ሰላማዊ እንቅልፍ  ለመተኛት የመኝታ ቤትዎ የቤት ዕቃዎች ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ።  ከመጠን እና ቁሳቁስ እስከ ተግባራዊነት እና ዘይቤ ድረስ ለእርስዎ የሚሆኑ ትክክለኛ የቤት እቃዎችን መፈለግ አስፈላጊ ነው ፡፡ ለሚወዱት ምቹ  እንቅልፍ፣ ዘና ለማለት የመኝታ ቤትዎን ዕቃዎች በሚመርጡበት ጊዜ ከግምት ውስጥ መግባት ያለባቸውን ልብ ይበሉ።

ለብዙዎቻችን የመኝታ ክፍሎቻችንን መለዋወጥ አስቸጋሪ ሆኖ ይታየናል፤ በመሆኑም  ደጋግመን  ስናስውብ እንኳን መኝታ ቤቱ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ነገሮችን ልብ ባለማለታችን እና ቅደም ተከተሉን ባለመጠበቃችን የጊዜ ብክነት ከማስከተል በዘለለ የምንፈይዳቸው ነገሮች ትርጉም አልባ ሆነው ይታያሉ፡፡

የመኝታ ክፍል ክፍተት

በመኝታ ክፍሎ ውስጥ የሚገኘውን የቦታ ስፋት ያስተውሉ፡፡ለልብስ ባስቀመጫ የሚሆኑ ቁምሳጥኖች  ትክክለኛ አቀማመጥ እና ቦታ የትኛው ነው? ጥሩ መጠን ያለው የልብስ ማስቀመጫ ቢያንስ ስድስት ጫማ ርዝመት ሊኖረው ይገባል ፡፡ በአልጋው እና በሌሎች ቁሳቁሶች መካከል ምን ያህል ቦታ ሊተው ይገባዋል? ትልቅ መኝታ ቤት ካለዎት በአነስተኛ  የመቀመጫ ቦታ ብዙ ነገር ማስተናገድ ሚችሉ ሲሆን የእንጨት አልጋዎች አነስተኛ ቦታን የሚይዙ በመሆናቸው ለልጆች መኝታ ክፍሎች ጥሩ አማራጭ ናቸው ፡፡ ትክክለኛዎቹ የቤት ዕቃዎች መጠነኛ ክፍል ሳይበዛባቸው ክፍልዎን ጥሩ አድርገው ሊያሳዩ ይችላሉ።

የአልጋ ምርጫ

አልጋ በማንኛውም የመኝታ ክፍል እምብርት ላይ መሆን የሚገባቸው ስለሆነ ይህን ተግባር ቅድሚያ ይስጡት፣ ቀጥሎም በዙሪያው ያሉትን ሌሎች ነገሮች ሁሉ ያጣምሩ። የትኛውን የመኝታ አልጋ መምረጥ እንዳለብዎ እርግጠኛ ካልሆኑ የመኝታ ቤትዎን ልኬቶች ለክተው ያንን እንደ መመሪያ ይጠቀሙ ፡፡ በዚህ ቦታ ውስጥ ካሉ ሌሎች ነገሮች ሁሉ ጋር በቀላሉ የሚስማማዎትን እና የሚወዱትን ቀለም የሚያሳይ መኝታ ይፈልጉ፡፡እርስዎ የሚመርጡት የውስጥ ማስጌጫ ዘይቤ ምንድ ነው? ጥንታዊ ወይስ ባህላዊ? የመረጧቸው የቤት ዕቃዎች ይህንን ዘይቤ ማንፀባረቅ አለባቸው ፡፡ በተጨማሪም ማቆየት የሚፈልጓቸው ነባር ቅርጻቅርፆች ካሉዎት ከእነሱ ጋር የሚስማሙ አዳዲስ ቅርጻቅርፆች በማካተት ውበቱን መጨመር ይችላሉ፡፡ የመኝታ ቤቱ ጌጣጌጥ ሰላማዊ እና የማይረብሽ መሆን ስለሚኖርበት በአንድ ወጥ ጭብጥ ዙሪያ ለመስራት ይሞክሩ ፡፡

ጥራት

በጣም አስፈላጊው ነገር ለመኝታ ክፍሉ አዲሱ የቤት እቃዎ ጥራት ያለው ቁሳቁስ በመጠቀም መገንባቱን ያረጋግጡ ፡፡ መቃኖች ከጠንካራ  እንጨት የተሠሩ መሆን አለባቸው ፣ ቁም ሳጥኖች እና ባለመስታወት ኮመዲኖች ላይ መሳቢያዎች ሲከፍቷቸው እና ሲዘጉዋቸው በእርጋታ መንሸራተት አለባቸው ። የሚፈልጓቸውን የቤት እቃዎች የጥራት ደረጃ ለመለየት ይህ የተሻለው መንገድ ነው ፡፡ የቤት እቃዎች ኢንቬስትሜንት መሆናቸውን ያስታውሱ ስለሆነም ለሚመጡት ዓመታት ፍላጎቶችዎን የሚያሟሉ እቃዎችን መምረጥዎ በጣም አስፈላጊ ነው ፡፡

ቁም ሳጥኖች

ቁም ሳጥኖች ለመኝታ ቤትዎ ዉበት ከመስጠት ባለፈ  ለእቃ ማስቀመጫነት ያገለግላሉ ፡፡መብራት እና ሰዓት ከላይ ፣ እስካርፍ እና መነፅሮች በመካከለኛው መደርደሪያ ላይ ቢያስቀምጡ ለእይታ ጥሩ ይሆናሉ፡፡

የመኝታ ክፍል ቀለም ጥምረት

ለቤት ዕቃዎችዎ እና  ግድግዳዎችዎ  የመረጧቸው ቀለሞች በመኝታ ክፍልዎ ውስጥ የሚፈልጉትን ድባብ ይፈጥራሉ ፡፡ ሰማያዊ፣ ነጭ እና ግራጫማ ቀለሞች የተረጋጋ፣ጸጥ ያለ እና ጥሩ የእረፍት ምሽት ሊሰጡዎት የሚችሉ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ቀይ እና ቢጫ ቀለሞችን በጥምረት መጠቀም ለቤቱ ፍካት በመስጠት ለመነቃቃት እና ለተነሳሽነት ያገለግላሉ፡፡ ጥቁር እና ሐምራዊ ቀለምንም በማቀላቀል መጠቀም ለቤቶ ክቡድነት በማላበስ ግርማሞገስ ያጎናፅፋል፡፡በመሆኑም በጣምራ ሊገለገሉባቸው የሚችሉትን የቀለም አይነቶች በመምረጥ መኝታ ቤቶን ማስዋብ ይችላሉ፡፡ ሥዕሎች እና ቀለሞች በሁሉም ቦታ ላይ በሚሆኑበት ግዜ ለማስጌጥ ከባድ ነው ብሎም መኝታ ቤታችን ከማስጌጥ ይልቅ አሰልቺ እንዲሆን ያደርጉታል ፡፡ ይበልጥ  ቀለሞቹን ለማመጣጠን  እንደ አረንጓዴ እና ሀምራዊ ያሉ ጠንካራ ቀለሞች ለማተኮር ሲረዱ ቀለል ያሉት ቀለሞች ደግሞ (እንደ ነጭ ያሉት)  እይታው እንዲመጣጠን ይረዳሉ፡፡

የመኝታ መብራት

በመኝታ ቤትዎ ውስጥ ያለው መብራት ደብዛዛ እና  የተመጣጠነ ጨረር የሚፈነጥቅ መሆን እንዳለበት ይነገራል፡፡ የተለያዩ መፃህፍትን ለማንበብ ከፈለጉ ከራስጌዎ አጠገብ መኖር ያለበት የግድግዳ መብራት የግድ አስፈላጊ ነው። መብራቱ ደብዘዝ እንዲል የሚፈለገውም አይንን እንዳይጎዳ እና በጣም ደማቅ መብራቶች እንብዛም ለመኝታ ቤቱ አስፈላጊ ባለመሆናቸው ነው፤በመሆኑም በመኝታ ክፍሉ ውስጥ የሚያንጸባርቁ መብራቶችን እና ከፍተኛ ጨረር የሚፈነጥቁ መብራቶችን ያስወግዱ፤የመኝታ ቤትዎን አዲስ ለማድረግ ምቹ ወንበር ፣ ቋሚ መብራት እና  መጽሐፍ ያስቀምጡ፡፡በተለይ ደሞ በአልጋ ላይ በመሆን ማንበብ የሚመችዎ ከሆነ ብርሃን በበቂ እና  በትክክለኛው አንግል ማግኘት የበለጠ ምቾት ይሰጥዎታል።

 በጀት

የቤት ዕቃዎች መግዛት ብዙ ገንዘብ ሊያስከፍሉ ይችላሉ ፡፡ ስለሆነም ቀድሞ በጀት መበጀት  ያስፈልግዎታል ፡፡ በቂ ገንዘብ ከሌሎት ሁሉንም ነገር በአንድ ጊዜ ማግኘት እና የግሎ ለማድረግ አስቸጋሪ ሊሆን ስለሚችል ደረጃ በደረጃ ማድረግ የተሻለ ነው ፡፡በጀት ለመበጀት የመጀመሪያው ነጥብ ዋጋ ማወዳደር ነው፡፡ ወደ ብዙ መደብሮች በመሄድ ከእሶ ዝንባሌ ጋር የሚስማማውን ለመምረጥ ጥራቱን ይፈትሹ በተጨማሪም ከእርሶ አቅም ጋር የሚመጣጠነውን ይሸምቱ።የመኝታ ቤትዎን የቤት ዕቃዎች ስብስብ በሚመርጡበት ጊዜ ሁሉንም መስፈርቶች ለማሟላት ይሞክሩ፤ ሁሉም መሟላት ያለባቸው ነገሮች ከተሟሉ የእርስዎ መሠረታዊ ፍላጎት እና የጥራት መስፈርት በጥሩ ሁኔታ ተሸፍኗል ማለት ይቻላል፡፡

Pin It on Pinterest

Share This