ምቹ አልጋ ከልጅ እስከ አዋቂ ጥሩ እረፈት ወይም እንቅልፍ እንድናገኝ ከማገዙም ባሻገር አልጋችን ላይ ሆነን ለማንበብ ወይም ተያያዥ ስራዎችን ለመስራት ያግዛል።

የምቹ አልጋ ጥቅሞች

ምቹ አልጋ የጤና ችግር ላለበት ሰው በጤና ባለሙያዎች ወይም በፊዚዮቴራፒስት ዘንድ በቀዳሚነት ይመከራል። ነገር ግን ምቹ አልጋ ለመጠቀም የጤና ችግር ያለብን ሰው መሆን የለብንም።ምቹ እረፍት ለማግኘት ምቹ አልጋ ተመራጭ ነው።

በህይወት ዘይቤ ዉስጥ ምቹ አልጋ

ለማንበብ እና ቴሌቪዥን ለመመልከት:-ምቹ አልጋ የምንጠቀም ከሆነ  ለአንገት እና ለጀርባ ህመም የመጋለጥ እድላችንን እንቀንሳለን።እንዲሁም ከድካም በኋላ በቂ እረፍት ለማግኘትም ይጠቅማል

 የጤና ጥቅሞቹ

ለጤናማ የደም ዝውውር:-በየጊዜው እግራችን ወይም እጃችን  የሚወፍር ከሆነ እና የክብደት ለውጥ ካመጣን ፤ የምንጠቀምበትን አልጋ መፈተሽ ተገቢ ነው። ምቹ አልጋ የደም ዝውውራችንን በማስተካከል በየጊዜው የሚያጋጥመን የሰውነት መጨመር እንዲስተካከል ይረዳናል።እንዲሁም ደካማ የሚባል የደም ዝውውር ካለብን  ወይም ከፍተኛ የደም ግፊት ካለብን እና ስኳር ካለብን የምንጠቀመዉን አልጋ ምቹ ማድረግ አለብን።

ለሚስተካከሉ አልጋዎች ወይም ለሆስፒታል አልጋዎች እግራችንን ከስድስት ኢንች እስከ አስራ ሁለት ኢንች ከፍ ብሎ መተኛት የተሻለ የድም ዝውውር እንዲኖረን ይረዳናል። ጤናማ የሆነ የደም ዝውውር ከአንጎላችን ጀምሮ  ተመጣጣኝ የሆነ የኦክስጅን እና የንጥረ ነገር ክምችት ለሁሉም የሰዉነታችንን ክፍል ያደርሳል። ጤናማ የሆነ አንጎል ካለን ደግሞ ጥሩ የሆነ የአእምሮ ጤንነት እንዲሁም ዉጤታማ እንድንሆን እና እንዳንጨናነቅ ይረዳናል።

ጥሩ የደም ዝውውር መኖሩ የቆዳችንን ህዋስ ለማምረት እና የአጥንታችንን ጥንካሬ እና ቅርፅ ለመጠበቅ የሚረዳንን ኮላጅን ፕሮቲን ለማምረት  ይረዳናል።እንዲሁም የቆዳችን ጤናማነት ደግሞ እራሳችንን ከቫይረስ የመከላከል አቅማችንን ይጨምርልናል።

ለአጥንት መገጣጠሚያ ችግር:-በአመት ዉስጥ ከፍተኛ የታካሚ ቁጥር ያለው የመገጣጠሚያ በሽታ ሪፖርት ይደረጋል። ምቹ አልጋ የተመጣጣነ የሰውነት ግፊት በማሳደር ለመገጣጠሚያ በሽታ ተጋላጭነታችንን ይቀንሳል።

አሲድክ የሆኑ ህመሞችን ለመቀነስ:-ከራሳችን እና ከሰውነታችን በከፊል ከፍ ብለን መተኛት  የመሬት የስበት ኃይል  በተመጣጠን መልኩ ሰውነታችን ላይ እንዲሠራ እናደርጋለን እንዲሁም የሆዳችንን ንጥረ ነገሮች  ወደ ቧንቧ ውስጥ እንዳይገቡ በመከልከል ፣ የልብ ቃጠሎ (ሃርት በርንን ) እንከላከላለን ፡፡   

ለጀርባ ህመም:-በተደጋጋሚ ብዙ ሰዎች በቀን ዉሎአችን ዉስጥ የጀርባ ህመም ተሰማኝ ሲሉ ማድመጥ እንግዳ ነገር አይደለም። ለዚህም እንደ ዋነኛ ምክንያት ተደርጎ የሚወሰደው ምቹ አልጋ ወይም የተስተካከል አልጋ አለመጠቀም ነው። የተስተካከለ አልጋ የሰውነት ክብደታችንን በእኩል መጠን ለሁሉም የሰዉነት ክፍላችን በማከፋፈል ጀርባችን ላይ የሚያድረዉን ተጽንኦ ይቀንሳል። እንዲሁም የተስተካከለ ቁመና እንዲኖረን ያግዛል። ለምስሌ አልጋችን የሚተጣጠፍ ከሆነ፣ እግራችንን ከፍ አርገን መተኛት የታችኛዉን የወገባችንን ክፍል ተጾንኦ ለመቀነስ ይረዳል።

ማንኮራፋትን ለማቆም:-በዋነኛት  በምንተኛበት ጊዜ ከሚረብሹን ነገሮች አንዱ እና ዋነኛው ነገር ማንኮራፋት ነው።አንዳንዴ እንደውም የሚያንኮራፋው ድምጽ ከፍተኛ ከሆነ ክፍል ለይተን ልንተኛ ሁሉ እንችላለን።

ነገር ግን በተስተካካለ አልጋ የምንተኛ ከሆነ የማንኮራፋት እድላችንን ይቀንሳል።ይህም ማለት በቀላሉ  ሊስተካከሉ የሚችሉ አልጋዎች (አጀስቴብል አልጋዎች) ከሆኑ  ከትራስ አካባቢ ከፍታ ለመስጠት በሪሞት መቆጣጠር እንችላለን።

ማንኮራፋት አብዛኛውን ጊዜ የሚፈጠረው ተንጋለን በምንተኛበት ወይም ከአንገታችን ቀና ባላልንበት ጊዜ ነው። ይህም ማለት ምላሳች እና ስስ ህዋሳቸ የአየር መተንፈሻ ቱቧችንን በሚዘጉበት ወይም በሚያጠቡበት ጊዜ የማንኮራፈት እድላችን ከፍተኛ ይሆናል።

ትራሳችንን ከፍ ማድረግ ትንፋሻችንን በበቂ ሁኔታ እንዲንቀሳቀስ እና ለማንኮራፋት የሚዳርገንን የትንፋሽ እርግብግቢት ይቀንሳል። ከወገብ በላይ ያለው የሰውነታችን ክፍል ከፍ ወይም ቀና በሚልበት ጊዜ  የአንገት መሸማቀቅ እና  የትክሻ ህመም ይከላከላል። ነገር ግን በመጨናነቅ ምክንያት በምንተንፍስበት ጊዜ ፣ በሰውነት ውስጥ የተስትካካለ የውሃ ፍሰት እንዳይኖር ያደርጋል።

ምቹ ወይም የተስተካከለ አልጋ እና ምቹ ትራስ ምቾት ያለው እንቅልፍ እንድናገኝ ይረዱናል። 200 ሴንቲ ሜትር ወይም 6’6 ኢንች አካባቢ  እርዝማኔ ያለው ትራስ እርዝማኔ ካላቸው ትራሶች የተሻላ ምቾት ይሰጣል።እንዲሁም የትራሱ ዉፍረት ከ አስር ኢንች ወይም ከ ሃያ አምስት ሴንቲ ሜትር ውፍረት ያነሰ ቢሆን ይመከራል።ነገር ግን የትራሱ ዉፍረት ከዚህ ከበለጠ ምቾት አይሰጠንም።

ለምግብ መሸራሸር:-የተስተካከለ እና ምቹ አልጋ የበላነው ምግብ በቀላሉ እና ጤናማ በሆነ መንገድ እንዲሸራሸር ይረዳናል።

ከቀዶ ጥገና ቶሎ ለማገገም:-ከቀዶ ጥገና በኋላ እንዲሁም እንስቶች ልጅ ከወለዱ በኋላ በቂ እረፍት ማረግ አስፈላጊ ነው። ብዙን ጊዜ ፊዚሺያኖች ከህመማችን ቶሎ እንድናገግም እንዴት መተኛት እንዳለብን ይመክራሉ።

በቀዶ ጥገና ጉዳቶች እንዲሁም ከቁስል ህመሞች የሚመጡ ምቾት ማጣት እና አንዳንድ ጊዜ የተወሰኑ ቀዶ ጥገናዎችን ተከትሎ የሚመጣ ጭንቀት ፣ ምቹ የእንቅልፍ ቦታ ማግኘቱ ከባድ ሊሆን ይችላል ፡፡ የማገገሚያውን ሂደት ለማፋጠን ሐኪሞች ብዙውን ጊዜ በተወሰነ መልኩ የእንቅልፍ ሁኔታን ይመክራሉ። በእርግዝና ወቅት የሚፈጠረው የሆድ ግፊት መጨመር በአየር መተላለፊያዎች ላይ ውስንነትን ስለሚፈጥር ከባድ የሚባል  የእንቅልፍ እጦት እንዲጀምር ያነሳሳል ፡፡ ከወሊድ በኋላ በተደጋጋሚ የሚቀጥለው ይህ የእንቅልፍ ችግር  በሚወለዱት ልጆች ላይ የህይወት ደስተኛነት ላይ ተጓዳኝ ጉዳት ያደርሳል።

እንደ አንዳንድ ድህረ ገፅ ገለፃ ከሆነ ከወሊድ በኋላ ከቀላል እስከ ከባድ በሚባል ደረጃ በእንቅልፍ ማጣት ምክንያት ይሰቃዩ የነበሩ 50 % እንስቶች የላይኛውን የሰዉነት ክፍላቸው በአርባ አምስት ዲግሪ ከፍ ብለው በመተኛታቸው ምክንያት ከዚህ በሽታ በቀላሉ እንዳገገሙ ይፋ የሆኑ የምርምር ውጤቶችን ይገልፃሉ፡፡የሚገርመው ነገር ደግሞ ይህ ተመሳሳይ አቀማመጥ በሆድ ውስጥ ያለውን ውጥረትን ለማገገም ለሴቶች ይመከራል ፡፡ከቀዶ ጥገና ያገገሙ ሰዎች  ተመሳሳይ ችግር ላጋጠማቸው ለብዙ ሰዎች እንደ ህመማቸው አይነት የጤና ባለሙያ እርዳታ ቢጠይቁ  ጥሩ  እንደሆነ ይነገራል።

እግራችንን   ከፍ አድርገን መተኛት የሰዉነታችንን የተፈጥሮ አካል ወይም የጀርባ አጥንታችንን ደግፎ መያዝ ይችላል። እንዲሁም የሰዉነት ክብደታችንን በኩል መጠን ለሁሉም የሰዉነት አካላችን እንዲደርስ ይረዳናል። ለምሳሌ ፤ አልጋችን መስተካከል የሚችል ከሆነ የላይኛዉን የሰውነት ክፍላችንን በ45 ድግሪ ቀና ብሎ መተኛት ወይም ተንጋሎ መተኛት ክብደት ለመቀነስ ለሚሰሩ ሰዎች ምቹ እንቅልፍ ለመተኛት አይነተኛ መፍትሄ እንደሆነ ሪፖርቶች ይገልፃሉ። እንዲሁም የልብ ቀዶ ጥገና ለሚሰሩም ሰዎችም የላይኛዉን የሰውነት ክፍላችንን ቀና አድርጎ ማስተኛት የሚችል አልጋ ይመከራል። አልያም አልጋው መስተካከል የሚችል ከሆነ አልጋችንን ማስተካከል ተገቢ ነው።  የትክሻ ቀዶ ጥገና ለሚያጋጥማቸው ሰዎች ደግሞ  በተወሰነ መጠን የላይኛዉን ሰዉነታቸውን ከፍ ማድረግ ከገጠማቸው ጉዳቱ ቶሎ እንዲያገግሙ ያግዛቸዋል።

ለተመጣጠነ የጀርባ እና የእግር ግፊት:-ለረጅም ሰዓታት በማያ ገፅ ላይ የመንተኛ ከሆነ ወይም ተስማሚዉን የአልጋ አይነት ካልተጠቀምን በአከርካሪ አጥንታችን ዉስጥ የሚገኙትን የአከርካሪ አጥንቶች ክፍል ልንጎዳ  እና ልንጨምቅ እንችላለን።ይህ ደግሞ በ ‹ስካይቲካል ነርቭ› ላይ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል ፣ ከዝቅተኛው የጀርባችን ክፍል እስከ እግሮቻችን ዝቅተኛ የእግር ክፍል ድረስ በማንኛውም ቦታ ለህመም ይዳርገናል ፡፡ብዙውን ጊዜ የታችኛው የጀርባችንን ክፍል ተገቢውን ድጋፍ ካላገኘ የእንቅልፍ ስርዓታችን ላይ  ተፅንኦ ያሳዳርል ፡፡

 በትንሹ እግሮቻችንን ከፍ አድርገን መተኛት ለአከርካሪ አጥንታችን የተፈጥሮ እጥፋትነት ምቾት ይሰጣል እንዲሁም ክብደታችንን በዳሌ፣ በወገብ እንዲሁም በሽንጥ እኩል እንዲሰራጭ ያስችለዋል ፡፡ምቹ አልጋ እና ምቹ ፍራሽ እንዲሁም ውብ መኝታ ቤት በቂ እረፍት አግኝተን የቀን ውላችንን ሙሉ ለማድረግ ይረዳናል።ነግር ግን ከዚህ በተቃራኒው የሚሆን ከሆነ በቂ እረፍት ስለማናገኝ በቀን ዉሎአችን እንቸገራለን።

ከተኛን በኋላ ፈጣን የአይን ንቅናቄ (አርኤም) እንቅልፍ ከ70-90 ደቂቃዎች አካባቢ መጀመር አለበት ፡፡ ይህ እንዲሆን ደግሞ ምቹ አልጋ ማግኘት ግድ ይላል።ምክንያቱም የአርኤም እንቅልፍ የመማር ችሎታችን ላይ  እንዲሁም የማስታወስ አቅማች ላይ ወሳኝ የነርቭ ግንኙነቶች በመፍጠር አዎንታዊ ተጽዕኖ  ያሳድራል ።

Pin It on Pinterest

Share This