አብዛኛውን ጊዜ የቦታ ንድፍ የተለያዩ ስያሜ ያላቸው የቤት-ዕቃዎች አባላትን እንዴት እንደሚያካትት እና የቦታውን ስሜት እንደሚያመጣ ሙሉለሙሉ መረዳት መቻል አዳጋች ይሆናል፡፡ ይህን አይነት አረዳድ ለውጫዊ አካባቢ ንድፍ አውጪዎች ፈጠራ የተሞላበት ስራን የመስራት እድል እና ለረጅም ጊዜ ያስቀመጧቸውን ዓላማዎች ቦታዎችን በመቅረፅ እንዲያሳኩ ያግዛል፡፡

የመንገድ ላይ የቤት-ዕቃ ከህዝብ ቦታ ጋር የተዋሃደ ሲሆን ማንነት በዙሪያው የቦታ ስሜትን ይፈጥራል፡፡ የመንገድ ላይ የቤት-ዕቃዎች የሚያስገኘው፤ ለምሳሌ፡ መጓጓዝን ለማመቻቸት ወይም ከመንገዱ ቀጥሎ ያለውን መሬት ጥቅም ላይ ማዋል በከተማ አካባቢዎች መንገዱን የበለጠ ማራኪ ስነውበት እንዲኖረው ማድረግ፡፡ ቢሆንም እነዚህ ቁሶች በመጋጠሚያ ጎን ሲደረጉ የአሽከረካሪዎችን ዕይታ ለያደናቅፉ ይችላሉ፡፡ በተለይም በዙሪያቸው ህዝብ የበዛበት ከሆነ፤ ለመንገዱ የሚቀርቡ ከሆነ ደግሞ የእግረኞችን ዕይታ ማደናቀፍ የለባቸውም፡፡

የቤት-ዕቃው አላማ እቅዱን በትክክል እንዲያቀርብ የቦታውን የአሁን እና ተፈላጊ የአጠቃቀም ንድፍ ከግምት ውስጥ ማስገባት፤ ጥራት ያለው የቤት-ዕቃ ዋጋው ውድ በመሆኑ በሚያስፈልግበት ቦታ ብቻ ጥቅም ላይ መዋል ይኖርበታል፡፡ የመንገድ ላይ የቤት-ዕቃዎችን በመምረጥ ወይም ንድፍ በማውጣት ውስጥ የተለያዩ ዘዴዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ፡ ቀጣይነት ያለው ለዛ ለመኪና እና እግረኛ መንገዶች የተዋቀረ ምርጫ ወይም የመንገድ መልኮቹ ራሳቸው እንደ ጥበብ ውጤቶች ሊነደፉ ይችላሉ፡፡ 

በአጠቃላይ የመንገድ ላይ የቤት-ዕቃዎችን በመምረጥ እና ቦታ መርጦ በማስቀመጥ ውስጥ አምስት መሰረታዊ መስፈርቶች አሉ፡፡ ማለትም የእቃው አስፈላጊነት እና አላማ እቅዱን ማሳካት መቻል ፣ አቀማመጥ (እያንዳንዱ እቃ በየት ቦታ ላይ መቀመጥ አለበት)፣ ዘይቤ እና መልክ (በተለያዩ እቃዎች መካከል ያለመቋረጥ ወይም ግንኙነት እንዲኖር)፣ ዘላቂነት(የተጠበቀውን አገባብ እንዲሰጥ) እና ዋጋ፡፡

የመንገድ ላይ የቤት-ዕቃ አስፈላጊነት

የመንገድ ላይ የቤት-ዕቃዎች ለማረፍ፣ ለመቀመጥ እና ለመመገብ እና ከሌሎች ጋር ማህበራዊ ግንኙነት ለመመስረት የሚመች አካባቢን ይፈጥራሉ፡፡ እንደዚህ አይነት አካባቢዎች አድሜያቸው ለገፋ፣ እንቅስቃሴያቸው ለተገደበ እና ህፃናትን ለያዙአዋቂዎች የሚመች አካባቢን ከመፍጠራቸውም በላይ ጥሩ አየርን ለማግኘት ያግዛሉ፡፡

ተገቢ በሆነ መንገድ የተመረጡ እና የተቀመጡ የቤት-ዕቃዎች ሰዎችን  ከቤት ውጪ ወዳሉ ቦታዎች ይስባሉ፡፡ ዋናው  ጥሪ ከቤት ውጪ ወዳሉ ቦታዎች የሚያስደስት ተቀባይነት፣ መዝናናት እና ተሳታፊነት እንዲሰማቸው ማድረግ ነው፡፡ የከተማ ቦታዎች የቤት-ዕቃዎች በጥራት፣በጠባያቸው እና አንድ የማንነት ስሜትን በመፍጠር እንዲሁም በከተማው ውስጥ ባላቸው ስርጭት፣ በተለያዩ ከተሞች እንደሚታየው የለንደን ቀያይ የስልክ ጎጆዎች እና የፓሪስ የምድር ውስጥ ባቡር መግቢያዎች ለከተሞቹ ማንነት ድንቅ እና ተፈላጊ መሆን ከቻሉት ውስጥ እንደ ምሳሌ ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው፡፡ የመንገድ ላይ የቤት-ዕቃዎች ለሚገኙበት አካባቢ የጥራት መስፈርት እና ግምት እና ፕላን ለማድረግ እንደ መነሻ ነጥብ ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡

የመንገድ ላይ የቤት-ዕቃዎችን ንድፍ ማዘጋጀት

የመንገድ ላይ የቤት-ዕቃዎችን ንድፍ ለማዘጋጀት መናፈሻ ቦታ፣መንገድ፣የገበያ ማዕከል፣ የመዝናኛ አካባቢም ይሁን ሞል፤ በመጀመሪያ በግምት ውስጥ የገባውን ቦታ አይነት ማወቅ እና ፍችውን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ የመጀመሪያዎቹ ፍች ሰጪ ጥያቄዎች የቦታው ዋነኛ ተጠቃሚዎች እነማን ናቸው፣ለምን አላማ እቅድ እና በምን ጊዜ ጥቅም ላይ እንደሚውል እና ተጠቃሚዎች በቦታው በሚደርሱበት ጊዜ እንዴት አገልግሎቱን ሊሰጥ ይችላል የሚለው መሆን አለባቸው፡፡የተጠቃሚዎችን ፍላጎት ወይም የአካባቢውን የአየር ሁኔታ ከግምት ባላስገባ ሁኔታ በተለምዶ የቤት-ዕቃዎቹ ሰፋ ያለ የንድፍ እሳቤ በታቀደበት እና በተዋቀረበት ሲከተሩ የበለጠ የተሳኩ ይሆናሉ፡፡

የአሰራር ወይም ባህርይ ምክንያቶች

የአቀማመጥ ባህርይ እና ቅርፅ

ግሄል የተባለ ፀሀፊ እንዳለው ከሆነ፤ ለብቻ ለመቀመጥ እና ማህበራዊ መደብን ያማከለ መሆን ይገባቸዋል፡፡ እነዚህን ሁለት ቅድመ ሁኔታዎች ያሟላ የቤት-ዕቃ ሲሆን የተለያዩ እና ብዛት ያላቸውን ተጠቃሚዎች ይጋብዛል፡፡ ከሌሎች ርቀታቸውን መጠበቅ የሚፈልጉ ሰዎች ረጅም ሙሉ አግዳሚ ወንበሮች ተመራጭ ናቸው፡፡ ቀጥታ የሚባሉ እንደ ደረጃ፣አፋፍ ወይም ቀጥታ አግዳሚ ወንበሮች በሰዎች መካከል ተፈጥሯዊ የሆነ ርቀትን ይፈጥራሉ፤ ያልተፈለገ ዕይታንም ያስቀራሉ፡፡ ሌላው አማራጭ የማይገናኙ ተጠቃሚዎችን መጠነኛ በሆነ ርቀት ክብ የሆነ አግዳሚ ወንበር ሲሆን የከተማ ውስጥ አግዳሚ ወንበሮች ርቀትን የሚጠብቁ ቢሆኑም ተግባቦትን በመፍጠር እና በመደገፍ ላይ ግን ጥሩ የሚባሉ አይደሉም፡፡ ለሁለት ሰዎች ብቻ ንግግርን ለማድረግ ይቻላል፡፡ ነገርግን በቡድን ለመጡ ሰዎች የአግዳሚ ወንበር ጋባዥ አይደለም፡፡ ክራንክ ሻው እናዳመለከተው ከሆነ አግዳሚ ወንበርን በመጠኑ በማዕዘን መከፈት እና መዘጋት የሚችል አድርጎ ማዘጋጀት ይቻላል፡፡ ይህም ንግግርን ለማድረግ አማራጭን እንዲሰጥ ታስቦ ነው፡፡ ተንቀሳቃሽ ወንበሮች እና ጠረጴዛዎችም ሊጨመሩለት ይችላሉ፡፡ ህዝብ በሚበዛባቸው ቦታዎች የሚገኙ ስርጉድ መቀመጫ ያላቸው ወንበሮች እብጥ መቀመጫ ካላቸው በበለጠ የማህበራዊ ግንኙነት መቶኛ ድርሻ አላቸው፡፡ ስርጉድ መቀመጫ ያለው ወንበር የገፅለገፅ ግንኙነትን እና ተፅዕኖ ማሳደርን ያበረታታል፡፡

የተጠቃሚዎች ልዩነት

የተለያዩ ተጠቃሚዎች የተለያየ ፍላጎት እና ባህርይ አላቸው፡፡ መቀመጫ ቦታዎች ይህን ልዩነት ማሳየታቸው ጥቅሙ የሚሆነው የተለያዩ ተጠቃሚዎችን የሚጋብዝ አካባቢን መፍጠር ነው፡፡ በተለይም እድሜያቸው የገፋ የሚባሉ ሰዎች እና የከተማ ላይ መቀመጫ የቤትዕቃዎች የማይነጣጠሉ ናቸው፡፡ በአካላዊ እና ስነ-አእምሮአዊ ጤናቸው እና በማህበራዊ ግንኙነታቸው ላይ የሚኖረው አስተዋፅኦም ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ እድሜያቸው የገፋ ተብለው ለሚታወቁ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚሆን የከተማ የንድፍ መስፈርት ከቤት ውጪ ያለ መቀመጫ፣የከተማ የቤት-ዕቃ፣የጠፈር አካባቢ፣ለማረፊያ ነት የሚሆን የመቀመጫ ቦታ፣የጋራ ስፍራ፣ልዩ ቅንብር እና የመወያያ ስፍራ ተብሎ ሊጠራ ይችላል፡፡

የምቾት ልዩነት

በህዝብ ክፍት ቦታዎች ያለው ምቾት በብዙ ምክንያቶች ሊጠቃ ይችላል፡፡ ሊረዱ በሚችሉት የደህንነት ደረጃ፣የሰዎች እና የአካባቢ ቅርርብ፣የአየር ሁኔታ፣አካላዊ ሁኔታ፣ምቾት እና የመሳሰሉት ምክንያት ከሚባሉት ውስጥ ናቸው፡፡

ስፑነር በ2014 እንደለየው፤ በቂ መቀመጫ፣ተመጣጣኝ የጫጫታ ድምፅ ደረጃ፣ምቹ ደቂቀ አየር ንብረት እና ዕፅዋትን ለማየት የሚሆን የዕይታ መዳረሻ እንደ ምቾት ምክንያቶች ሊታዩ የሚችሉ ናቸው፡፡ በዚህ ክፍል ስር አየር ንብረታዊ(አካባቢያዊ) ምቾት፣ማህበረሰባዊ ምቾት፣ቁሳዊ እና የመቀመጫ ብዛት የሚታይ ይሆናል፡፡ ስነልቦናዊ ምቾትም እንደ ምቾት መለኪያ ሊታይ የሚችል ነው፡፡

አየር ንብረታዊ(አካባቢያዊ) ምቾት

በሰዎች ላይ የተጣሉ አካባቢያዊ ሁኔታዎች ሰዎች በእነርሱ ላይ ያላቸውን ልምምድ ሊያሻሽሉ ወይም ሊያበላሹ ይችላሉ፡፡ አካባቢያዊ አላማን ከክፍት ማህበረሰባዊ ቦታ ንድፍ ጋር ማያያዝ ውጫዊ አካባቢን በተሸለ ለመጠቀም ይረዳል፡፡ ከአየር ንብረትን መጠበቅ እና በሶስት የአየር ንብረት ደረጃዎች ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡ እነዚህም ልሂቅ፣በአንድ ቦታ ላይ የሆነ እና ደቂቅ ናቸው፡፡

ማህበረሰባዊ ምቾት

ማህበረሰባዊ ምቾት በ1980 ኃይት በተባለ ሰው የተረጋገጠ ሲሆን ፍቺውም ምርጫ ማለት ነው፡፡ ፊትለፊት ቀጥ ብሎ መቀመጥ፣በጀርባ ተደግፎ መቀመጥ፣ወደ ጎን መደገፍ፣ፀሀይ በፈነጠቀችበት ቦታ መቀመጥ፣በጥላ ውስጥ መቀመጥ፣በቡድን መቀመጥ፣ለብቻ ሊሆን ይችላል፡፡ ከቁሳዊ ምቾት በተጨማሪ ማህበረሰባዊ ምቾት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ኃይት እንዳለውም ምቾት አግድም የሆኑ ጫፎችን በተፈጥሮ ለመቀመጫ የሚሆኑ እንዲሆኑ ማድረግ ወይም ሌሎች ዝርግ ገፆችን ተጨማሪ የመቀመጫ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ነው፡፡

Pin It on Pinterest

Share This