ከቤት-ዕቃ የምንፈልገውን ያህል ደስታ ለማግኘት የሚከተለውን መመሪያ መከተል እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡የቤት-ዕቃችንን ውበቱን እንደጠበቀ እንዴት ማቆየት እንችላለን?

 • አጠቃቀሙን በሚገልፀው ወረቀት ላይ ባለው መሰረት ጊዜውን ጠብቆ እድሳት ማድረግ
 • የቤት-ዕቃውን እርጥበት ባለው ጨርቅ ካፀዳን በኃላ በደረቅ እንጨት መጥረግ
 • ምንጊዜም ፈሳሽ ጠብ ካለበት በፍጥነት ማፅዳት
 • ቅባታማነት ባለው ሴንቴቲክ በሆነ ጨርቅ ተሸፍኖ ከሆነ ከ24 ሰዓት በላይ አለማቆየት
 • ሁልዜም ትኩስ ወይም እርጥበታማ ዕቃዎችን ማስቀመጫ መጠቀም
 • ሹልነት ወይም ስለት ያላቸውን መሳሪያዎች በምንጠቀምበት ጊዜ ጥብቅ መደገፊያን መጠቀም
 • የእንጨት የቤት-ዕቃዎችን ቀለም ባለበት ጠብቆ ለማቆየት ከቀጥተኛ የፀሐይብርሃን በተቻለን አቅም ማራቅ
 • የቤት-ዕቃን እጅግ ከፍ ያለ ሙቀት ካላቸው ምድጃዎች አቅራቢያ አለማስቀመጥ
 • ጉዳት ደርሶበት ከተገኘ ወደሚመለከተው ባለሙያ ማሳወቅ

የእንክብካቤ መመሪያዎቹ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አይነቶች በመጠገን እና ጥንቃቄ ማድረግን ያስረዳል

 • ሳሙናን የሚቀበሉ ገፆች
 • ዘይትን የሚቀበሉ ገፆች
 • በእንጨት መንከባከቢያዎችን የሚቀበሉ ገፆች
 • በቅብ የሚጠበቁ የቤት-ዕቃ ገፆች
 • የሚጠረዙ ገፆች

ሳሙናን የሚቀበሉ ገፆች

የዕለት ተዕለት እንክብካቤዎች፡ በጨርቅ መጥረግ፤ ሙሉለሙሉ በሳሙናማው ውህድ ውስጥ እርጥበቱን ከወሰደ በኃላ መጨመቅ የሚችል ቢሆን ይመረጣል፡፡ለማጠቢያነት የሚያገለግል የትኛውንም ፈሳሽ በቤት-ዕቃው ገፅ ላይ ማሳረፍ እና መጠቀም አይገባም፡፡ሁሉም በሳሙና የተፀዱ የቤት-ዕቃዎች የሚፈለገውን ያህል የዘይት ይዘት ባላቸው ነጭ ሳሙናዎች መፀዳት ይኖርበታል፡፡

የሳሙና ውህድ፡ ሁለት የሻይ ማንኪያ የደቀቀ ነጭ ሳሙና በአንድ ሊትር የፈላ ውሃ ውስጥ መጨመር፡፡ ሳሙናው እንዲደባለቅ ማድረግ እና ውህዱ እንዲቀዘቅዝ ማድረግ (ከበዛ እስከ 20ዲግሪሴንቲግሬድ፡፡ እንክብካቤውን ከመጀመር በፊት ውህዱን በሚገባ ማማሰል፡፡ ተግባር ላይ ለማዋል በሳሙናው ዘይት ውስጥ የተነከረ ስፖንጅ መጠቀም፡፡ ይህም በተቻለ መጠን አነስተኛ የሆነ የውሃ ይዘት ያለው እና በቂ የሚባል የሳሙና ዘይት ውስጥ ከሶስት እስከ አምስት ደቂቃ አሰቀምጦ ማቆየት ነው፡፡ ሳሙናው ከመጠረጉ በፊት ከደረቀም ተጨማሪ ሳሙናን ማድረግ እና ትርፍ ሳሙናውን መጥረግ ነው፡፡ የሳሙና ውህዱን በቀጥታ የቤት-ዕቃው ገፅ ላይ ማፍሰስ ተገቢ አይደለም፡፡ የቤት-ዕቃው የሳሙናውን ዘይት እንጂ ውሃውን አይፈልግም፡፡ ከመጠን በላይ የሆነ ውሃን የምናሳርፍበት ከሆነ እንጨቱ ይደርቃል፤ ስንጥቅም ሊፈጠርበት ይችላል፡፡

ማለስለሻ ሽቦን ወይም ቅባት ማስወገጃዎችን መቼም ቢሆን መጠቀም አይገባም፡፡ተመርቶ አገልግሎት መስጠት የጀመረበት የመጀመሪያዎቹን አስራአራት ቀናት በሙሉ ማከም ያስፈልጋል፡፡ በመቀጠል ግን የሚያስፈልግበትን ጊዜ እያየን ማከም ይቻላል፡፡እምብዛም አገልግሎት የማይሰጡ የቤት-ዕቃዎችም ቢሆኑ በሚያስፈልጋቸው ጊዜ እና የሚያስፈልጋቸውን የማከም አይነት በቋሚነት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡የቤት-ዕቃው በጣም የቆሸሸም እንደሆነ፤ በሳሙናና እና ውሃ ውህድ እና የማብሰያቤት ስፖንጅን በመጠቀም ሻካራውን ገፅ በእንጨቱ ቅንጣት አቅጣጫ በማሸት ማፅዳት እና  ቆሻሻውን ሳሙና ወዲያውኑ ማስወገድ ይቻላል፡፡ የቤት-ዕቃው ከተጫረ፤ በመጀመሪያ የእንጨቱን ቅንጣቶች አቅጣጫ በተከተለ መልኩ በብርጭቆ ወረቀት መወልወል እና በሳሙና የሚሰጠውን ጥገና ከመስጠት በፊት በስፖንጅ መወልወል ነው፡፡ ወደ ጠረጴዛ የመጣንም እንደሆነ ከሚታየው የእንጨቱ የላይኛው ክፍል ገፅ በተጨማሪ የማይታየውን የታችኛውን ገፅ ከውጥረት ለመጠበቅ ወይም ለማስተካከል እንጨቱን ማከም ያስፈልጋል፡፡የቤት-ዕቃውን ለመጀመሪያ ጊዜ በምናክምበት ጊዜ የእንጨት ቅንጣቶቹ ወደ ላይ ወጣ ብለው ሊታዩ እና እንጨቱ ሻካራነት እንዲያመጣ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡

በማፅጃ ስፖንጅ በሚፀዳበት ጊዜ ጥንቃቄ ሊታከልበት ይገባል፡፡  ፍንጭ፡- የሳሙናውን ውህድ ቆጥቦ ማጠራቀም እና ስፖንጁን በሳሙናው ውስጥ ማኖር፤ መያዣውንም አጥብቆ ማሸግ፡፡ ሳሙናው ከመጠን በላይ ከወፈረ በሚፈላ ውሃ ማቅጠን ነው፡፡

ዘይትን የሚቀበሉ ገፆች

የዘወትር ህክምና (እንክብካቤ)፡ እርጥበታማ በሆነ ጨርቅ መጥረግ እና በመቀጠልም በደረቅ ጨርቅ መልሶ ማድረቅ፡፡ለጥገና ሁልጊዜም ቢሆን የዘይት ህክምናውን ከመጀመር በፊት ማፅዳት የግድ ነው፡፡ደማቅ ቀለም የሌለው ጨርቅ መጠቀም፤ በእንጨቱ ላይ ጭረት ካለም በብርጭቆ ወረቀት ወይም በሻካራ ስፖንጅ መወልወል ነው፡፡ጥቂት ዘይትን በእንጨቱ ላይ በማድረግ የእንጨቱን ቅንጣት በመከተል ማለስለስ፣ ወዲያውኑ በደረቅ ጨርቅ መጥረግ ተገቢ ነው፡፡ በጨርቅ ላይ በቂ የሆነ ዘይትን ማፍሰስ እና በሚገባ እንዲዳረስልንም ጨርቁን በመጠቀም የተደላደለ ንብር ያለውን የቤት-ዕቃ መጥረግ፣ እንዲሰርግም ከሶስት እስከ አምስት ደቂቃ መተው ከዚያም በደረቅ ጨርቅ ከመጥረግ በፊት ትርፍ የሆነውን ዘይት መጥረግ ነው፡፡ ይህንኑ ህክምና (አያያዝ) በአመት ሁለት ወይም ሶስት ጊዜ በሚያስፈልግበት ጊዜ እና አይነት አይቶ እንደሁኔታው መደጋገም፡፡ የላይኛውን ገፅ ለማፅዳት አንድ በአንድ የሻይ ማንኪያ ውህድ ውስጥ እርጥበት አግኝቶ የበሰበሰ እና የተጨመቀ ጨርቅን መጠቀም፡፡

ማስታወሻ፡ ማጠቢያ ፈሳሾችን በፍፁም መጠቀም አይገባም፡፡ የዘይት ሕክምናውን ከመጀመር በፊት እንጨቱ እንዲደርቅ አስራሁለት ሰዓታትን መስጠት ነው፡፡ ዘይትን በቀጥታ ወደ የቤት-ዕቃው ማፍሰስ ወይም የብርጭቆ ወረቀትን በዚህ ጊዜ መጠቀም አይገባም፡፡ የቤት-ዕቃውን ጥቅም ላይ ማዋል በተጀመረባቸው የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ዘይታማ ገፆችን ማጠብ መደረግ የሌለበት ነገር ነው፡፡ ምክንያቱም ይህ ህይወታዊ ዘይት ለመጠንከር ጊዜን ይወስዳል፡፡ በዚህ መልኩ የምናዘጋጃቸው የቤት-ዕቃዎች ጥቅም ላይ ከመዋላቸው በፊት ለአራት ሳምንታት ማከም ይገባል፡፡

በእንጨት መንከባከቢያዎች የሚቀበሉ ገፆች

የእንጨት መንከባከቢያ ጥልቀት ያለው እንክብካቤን ለማድረግ ተመራጭ ሲሆን ለመጠገንም ቀላልነት ያለው ነው፡፡ የእንጨት መጠገኛ ማፅዳትን እና መንከባከብን ያቀናጀ ነው፡፡የመንከባከቢያ ውጤቱ ቀጭን ተከላካይ ገፅን በመጨመር ከፍ ያለ የመቋቋም ሀይል ከመስጠቱም በላይ ገፁን ያፀዳል፡፡ ገፁም ብሩህ እና ንፁህነቱን ይዞ የሚቀጥል ይሆናል፡፡የዘወትር ህክምና (እንክብካቤ)፡ ለዘወትር እንክብካቤ ማፅጃ (መንከባከቢያውን) በቀጥታ ገፁ ላይ መርጨት በመቀጠልም በንፁህና ደረቅ ጨርቅ መጥረግ ነው፡፡በልዩነት ደረቅ የሆኑ ገፆች፡ ማፅጃ (መንከባከቢያውን) በቀጥታ ገፁ ላይ መርጨት እና ወደ እንጨቱ ቅንጣቶች አቅጣጫ በመፈተጊያ ማሸት እና በቂ የሆነ እርጥበት ባለው ጨርቅ መጥረግ ነው፡፡ እንጨቱ ከህክምናው በኃላ ካኮፈኮፈ ጥቂት ማለስለሻን በመጠቀም ማለስለስ ጥሩ የሚባል ነው፡፡

በቅብ የሚጠበቁ የቤት-ዕቃ ገፆች

የዘወትር ህክምና (እንክብካቤ)፡ለዘወትር እንክብካቤ በንፁህ እርጥበታማ ጨርቅ መወልወል እና በደረቅ ጨርቅ መጥረግና ማድረቅ ነው፡፡ በመቀጠልም ደረቅ ጨርቅን በመጠቀም መጥረግ እና ማድረቅ ሲሆን በቅብ የሚጠበቁ የቤት-ዕቃ ገፆች ትክክለኛ የሚባል የመጠገኛ ውጤት የላቸውም፡፡

የመጠበቂያ ቅቦችን መጠቀም ገፆችን እንደማሸግ ይቆጠራል፡፡ ፈሳሾች፣አቧራና የመሳሰሉት ወደ ውስጥ እንዳይገቡ ያደርጋል፡፡ የመጠበቂያ ቅቦች ያላቸው የቤት-ዕቃ ገፆች በአጠቃላይ ለአካላዊ ጉዳቶች በቀላሉ ሊጋለጡ የሚችሉ ናቸው፡፡ እነዚህ የቤት-ዕቃ ገፆች ጥቃቅን በሆኑ ጭረቶች ወይም ግጭቶች እጅግ ሊጎዱ የሚችሉ እና ጉዳታቸውም ሊጠገን የሚችል አይደለም፡፡

የሚጠረዙ ገፆች

የዘወትር ህክምና (እንክብካቤ)፡ለዘወትር እንክብካቤ በንፁህ እርጥበታማ ጨርቅ መወልወል እና በደረቅ ጨርቅ መጥረግና ማድረቅ ነው፡፡ በተለየ ሁኔታ ለቆሸሹ ገፆችም ይህንኑ እንክብካቤ መድገም ነው፡፡ከፍተኛ ግፊት ባለው ሁኔታ የተደረጉ ጥረዛዎች እጅግ ጠንካራ እና ጤናማ ሲሆኑ የተለየ ጥገና የሚያስፈልጋቸው አይደሉም፡፡ በአጠቃላይ ጥቅም፤ ንፅህናውን በጠበቀ ሁኔታ ማቆየት ቀላል ነው፡፡

ማስታወስ የሚገቡን ነጥቦች እነዚህ ናቸው

 • ጥርዞች እንደ መጥበሻ፣ትኩስ መጠጥ ማቅረቢያ ብርጭቆዎች ያሉ የጋሉ ዕቃዎችን መቋቋም አይችሉም
 • ለስለስ ያሉ የሚያነፁ ነገሮችን መጠቀም ይመከራል
 • እንደ ብርጭቆ ወረቀት ወይም የማሻ ዱቄት ያሉ ማፅጃዎችን በፍፁም አለመጠቀም
 • ሰም እና መሠል ቁሶች ቆሻሻን ስለሚሰበስቡ መጠቀም አያስፈልግም
 • ከጠርዝ ማፅጃ ውጪ የሆኑ ማፅጃዎችን ከተጠቀምን በመቀጠል ሞቅ ባለ ውሃ ማፅዳት ያስፈልጋል፡፡

Pin It on Pinterest

Share This