በዕለት ከዕለት ኑሮአችን ውስጥ ከምንጠቀምባቸው የፈርኒቸር ምርቶች ዉስጥ የቆዳ ፈርኒቸሮች ይገኙበታል። ለምሳሌ፣ የቆዳ ፈርኒቸር  ሶፋዎችን፣ወንበሮችን  ያጠቃልላል። ስለዚህ ለእነዚህ ምርቶች ተገቢውን እንክብካቤው ወይም ንጽህና መጠበቅ ያስፈልጋል። የቆዳ ፈርኒቸሮችን በተንከባከብናችው ልክ እረዘም ላለ ጊዜ መጠቀም እንችላለን ነገር ግን እንደሌሎች የፈርኒቸር ዉጤቶች በቀላሉ ለማጽዳት ምቹ ስላልሆኑ ተገቢውን የንጽህና መንገድ መከተል ጥሩ ነው።

ቅድመ ጥንቃቄ

 • የቆዳ ዕቃዎችን ከፍተኛ የፀሐይ ብርሃን ካለበት ቦታ ቢያንስ ስድስት ኢንች ማራቅ ፡፡ የፀሐይ ብርሃን ቆዳውን በማድረቅ በቀላሉ እንዲበላሽ ያደርገዋል ፡፡ ቆዳው ተጣጣፊ ከሆነ በቶሎ መሰንጠቅ እና መበላሸት ይጀምራል ፡፡
 • ዕቃዎቹን በማንጠቀምበት ጊዜ በቀዝቃዛና ደረቅ በሆነ ቦታ ውስጥ ማቆየት፡፡ እቃዎችን በእርጥበት ወይም እርጥብ ምድር ቤት ውስጥ ማስቀመጥ ፈርኒቸሮቹ እንዲበላሹ ያደርጋል።
 • የቆዳ ፈርኒቸሩን በፕላስቲክ ውስጥ አለማስቀመጥ ምክያቱም ቆዳውን አየር ከማግኘት መከልከል የቆዳ ፈርኒቸራችንን  በቀላሉ እንዲበላሽ ይጋብዛል።
 • የቆዳ ዕቃዎች አንዴ ከተበላሹ በኋላ በፊት ወደ ነበራቸው ውበት በቶሎ መመለስ ያስቸግራል ስለዚህ ቅድመ መከላከል ማድረግ ተገቢ ነው።
 • የቆዳ ዕቃዎችን የምናሳሳቸው ወይም የምንለጥጣቸው ከሆነ መደበኛ ቅርጻቸውን ያጣሉ።
 • በዉሃ ሳናበዛ በትንሹ ማርጠብ ወይም ማቀዝቀዝ

የቆዳ ዕቃዎቻችን በጣም ከደረቁ ወይም የመኮማተር ባህሪ የሚያሳዩ ከሆነ ሳይበዛ በትንሹ ማቀዝቀዝ ይመከራል።እንዲሁም የቆዳ ዕቃዎችን ያመረቱትን ድርጅት ማግኘት ከቻልን ማማከር።ብዙ አይነት  የቆዳ ዕቃዎችን የማጽጃ መንገዶች  ቢኖሩም የተለመዱት ግን ለዚህ አላማ የተሰሩ እና ፈርኒቸራችንን የማይጎዱ ቅባቶች እና ዘይቶች ናቸው።የቆዳ ዕቃዎችን ከአገልግሎት በአራቅናቸው ቁጥር የመበላሸት እድላቸውም በዛው ልክ ከፍተኛ ነው።

  የቆዳ ዕቃዎችን ማጽዳት

የቆዳ ዕቃዎችን ቢያንስ ከሳምንት አንድ ጊዜ በደረቅ ጨርቅ ማጽዳት። ነገር ግን ቶሎ ቶሎ ማጽዳት ካልቻልን፣ ሌላ ጊዜ በምናጸዳበት ጊዜ በጣም ያስቸግሩናል።ቆሻሻ ነገሮች በቆዳ ዕቃዎችን ላይ ሲቆዩ የእቃዎችን ሸካራነት እና የመኮማተር ባህሪ ይጨምራሉ።የቆዳ ዕቃዎችን በምናጸዳበት ጊዜ መጀመሪያ በንጹህ እጃችን መወልወል፤ በመቀጠል በደረቅ ጨርቅ መወልወል።

 • ምንም አይነት ሳሙና አለመጠቀም:-የኬሚካል ሳሙና ወይም ማጽጃ መጠቀም የቆዳ ዕቃዎችን ዉበት ለመጠበቅ    የሚያገልግለዉን የተፈጥሮ ዘይት ያሳጣናል።እንዲሁም የኬሚካል ሳሙና የቆዳ ዕቃዎችን በቀላሉ እንዲደርቁ ያደርጋል።
 • በለስላሳ እና መቶ ፐርሰንት ከጥጥ በተሰራ ነጭ ጨርቅ ማጽዳት
 • የቆዳ ፈርኒቸሮቻችን በቂ አየር እንዲያገኙ ማድረግ
 • በሌዘር ወይም በቆዳ ኮንዲሽነሮች ከ ሶስት እስክ ስድስት ወር ዉስጥ ባለው ማለስለስ
 • በአሞኒያ እንዲሁም በዉሃ የሚሟሙ ንጥረ ነገሮች አለመጠቀም
 • በእስክሪብቶም ሆነ በሌላ ቁስ በቀላሉ ስለሚጎዱ  ህጻናት የቆዳ ፈርኒቸሮችን እንዳይቧጭሩ ወይም እንዳያበላሹ መምከር
 • በእርጋታ ማድረቅ፡-አንዳንድ ጊዜ የቆዳ ዕቃዎቻችን ሳናስበው ለእርጥበት ሊዳረጉ ይችላሉ ለምሳሌ ቤት በምናጸዳበት ጊዜ ።ስለዚህ ቶሎ ለማድረቅ የጸሃይ ብርሃን ላይ አለማድረግ ወይም እሳት አካባቢ አለማድረግ።የቆዳ ዕቃዎቻችን ለከፍተኛ ሙቀት ባጋለጥንበት ጊዜ ኬሚካላዊ ቅርጻቸው ከማጣታቸው ባሻገር ቶሎ እንዲበላሹ ይዳርጋቸዋል።

 የተሸረካከቱ የቆዳ ዕቃዎችን ማስተካከል

በተቻለ መጠን የቆዳ ዕቃዎቻችን ለመሸረካከት እንዳይጋለጡ ተገቢዉን ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ ነገር ግን ይህን ማድረግ ካልቻልን ለማስተካከል ከዚህ በታች የጠቀስናቸው  ነገሮች ይመከራሉ።

ሙቅ ጨርቅ መጠቀም:-ብዙን ጊዜ የቆዳ ዕቃዎችን መሸረኳኮትወይም መኮራመት በሚያጋጥሙበት ጊዜ  በተወሰነ ሞቃታማ ጨርቅ በዝግታ የተበላሸውን ቦታ ማሸት።

ማጥቆሪያ  መጠቀም:-ምንም እንኳን ማጥቆርያ መጠቀም የሚመከር ባይሆንም የተበላሸዉን ቦታ ቶሎ ከቀሪው ቦታ ጋር ለማመሳሰል ማጥቆሪያ መጠቀም ይቻላል።

የቆዳ ፈርኒቸራችን ያለውን  አይነት ቀለም ከመርጠን በኋላ ደረቅ ብሩሽ ተጠቅመን የተበላሸዉን የፈርኒቸራችን ክፍል መቀባት፤ ቀብተን ከጨረስን በኋላ በደረቅ ጨርቅ ማዳረቅ።

ፈርኒቸራችን ከመጠን በላይ ዉሃ ከያዘ፤ ስፖንጅ ወይም በደንብ ዉሃ መቋጠር በሚችል ጨርቅ እርጥበቱን ለመቀነስ መሞከር ነገር ግን ፈርኒቸራችን ለማዳረቅ  ምንም አይነት ሙቀት አለመጠቀም።

ባለሙያ  መጥራት:-የቆዳ ዕቃዎች የተጎዱበት መጠን በጣም ከፍተኛ ከሆነ እና በእኛ አቅም ማስተካከል ካልቻልን የፈርኒቸር ባለሙያ ማናገር።

የቆዳ ሶፋ

እስካሁን በአጠቃላይ የቆዳ ፈርኒቸሮችን እንዴት እንጠቀም የሚለዉን ካየን ለቤታችን ሆነ ለስራ ቦታችን ዉበት የሚያጎናጽፍልንን የቆዳ ሶፋን ወይም ሌዘር ሶፋን እንዴት እንከባከባለን የሚለውን ሃሳብ እንይ።

ሶፋችንን ቢያንስ ከሁለት እስከ አራት ሳምንት ዉስጥ አንድ ጊዜ ማጽዳት ይጠበቅብናል ነገር ግን ሶፋችንን በስፕሬይ አለማጽዳት ምክንያቱም ስፕሬዩ የያዘው የኬሚካል ዉህድ ከሶፋችን ቆዳ ተፈጥሮአዊ የኬሚካል  ውህድ ጋር በእጅጉ አይስማማም ይህም የሶፋችንን ዉበት ያሳጣል።ለስላሳ ማጽጃዎችን ተጠቅመን ሁሉንም የሶፋችንን ክፍል በደንብ ማጽዳት ተገቢ ነው።  ሶፋችን አጽድተን ከጨረስን በኋላ ቢያንስ ለአንድ ቀን ከሶፋው ላይ አለመቀመጥ እንዲሁም ሁሉንም መስኮቶች እና በሮች መክፈት።

ቀላል ቀለም ያላቸው የቆዳ አይነቶች ለምሳሌ ነጭ፣ክሬም እና አመዳማ ቀለም ያላቸው ሶፋዎች በቀላሉ ሌላ ቀለም የመሣብ አቅማቸው  ከፍተኛ ነው። ስለዚህ የሶፋ ልብስ ወይም ክሬም መጠቀም እነዚህ ነገሮችን ለመከላከል ያግዛል።  የሶፋ ቆዳን ከቆሻሻ የሚከላከሉ ልብሶች ሶፋውን ከጠጣር ቆሻሻ ብቻ ሳይሆን ሶፋው ላይ ከሚፈሱ ፈሳሽ ቆሻሻዎች የመከላከል አቅም አላቸው።

የፀሃይ ብርሃን እና የቆዳ ሶፋዎች

የቆዳ ሶፋችን ለስላሳ እና ዉብ እንደሆነ ለማቆየት ከፀሃይ ብርሃን ቢያንስ ከ6 ኢንች ርቆ መቀመጥ እንዳለበት ባለሞያዎች ያስረዳሉ።ብዙን ጊዜ የቆዳ ሶፋችንን ለፀሃይ እና ለከፍተኛ ሙቀት የምንዳርግ ከሆነ ሶፋችን ልስላሴውን አጥቶ ለሸካራነት እና ለዛ ቢስ እንዲሆን እንዳርገዋለን።

ስለዚህ  በቤታችንን ሆነ በመስሪያ ቦታችን ዉስጥ ሶፋችንን በምናስቀምጥበት ጊዜ ከፍተኛ የፀሃይ ብርሃን በሚያገኝ መስኮት በኩል አለማስቀመጥ። እንዲሁም ከምድጃ፣ ኤየር ኮንዲሽነሮች እና ራዲያተሮች በስድስት ኢንች እርቀት ማስቀመጥ ተገቢ ነው። የመንኖርበት ቦታ ጠባብ ከሆነ ደግሞ በአንፃራዊነት ዝቅተኛ ሙቀት ካለበት ቦታ ላይ  ሌዘር ሶፋችንን  ማስቀመጥ።

ፈሳሽ ቆሻሻ እና የቆዳ ሶፋዎች

ምንም እንኳን የቆዳ ሶፋዎችን ከሌሎች የጨርቅ ሶፋዎች በጥንካሬቸው እና ለረዥም ጊዜ በመቆየታቸው ብናቃቸውም፣ አልፎ አልፎ በሚያጋጥማቸው ፈሳሽ ቆሻሻዎች እና ምግቦች ቶሎ የመቆሸሽ ባህሪይ አላቸው፤ ቶሎ ለማጽዳትም ሲያስቸግሩ ይስተዋላል።በሌዘር ሶፋችን ላይ ፈሳሽ ቆሻሻ ከተደፋበት ወዲያዉኑ ማፅዳት ሶፋችን የሚያጋጥመው የማርክ (የተለየ ቅለመት ወይም  ምልክት)    እና የመቆሸሸ እድል እንቀንሳለን።

በመጀመሪያ ፈሳሽ ቆሻሻው እንደተደፋ፣ ቆዳዉን ከማርጠቡ በፊት በፍጥነት በደረቅ ጨርቅ እርጥበቱን መቀነስ ወይም መጥረግ። ነገር ግን እነዚህ   ፈሳሽ ቆሻሻዎች በሚያጋጥሙን ጊዜ ቅባት ያላቸው እንዲሁም ግሪሲ የሆኑ ማፅጃዎች ከመጠቀም ለሌዘር ሶፋችን የተሰሩ ማፅጃዎች መጠቀም። ስለዚህ  ለሌዘር ሶፋዎች የተሰሩ ማፅጃዎች በቤታችን ዉስጥ ማስቀመጥ ያስፈልጋል።

የቆዳ ሶፋችንን በየጊዜው ማለስለስ

የሶፋችን ቆዳ የእራሱ የሆነ በየጊዜው መቀባት ያለበት ዘይት አለው። የቆዳ ዘይቱ ሶፋችንን ለስላሳ እና ምቹ እንዲሆን ቢያግዝም በተደጋጋሚ መጠቀም የቆዳውን የተፈጥሮ ባህሪ ያሳጣዋል። ነገር ግን የሶፋ ቆዳውን ሳይብዛም እንዲሁም ሳያንስ ቅባቶችን መቀባት ቆዳው ከመሸረካከት እና ምቾት ካለመስጠት ባህሪ ይጠብቀዋል።በአሁን ወቅት የሌዘር ሶፋዎች ዋጋቸው በጣም ዉድ ነው ስለዚህ እንደ ዋጋቸው በቂ እና ተገቢውን አገልግሎታቸውን ወይም ረዘም ላለ ጊዜ ለመጠቀም በቂ እንክብካቤ ማድረግ ተገቢ ነው።ነገር ግን አብዛኞቻችን ከተወሰኑ ሰዎች በስተቀር የእኛ የራሳችን የሆኑት  የቤት እቃዎችን ዘወትር ስንከባከብ አይታይም። 

Pin It on Pinterest

Share This