ከእንጨት የተሰሩ የቤት-ዕቃዎችን በመምረጥ ውስጥ ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያላቸውን መምረጥ ግራ አጋቢ ሊሆን ይችላል፡፡ ብዛት ያላቸው ዘይቤዎች፣ቁሶችና የአሰራር ቴክኒኮች ስላሉ ከእነርሱ ውስጥ ብልህ የሚባለውን ምርጫ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ጥሩ የሚባለውን ምርጫ ለማድረግ የተቻለውን ያክል መረጃ መሰብሰብ አጋዥ ነው፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች ጥሩ ውሳኔ ለማሳለፍ ያግዛሉ፡፡

 • በገበያው ላይ ምን ይገኛል?
 • ጥራት ያለው አሰራር ማለት ምን ማለት ነው?
 • ጥራት ያለው አጨራረስ ምንድን ነው?
 • በመሰየሚያው ላይ ምን ይገኛል?
 • የዋስትናው ሁኔታ?

በገበያው ላይ ምን ይገኛል?

እንጨት ያማረ ገፅታ፣ዘላቂነት እና የአሰራር ቅለት ስላለው የቤት-ዕቃዎችን ለማምረት ጥቅም ላይ ከሚውሉ ታዋቂ ቁሶች ውስጥ አንዱ ሆኗል፡፡ የእንጨት የቤት-ዕቃዎች በተሰሩበት የእንጨት ሁኔታ ድፍን ወይም ተደራራቢ(ኮምፔንሳቶ) ተብለው ሊከፋፈሉ ይችላሉ፡፡ መደገፊያዎቻቸው ኮምፔንሳቶ ቢሆኑም በዋናነት አብዛኞቹ የቤት-ዕቃዎች ከድፍን እንጨት ይሰራሉ፡፡ ድፍን እንጨት ለጥንካሬውና መዛባትን፣መሰንጠቅን፣መወጠር እና መኮማተርን ለማስቀረት በሰፊው ጥቅም ላይ ይውላል፡፡

ሁሉም እንጨቶች ቅጠል አርጋፊ እና ቅምብብማ ተብለው መከፈል ይችላሉ፡፡ የእንጨቱ ጥንካሬ ከተገኘበት የዛፍ አይነት ጋር ግንኙነት አለው፡፡ ሁልጊዜም ባይሆን አብዛኛውን ጊዜ ቅጠል አርጋፊዎች ከቅምብብማ የበለጠ ጥንካሬ አላቸው፡፡ በቀላሉ፤ቅጠል አርጋፊ ቅጠል በብዛት ያላቸውን እንደ ወይራ፣ሉጥ፣ልምጭ ያሉትን ያካትታል፡፡ ቅምብብማ ደግሞ ቅምብብ የሚይዙ እንደ ጥድ ያሉትን ያካትታል፡፡ አብዛኞቹ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የቤት-ዕቃዎች ከቅጠል አርጋፊ ዛፎች የተሰሩ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳንድ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የቤትዕቃዎች አየተሰሩባቸው ቢሆንም ከቅምብብማ ዛፎች የሚገኙ እንጨቶች እምብዛም ውድ የማይባሉ የቤት-ዕቃዎችን ለማዘጋጀት ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ ከእነዚህ የሚዘጋጁ የቤትዕቃዎች ለመጫጫር እና ለመሰርጎድ ቅርብ ናቸው፡፡

የቤትዕቃዎችን ለመስራት የሚያገለግሉ የተለመዱ ጠንካራ እንጨቶች ወይራ፣ሉጥ፣ልምጭ፣ የአሜሪካ ለውዝ፤ቼሪ እና ሌሎችም ናቸው፡፡ የተለመዱት የቤት-ዕቃን ለመስራት የሚያገለግሉ ልል እንጨቶች ደግሞ ጥድ፣ቀይ የካሊፎርኒያ እንጨት እና የመሳሰሉት ሲሆኑ የእነዚህ እንጨቶች ዝርዝር ባህርይ እንደሚከተለው ተዘርዝሯል፡፡

አሽ. የአሽ ባህሪያት ከቅልመት በኃላ ያለው ሳቢነት፣ቀዳዳ ያላቸው ቀጥ ያሉ ጉልህ ቅንጣቶች፣ጥንካሬ፣ከፍተኛ ክብደት፣ፅኑነት እና ጥሩ ክውታ(ንዝረትን) የመቋቋም አቅም ናቸው፡፡

ቼሪ. የቼሪ ባህሪያት መጠነኛ ፅኑነት፣ከፍተኛ ጥንካሬ፣ዘላቂነት፣ጥሩ ንዝረት እና በግልጋሎት ብዛት የሚደርስ ጉዳትን የመቋቋም አቅም፣ደስ የሚል ቀለም እና ቀጥ ያለ ቅንጣት ከትናንሽ የራሱ የሆነ ቀዳዳ ያለው መሆኑ ነው፡፡

ሉጥ. የሉጥ ባህሪያት ከፍተኛ ክብደት፣ፅኑነት፣መጠረብ መቻል፣ለረጅም ጊዜ አገልግሎት መስጠት መቻል እና በሚቀልምበት ጊዜ ጎልቶ የሚወጣ አግድም የቅንጣት ንድፍ ናቸው፡፡ ሉጥ ብዙውን ጊዜ የበር ግድግዳ ላይ ማስዋቢያ፣ለሽፋን(ፎርማይካ) እና ለድፍን የእንጨት የቤት-ዕቃ መስሪያነት ይውላል፡፡

ጥድ. ጥድ ልል፣ክብደቱ ቀላል፣ለመስራት ቀላል፣አነስተኛ ጥንካሬ እና ቀለም እና ቫርኒሽ በደምብ የሚይዝ ነው፡፡ ምዕራባዊው ጥድ ከሌሎቹ የጥድ አይነቶች በተሻለ ጥንካሬ ያለው ነው፡፡ ጥድ መደርደሪያ፣ቁምሳጥን፣ከቤት ውጪ አገልግሎት የሚሰጡ የቤት-ዕቃዎችን እና አንዳንድ ጥራት ያላቸው የቤት-ዕቃዎችን ለመስራት ይውላል፡፡

ጥራት ያለው አሰራር ማለት ምን ማለት ነው?

የቤት-ዕቃዎችን በማዘጋጀት ውስጥ ጥራት በዋናነት በሁለት መለያ ባህርዮች ይታወቃል፡፡ እነዚህም የእንጨት የቤት-ዕቃውን አካላት ለመገጣጠም የምንጠቀምበት ዘዴ እና ጤናማ ጥንካሬያቸው ናቸው፡፡ ለተሻለ ጥንካሬ መገጣጠሚያዎች የማጣበቂያ ሙጫው በውጪ ምንም ያህል የማይታይ እና ጥብቅ መሆን አለባቸው፡፡

መገጣጠሚያዎች:- የቤት-ዕቃዎች ክፍሎች የተገጣጠሙበት መንገድ ለዘላቂነት  እና ለመልካቸው እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ከእነዚህ ዘዴዎች ውስጥም በአንዱ ወይም በሌሎችም ሊገጣጠሙ ይችላሉ፡፡ እነዚህም ቅትርቴ፣መቃን ደግፍ፣የሚገጥም ጫፍ፣በቢቴ መታሰር፣በሙጫ መጣበቅ፣በመቀርቀሪያ መቀርቀር፣በሽቦ መያያዝ እና ሌሎችም ናቸው፡፡

መገጣጠሚያዎችና መሰካካት የሚችሉ እንጨቶች በመሰኪያ እና ከሁለት የተለያዩ እንጨቶች ጉጣጉጥነት የሚሰሩ እና ጠንካራ ሲሆኑ አብዛኛውን ጊዜ መቃንና የወንበር እግሮችን ለመስራት ይውላሉ፡፡  

ጤናማነት እና ጥንካሬ. ይህንን በሚገባ ማወቅ የእንጨት የቤት-ዕቃዎችን በመምረጥ ውስጥ እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ከዚህ በታች ያሉት የጤናማነት እና ጥንካሬን ፍንጭ ለማግኘት የሚያስፈልጉ፤ መታየት ያለባቸው ባህሪያት ናቸው፡፡

 • ውጫዊ መሰላሎች ወይም ቋሚዎች ከቤት-ዕቃው የታችኛው ክፍል ድረስ መውጣት አለባቸው፡፡ ይህም መሰላሎቹ ወይም ቋሚዎቹ የመሰበር ዕድል ይቀንሰዋል፡፡
 • ከቤት-ዕቃው ጋር የተጋጠሙት መሰላሎች እና ቋሚዎች ብዛት የቤት-ዕቃውን ጤናማነት እና ጥንካሬ ማሳያም ናቸው፡፡

ጥራት ያለው አጨራረስ ምንድን ነው?

ጥራት ያለው አጨራረስ ሶስት ዋና ዋና ደረጃዎችን ያጠቃልላል፡፡ እነዚህም ማለስለስ፣ማቅለም እና ማሳመር ናቸው፡፡ ከእነዚህ ደረጃዎች ውስጥ አንዱ እንኳን በትክክል ካልተሰራ አጨራረሱ ማማር ያለበትን ያክል ውበት አይኖረውም፡፡

 • ማለስለስ. አምራቹ ጥሩ የማቅለም፣የማሳመርና የመቦረሽ ሊሰራ ይችላል፡፡ ነገር ግን በመጀመሪያው ደረጃ የሻካራነት ምልክት(ዱካ) ካለው፣በቂ ማለስለስ ካልተደረገለት ወይም ከእንጨቱ ቅንጣቶች በተቃራኒ አቅጣጫ ከተለሰለሰ፤ ቅልመቱ እና ማሳመሩ ደካማ ነጥቦችን ብቻ ያጎላል፡፡ ያልተለሰለሱ ቦታዎች ብዛት ያለው ቀለም ይመጣሉ፡፡

የቤት-ዕቃ በአግባቡ መለስለሱነን ለማረጋገጥ፤ ካለቀለት በኃላ ብርሃን ከተለያዩ ማዕዘናት እንዲያርፍበት በማድረግ እና የራስንም ቦታ በመቀያየር ማየት ያስፈልጋል፡፡ አጨራረሱ በእንዳንድ ቦታዎች ላይ ሽፍታ ያለበት፣ደብዛዛ ወይም በመላ ቅንጣቶቹ ላይ ጥቁር መስመር ካለበት ውጫዊ ገፁ ከመቀባቱ በፊት በደምብ አልተለሰለሰም ማለት ነው፡፡

 • ማቅለም. ጥሩ የቀለም ቅብ የእንጨቱን ተፈጥሯዊ ውበት ይጨምራል፣ጥሩ ቀለም እና ጠባይ ይጨምራል፣ሌላ አይነት ገፅታ ይሰጣል በተጨማሪም ልዩነት ያላቸውን የእንጨት አይነቶች ተመሳሳይ ገፅታ እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡ የቅልመትን ጥራት ለማረጋገጥ በእንጨቱ መላ ገፅታ ላይ ቀለሙ በትክክል መዳረሱን ማየት ይቻላል፡፡ ከሌላው ቦታ በበለጠ ቀለም የበዛበት ቦታ መኖር የለበትም ይህም ማለት ምንም ጥቁር ነጥብ ባለመኖሩ፣አንዱ የቤት-ዕቃው ጎን ከሌላው የበለጠ ደማቅ መሆን የለበትም፣ጫፍ ላይ ያለው ቀለም ከሌሎች ገጦች ጋር ተመሳሳይ ቃና ሊኖረው ይገባል፤ በነዚህ የቅልመትን ጥራት መረጋገጥ ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ የቤት-ዕቃውን ዕድሜ ከፍ ያለ እንዲመስል ተጨማሪ ቀለም ሊጨመር ይችላል፡፡

በአንዳንድ አጋጣሚዎች ውበት ለመጨመር በሚል የእንጨቱ ገፅ ስርጉድ እና ጭረት እንዲኖረው በሰንሰለት ወይም በመሰል መሳሪያዎች ይመታል፡፡ ይህ ሁኔታ ውበት ከማጉላት ይልቅ የእንጨቱን የጥራት ደረጃ የሚቀንስ ነው፡፡

 • አጨራረስ. አጨራረሶች በተለያየ የጥራት ደረጃ ከከፍተኛ ወዝ እና አነስተኛ ወዝ ይኖራቸዋል፡፡ ከፍተኛ ጥራት ያለው አጨራረስ ሀር መሳይ ልስላሴ ያለው እና ከሻካራነጥቦች፣ከአቧራ ፍንጥቅጣቂ ወይም ኩፍኩፍታ ነፃ የሆነ ነው፡፡ የቤት-ዕቃ አጨራረስ ልስላሴን ለማረጋገጥ ናይሎን በእጅ ላይ አስቀምጦ ባለቀለት ገፅ ላይ ማንሸራተት ነው፡፡ ናይሎኑ ከያዘ ወይም ከተነጨ፤ በትክክል አልተለሰለሰም ወይም አጨራረሱ ትክክል አይደለም ማለት ነው፡፡ በአጨራረሱ ላይ ብዛት ባላቸው አነስተኛ የአጨራረስ ሽፋኖች እና በቅቦች መካከል ባለ ጥሩ የማለስለስ ስራ የተገኘ ጥልቀት እና መበልፀግን መሻት ያስፈልጋል፡፡ አጨራረሱ በሚፈተሽበት ጊዜ በቂ ብርሃን መኖር አለበት፡፡ የቤት-ዕቃው ጠርዝ እና ጫፍ ከፍተኛ ጥራት ባለው የመጨረሻ መሳሪያ መሸፈን አለበት ከጣት ምልክትም ነፃ መሆን አለበት፡፡ የተሞሉ ስንጥቆች እና ቀዳዳዎች ከፍተኛ ጥራት ባለው የመጨረሻ መሳሪያ መሸፈናቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

ደካማ አጨራረስ ያረፈበት የቤት-ዕቃ ከእነዚህ ባህሪያት ውስጥ አንዱን ወይም ብዙ ባህሪያትን ያሳያል፡፡ እነዚህም ሻካራነት፣መጠን ያለፈ ማብረቅረቅ፣የእንጨቱን ቅንጣቶች ማየት እስከሚከብድ ድረስ ደብዛዛ መሆን፣የተሰነጠቁ ጠርዞች፣ጭረቶች፣ጎድጓዳ ቦታዎች ወይም የአቧራ ፍንጥቅጣቂ ወይም ኩፍኩፍታ እና የእምባ ጠብታ መሰል ነገሮችን በጠርዞች አካባቢ እና በገፁ ላይኛው እና ታችኛው ክፍል ላይ መታየት ናቸው፡፡ እነዚህ የእምባ ጠብታ መሰል ነገሮች ከመጠን በላይ የሆነ የመጨረሻ ቅብ ጠርዝ እና በገፅ ላይ ወርዶ ሲደርቅ የሚታዩ ናቸው፡፡

በመሰየሚያው ላይ ምን ይገኛል?

በእንጨት ለሚሰሩ የቤት-ዕቃዎች መሰየሚያ ማዘጋጀት በሰሪው ፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ በመሆኑም መሰየሚያ ማግኘት እንደ መታደል ሊታይ ይችላል፡፡ መሰየሚያዎች አሳሳች እና ሀሰተኛ የእንጨት ወይም የእንጨት ቅጅ ውከላ ሊኖራቸው አይገባም፤ እነዚህን ሁኔታዎችን ማሟላትም ይኖርባቸዋል፡፡

 1. እውነተኛ-ይህ ማለት ተጋላጭ የሆኑ መዋቅራዊ ክፍሎች እና ዝርግ ገፆች ከተጠቀሰው የእንጨት አይነት መሰራታቸውን ማሳየት ነው፡፡ ለምሳሌ-የዋልነት ኮምፔንሳቶ “እውነተኛ ዋልነት” የሚል መሰየሚያ ይኖረዋል፡፡
 2. ድፍን-ይህ ማለት ተጋላጭ የሆኑ መቃኖች እና የበር ግድግዳ ማስዋቢያዎች ከድፍን ጣውላ እንጂ ከኮምፔንሳቶ ወይም ከተነባበረ ሳንቃ አለመሰራታቸውን ማሳየት ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ-“ድፍን ሉጥ”
 3. ህብር-ይህ ሁለት ወይም ከዛ በላይ የሆኑ የእንጨት አይነቶች ጥቅም ላይ መዋላቸውን በመሰየሚያው ላይ መግለፅ ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ-ጥድ ከሙጫ ዛፍ ጋር
 4. ቅጅ-ይህ ማለት እትም ወይም ቅብ የቅንጣት ንድፍ ሞዴል በጠንካራ እንጨት፣ በብረት፣በፕላስቲክ ወይም ጣውላ ላይ መቀዳቱን ማሳየት ነው፡፡ ለምሳሌ-“የሉጥ ቅንጣት ንድፍ ቅጅ በጠንካራ ጣውላ ላይ”
 5. ሌሎች በመሰየሚያ ላይ ያሉ ስሞች አሳሳች ይሆናሉ፡፡ ለምሳሌ-ሉጥተብሎ ስለተፃፈ ብቻ ከሉጥ እንጨት መሰራቱን አይገልፅም፡፡  

Pin It on Pinterest

Share This