“ዘመናዊ” የሚለው ቃል ብዙውን ጊዜ ከቴክኖሎጂ እና ከወደፊት ሀሳቦች ጋር የተቆራኘ ነው ፣ ሆኖም ግን ወደ ውስጣዊ ዲዛይኖች ሲመጣ ይህ ጽንሰ-ሀሳብ  የሚያተኩረው እርስዎ በመገኘትዎ ውስጥ ሊደሰቱባቸው  በሚችሏቸው ተግባራዊ በሚሆኑ ፣ በሚያምሩ እና ነፃ በሆኑ ቦታዎች ላይ ነው፡፡የመመገቢያ ክፍሎች ምናልባት ቤተሰቦች እና ጓደኛሞች አንድ ላይ ምግብ በጋራ የሚበሉበት እና አይረሴ ጊዜን የሚያሳልፉበት ከቴክኖሎጂ ነፃ የሆነ አከባቢ የመጨረሻ ምሰሶ ናቸው ፡፡

ይህ አካባቢ የሚያጽናና በመሆኑ በእኩል ደረጃ ማራኪ መሆኑን ማረጋገጥ መሰረታዊ ነገር ነው ፣ ስለሆነም ከተመረጡ ዘመናዊ የ ቤት ዉስጥ ጠቃሚ ምክሮች አንዳንድ ቆንጆ እና  ዘመናዊ የመመገቢያ ክፍል ሀሳቦችን ለእርስዎ እናካፍላለን ፡፡እነዚህ ውብ ዘመናዊ የመመገቢያ ክፍል ሀሳቦች የጂኦሜትሪክ አባሎችን ፣ ዘመናዊ ማስጌጫዎችን እና የንድፍ ስራዎችን ከዲዛይነሮች በቀጥታ የተወሰዱ በመሆናቸው መደበኛ የመመገቢያ ቦታን ወደ ውብ እና ማራኪ ስፍራዎች እንዲቀይሩ ይረዱዎታል ፡፡

የመመገቢያ ክፍሉ ከሳሎን ወይም አንዳንድ ጊዜ ከኩሽና ጋር በተቀላቀለበት በዚህ ዘመናዊና የተቀናጀ ማህበራዊ ቦታ ውስጥ ፣ምግብ በሚመገቡበት ጊዜ ለመዝናኛ ምቹ የሆነ ቦታ መገንባት ፈታኝና ፈጠራን የሚጠይቅ ስራ ነው ፡፡ ይሁን እንጂ የቤት ውስጥ ዲዛይነሮች እና የቤትዉበት ባለሙያዎች የዘመናዊ የቤት ባለቤቶችን መስፈርቶች ስለሚረዱ እንደዚህ ያሉ አካባቢዎችን ለመንደፍ ሊረዱ ይችላሉ ፡፡

የመመገቢያ ክፍሎች ብዙም ጥቅም የማይሰጡ አማካይ ቦታዎች ብቻ አይደሉም ፤ እነዚህ ክፍሎች ታላላቅ መግለጫዎችን ለማቅረብ እና በእንግዶች የሚጎበኙ እጅግ በጣም የላቁ የንድፍ ሀሳቦችን ወደ ቤት ለማምጣት የሚያገለግሉ ቦታዎችም ጭምር  ናቸው ፡፡

ሥዕላዊ ግድግዳ

የመመገቢያ ክፍል በመደበኛ የመመገቢያ  ቦታነት ብቻ መገደብ የለበትም። በዚህ የመመገቢያ ክፍል ውስጥ ግድግዳዎቹ ለውበት ሲባል ፣ ለከባቢ አየር ቀለል ያለ ሰማያዊ ቀለም የተቀቡ ቢሆኑ ይመረጣል ፡፡ ብዙ ገጸ-ባህሪያትን የሚያጎሉ የሥዕል ግድግዳዎችን በመፍጠር ዉበትን ማላበስም ይቻላል።

የእንጨት እቃዎች ዉበት እና ማራኪነት ለመመገቢያ ክፍሉ ቅርብ የሆነ ክፍፍልን ለመፍጠር በሰፊው ጥቅም ላይ  የሚውል ሲሆን በግድግዳ ላይ በሚቀመጡ ትልልቅ ሥዕሎች  እና ከጣሪያው ላይ ተንጠልጥለው በሚበሩ ብርሃናማ  መብራቶች ደግሞ  የበለጠ ማስጌጥ ይቻላል፡፡

ክብ ጠረጴዛ መጠቀም

አንድ ክብ የመመገቢያ ጠረጴዛ በመመገቢያ ክፍሉ ውስጥ ላልተቋረጠ የውይይት ፍሰት ተስማሚ ሲሆን ሰዎች የትም ቢቀመጡ እርስ በእርስ መተያየትይችላሉ፡፡ በክብ ጠረጴዛ ፣ ተጨማሪ ወንበሮች በሚፈለጉበት ጊዜ ጠረጴዛውን ሳይጨናነቁ በምቾት ሊጨመሩ ይችላሉ ፡፡

በሚያምር ሁኔታ የተደራጀ ማራኪ የሆነ የመመገቢያ ክፍል

ዘመናዊ የመመገቢያ ክፍሎች ሁሉንም ቅርጾች ፣ መጠኖች እና ቀለሞችን አመጣጥነዉ የያዙ ናቸዉ  ፡፡ ስለሆነም ከአሁን በኋላ ልሙጥ ነጭ ወይም ቀለል ያለ ቀለም ብቻ ተመራጭ አይደለም፡፡ ለስላሳ ያለ ጥቁር ቀለም ያለው  የመመገቢያ ክፍል ነገሮችን የተራቀቁ እና አንጸባራቂ እንዲሆኑ በማስቻል ውበትን እና ምቾትን በመፍጠር የቀለማት ህብረትና አንፀባራቂ ተንጠልጣይ መብራቶች ውበታቸው ጎልቶ  እንዲታዩ ያስችላቸዋል ፡፡ደብዛዛ ቀለሞች ፣ የእንጨት ምርቶች ፣ ግድግዳ ላይ  የሚንጠለጠሉ ግዙፍ መብራቶች እና የተለያየ ቅርፅ ያላቸው የመስታወት በሮ ያሏቸው የመመገቢያ ክፍሎች ለረጅም ሰዓታት ዘና ያለ ውይይቶች ለድረግ ፍጹም ተመራጮች ናቸዉ ፡፡

 እይታ ያላቸዉየመመገቢያ ክፍሎች

ከድንጋይ ግድግዳ እና ከድንጋይ ወለል መካከል የሚፈጠረው ተፈጥሯዊ ውበት አስደናቂ ስለሆነ የመመገቢያ ክፍል በተፈጥሮ ብርሃን እንዲሞላ ያግዛል፤ በይበልጥም ክፍሉ ውስጥ ያሉ ቦታዎች በመስታወታማ በር የተከፋፈሉ ከሆነ  የተፈጥሮን ዉበት ወደ ክፍሉ በመሳብ  ማራኪ እይታን በመፍጠር አስደሳችነታቸውን የበለጠ ያጎሉታል፡፡

መዝናኛ ክፍል ያላቸው የመመገቢያ ክፍሎች

ከመዝናኛ ክፍል ጋር የተጣመረ የመመገቢያ ክፍል፤ ምቹ ወንበሮች፣ ቀለል ያለ ትልቅ የእንጨት የመመገቢያ ጠረጴዛን ካካተተ እንዲሁም በመመገቢያ ክፍሉ ውስጥ የቴሌቪዥን እና የመዝናኛ ክፍል ከተጨመረበት ከወዳጅ ዘመድ ጋር ረዘም ያለ የእረፍት ጊዜን ለማሳፍ ይመረጣል፡፡

ማራኪ እይታ ያለው የመመገቢያ ክፍል

የመኖሪያ ስፍራን ከመመገቢያ  ክፍል ጋር አብሮ የማዛመድ ጥበብ ለረዥም ጊዜ ፈታኝ ሆኖ ቆይቷል፤ሆኖም ተመሳሳይ የመኖርያ እና  የመመገቢያ ክፍል ቁሳቁስ ፣ ማራኪ ውበት ያለው ግዙፍ የመስታወት ግድግዳ በማከል የአከባቢን ውበት በማጉላት  መመገቢያ ክፍልን ተስማሚ በማድረግ ምቹ ሁኔታን መፍጠር ይቻላል፡፡

ወቅታዊ እና ጥራት ያለው የመመገቢያ ክፍል

የሶፋዎች  ፣ የጠረጴዛዎች  እና የአግዳሚ ወንበሮች ጥምረት  በመመገቢያ ክፍል ውስጥ ልዩ የሆነ ማራኪነትን ይፈጥራል ፡፡ይህም በአንፃራዊነት አከባቢው የተለየ ግርማ ሞገስ እንዲላበስ ያግዛል፡፡በተጨማሪም አንዳንድ የእፅዋት ዝርያዎችን በእነዚህ ክፍል ውስጥ ማካተት ስሜትን የሚያድስና  በመመገቢያ ክፍል እንዲሁም ሳሎን ውስጥ ህይወትን እና ዉበትን የሚዘራ ነው።

ሰፊ የመመገቢያ ጠረጴዛን መጠቀም

አንድ ትልቅ ስብሰባ ሁሉንም ሰው ለማስተናገድ እንዲሁም ብዙ ተሰብሳቢን  ለማስተናገድ  ትልቅ የመሰብሰቢያ ጠረጴዛን ይፈልጋል ፤እንደዚሁም ሁሉ በርካታ የቤተሰብ አባላት ላሉበት መኖሪያ ቤት እና ለተለያዩ ግብዣዎች ይህን የመመገቢያ ጠረጴዛ መጠቀም በቦታ ጥበት ሊፈጠር የሚችልን እንግልት በማስቀረት ምቾትን ይፈጥራል፡፡

የቀለም ሁኔታ

የቀለም ምርጫ በቀለም ተስማሚነት ላይ የሚያተኩር ሲሆን  በይበልጥ ከብርሀን ነፀብራቅ ጋር  የሚፈጥረው ውህደት አንድን ክፍል አጓጊ ሊያደርገው እና ለእይታም ተስማሚ እና ተመራጭ የማድረግ አቅሙ ከፍተኛ ነው፡፡በመሆኑም ብርሀን ከሚገባበት መስኮት  ለፊት ያለው ስፍራ የቀም ሁኔታው ቀድሞ የተጠና ቢሆን እንግዶችን ለማዝናናት ተስማሚ ቦታን በመፍጠር ረገድ ትልቅ ሚናን ይጫወታል ፡፡

Pin It on Pinterest

Share This