የጥሬ-ዕቃ ብቁነት እና የምርት ፅዳትን የመጨመር የተረጋገጡ ጠቀሜታዎች

በ1990 ዩ ኤን ኢ ፒ ፅዳት ያለው ምርት ቀጣይነት ያለው ምርቶችን እና አገልግሎቶችን ሰዎችንና አካባቢን በማይጎዳ መልኩ ለማሰናዳት የተዘጋጀ የተዋሃደ አካባቢያዊ እቅድን የፀዳ አመራረት በማለት ፍች ሰጥቶታል፡፡ የፀዳ አመራረት እሳቤ በአለም አቀፍ ደረጃ በስፋት ተቀባይነት አግኝቷል፤ ተበረታቷልም፡፡ ፅዳት ያለው ምርትን በተግባር ላይ ለማዋል የሚያስፈልጉት ዘዴዎች ቀላል ይበልጥ ውስብስብ ሊባሉ የሚችሉ ናቸው፡፡ እንደዚህ ያሉ ምርቶች አማካይ ትኩረት የሚያደርጉት 1) ንብረቶች ጥቅም ላይ የሚውሉበትን ቅልጥፍና መጨመር እና/ወይም 2) ንብረቶች በራስ ላይ የሚመጣ ወጪ ሳይኖር በትክክል ጥቅም ላይ መዋላቸውን እና በንግድ ድርጅቱ የመጨረሻ አቅም፣በአካባቢ እና በሰራተኞች እና በማህበረሰብ ጤና እና ደህነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አለማድረሱን ነው፡፡ መደበኛ የጥሬ-ዕቃ ብቁነት እና የምርት ፅዳትን የመጨመር አማካዮች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡፡

  • የተለያዩ ቁሶችን መተካት
  • አስማሚ ዘዴዎች
  • የዘዴዎችን አመራር ማሻሻል
  • መሳሪያዎችን ማሳደግ
  • ምርቶችን ደግሞ መንደፍ

ከማጣበቂያዎች የሚመጣን የአየር ብክለት መቆጣጠር

የንግድ ጉዳዮች፡

ተፈጥሮአዊ ወይም ሰውሰራሽ ማጣበቂያዎች የእንጨት የቤት-ዕቃ ክፍሎችን ለመገጣጠም ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ፡፡ በዚህ ኢንዱስትሪ ያሉ ምቾት ያለው ሽፋን ለሚጨመርላቸው የቤት-ዕቃዎች የሚውሉ የማጣበቂያዎች ቅመራዎች መርዛማ አሟሚዎችን ሲይዙ ይህ ምቾት ያለው ሽፋን ለማይጨመርላቸው ደግሞ ትኩስ ቅላጭ ይሆናሉ፡፡ ማጣበቂያዎች ኮምፔንሳቶ ለማዘጋጀትም ሊውሉ ይችላሉ፡፡ እነዚህን ማጣበቂያዎች በሌሎች አማራጮች መተካት የማምረቻም ወጪንም ሆነ አካባቢያዊ ጉዳትን ይቀንሳል፡፡

አካባቢያዊ ጉዳዮች፡

ለመገጣጠምም ሆነ ለሽፋን ጥቅም ላይ የሚውል ማጣበቂያ አሟሚን ወደ አየር ይለቃል፡፡ ይህም የሰራተኞችን ጤና እና አካባቢያዊ ሁኔታዎችን ያቃውሳል፡፡

ማህበረሰባዊ እና የስራ ጤናማነት እና ደህንነት ጉዳዮች:

ደካማ የስራ ሁኔታዎች የሰራተኞችን ጤና ላይ ይበልጥ ተፅዕኖ ያሳድራሉ፡፡ ማጣበቂያዎችን ስራ ላይ ከማዋል የሚመጣ የአየር ልቀት ጭማሪ በሰራተኞች እና በአካባቢው ማህበረሰብ ላይ የመተንፈሻ አካላትን ያመጣል፤ ያባብሳል፡፡ ጤናማ ያልሆነ የስራ ሀይል ምርታማ ላይሆን፣ስራውን በተደጋጋሚ ሊያጣ እና ዋጋ የሚያስከፍሉ ስህተቶችን ሊፈፅም ይችላል፡፡

እነዚህን ከመጠን በላይ የሆነ የአየር ብክለትን የሚያመጡ ማጠበቂያዎችን እና የጥሬ-ዕቃ ብቁነት እና የምርት ፅዳትን የሚያረጋግጡ ዘዴዎችን ለመለየት የሚከተሉትን ጥያቄዎች መጠየቅ አጋዥነት አለው፡፡

  • የቶቹ የማጣበቂያ መተግበሪያዎች ይበልጥ ብቁ እና አነስተኛ የሆነ የቆሻሻ ልቀትን ውጤት ያመጣሉ?
  • አሁን ለሚገኙት ማጣበቂያዎች መተኪያ የሚሆኑ አነስተኛ መርዛማነት ያላቸው መተኪያዎች አሉ?
  • ሰራተኞችን ከአየር ልቀት ለመጠበቅ ምን የደህንነት መጠበቂያ እርምጃዎችን መውሰድ ይቻላል?

ለቅብ ከሚውሉ ቁሶች የሚመጣን የአየር ብክለት መቆጣጠር

የንግድ ጉዳዮች፡

የቅብ ቁሳቁስን ማለትም እንደ ጠብታ፣ቅልመት እና የመጨረሻ አጨራረስ ጥቅም ላይ ማዋል ከባድ የሆነ የጤና ችግርን ሊያመጣ ይችላል፡፡ ለቅብነት ጥቅም ላይ በሚውለው ቁስ ውስጥ የሚገኙት አሟሚዎች ለእነዚህ ተቀጣጣይ ካርቦናማ ኬሚካሎች አየር ልቀት መነሻ ናቸው፡፡ እነዚህ ተቀጣጣይ ካርቦናማ ኬሚካሎች ወደ አየር የሚቀላቀሉት ቅቡ በሚደረግበት ጊዜ ወይም ማጠራቀሚያቸው ክፍት በሚቆይበት ጊዜ ነው፡፡ የእነዚህ ተቀጣጣይ ካርቦናማ ኬሚካሎችን ልቀት እና በሰራተኛው ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት እንዲሁም የማምረቻ ወጪን እና አካባቢያዊ ጉዳትን ለመቀነሰ የሚሆኑ የተለያዩ አማራጮች አሉ፡፡

አካባቢያዊ ጉዳዮች፡

የቅብ ቁሶች ጥቅም ላይ መዋል ተቀጣጣይ ካርቦናማ ኬሚካሎች ወደ አካባቢ እንዲለቀቁ ያደርጋል፡፡ ይህም ስርአተ ምህዳርን እና የሰራተኞችን ጤንነት ይጎዳል፡፡

ማህበረሰባዊ እና የስራ ጤናማነት እና ደህንነት ጉዳዮች:

የቅብ ቁሶችን ጥቅም ላይ ማዋል የተቀጣጣይ ካርቦናማ ኬሚካሎችን ልቀት በመጨመር የሰራተኞችን የመተንፈሻ አካል ጤንነት ያቃውሳል፡፡ ይህም ሰራተኞች ስራቸውን በአግባቡ እንዳያከናውኑ ምክንያት ይሆናል፡፡

እነዚህን ከመጠን በላይ የሆነ የአየር ብክለትን የሚያመጡ ማጣበቂያዎችን እና የጥሬ-ዕቃ ብቁነት እና የምርት ፅዳትን የሚያረጋግጡ ዘዴዎችን ለመለየት የሚከተሉትን ጥያቄዎች መጠየቅ አጋዥነት አለው፡፡

  • የቶቹ የማጣበቂያ መተግበሪያዎች ይበልጥ ብቁ እና አነስተኛ የሆነ የቆሻሻ ልቀትን ውጤት ያመጣሉ?
  • አሁን ለሚገኙት ማጣበቂያዎች መተኪያ የሚሆኑ አነስተኛ የተቀጣጣይ ካርቦናማ ኬሚካሎችን ልቀት ያላቸው መተኪያዎች አሉ?
  • ሰራተኞችን ከተቀጣጣይ ካርቦናማ ኬሚካሎች ለመጠበቅ ምን የደህንነት መጠበቂያ መሳሪያዎችን ወይም እርምጃዎችን መውሰድ ይቻላል?

የድምፅ ብክለትን መቀነስ

የንግድ ጉዳዮች፡

የድምፅ ብክለት ሜካኒካላዊ እንቅስቃሴ ባለው ማጓጓዣ፣መቁረጥ፣መፍጨት፣ቅርፅ መስጠት እና በአቧራ አውጭ ማውጫ ሊከሰት ይችላል፡፡ የድምፅ ብክለት ተፅዕኖ በድምፁ ድግግሞሽ እና መስሚያ መከላከያው ተፈጥሮ ላይ ይወሰናል፡፡ የድምፅ ብክለት የጤና እና የደህንነት አደጋ በሰራተኞች ላይ ያመጣል፡፡ ጉዳቱን ለመቀነስም የደህንነት እርምጃዎች መወሰድ አለባቸው፡፡

አካባቢያዊ ጉዳዮች፡

ከእንጨት ማቀነባበሪያ እና የቤት-ዕቃ የመስሪያ ክንዋኔዎች በስራ አካባቢው እና በሰራተኞች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ይኖረዋል፡፡

ማህበረሰባዊ እና የስራ ጤናማነት እና ደህንነት ጉዳዮች:

ሰራተኞች የመስማት ችሎታ ማጣት እና ከበካይ ድምፆች ልቀት ምክንያት የሚመጣ ጭንቀት ሊያጠቃቸው ይችላል፡፡ ይህም በጤና ላይ የሚደርሰው ከፍተኛ የሆነ ተፅዕኖ ሲሆን ጤናማ ያልሆነ የስራ ኃይል ምርታማ ላይሆን ይችላል፡፡ በአካባቢው የሚኖሩ ሰዎችም ዝቅተኛ የኖሮ ደረጃን ጨምሮ የበካይ ድምፆች ልቀት አሉታዊ ተፅዕኖዎች ተጠቂ ይሆናሉ፡፡

እነዚህን ከመጠን በላይ የሆነ የድምፅ ብክለትን የሚያመጡ ምክንያቶች እና የምርት ፅዳትን የሚያረጋግጡ ዘዴዎችን ለመለየት የሚከተሉትን ጥያቄዎች መጠየቅ አጋዥነት አለው፡፡

  • የድምፅ ብክለትን ለማስተዳደር ምን እርምጃዎችን በተግባር ላይ ማዋል ይቻላል?
  • ሰራተኞችን ከድምፅ ብክለት ለመጠበቅ ምንምን የደህንነት መጠበቂያ አማራጮች አሉ?

የአፈር እና ውሀ ብክለትን መከላከል

የንግድ ጉዳዮች፡

የቤት-ዕቃዎችን ማዘጋጀት የእንጨት ማቆያ እና ቅብ ቁሶችን መጠቀም ይጠይቃል፡፡ እነዚህ ሁሉም አሟሚ ያላቸው ናቸው፡፡ ማቆያዎቹ እና የቅብ ቁሶቹ ከቤት-ዕቃው ላይ የሚንጠባጠቡ ከሆነ ፈሳሽን እና አፈርን ይበክላሉ፡፡ ዋነኞቹ በእንጨት ማቆየት ሂደት ውስጥ ያሉ በካዮች ባለብዙ ኑክሊየር መዓዛ ያለው ሀይድሮ ካርበን፣ፔንታክሎሮፌኖል፣ተባይ ማጥፊያዎች፣ዳዮክሲኖች፣ለቅብ አገልግሎት የሚውል የክሮሚየም ውህድ፣መዳብ እና አርሴኒክ(ከባድ መርዝ) ሲሆኑ በእነዚህ ብቻ ይገደባል ማለት ግን አይደለም፡፡

በረጅም ጊዜ፤ የተበከለ ፍሳሽ በአካባቢ ውሃ ውስጥ የመርዘኛ ውህድ የሰዎችን ጤና እና የተቋሙን ምታማነት በሚጎዳ መጠን ይጨምራል፡፡ ይህም እንጨት ማቀነባበሪያዎች ተጨማሪ የውሃ ክፍያ እንዲከፍሉ እና በአካባቢያቸው የሚገኘውን ውሃ መልሰው እንዲጠቀሙ ያደርጋቸዋል፡፡

Pin It on Pinterest

Share This