የሰውን ልጅ የእውቀት አድማስ  ለማስፋት ፣   ጸጥ ባለ ቦታ ላይ ተንሰራፍቶ፣ በምሁራን በተመረጡ እና በተከተቡ መጽሃፍት፣ ጋዜጦች፣ ዶክመንቶች፣ዲ.ቪ.ዲዎች፣ ኢ መጽሃፍቶች፣ሲዲዎች እና ማይክሮፊልሞች  ታጅቦ ቤተ መጽሃፍት ለትውልድ አገልግሎት ይሰጣል።

ቤተ መጽሃፍት ከምድረ ቀድምቷ ሃገራችን ኢትዮጵያ በ5004 ኪሎ ሜትር ርቃ በምድር እስያ  ደቡባዊ ምዕራብ አቅጣጫ በምትገኘው ክርሰንት ወይም በዛሬዋ ኢራቅ አካባቢ በ3000 አመተ አለም ከክርስቶስ ልደት በፊት እንደተጀመር መዛግብት ያስረዳሉ። በሃገራችን ደግሞ የመጀመሪያው ብሄራዊ ቤተ መጽሃፍት በአጼ ሃይሌ ስላሴ ዘመነ መንግስት በአዲስ አበባ በ1930 አመተ ምህረት እንደተጀመር ይነገራል።

ነገር ግን ቤተ መጽሃፍታችን እንደተጀመረበት የእድሜ እርዝማኔ እንዳደጉት ሃገራት ቀላል እና ቀላጣፋ አገልግሎት ሲሰጥ አይስተዋልም፤ ለዚህም እንደ ዋና ምክንያት የምናነሳው የፈርኒቸር ወይም ቤተ መጽሃፍት ዉስጥ የምንገለገልባቸው ቁሶች ከጤና፣ ከምቾት አንጻር የሚሰጡትን አገልግሎት የፈርኒቸር ባለሙያዎች በደንብ ግንዛቤ አለመኖር  ወይም  በተለምዶ መስራት ነው።

አንባቢያን ረዘም ያለ ሰአት የሚያሳልፉባቸው የቤተ መጽሃፍት ፈርኒቸሮች ሲሰሩ  ሊታሰቡባቸው የሚገቡ ጠቃሚ እና አንኳር ሃሳቦችን እናያለን።

ራዕይ እና ግቦች

በመጀመሪያ ፣ ለቦታው አጠቃላይ እይታ እና ግቦችን ማሰብ ተገቢ ነው ፡፡ ግቦችን ለማስቀመጥ  የሚከተሉትን ጥያቄዎች እራሳችንን መጠየቅ አለብን።

  • የቤተ መጽሃፍት ተጠቃሚዉን ፍላጎት ማወቅ
  • የመጨረሻዉን ዲዛይን ማሰብ
  • ቤተ መጽሃፍቱ የሚሰጣቸውን አገልግሎት በደንብ ማጤን

የፈርኒቸሮች አገልግሎት

የቤተ መጽሃፍታችን ፈርኒቸሮችን እንዴት አገልግሎት እንደሚሰጡ  ከፍጥነት እና ከምቾት አንጻር መመልከት።

ዉበት

ቤተ መጽሃፍቱ ዉበቱን የጠበቀ እና ማራኪ እንዲሆን፤ እንዲሁም ቤተ መጽሃፍቱ ያለበትን አካባቢ ታሪክ፣ ባህል እና ማንነት የሚገልጽ ቢሆን ለእንግዶችም ሆነ ለአካባቢ ማህበረሰብ በእይታ ወይም በጉብኝት ብቻ ግላጭ እና ቁም ነገር አዘል ይሆናል።

የፈርኒቸሮች ጥንካሬ

ለቤተ-መጽሐፍታችን ፈርኒቸሮችን በምንመርጥበት ጊዜ ዘላቂነት ከግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ ነው ፡፡ በጥሩ ሁኔታ ዲዛይን የተደረጉ ፈርኒቸሮች  ዘመን ተሻጋሪዎች ሆነው እናገኛቸዋል ፡፡

ለግል ንባብ

ግለሰቦች በዋናነት ቤተ-መጻሕፍትን የሚጎበኙት ራሳቸውን ችለው ለማጥናት ወይም አንድን የተወሰነ ርዕስ ለማጥናት ነው ፡፡ ለእነዚህ ሰዎች  ምቹ  መቀመጫዎች እና ንባብን የሚያበረታቱ የሳሎን ወንበሮችን በመጋበዝ የተለያዩ የመቀመጫ አማራጮችን እናቀርባለን ፡፡ ለግለሰቦች የምንሰጠው የቤተ-መጻሕፍት የቤት ዕቃዎች ስብስብ በአንድ ጊዜ ብዙ የማጣቀሻ ቁሳቁሶችን ለመጠቀም የሚያስችል ሲሆን ጫጫታ እና ትኩረትን የሚከፋፍሉ ነገሮችን የሚቀንሱ እና የግል ትኩረትን የሚሰበሰቡ መሆን አለባቸው ፡፡እንዲሁም ላፕቶፕዎችን እና የንባብ መሳሪያዎችን አንድ  ላይ መያዝ እንዲችል የግል ማንበቢያችን  42 ኢንች በ 30 ኢንች ቢሆን ይመረጣል።

በቡድን ለማንበብ

ቤተ-መጻሕፍትን አልፎ አልፎ የቡድን ንባብ ለማዳበር፣ በጋራ ፕሮጀችቶችን ለመስራት፣ ቱቶር ለመስጠት እንዲሁም ለውይይት እንጠቀምበታለን።ይህንን አላማ ለማሳካት ደግሞ የፈርኒቸሮችን የአሰራር ዲዛይን ይጠይቃል። ለግሩብ ስራ የሚሆኑ ፈርኒቸሮችን ዲዛይን ስናረግ እና የሚቀመጡበትን ቦታ ስንመርጥ ሌሎችን የማይረብሽ ቦታ መሆን አለበት።

ለቴክኖሎጂ እና ለሚዲያ አጠቃቀም

ቤተ-መጻሕፍቶች ዛሬ  ላይ መጽሃፍትን ብቻ ከመያዝ ባሻገር የተንቀሳቃሽ ምስል እና መልቲ ሚዲያን ያካተተ አገልግሎት ይሰጣሉ።ስለዚህ ቤተ-መጻሕፍታችን የኤልክትሪክ ሃይል ለኮምፒተሮች፣ለስልኮች የሚያስተላልፍበትን መንገድ ከፈርኒቸሮች ጋር አብሮ ማዘመን ተገቢ ነው።

የቤተ መጽሃፍት ጠረጴዛዎች እና ወንበሮች

 ብዙን ጊዜ ክብ ጠረጴዛዎች ለቡድን ጥናቶች ይመክራሉ ምክንያቱም ለውይይት ምቹ ናቸው።አራት ማዕዘን ጠረጴዛዎች ደግሞ ለግል ንባብ ይመከራሉ። እያንዳንዱ ጠረጴዛ ቢያንስ ስድስት ካሬ ጫማ ቦታ ለአንባቢያን መስጠት አለበት ።ቀጥ ያሉ ወንበሮች (ከጠረጴዛ   ጋር በቁመት መዛመድ የሚችሉ) ብዙውን ጊዜያቸውን በቤተ-መጻሕፍ ዉስጥ ለሚያሳልፉ አንባቢያን የተሻሉ መፍትሔ ናቸው ፡፡ፈርኒቸሮችን ከመግዛታችን በፊት በእነዚህ ወንበሮች ተቀመጦ  ምቾታቸዉን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ፡፡ ተቀምጠን በምንፈትን ጊዜ መጠየቅ ያለቡን ነጥቦች፡

  • እግሮቻችን በ90 ድግሪ አንግል ወንበሩ  ማስቀመጥ መቻሉን፤ ምክንያቱም ትኩረታችንን ለመሰብሰብ እግሮቻቸን 90  ድግሪ ማጠፍ ተገቢ ስለሆነ
  • ለአካል ጉዳተኞች ምቹ አገልግሎት መስጠት መቻሉን ማረጋገጥ
  • ለረዥም እና አጭር ቁመት ላላቸው ተጠቃሚዎች ያማከለ ቁመት ያለው ወንበር ማድረግ

የቤተ የመጻህፍት መደርደሪያ

የተለመደው የመደርደሪያ ቁመት አስራ ሁለት ኢንች ሆኖ በተጠቃሚዎች አይን ትይዩ መሆን አለበት ይህም ማለት አራት ወይም አምስት ጫማ ከፍታ ማለት ነው። እንዲሁም በመደርደሪያዎች መካከል ያለው ልዩነት ከስምንት እስከ አስራ ሁለት ኢንች እርቀት ቢኖረው ይመረጣል።

የመደርደሪያችን ስፋት ቤተ መጻሃፍታችን በቂ ቦታ ካለው 12 ኢንች ቢሆን ተግቢ ነው ነገር ግን በቂ ቦታ ማግኘት ካልቻልን ዘጠኝ ኢንች እንዲሆን ይመከራል። በአማካኝ የአብዛኛው መደርደሪያዎች ክብደት ከ50 እስከ 100 ኪሎ ግራም ክብደትን ይመዝናሉ።  

የቤተ መጻህፍት ወንበር

ለጥናት የተሻለ ምቾት የሚሰጡ ወንበሮች ቀጥ ብለን መቀመጥ  እንድንችል እና ዉጤታማ እንድንሆን  ይረዱናል።ከዚህ በታች ለንባብ ምቾት የሚሰጡ ወንበሮችን እናያለን።

ለጀርባችን ምቾት የሚሰጡ ወንበሮች:-ረዘም ላለ ሰአት በምናነብበት ጊዜ ለትክሻች እና  እንዲሁም ለወገብ ህመም የመጋለጥ አድላችን ከፍተኛ ነው። ነገር ግን ከፍታ ያላቸው እና ለጀርባችን ምቾት የሚሰጡ ወንበሮችን መጠቀም፣ለበሽታ የመጋለጥ እድላችንን ይቀንሱታል።

በተደጋጋሚ ወይም አልፎ አልፎ በሚከሰት የሆድ ህመም የሚሠቃዩ አንባቢያን በእነዚህ ወንበሮች  ላይ እንዲቀመጡ ይመከራል ፡፡ አብዛኛዉን ጊዜ በቤተ መጻህፍት ዉስጥ አንባቢያን ቀኑን ሙሉ ተቀምጠው ሲያነቡ ይስተዋላል ስለዚህ በሰዎች ወገብ ላይ ጭንቀትን የሚቀንስ  ወይም ለጀርባችን ምቾት የሚሰጡ ወንበሮች ላይ ኢንቬስት ማድረግ አንባቢያን የበለጠ ደስተኞች እንዲሆኑ እና ጥሩ ስሜት እንዲሰማቸው  ያደርጋል ፡፡

ተሽከርካሪ ወንበሮች:-ተሽከርካሪ ወንበሮች ከተቀመጥንበት ሳንነሳ የምንፈልግውን ነገር እየተዟዟርን መከወን እንችላለን በተለይም መነሳት ለማይችሉ የአካል ጉዳተኞች ተመራጭ ነው።

ሶፋ ወንበሮች:-የሶፋ ወንበሮች ረዘም ላለ ሰአት አይመከሩም ምክንያቱም ለጤናችን ከሚሰጡን ጥቅሞች ይልቅ ለቤተ መጽሃፍታችን የተሻለ  ውበት  ለመስጠት ያግዛሉ ስለዚህ የሶፋ ወንበሮች እርፍት ከምናደርግባቸው ክፍል ዉስጥ ቢቀመጡ ተመራጭ ይሆናል።

የቤተ መጻህፍት ጠረጴዛ

የቤተ-መጻህፍት ጠረጴዛዎች ለመፃፍና ለማጥናት ስለምንጠቀምባቸው መደበኛዉን የጠረጴዛ ቁመት ወይም  ከ 28 እስከ 30 ኢንች ቁመት ያላቸው መሆን አለባቸው ፡፡ ብዙዎቹ አራት ማዕዘን ወይም ሞላላ ቅርፅ   አላቸው ፡፡የቤተ መጻህፍት ጠረጴዛችን ብዙውን ጊዜ ከእንጨት የተሠሩ ቢሆኑ ይመከራል ይህም ማለት ዝግባ፣ ጽድ እንዲሁም ከዋርካ የተሰሩ ቢሆኑ ይመረጣል ምክንያቱም ከብረት የሚሰሩ ጠረጰዛዎች በቅዝቃዜ ወቅት ብርድ የመሳብ እና በሙቀት ወቅት ደግሞ የመሞቃቸው መጠን ከፍተኛ ስለሆነ ነው።

የቤተ መጻህፍት ቀለም

ለቤተ-መጽሐፍታችን የምንጠቀመዉ ቀለም  ፈዛዛ ወይም በተለምዶ ትኩረት የማይስብ እና ለእይታ  ምቾት እንዲሁም እረፍት የሚሰጥ መሆን አለበት ፡፡ ግድግዳዎቹን  በምንቀባበት ጊዜ ደማቅ  የሚያብረቀርቁ ወይም በጣም ደብዛዛ  እና የሚረብሹ ቀለሞችን አለመጠቀም ፤ ለምሳሌ ፣ ፀሐያማ ቢጫ ፣ ደማቅ ብርቱካናማ ፣   እና ኖራ ቀለሞች  አንባቢያን እንዲያነቡ የመጋበዝ እድላቸው በአንጻራዊነት  ደካማ ነው ፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ቀለል ያሉ እንደ  ወርቃማ ፣ ነጻ ያለ ሰማያዊ፣ወይራ አረንጓዴ እንዲሁም የክሪም ቀለሞች የንባብ ፍላጎትን የሚያበረታቱ ቀለሞች ምድብ ዉስጥ ይካተታሉ።

መብራቶች

በቤተ-መጻህፍታችን ዉስጥ የምንጠቀምባቸው መብራቶች ለመደርደሪያዎቹ እና ለአንባቢያን በቂ ብርሃን የሚሰጡ ነገር ግን  ዝቅተኛ አጠቃላይ የኤሌክትሪክ ጭነት ወይም የኤሌክትሪክ ሎድ የሚጠቀሙ ቢሆን ይመረጣል ፡፡

Pin It on Pinterest

Share This