አዲስ ቤት ስንገባም ሆነ የቤት ዕቃዎችን እንደገና ስናደራጅ ፣ እራሳችን ከምንጠይቃቸው ብዙ ጥያቄዎች መካከል አንዱ “ቴሌቪዥኔን የት ላስቀምጥ ?” የሚል ነው ፡፡ ጥሩ የሚባለዉን ቦታም ለመምረጥ ብዙን ጊዜ ስንቸገር ይታያል ፡፡

በዚች ጦማር  አንዳንድ ጠቃሚ የሚባሉ ምክሮችን ልንሰጣችሁ ወደድን።

 ቴሌቪዥን በምናስቀምጥበት ጊዜ ከግምት ውስጥ መግባት ያለባቸው ሦስት ነገሮች ከዚህ በታች በዝርዝር ተቀምጠዋል

ክፍል

የክፍላችንን አቀማመጥ ማጤን እና የት ማስቀመጥ እንዳለብንን ማወቅ፤ ስራችንን ያቀልልናል፤ ለምሳሌ በየትኛው ግድግዳ ላይ መስኮታችን እና በራችን እንደተሰራ ግንዛቤ ዉስጥ ማስገባት፤ ፎቶ ግራፎች ወይም የአርት ጥበቦች ባሉበት እና በጣም የተጨናነቀ ቦታ ላይ አለማስቀመጥ።እንዲሁም  ወደ ቤት ዉስጥ የሚገባው የጸሃይ ብርሃን ፣  የቴሌቪዥኑን ስክሪን የማያገኝበት ቦታ ላይ ማስቀመጥ። ብዙን ጊዜ ቴሌቪዥናችን በሳሎን ዉስጥ ቢሆን ይመረጣል።

ቴሌቪዥናችን ከምኝታ ቤታችን ውጭ ማድረግ የሚሰጡንን ጥቅም እንይ፦

ለተሻል እንቅልፍ

ከመተኛታችን በፊት ቴሌቪዥን መመልከት የእንቅልፍ ዑደትን የሚያስተጓጉል መሆኑን የሚያመለክቱ ጥናቶች አሉ ፡፡ ቴሌቪዥኑን ከመኝታ ቤት ማውጣት  የተሻለ እንቅልፍ እንድናገኝ ይረዳል። ይህም ማለት እኛም በቂ እረፍት እንድናገኝ እና የበለጠ ውጤታማ እንድንሆን ያስችላል ።

የቀን ዉሎን ለመገምገም

ምሽት ላይ የቀን ዉሎን  መገምገም፤ ከስህተቶች ለመማር እና እራስን ለማሻሻል ያግዛል፤ ነገር ግን አብዛኛው ሰው ከምኝታ በፊት ቴሌቪዥን ወይም ሌላ መሰል ነገሮች ላይ ጊዜውን ሲያሳልፍ ይታያል።

የቀን ዉሎን በንጽህ ህሊና ለመንደፍ

እያንዳንዱ ቀን አዲስ ቀን ነው፤ አዲስ እና ንጹህ ህሊና ይፈጥራል። ስለዚህ በዚህ ባዶ ህሊና ላይ ቀን ላይ ምን መስራት እንዳለብን እቅድ ማዘጋጅት ይኖርብናል። ቴሌቪዥናችን በመኝታ ክፍላችን ዉስጥ ማስቀመጥ፤ የቀን እቅዳችንን በአግባቡ እንዳንነድፍ ሊያዘናጋን ይችላል።

ለልጆች

በመኝታ ክፍሎቻቸው ውስጥ ቴሌቪዥኖች ያላቸው ልጆች በትምህርት ቤት ፈተናዎች ዝቅተኛ ውጤት ያስመዘገቡ እና የመኝታ ችግር ያለባቸው እንድሆኑ ይነገራል ፡፡ እንዲሁም በመኝታ ክፍሉ ውስጥ ቴሌቪዥን መኖሩ ከመጠን በላይ ለሆነ ክብደት ተጋላጭነት ይዳርጋል ፡፡ እንዲሁም ልጆች የሚከታተሉዋቸውን ፕሮግራም ለመቆጣጠር አዳጋች ነው።

ለተሰራበት አላማ ማዋል

ወጥ ቤቶችን ለማብሰያነት እንጠቀማለን ፣ የመመገቢያ ክፍሎች ለመመገብ፣ የመጫወቻ ክፍሎች እንዲሁ ለመጫወቻነት እንጠቀማለን። የስራ ቁሳቁሶችን ፣ ኮምፒውተሮችን እና ቴሌቪዥኖችን  ከክፍሉ     ውጭ በመውሰድ መኝታ ቤታችንንም ለምኝታ ብቻ መጠቀም ተገቢ ነው፡፡

ቴሌቪዥኖች አቧራ ይስባሉ

ሁሉም የአሌክትሪክ ቁሶች በተለይም ስታቲክ ኤሌክትሪኮች  አቧራ የመሳብ አቅማቸው ከፍተኛ ነው።የተሻለ አየር ለማግኘት እነዚህ ቁሶች ከኛ ማራቅ ተገቢ ነው።

የንባብ ክህሎት ለማዳበር

ምሽት ላይ በትንሹ ማንባብ ቶሎ እንድንተኛ ያግዛል ፡፡ ከንባብ የምናገኛቸው ጥቅሞች  ከቴሌቪዥን ከምናገናኛችው ጥቅሞች የበለጡ ናቸው ፡፡ቴሌቪዥናችንን ከመኝታ ቤት ውስጥ ማውጣት የበለጠ እንድናነብ ያበረታታል።

የትዳር ፍቅርን ለመጨመር

አንዳንድ ጥንዶች ለፍቅራቸው መስጠት ከሚገባቸው ሰአት በላይ ለቴሌቭዥን ፕሮግራም የሚሰጡት ሰአት ሲበልጥ ይስተዋላል ይህም በትዳራቸው ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ያሳርፋል፡፡

የቤት ዕቃዎች

ሳሎናችን ዉስጥ የቤት እቃዎች አቀማመጥ ወሳኝ ነገር ሲሆን ቴሌቭዥናችንን ዋና ቦታ (Focal point ) ላይ ማስቀመጥ ይመከራል፤ ይህም ማለት በተለምዶ ኮርነር ላይ ማስቀመጥ ሳይሆን ሁሉም ሰው ከአለበት አቅጣጫ ላይ ሆኖ ማየት የሚችልበት ቢሆን ይመረጣል።

ቴሌቪዥን

ቀደም ሲል ከነበሩት ቴሌቪዥኖች ዛሬ ላይ ያሉት ቴሌቪዥኖች በቅርጽ ትልቅ ናቸው። ስለዚህ  የቴሌቪዥናችን መጠን ቦታዉን ይወስነዋል።እንዲሁም የቴሌቪዥን አቀማመጣችን  በእይታችን ላይ ተጽዕኖ እንደማይኖረው ማረጋገጥ። ለምሳሌ ፣ በቀጥታ የማይመለከቷቸው ከሆነ ኤል.ሲ.ዲ ቴሌቪዥኖች ደብዛዛ ሆነው ሊታዩ ይችላሉ ፣ ስለሆነም በእያንዳንዱ ማእዘን (ወይም ቢያንስ በክፍሉ ውስጥ ባለው እያንዳንዱ መቀመጫ) ቴሌቪዥኑን  ማየት እንደምንችል እርግጠኛ መሆን ተገቢ ነው።

የጥናት ባለሙያዎች እንደሚገልጹት የቴሌቭዝናችንን መጠን እና የእይታ እርቀትን እንደሚከተለው ያቀርቡታል፡-

 • 26 ”  ስክሪን = ከ 3 እስከ 5.5 ጫማ
 • 32 ”  ስክሪን  = ከ 4 እስከ 6.5 ጫማ
 • 37 ”  ስክሪን  = ከ 4.5 እስከ 7.5 ጫማ
 • 40 ”  ስክሪን   = ከ 5 እስከ 8.5 ጫማ
 • 46 ”  ስክሪን  = ከ 6 እስከ 9.5 ጫማ
 • 52 ”  ስክሪን  = ከ 6.5 እስከ 11 ጫማ
 • 58 ”  ስክሪን = ከ 7 እስከ 12 ጫማ
 • 65 ”  ስክሪን = ከ 8 እስከ 13.5 ጫማ
 • 70 ”  ስክሪን = ከ 9 እስከ 15 ጫማ

ቴሌቪዥናችንን ለመመልከት የሚመከርው ርቀት ከቴሌቪዥኑ ሰያፍ(diagonal) ርዝመት 2.5 እጥፍ የሚበልጥ መሆን       አለበት። ከፍተኛ ጥራት ላላቸው ቴሌቪዥኖች ፣ ከቴሌቪዥኑ ርዝመት 1.5 እጥፍ የበለጠ ርቀት ቢኖራቸው ጥሩ ነው፡፡

ቴሌቭዝናችን ስናስቀምጥ ማድረግ ያለብን እና ማድረግ የሌለብንን ነገሮች፡-

ሀ – ማድረግ ያለብን ነገሮች

 • ቲቪው የሚቀመጥበት ቁመት መመጠን

ምንም እንኳን ይህ ነው ተብሎ የተመጠነ ከፍታ ባይኖረውም፤ ቴሌቭዝናችን በአይናችን ከፍታ ልክ ወይም ዝቅ ማረግ ይመከራል።

 • ቴሌቭዝናችን የሚቀመጥበትን ቦታ ማጤን

 የክፍል መብራት እና ነፀብራቆች የቴሌቪዥን ምስሎችን ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ስለሚያሳድሩ እነሱንም ከግምት ዉስጥ ማስግባት፡፡

 ማድረግ የሌለብን ነገሮች

 •  ከእሳት ምድጃ በላይ ማስቀመጥ
 • ለእይታ በማይመች ቦታ ላይ ማስቀመጥ

ቴሌቪዥናችንን በሁለት መንገድ ማስቀመጥ እንችላለን። የመጀመሪያው ቲቪ ስታንድ ላይ ማስቀመጥ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ግድግዳ ላይ መለጠፍ ነው።

ሀ- ቲቪ ስታንድ መጠቀም

ቀላሉ እና ቶሎ ለማስቀመጥ የሚመቸው ቲቪ ስታንድ ነው፤ ጠፍጣፋ ቦታ ላይ ማስቀመጥ ሲሆን ዘመናዊ እና ጠፍጣፋ የምንላቸው ቴሌቪዥኖች ለምሳሌ ኤል.ኢ.ዲ፣ ፕላዝማ የመሳሰሉት ቲቪዎች ቲቭ ስታንድ አካተው ገበያ ላይ ዉላሉ።

እነዚህ ብዙውን ጊዜ  ለማስቀመጥ በጣም ቀላል ናቸው ፣ ስለዚህ በመሰረታዊ መሳሪያዎች በፍጥነት በቤት ውስጥ ሊከናወኑ ይችላሉ። የጠረጴዛ ወይም የቴሌቪዥን ማቆሚያ በቦታው ካለ በቀላሉ ቴሌቪዥኑን በእሱ ላይ ማስቀመጥ ይችላል ፡፡

ቴሌቪዥኑን ለማስቀመጥ የጠረጴዛ አናት ወይም ሌላ ጠፍጣፋ ቦታ ያስፈልጋል ስለዚህ የወለል ወይም የክፍላችንን ቦታ ይይዛል፡፡

ሌላው የቲቪ ስታንድ ጉዳት የቲቪውን ደህንነት ጨምሮ በቤት ውስጥ ያሉ ህፃናት ጋርም ሊደርስ ይችላል፡፡ ቴሌቪዥኑ ከማንኛውም ነገር ጋር ስላልተያያዘ  ቴሌቪዥኑን ራሱ ሊጎዳ ወይም  ሰው ሊጎዳ ይችላል ምክንያቱም በትንሽ እና ድንገተኛ ግፊት በቀላሉ መውደቅ ስለሚችል።

ለ – ግድግዳ ላይ መለጠፍ

ቴሌቪዥናችንንግድግዳ ላይ መለጠፍ የክፍላችንን ቦታ በአግባቡ እንድንጠቀም እና በቀላሉ ቴሌቪዥናችንን ላይ ጉዳት እንዳይደርስበት ይረዳናል። ነግር ግን የሚሰጠው ጥቅም  እንዳለ ሆኖ ይህንን ለመስራት በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎችን ማማከር ይጠይቃል።

በተጨማሪም  ከባድ ንዝረቶች ባሉባቸው አካባቢዎች ለምሳሌ በግንባታ ቦታዎች ፣ በባቡር ሀዲዶች ወይም በባቡር ጣቢያዎች አጠገብ ተጨማሪ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን ፡፡

እንዲሁም ከቴሌቪዥናችንን ጀርባ ላይ ያሉትን ገመዶች እና ፖርቶች(ቀዳዳዎች) ለማግኘት ከባድ ነው ምክንያቱም በቴሌቪዥናችንን እና በግድግዳው መካካል ያለው ርቀት ትንሽ ስለሚሆን።

ይህ መሣሪያዎችን(Equipments) ከቴሌቪዥን ጋር በማገናኘት ረገድም ችግር ሊፈጥር ይችላል፤ ወይም ይህን ለማድረግ ሌሎች ኬብሎችን ይፈልጋል ፡፡ በተጨማሪም እንደ ግድግዳው እና ኤችዲኤምአይ ያሉ ኬብሎች በግልፅ ግድግዳው ውስጥ ካልተደበቁ ሊታዩ ይችላሉ ፣ ይህም ሌላ ተጨማሪ የኤሌክትሪክ እና ሲቪል ሥራን ይፈልጋል ፡፡

Pin It on Pinterest

Share This