ለመራመድ ለመተካት የሚሆን ተሸከርካሪ ያለው ወንበር ተሸከርካሪ ወንበር ይባላል፡፡ የአካል ጉዳት ላለባቸው፣እድሜያቸው እጅግ ለገፋ ሰዎች እና መራመድ ለሚከብዳቸው ህፃናት ጥቅም ይሰጣሉ፡፡ እነዚህ ቁሶች ራሳቸውን የሚያሽከረክሩ፣በሞተር የሚሽከረከሩ፣በተሳታፊ እርዳታ (ግፊት) የሚንቀሳቀሱ ናቸው፡፡
የመጀመሪያው ተሸከርካሪ ወንበር በ1595 የተሰራ ሲሆን ፊሊፕ ለተባለው የስፔን ንጉስ የተሰራ ነበር፡፡ በመቀጠል በ1655፤ ስቴፈን ፋርፍለር ባለሶስት ተሽከርካሪ ቻሲስ፣ራሱን የሚያሽከረክር ተሽከርካሪ ሰራ፡፡ በ1783 የባዝ ታወኑ ጆን ዳውሰን ባዝ ተሽከርካሪ ወንበር የተባለውን ተሽከርካሪ ወንበር ፈጠረ፡፡ ወንበሩ ሁለት ትላልቅ ተሽከርካሪዎችና አንድ አነስተኛ ተሽከርካሪ ያለው ነው፡፡ የመጀመሪያው ባለሞተር ተሽከርካሪ ወንበር በ1916 በብሪታኒያ መሃንዲሶች የተሰራ ሲሆን በ1932 ሃሪ ጄኒንግስ የመጀመሪያውን ታጣፊ ተሽከርካሪ ወንበር ሰርቷል፡፡
የተለያዩ የተሽከርካሪ ወንበር አይነቶች
የተለያዩ የተሽከርካሪ አሉ፡፡ ተሽከርካሪ ወንበሮችን ለመንቀሳቀስ በሚጠቀሙበት ሀይል መከፋፈል ይቻላል፡፡ ተሽከርካሪ ወንበሮች በሁለት ይከፈላሉ፡፡
- የእጅ ተሽከርካሪ ወንበር
- በኤሌክትሪክ ጉልበት የሚሰራ ተሽከርካሪ ወንበር
የእጅ ተሽከርካሪ ወንበር
እነዚህ በሰው ጉልበት የሚንቀሳቀሱ፤ በራሳቸው ተሽከርካሪ የሚጠቀሙ ወይም በአጋዥ የሚሽከረከሩ ናቸው፡፡ እነዚህ ተሽከርካሪ ወንበሮች በተለምዶ አገልግሎቱ የሚያስፈልጋቸው ተሳፈሪዎችን ወደ መቀመጫ ቦታው ለመውሰድ ያገለግላሉ፡፡ ተሽከርካሪ ወንበሮቹ ለመጓዝ ክፈፍ ያለው ትላልቅ የኃላ ተሽከርካሪ፣ቅርፅ የተሰጠው መቀመጫ፣ቀላል ክብደት፣መግፊያ እጀታ፣የጀርባ ማሳረፊያ ድጋፍ እና የእጅ ፍሬን በሌለው ሁኔታ የተነደፉ ናቸው፡፡ የእጅ ተሽከርካሪ ወንበር በሁለት ይከፈላል፡፡ እነዚህም
- ቀጥያለ(ግትር) ተሽከርካሪ ወንበር
- ታጣፊ ተሽከርካሪ ወንበር
በኤሌክትሪክ ጉልበት የሚንቀሳቀስ ተሽከርካሪ ወንበር
በኤሌክትሪክ በሚሰራ ሞተር ያለው ተሽከርካሪ ወንበር ሲሆን ይህ ተሽከርካሪ ወንበር የመምሪያ መቆጣጠሪያ ያስፈልገዋል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ በእጅ ማስደገፊያ ላይ የሚገጠም በመጠን ትንሽ ጆይ ስቲክ ይሆናል፡፡ ይህን በእጅ በመነካካት የሚሰራ ጆይስቲክ መጠቀም ለማይችሉ ሰዎች በጭንቅላት ለመጠቀም የሚቻል ማብሪያ ማጥፊያ እና በአገጭ ለመጠቀም የሚቻል ጆይስቲክ ያላቸው ናቸው፡፡ ሌሎች ልዩ የሆኑ መቆጣጠሪያዎች ራሱን ለቻለ የተሽከርካሪ ወንበር አሰራር ሊቀርቡ ይችላሉ፡፡ ሞተር የተገጠመላቸው ተሽከርካሪ ወንበሮች እጅን በመጠቀም ማሽከርከር ለማይችሉ ወይም በእጅ እያንቀሳቀሱ ለመጓጓዝ የሚያዳግት ረጅም ርቀት ለሚጓዙ አስፈላጊ ናቸው፡፡ እነዚህ ተሽከርካሪ ወንበሮች የተለመደ አድካሚ ጉዞ ለሚያደርጉ ባቻ ሳይሆን የልብ ስርዓት መዛባት ህመም ለሚያጠቃቸውም ሰዎች ጥቅም ላይ ይውላል፡፡
ግትር መቃን ያለው ተሽከርካሪ ወንበር ጥቅሞች
- አካል ክፍሎቹ ከአሉሚኒየም ቅይጥ ስለሚሰሩ ለማደስ አነስተኛ ወጪ ይጠይቃል
- ከፍተኛ ክብደቶችን ማስተናገድ መቻል
- አነስተኛ ክብደት
- አነስተኛ ዋጋ(በቀላሉ የሚገኝ)
ግትር መቃን ያለው ተሽከርካሪ ወንበር ጉዳት
- አለመተጣጠፍ (የተጨማሪ ስፍራ ማስፈለግ)
- እንደ አስፈላጊነቱ የማይስተካከል የጀርባ መደገፊያ እና የእጅ ማሳረፊያ
- ወደኃላ መሄድን ማስቆሚያ መጥፋት
- እንደ አስፈላጊነቱ የማይስተካከል ምግብ ማስቀመጫ
የባለንብርብር መቃን ተሽከርካሪ ወንበር ጥቅሞች
- ተጣጣፊው አነስተኛ የሆነ ስፍራ መያዙ
- አነስተኛ ስፍራ ስለሚፈልግ ለማጓጓዝ ቀላል መሆኑ
- መከዳ ያለው የጀርባ መደገፊያ እና እንደ አስፈላጊነቱ የሚስተካከል የእግር ማሳረፊያ
- ጉድለት ወይም እንከን ቢኖር እንኳን መስተካከል የሚችል ንድፍ
የባለንብርብር መቃን ተሽከርካሪ ወንበር ጉዳቶች
- የሚለጠጥ የጀርባ መደገፊያ ስላለው ተደጋጋሚ ጫና ይፈጥራል
- አካሉ ከማይዝግ አረብ ብረት ስለሚሰራ ክብደቱ ከፍ ያለ ይሆናል
- ቅጥ ካጣ አካባቢ ጋር ንክኪ በሚፈጥርበት ጊዜ ዘላቂነቱን ማጣት
- የእድሳት ወጪው ከፍ ያለ ነው
የሰው ሰፍራ ልኬት እና ስነምቾት
ስነምቾት ሰው በሚኖርበት አካባቢ ካሉ አካላት ጋር ያለውን መስተጋብር የሚያሳይ ሳይንሳዊ ማሳያ ነው፡፡ ስነምቾት የጤና እና ምርታማነትን ግቦች ለማሟላት የሚያገለግል ነው፡፡
የተሽከርካሪ ወንበር ተጠቃሚዎች እና ስነምቾት
የተሽከርካሪ ወንበር ስነምቾት ከተሽከርካሪ ወንበሩ ስነእንቅስቃሴ እና ከተጠቃሚው አካላዊ ሁኔታ ጋር የተዛመደ ነው፡፡ ስነምቾትን ጠብቆ ንድፍ የወጣለት ተሽከርካሪ ወንበር ለረጅም ጊዜ አገልግሎት በመስጠት የሚመጣ ውጥረትን ይቀንሳል፡፡ በተሽከርካሪ ወንበር ላይ ያለ ስነምቾት አራት ቁልፍ መስፈርትን ከግምት ያስገባል፡፡ እነዚህም ጉልበት፣ድግግሞሽ፣ቆይታ እና አቋም ናቸው፡፡
በተሸከካሪ ወንበር ላይ አስፈላጊ እና ትልቅ ሚና የሚጫወተው መቀመጫው ነው፡፡ ስለዚህም የተሽከርካሪ ወንበርን ምቹነት ምርጥ የሚባለው ደረጃ ላይ ለማድረስ አበዛኛውን ትኩረት ለመቀመጫው ንድፍ ይሰጣል፡፡ይህ አውራ ህግ በሁሉም አይነቶች ላይ የሚሰራ ሲሆን በዋናነት የመቀመጫውን ልኬት ለመወሰን ጥቅም ላይ ይውላል፡፡
የፅንሰ ሃሳብ ግኝት
የምርት ንድፍ ዝርዝር እና ጥራት ያለው ገቢር ማሰማራት እነዚህ የደንበኛን ፍላጎት ድምፅ ፍሬነገር በግልፅ ማብራሪያ ያስረዳሉ
የደንበኛ ፍላጎት ድምፅ
- እንደአስፈላጊነቱ የሚስተካከል የእጅ ማስደገፊያ
- የተሻሻለ የጀርባ መደገፊያ ንድፍ
- እንደአስፈላጊነቱ የሚስተካከል እና መከዳ ያለው የእግር ማሳረፊያ
- የተሻሻለ የፍጥነት መቀነሻ (ፍሬን) ንድፍ
- በርከት ያለ ጥቅም(አገልግሎት)
- አነስተኛ ክብደት
- አነስተኛ ዋጋ
- ለማጓጓዝ ቀላል
ሙያዊ ድምፅ
- የቁሳቁስ ለውጥ
- ምቾት ያለው ንድፍ
- ለመገልገል የሚመች
- ክብደት
- የአሰራር ዘዴ
- ደህንነት
- ኢኮኖሚን ያገናዘበ
ባህሪያት | መግለጫ | ዝርዝር |
ልኬታዊ ዝርዝሮች | በክፍት ቦታ ላይ ያለ ልኬት | ርዝመት=1140 ሚሜ ስፋት=700ሚሜ ቁመት=1250ሚሜ |
ከታጠፈ በኃላ ያለ ልኬት | ርዝመት=1140 ሚሜ ስፋት=300ሚሜ ቁመት=1250ሚሜ | |
ስነ-ምቾት | ግምታዊ የተጣራ ክብደት | 24 ኪግ |
ከፍተኛ የክብደት እርከን | እስከ 190 ኪግ | |
ቁስ | ቱቦ፣የሽክርክሪት ክፈፍ | 304 የሚባል መጠሪያ ኮድ ያለው አረብ ብረት |
መቀመጫ እና እጀታ | ግትር ፕላስቲክ፣ጥጥ፣ቆዳ | |
ሽክርክሪት | ልኬት | ለኃላ ሽክርክሪት 610ሚሜ የሆነ ድፍን ጎማ ለፊተኛ ሽክርክሪት 210 ሚሜ የሆነ ድፍን ጎማ |
ደህንነት | የታማሚ ደህንነት | ለስላሳ ገፅ እና የደህንነት ቀበቶ |
ስነ-ውበት | አካል | ለስላሳ እጥፋት፣ቀጥታ እና ስለታም ጠርዞች |
ቀለሞች | ነጭ፣ግራጫ፣ጥቁር(በብዛት) | |
ዋጋ | በአንድ ምርት ያለ ዋጋ | በግምት ከ5000 እስከ 7000 |
ሰንጠረዥ 1. የምርት ንድፍ ዝርዝር እና ጥራት ያለው ገቢር ማሰማራት
መግለጫ | ዝርዝር |
እጅ ማስደገፊያ እግር ማስደገፊያ | በአግባቡ ምቾቱ የተጠበቀ የእጅ ማስደገፊያ እንደ አስፈላጊነቱ የሚስተካከል የእግር ማስደገፊያ |
የአመራረት ሂደት | መቁረጥ፣ማጠፍ፣መበየድ፣መሞረድ፣የምርቱን ክፍሎች መሙላት እና መገጣጠም |
ስነ ምቾት | የጭንቅላት ማሳረፊያ፣የእጅ ማሳረፊያ፣የእግር ማሳረፊያ |
ደህንነት | በአደጋ ጊዜ በቶሎ ማስቆም የሚችል ፍሬን፣ከስለታም ጠርዞች ነፃ የሆነ፣የማስጠንቀቂያ ደወል፣የአደጋ ጊዜ ብርሃን |
ተጨማሪ ባህሪያት | እንደ አስፈላጊነቱ የሚስተካከል የጉልበት ማስደገፊያ፣የውሃ ጠርሙስ ፣ምግቦችንና መፅሀፍትን መያዣ |