ከወዳጅ ዘመድ ጋር  እንዲሁም ከልጆቻችን ጋር ንፅህ አየር እያገኘን ጥሩ ጊዜ ለማሳለፍ የቤታችንን ግቢ አስውበን ግቢያችን ውስጥ ማሳለፍ ይቻላል። ግቢያችን ዉስጥ በቂ ቦታ ቢኖረም ባይኖረንም በቂ እውቀት ያላቸውን ባለሙያዎች መጠየቅ እና በእነሱ ታግዞ ማስጌጥ ይቻላል። የግቢያችንን መናፈሻ ግቢያችንን ሙቀት በሚጨምርበት ጊዜ ብቻ አይደለም መጠቀም ያለብን፤ የግቢ ዉስጥ መናፈሻችን ታስቦበት በደንብ ዲዛይን ከተደረግ ሙቀት እና ቅዝቃዜ ሳይገድበን  አመቱን ሙሉ መጠቀም እንችላለን።

ከዚህ በታች ደግሞ የግቢ ዉስጥ መናፈሻንን እንዴት እንድምናዘምን የተለያዩ ሃሳቦችን እናያለን።

ለአየር ሁኔታው ተስማሚ የሆነ እና  ሁለገብ አገልግሎት የሚሰጡ የቤት እቃዎችን መምረጥ

በግቢያችን ዉስጥ የምንጠቀማቸው የፈርኒቸር እቃዎች ዘላቂ እና  ላለንበት አየር ንብረት  ምቹ መሆናቸው ማረጋገጥ አለብን ፡፡ ከቤት ውጭ ላሉ አገልግሎቶች የ በጣም ጥሩ እና  በጣም ተመራጭ ከሚባሉት ቁሳቁሶች  ውስጥ ጥቂቶቹን እነሆ

 • የማይዝግ ብረት
 • ሰው ሠራሽ ሬንጅ (ዊኬር)
 • አሉሚኒየም
 • እንደ ዋርካ ፣ ጥድ ፣ ባህር ዛፍ እና አርዘ ሊባኖስ ያሉ እንጨቶች
 • ፕላስቲክ
 • እንደ ጥጥ ሸራ ያሉ ጨርቆች

ከእነዚህ ቁሳቁሶች የተሠሩ እቃዎችን መምረጥ ዉበት ከመሳብ በላይ የቤት እቃዎቻችን በጥሩ ሁኔታ ላይ እንዲቆዩ ማረጋገጥ እንችላለን፡፡ የአየር ሁኔታን የሚያረጋግጡ ለግቢ መናፈሻ የሚሆኑ የቤት እቃዎችን እራሳችን መምረጥ አልያም ደግሞ የቅርብ ወዳጅ ማማከር። 

እንዲሁም ዘላቂ የቤት እቃዎችን መምረጥም እና ብዝሃ ጥቅም ሊሰጡን የሚችሉ ፈርኒቸሮችን መምረጥ ተገቢ ነው። ለምሳሌ የቤንች መቀመጫ ሆኖ እንደ መደርደሪያነት የሚያገለግል እና ሁለት ጥቅም በአንድ ላይ የሚሰጥ ቢሆን ይመረጣል። እቃዎችን ወይም ፈርኒቸሮችን በምንመርጥበት ጊዜ ያለንን ክፍት ቦታ በደንብ ማወቅ ያስፈልጋል።

ማራኪ መብራት

የቤታችንን የግቢ መናፈሻ ለማሳመር ስናስብ አንዱ እና አስፈላጊው ነገር  የምሽት መብራት አመራረጣችን ነው። የምንጠቀመዉ መብራት የተመጠነ ጨረር መልቀቁን ማረጋገጥ አለብን ይህም ማለት ለአይናችን ጉዳት የማያደርስ እና በጣም ደብዛዛ ያልሆነ ማለት ነው።የሶላር መብራቶች ለአካባቢ አየር ተመራጪ ሲሆኑ ኤልኢዲ መብራቶች ደግሞ ለእይታ ምቹ ናቸው።

ከቤት ውጭ መጠቀም የምንችላቸው መብራቶች 

 • በግቢ ጣሪያ ወይም ግድግዳዎች ውስጥ የተጫኑ የኤሌክትሪክ መብራቶች
 • ሻማዎች
 • ችቦዎች
 • የአትክልት መብራቶች
 • በመንገዶች ወይም በቤት ዕቃዎች ስር የሚተከሉ ኤልኢዲ መብራቶች

ከላይ የተዘረዘሩትን የመናፈሻ  መብራት  አይነቶች እንደ አስፈላጊነታቸው መርጠን መጠቀም እንችላለን፡፡ እንዲሁም የምንመርጣቸው የመብራት አይነቶች  የሚያወጡት ብርሃን ወይም ጨረር እኛንም ሆነ ጎረቤታችንን መረበሽ የለበትም። እንዲሁም ከተፈጥሮ ዉበት ጋር የማይገጭ መሆን አለበት ይህም ማለት  ከጨረቃ ድምቀት ጋር የማይጋጭ ቢሆን ተመራጭ ነው።

የመመገቢያ እና የማብሰያ ቦታዎችን ማካተት

የግቢያችን  መናፈሻ በምንፈጥርበት ጊዜ   የመመገቢያ እና የማብስያ ቦታ ማካተት ተገቢ ነው ፡፡ ተወዳጅ ከሆኑ የመናፈሻ ማብሰያ አማራጮች ሃገራዊ የሆኑ እና በብዛት የምንጠቀምባቸው ከእንጨት የሚሰሩ ምድጃዎችን እና የእሳት ማገዶዎችን ያካትታሉ ፡፡ እነዚህን ብርድ ሲሆን ሰብሰብ ብለን ሙቀት ለማግኘት ያስችላሉ፤በተጨማሪም የማብሰያ ክፍል ካቢኔት ማስገጠምም ይቻላል።

ፍሪጅ ፣ መታጠቢያ ገንዳ እና የማብሰያ ቁሳቁሶችን መጨመር  የግቢያችንን መናፈሻን የበለጠ  በማሳመር ሊያዘምነው ይችላል  ፡፡

 ከቤት ውጭ ምግብን ለማቅረብ እና እንግዶችን ለማስተናገድ ቢያንስ አንድ ረዥም ጠረጴዛ እና መቀመጫዎችን እንዲሁም  ጃንጥላ  ማካተት ተገቢ ነው።

ለግቢያችን መናፈሻ ማካተት ያለብን ነገሮች

 • ምቹ ትራሶችን መጠቀም ፡፡
 • ዉበታችን ለመጠበቅ መስታወት ማካተት ፡፡
 • የተለያዩ ተክሎችን እና  እጽዋቶችን መምረጥ ፡፡
 • የዉሃ ገንዳ ማካተት
 • ተጨማሪ የጠረጴዛ ቦታ ከፈለጉ የጎን ጠረጴዛዎችን ወይም ታጣፊ ጠረጴዛዎችን ማካተት  ፡፡
 • ሶፋ መቀመጫዎች
 • መደርደሪያዎች

ዋና ቦታን መለየት

ዋና ቦታን ለቤት ውስጥ ክፍሎች ብቻ አይደለም የምንመርጠው ፡፡ ለግቢያችን  መናፈሻ ቦታን በአግባቡ ለመጠቀም ስለሚረዳን መምረጡ ተገቢ ነው ፡፡ ዋና ቦታችን ወይም ተመራጭ ቦታችን  ላይ ቢካተቱ ተመራጭ ሊሆኑ የሚችሉ  ነገሮች የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ።

 • እንደ ኩሬ ወይም ትንሽ ምንጭ ያሉ የውሃ ገንዳዎች
 • የእሳት ምድጃ
 • ግድግዳ ላይ የሚቀረፁ የጥበብ ዉጤቶች
 • አስገራሚ እና ማራኪ የቤት እቃዎች
 • በዋና ቦታችን ዙሪያ ደግሞ ልዩ ልዩ የቤት ዕቃዎች እና ሌሎች እፅዋቶች ማሰቀመጥ ።

ምቹ  የወንበር አማራጮችን ማቅረብ

በመጀመሪያ በመናፈሻ ቦታ በምንሆንባቸው ጊዜያት  ጥሩ ጊዜ ለማሳለፍ አማራጭ ወንበሮች መኖር አለባቸው።  ለእኛም  ሆነ ለምናስተናግዳቸው እንግዶች ለመቀመጥ እና ለመዝናናት የሚጋብዝ ቦታ ማድረግ ያስፈልጋል ፡፡ ለህፃናት፣ለወጣቶች፣ለሽማግሌዎች እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የሆኑ ወንበሮችን ማካተት ይመከራል።

ልንጠቀምባቸው የሚችሉ የተለያዩ የወንበር  ምርጫዎች አሉ ፡፡ ለምሳሌ አግዳሚ ወንበሮች ፣ የግል ወንበሮች ፣ ሶፋዎች እና ባህላዊ ወንበሮች ይገኙበታል  ፡፡

ለበጋ ወቅት

የግቢያችን መናፈሻ በበጋ ወቀት ጥላ ከሌለው በምንፈልገው መጠን ልንዝናናበት አንችልም፤ በተለይም ከፍተኛ ሙቀት በሚኖርበት ጊዜ መናፈሻንን መጠቀም አንችልም።ስለዚህ ወቅትን እና ሰዓትን ሳንለይ ዓመቱን ሙሉ መጠቀም እንድንችል፤ ከቀላል ነግሮች የሚሰሩ ጣሪያዎች ወይም ሼድ መጠቀም ከዚያም አልፎ ንጹህ አየር እና በቂ ጥላ ለማግኘት እፅዋቶችን እና አትክልቶችን ማካተት ተገቢ ነው።በበጋ ወቅት የመኖሪያ ቦታዎ ቀዝቀዝ እንዲል ትላልቅ  ቅጠላማ ዛፍች ይመከራሉ።

ለክረምት ወቅት

በበጋ ወቅት ሙቀቱን ለመራቅ እንደምንፈልግ ፣ በክረምት ወቅት ደግሞ  ሙቀትን በእጅጉ እንፈልጋለን። በብርድ ምክንያት ጊዜችንን በሙሉ የግድ  በቤት ውስጥ እናጠፋለን ማለት አይደለም። ከቤት ውጭ የመኖሪያ ቦታን ዓመቱን በሙሉ መጠቀም መቻል ያስፈልጋል ፣ ስለዚህ ለቀዝቃዛ ወራት ሙቀት እንዴት ማግኘት እንዳለብን መፍትሄዎች ማሰብ ተገቢ ነው ፡፡

የተለመዱ በመናፈሻ ቦታችን  ሙቀትን ከሚሰጡን አማራጮች መካከል  የእሳት ምድጃዎች  በዋናነት ይጠቀሳሉ ፡፡

የእደ ጥበብ ውጤቶች

በመናፈሻ ቦታችን የእደ ጥበቦች ውጤቶችን ማካተት ተገቢ ነው። ባህላዊ ወይም ሀገራዊ የሆኑ የእደ ጥበብ ዉጤቶችን በመናፈሻ ቦታች ላይ ብናካትት የበለጠ ሳቢ እና ማራኪ እናደርገዋለን። ለምሳሌ ያለንበትን ቦታ ታሪክ እና ባህል የሚገልጹ ከእንጨት እና ከሸክላ የተሰሩ እንዲሁም ግድግዳ ላይ የሚሳሉ የጥበብ ዉጤቶችን ማካተት መናፈሻችንን እንድንወደው ያደርገናል።

አትክልት እና እጽዋት

አትክልትን እና እጽዋትን በቤታችን መናፈሻ ዉስጥ መጨመር መጠነ ሰፊ ጥቅም እድናገኝ ያግዛሉ። የሰው ልጅ በተፈጥሮ ከእጽዋት ለመኖር የሚያስፈልገውን ኦክስጂን ወይም ንፁህ አየር ያገኛል ይህም ማለት እጽዋትን መትከል በተጓድኝ ለጤናችን ጠቃሚ ናቸው ማለት ነው፤ እንዲሁም ለመናፈሻችን ዉበትን ይጨምራሉ፤ ከዚህ አልፎም በሙቀት ጊዜ እንደ ጥላ እንጠቀማቸዋለን።   

Pin It on Pinterest

Share This