የመዝገበ ቃላት እና የአውደጥበብ ምንጮች የቤት-ዕቃዎችን ለመግለፅ እንደ ተቀጥላዎች፣ መሳሪያ እና ተንቀሳቃሽ እቃዎች ያሉ ስያሜዎችን ይጠቀማሉ፡፡ የቤት-ዕቃን መንደፍ በስሜት፣ማስተዋል፣የንድፍ ችሎታ፣የምህንድስና መስፈርቶች እና ችግር ፈቺ የሆነ እና ስፋት ያለው እውቀት ያስፈልጋል፡፡ ንድፍም ለመስራት የሚያነሳሳ መንፈስ፣እሳቤ እና ቁርጠኛ የሆነ ለሌሎች ምቾት የመስጠት ፍላጎት ያስፈልጋል፡፡

የቤት-ዕቃን ንድፍ ከማውጣት ወደ መፈብረክ የመሄዱ የማይቀር ለውጥ ግልፅ እና ድብቅ የሆነውን መፈብረክ በመንደፍ ሂደት ያለውን ተፅዕኖ ያስገኛል፡፡ ወደ የቤት-እቃ ንድፍ ማውጣት ከመሄድ በፊት በሁለቱ መካከል ያለውን መሰረተ አመጣጥ እና ትብብር ማጤን አስፈላጊ ነው፡፡

የቤት-ዕቃ

አንድን ክፍል ወይም ህንፃ ለኑሮ ወይም ለስራ የተመቸ እንዲሆን እንደ ጠረጴዛ፣ወንበር ወይም መፃፊያ ጠረጴዛ እና ሌሎችም ለአንድ ስራ ወይም ተግባር ለመፈፀም የሚያግዙ አነስተኛ ተቀጥላ  እቃዎች ናቸው፡፡ በብዙ መግለጫዎች፤ የቤት-ዕቃ ተንቀሳቃሽ የሆኑ አገልግሎት ሰጪ ነገሮችን ያጠቃልላል፡፡ እነዚህ ፈርጆችም

 • የሰው አካልን መደገፊያ መሳሪያዎች
 • የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን የሚደግፉ ክፍሎች እና ነገሮች
 • ማሳያ እና ማከማቻ
 • የጠፈር ክፍልፍል

የቤት-ዕቃዎች የሰዎችን አቀማመጥ፣እረፍት፣ስራ እና ጨዋታ ለማገዝ የተነደፉ እና የተፈበረኩ ናቸው፡፡ ይህ ገፅታ ስፋት ያለው የቤት-ዕቃ የተፈላጊ ተግባር መዋቅር የቤት-ዕቃው ዋነኛ ተግባር ነው፡፡ ምንም እንኳን ተግባር፣ጠቃሚነት እና ማህበረሰባዊ ጠቀሜታ የቤት-ዕቃ አስፈላጊ ሁኔታ ቢሆኑም ጠቀሜታ ታላቅ የሆነ ንድፍን የመቀስቀሱ ነገር ያልተለመደ ሁኔታ ነው፡፡

የቤት-ዕቃ ንድፍ በውበት፣በንድፍ መርህ፣በፅንሰ-ሃሳብ፣በቁሳቁስ ባህርያት፣በአመራረት ቴክኖሎጂዎች፣በንግድ ስራ ምጣኔ ሃብት፣በአካባቢያዊ የንድፍ መርሆች እና በሚገኝበት አካባቢ ሃሳብ የሚሳብ ሲሆን እነዚህም ከአሰራር፣መገልገያነት እና ማህበረሰባዊ ግልጋሎቱ ጋር የሚያዋህደው እና የሚያስተሳስረው ነው፡፡

ለቤት-ዕቃ ያለን ዕሳቤ እና ስሜት ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ተብለው የሚታወቁ ከቤት-ዕቃው ንድፍ ጋር የተያያዙ እነዚህ ናቸው

 • ስነውበት (የዘይቤ ትርጉም)
 • ታሪካዊ ክስትት (ካለፈው ጊዜ የተገኙ ምሳሌዎች)
 • የንድፍ መርሆች (አሃድነት፣መዋሃድ፣ደረጃ)
 • ተግባር እና ማህበረሰባዊ ጠቀሜታ (ስነምቾት፣ደስታ፣ቅርበት)
 • የንድፍ ሂደት (ስእል፣የተደጋገመ ሽፋን፣የሞዴል ጥናቶች፣በቁጥር የሚሰራ ሞዴል አወጣጥ
 • ቁስ (ምደባ፣ባህርይ፣ሊገኝ የሚችል፣ዋጋ)
 • የፍብረካ ሂደት (በእጅ፣በቁጥር የሚሰራ ኃይል)
 • አካባቢያዊ የንድፍ ነገረ ጉዳይ (ቀጣይነት፣መልሶ ለመጠቀም የሚሆን ቁሳቁስ፣የጋዝ ልቀትን ማስቀረት)
 • አካባቢያዊ አገባብ (ለቤት-ዕቃው የጠፈር አቀማመጥ)
 • ሙያዊ ተግባራት (ኢኮኖሚያዊ፣ህጋዊ እና የንግድ ስራ ውሳኔዎች)

ተፈላጊ ተግባርን ከግምት ውስጥ ማስገባት የንድፍ ሃሳቦችን ልማት ማስተላለፍ ይችላሉ፤ ማነሳሳት ላይ ግን እምብዛም ለውጥ ሲያመጡ አይታዩም፡፡ ሙያዊ ተግባራት በማህበረሰባዊ ጠቀሜታ ውስጥ በግንባታ እና ቀጠናን በማስፋት እና በስያሜ፤ መሰረት ያላቸው ነገሮች ናቸው፡፡

ሰፊ የማህበረሰባዊ ጠቀሜታ መደቦች በአንድ ተግባር ላይ የሚመረኮዙ እና በቦታ፣በስራ እና በጊዜ ተፅዕኖ የሚያድርባቸው ናቸው፡፡ የላቲን (ቅፅል) ፊደል ሞባይል ማለት ተንቀሳቃሽ ማለት ሲሆን ከቤት-ዕቃ አስፈላጊ ባህሪያት ውስጥም አንዱ ነው፡፡ የፈረንሳይኛው ሚዩብልስ፣ የቱርክኛው ሞቢልያ፣ የፖላንድኛው ናምጀስታጅ ሁሉም የእንግሊዘኛው ፍቺያቸው ፈርኒቸር (የቤት-ዕቃ) ነው፡፡ ከአንድ ህንፃ አካላዊ መዋቅር ንድፍ አውጪዎች በተንቀሳቃሽ አካላት እና በቋሚ አካላት ንድፍ አወጣጥ ላይ የጠፈር ግንኙነት ለመፍጠር የራሱ የሆነ እግዛ ያደርጋል፡፡ በመጠን፣አቀማመጥ እና የቤት-ዕቃዎቹ የሚቀመጡበት አቅጣጫ የቤት-ዕቃ ንድፍ አወጣጥን ከህንፃ ጥበብ እና ከቤት ውስጥ ንድፍ አወጣጥ ጋር በአንድ ላይ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ የቦታ ስርዓት እና የቦታ አደረጃጀት የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ::መደበኛ በጥበብ የተደረደሩ ቦታን የተረጋገጠ ቡድን የሚከፋፍል እና በኃላም ለጠፈር ጠቋሚነት አላማ እቅድ የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ መግድሮች በጎነ አራት ወይም ጎነ ሶስት፣ክብ ወይም ጎነ ሰባት ንብብሮሽ ሊሰራ ይችላል፡፡

መስመራዊ ፡ በጠፈር ቅደም ተከተል ወይም ዘይቤ መጠቀም እና የተዛመደ እና የተሰራ መሆን

የተጠቃለለ ፡ ወደ ማእከላዊ ቦታ ወይም ነጥብ ዙሪያ የጠፈር ትስስርን መፍጠር

ክቦሽ ፡ ከማዕከላዊ ስፍራ ወይም ነጥብ የፈነጠቀ፡፡ (እየተጥመለመለ ወይም እየተጠቀለለ በክብ፣በቀጥታ መስመር ወይም በጥምዝምዝ መስመር የሚሄድ

ክምችት ፡ እርስበርስበቅርበት የተሰበሰቡየአባሎች አነስተኛ ቡድን

ንድፍ ፡ ይህ ቃል በእንግሊዘኛው ዲዛይን ሲሆን መሰረቱም ዲዚግኔት የሚለው የግሪክ ቃል ነው፡፡ ትርጓሜውም ማመልከት ነው፡፡ አንዳንዴም እቅድ ማውጣት በሚል ሊታይ ይችላል፡፡ የቤት-ዕቃን ንድፍ በማውጣት ውስጥ ዋናው እውቀት እና ችሎታ እንዲሁም  የሚጨበጥ እና የማይጨበጥ የቤት-ዕቃን የሚያመጡ ሁኔታዎች ናቸው፡፡ተጨባጭ ሁኔታዎች የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፡፡

 • ቁሳቁስ (ባህሪያት፣ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ሃሳብ እና የአጨራረስ ጥራቶች
 • የፋብረካ ሂደቶች (መሳሪያዎች፣አፈፃፀም፣ጥራት እና ገደቦች)
 • ጥሬ እቃዎች (ጊዜ፣ገንዘብ እና ለመሳሪያዎች እና ለተለያዩ አቅርቦቶች ያለ ተደራሽነት)

 ተጨባጭ ያልሆኑ ሁኔታዎች የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፡፡

 • ማሰብ፣አላማ እቅድ፣ተግባር
 • ሙያዊ ልምምዶች
 • ስለ ሰውልጅ አካል እና ሁኔታዎቹ

የቤት-ዕቃ ንድፍ

የቤት-ዕቃንና ንድፍን በአንድ ላይ ማስኬድ አስፈላጊነቱ ሁለቱን በአንድ አዋህዶ የቀረበ ስነስርዓት ግልፅ ለማድረግ ነው፡፡ የቤት-ዕቃ ንድፍ የሚለው አዲስ ለሚመጣ የቤት ውስጠኛ ክፍል ንድፍ፣ኢንዱስተሪያዊ ንድፍ፣የፋሽን ዲዛይን፣ግራፋዊ ንድፍ እና ሌሎች ተስማሚ የሆኑ የንድፍ አይነቶች ሆኖም ጥልቀት ያለው እውቀት ነው፡፡ ከቤት-ዕቃ እና ከንድፍ ድምር የሚበልጥ ስፋት ያለው ነው፡፡

ምንም እንኳን አንዳንድ ሁኔታዎችን ማጥናት፣መማር እና መመልከት የሚቻል ቢሆን፤ የቤት-ዕቃን ንድፍ በሚያስፈልገው ደረጃ ለማድነቅ ልምምድ ያስፈልገዋል፡፡ ጥበብ፣ሳይንስ፣የንግድ ስራ እና የመሸጥ እቅድ እና የፋብሪካ ሂደቶችን የሚያጠቃልልም ነው፡፡ ንድፍ ውጪዎች፣አስተማሪዎች፣አምራቾች፣ኢንዱስትሪያዊ ስራ ፈጣሪዎች፣የሙዚየም ኃላፊዎች እና ደራሲዎች ስለ ቤት-ዕቃ ንድፍ ከፍ ያሉ የእውቀት አካላትን አዘጋጅተዋል፡፡ እነዚህም ሁሉ እውቀቶች  በመፅሀፍ፣በመፅሄት፣በሙዚየም እና በማሳያ ሰገነቶች እና በድረ ገፆች ለህዝብ በቀላሉ እንዲገኙ ተደርገዋል፡፡ ቁጥራቸው እየጨመረ እየመጣ ባሉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም የቤት-ዕቃ ንድፍን በጥበብ፣በኢንዱስትሪያዊ ንድፍ፣በቤት ውስጥ ንድፍ አዘገጃጀት እና የህንፃ ንድፍ ጥበብ  ውስጥ ኮርሶች ይሰጣሉ፡፡ ከእነዚህ የቤት-ዕቃ ንድፍ አዘገጃጀት ትምህርቶች መሀከል ጥናት እና ምርምር ለማድረግ የሚመረጡት ከታች የተዘረዘሩት ናቸው፡፡

 • ታሪክ (ማህበረሰባዊ እና ባህላዊ ገፅታ)
 • የሰው ምክንያቶች (የስነ ሰብዕ ልኬት፣የስራ ሁኔታ ጥናት)
 • ሰብዓዊነት (ስነ አእምሮ፣የህብረተሰብ ጥናት፣ሰዎች የተረዱበት ሁኔታ)
 • ፅንሰ ሃሳብ (ምርመራ፣የጥናት ዘዴዎች፣ስነ ውበት)
 • ንድፍ (ሂደቶች፣ገፆች፣አረአያዎች)
 • ችሎታ (መሳል፣ሞዴል ማዘጋጀት፣በቁጥር የሚሰራ ንድፍ እና ፍብረካ)
 • ቁሳቁስ (ባህርይ እና ብቃት)
 • የፋብረካ ሂደት (ዘዴ እና መንገዶች)
 • ሙያዊ ልምምድ

Pin It on Pinterest

Share This