ላይ የማዋል ሚናንም ይጫወታሉ፡፡

የአለም አቀፋዊ ንድፍ ፍልስፍና ከሰው ልጅ ብዝሃነት፣ማህበረሰባዊ መጠቃለል እና እኩልነት ጋር ተስማሚነት አለው፡፡ በመሰረቱ አላማው ፈጠራን የሚያበረታቱ መገልገያዎችን  ንድፎችን እድሜያቸው ለገፋ እና የአካል ጉዳት ላለባቸው ሰዎች ማምረት ነው፡፡ በተጨማሪም ይህ አለም አቀፋዊ ንድፍ ተለዋዋጭ፣ ስራን የሚሰራ እና ከግለሰባዊ እና እድሜያቸው ከገፋ እና የአካል ጉዳት ከደረሰባቸው ሰዎች ፍላጎት ጋር አብሮ፣ተለዋዋጭ እና ተያያዥ መሆን እንደሚገባው ያሳያል፡፡

እነዚህ መፍትሄዎች ከአካባቢ ጋር የተዛመደ እና በአካባቢው ከሚታገዝ የኑሮ ሁኔታን ለመፍጠር በሚያስችል ደረጃ ጥሩ የሚባሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ሁሉን አቀፍ እና ፈጠራ የተሞላበት ዘዴ የፈጠራ ችሎታ ያላቸው እና ስነምግባር የግጥሚያ ጥሪን በቤት እቃው ኢንዱስትሪ ላሉ ለሁሉም እቅድ አዘጋጆች፣ ንድፍ አውጪዎች  እና ስራ ፈጣሪዎች የሚያቀርብ ነው፡፡

ከስነልቦና አንፃር፤ ከጥናት ማድረጊያ የአሰራር ዘዴ እና ስነልቦናዊ እና የሰው ባህርይን የሚገዙ ህገ ደንቦች ሙያዊ ፍላጎት ያላቸውን በንድፍ፣ የቤት-ዕቃን በማምረት እና ለሰዎች የሚመች እና አጋዥ የሆነ የቤት-ዕቃን ለማምረት ይተጋሉ፡፡ ይህንን የሚረዱ የቤት-ዕቃ አምራቾች የጊዜውን ዕውቀት እና ሙያዊ ስልጣኔ መጠቀም እና ገበያውን መቀላቀል እና መቆጣጠር ይችላሉ፡፡

የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች የሚሆኑ የቤት-ዕቃዎች እና ግዢ በሚደረግበት ጊዜ መታየት ያለባቸው ነገሮች

ለቤት-ዕቃዎች፤ አንዱ ለሁሉም ይገጥማል የሚል አማራጭ የለውም፡፡ ትክክለኛውን የቤት-ዕቃ አማራጭ ማቅረብ በቤት-ዕቃው ተጠቃሚዎች ላይ የሚመሰረት ይሆናል፡፡ በተለይም በቡድን ለሚኖሩ እና ለጤና ተቋማት የሚሆኑ የቤት-ዕቃዎች ሲገዙ፤ ከፍተኛ ነፃነት እንዲኖር እና ዘይቤን እና መሰረታዊ ሃሳብን በአንድ ላይ አጣምሮ እንዲይዝ ያስፈልጋል፡፡

አቀራረብ ብቻውን አስፈላጊ ነገሮችን አያሟላም ነገር ግን ለሰዎች መዝናናትን ይሰጣል፡፡ ቀዝቃዛ የክሊኒክ ስሜትን የሚፈጥሩ የቤት-ዕቃዎች በደንበኞች ላይ ጉዳት ያለው ነው፡፡ ደንበኞች እንደ ተቋም አይደሉም፡፡ በመሆኑም የሚሸጡ የቤት-ዕቃዎች የአንድን ተቋም ዘይቤ መከተል የለባቸውም፡፡ የአንድ ተቋም ንብረት የሚመስል የቤት-ዕቃ የአካል ጉዳትና የመንቀሳቀስ ችግር የሚያጋጥማቸው አዋቂ ሰዎችን የማሳረፍ ስሜት አይሰጥም፡፡ በምትኩ፤ እሱን የሚመስሉ የቤት-ዕቃዎች ለድርጅቶች የሚያስተማምኑ  እና ደህንነታቸው የተጠበቀ ናቸው፡፡ ምቹ መቀመጫ፣ የመኝታ ቤት ዕቃዎች ስብስብ እና የቡድን መጠቀሚያ የቤት-ዕቃዎች ድርጅትን ጋባዥነት ያለው እና የሚያድስ አካባቢን ለተጠቃሚም ሆነ ለቤተሰብ መፍጠር ያስችላል፡፡

የእንቅስቃሴ ውሱንነት ያለባቸው ተጠቃሚዎች ለእንቅስቃሴ የሚያግዛቸውን እና ራሳቸውን እንዲችሉ የሚያበረታታቸውን የቤት-ዕቃ ይፈልጋሉ፡፡ እንደአስፈላጊነቱ የሚስተካካል የጠረጴዛ ከፍታ ተሽከርካሪ ወንበርን ወይም በሞተር የሚሰሩ ወንበሮችን የሚጠቀሙ ሰዎችን የሚያስማማ ነው፡፡ አጠር ያለ የመቀመጫ ጥልቀት እና ከፍ ያለ የእጅ ማሳረፊያ የእንቅስቃሴ ውሱንነት ላለባቸው በሽተኞች ራሳቸውን ችለው እንዲነሱ ያግዛል፡፡

ሌሎች የእድገት ውሱንነት ያለባቸው ወይም የእንቅስቃሴ ውሱንነት ያለባቸው አዋቂዎች ልዩ የሆነ መስፈርት አላቸው፡፡ አንዳንድ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ታማሚዎች ዘላቂነት ያላቸውን የቤት-ዕቃዎች ክብደት ላለው አጠቃቀም እና የባህርይ ጉዳይ ይፈልጓቸዋል፡፡ ሌሎች ደግሞ ወደ መታጠቢያ ቤት የመሄድ ጉዳይ ሊኖርባቸው ይችላል፡፡ በመሆኑም ፈሳሽን መቋቋም በሚችሉ ጨርቆች ወይም መወገድ በሚችሉ መቀመጫዎች  የመቀመጫ ወለል ከአደጋ ወይም ከመፍሰስ በኃላ በማፅዳት ማገልገል ይችላሉ፡፡ ይህ የቤት-ዕቃ በረጅም ጊዜ ሂደት ውስጥ ከዘይቤ ጋር በማያያዝ ሊሰጥ የሚችላቸው በጣም አስፈላጊ ችሎታ ነው፡፡

እድሜያቸው የገፋ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ በህንፃ ውስጠኛው ክፍል ለተወሰነ ጊዜ ለመቆየት ይመርጣሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ፅኑ የሆነ ፊዚዮሎጂካዊ ውጥረት በ ጡንቻዎቻቸው፣ጅማቶቻቸው እና በተለየ ድግሞ የጀርባቸው ዲስኮች ላይ ያጋጥማቸዋል፡፡ ትክክለኛ የሆነ የአቋቋም እና የአቀማማጥ የጡንቻ እና አጥንት ህመም ምልክቶችን ማስቀረት ይችላል፡፡

እነዚህ እድሜያቸው የገፋ ሰዎች ስር የሰደደ ህመም ይኖርባቸዋል፤ አደጋ የማስተናገድ እድላቸውም በአስደናቂ ሁኔታ ይጨምራል፡፡ አነስተኛ እና እየቀነሰ የሚሄድ ተንቀሳቃሽነት፣ ተጣጣፊነት፣ የጡንቻ ጥንካሬ፣ እጅግ ዝግ ያለ የአፀፋዊ መልስ፣ የአረማመድ ለውጥ፣ እግርን ለማንሳት የሚያጋጥም ክብደት እና  ሚዛንን እና ተክለ ቁመናን የመቆጣጠር ስሜት ማጣት ደግሞ በጉልህ የሚያጋጥማቸው ነው፡፡ ለሁለቱም ፆታዎች እድሜያቸው የገፋ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ ከወጣቶች ያነሰ ቁመት አላቸው፡፡ ስነምቾት እና የሰዎች ልኬት ከግምት ውስጥ የገባበት ንድፍ ከብረት የተሰሩ ወንበሮችን ቋሚነት ያላቸው፣ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ምቾት የሚሰጡ እንዲሆኑ ያግዛል፡፡ በተጨማሪም እነዚህ ወንበሮች እድሜያቸው ለገፋ ሰዎች ጤናን ይጠብቃሉ፡፡

የሰው አካል የተወሰኑ ነገሮችን በእጅጉ ይፈልጋል፡፡ ከሰዎች አካል ጋር አብሮ በተደጋጋሚ የሚንቀሳቀስ የቤት-ዕቃ ለምቾት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡

ንድፍ አውጪው የሁለቱንም አካላት ልኬት ከግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡ ከሰው ልጅ አካል ጋር የሚገኛኝ ዋነኛ ቦታ ስናይ የጀርባ እና የመቀመጫ ምቾት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን እና በታፋ እና በእግር አካባቢ ያለውን ደግሞ በአነስተኛ ሁኔታ አስፈላጊ መሆኑን እናያለን፡፡ ሊከሰቱ የሚችሉ ብዛት ያላቸው መመሳቀሎች በእነዚህ ውስጥ ማስቀረት የሚቻሉ ናቸው፡፡  

Pin It on Pinterest

Share This