ተለዋዋጭነት እና ተንቀሳቃሽነት ወደፊት ለሚመጡ የህንፃ ጥበብ የሚሆኑ እሳቤዎች ሲሆኑ ትኩረትም የሚያስፈልጋቸው ናቸው፡፡ የቤት-ልማትን ከሚያሰጉ አደጋዎች በኃላ ተለዋዋጭነትን መጠቀም በአስቸኳይ ጊዜዎች ጥቅም አለው፡፡ የተለዋዋጭነት ቤት-ዕቃዎች ታሪክ ከጥንታዊው ሰው ጋር ይያዛዛል፡፡ ቦታን ያገናዘበ የራሳቸውን መክፈቻ እና መዝጊያ ያለው መጠለያ መገንባት ሲጀምሩ ካለው ጊዜ ጋር ይያያዛል፡፡ ምንም እንኳን እነዚህ ቁስ አካላት ከቤት-ዕቃው ተንቀሳቃሽነት እና መለያየትን የሚጠቅሱ ቢሆንም በመዋቅር ንድፍ ውስጥ ቦታዎች በቁስ አካላት ይለያሉ፡፡ብዙ አይነት ጥቅም መስጠት ላለባቸው ቦታዎች ማጠራቀሚያ ቦታዎች መቅረብ አለባቸው፡፡ በተጨማሪም ተለጣፊ የቤት-ዕቃዎችን የመንደፍ አላማ እቅድ አካል ክፍሎቹን ማንቀሳቀስ፣ ማንሸራተት እና ማዋቀር እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

በመኖሪያ ቤት የቤት-ዕቃዎች ቴክኖሎጂ ውስጥ ያሉ የቅርብ ጊዜ እድገቶች

በአሁኑ ጊዜ በአዳዲስ ንድፍ ላይ በተመሰረቱ የቅርብ ጊዜ ልማቶች ውስጥ ሙያዊ ስልጣኔ እንደ ቄንጠኛ የቤት-ዕቃዎች ያሉ አዳዲስ ሃሳቦች ወይም ቴክኒኮችን የሚጠቀሙ የቤት-ዕቃዎችን ያስተዋውቃል፡፡ እነዚህ አዳዲስ የአሰራር ዘዴዎች የህይወትን ጥራት ራስን በማስማማት ችሎታ እና ከተፈጥሮ ጋር ተቀራራቢነት ባላቸው ቁሳቁሶች ከማሻሻሉም በላይ ተስማሚ ስነ-ምህዳራዊ ጠባይ ይጨምራሉ፡፡

የመኖሪያ ቤት የቤት-ዕቃ ቁሳቁስ የቅርብ ጊዜ እድገት

በህንፃ አሰራር ጥበብ እና ቁሳቁስ መካከል እስከ ኢንዱስትሪው አብዮት ድረስ ተራ ግንኙነት ነበራቸው፡፡ ቁሳቁስ ለአስፈላጊነታቸው እና ለተደራሽነታቸው ወይም ለቅርፅ እና ለሚያስጌጥ ባህሪያቸው በስርአትና ደንብ ይመረጣሉ፡፡

በቀደሙት ጊዜያት ነበሩት የቤት-ዕቃዎች በዘመናዊው ጊዜ እንደሚታየው፤ የማሟሟቅ ዘይቤን ሳይሆን ባህላዊ እና ተምሳሌታዊ ቅርፆችን ይጠቀሙ ነበር፤ለሚሰጠው ጥሩ እይታ እና ተፈጥሯዊነት ባህሪው ሲባል በዚያ ጊዜ የሚጠቀሙበት የመስሪያ ቁስ እንጨት ነበር፡፡

ፈጠራ የተሞላበት ምርት ለማምረት ሲሉ ንድፍ አውጪዎች የተለያዩ ቁሶችን ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡ ከእነዚህ ለመቀየር፣ለመጠቀም እና ንድፍ ለማውጣት ከሚመቹ ተለማጭ እና ምቾት ያላቸው ቁሶች ውስጥ ጨርቃጨርቅ ይጠቀሳሉ፡፡ ናንሲ ዌብስተር እንዳለውም “የተዋቀረ አካልን እጅግ አዘውትረን አንቀያይርም፡፡ ጨርቃጨርቅን በመጠቀም እያንዳንዱን አስር አመት ወይም ሁለት አመት ደግመን ደጋግመን ማሳመር እንችላለን፡፡ ጨርቃጨርቅ የማሻሻል፣የልስላሴ ሁኔታ እና የቀለም መለወጥ ውስንነት የለባቸውም፡፡ ናኖ ቁሳቁስን የመጠቀም ጥብቅ ምክንያት ቢኖርም የዚህ አዲስ ግኝት ዋጋ ከፍ ያለ መሆኑ አይካድም፡፡ ናኖ ቁሳቁስን መተግበር ለእያንዳንዱ የቤት-ዕቃ አካል እና ለሚሰጡት አገልግሎት አገባብ አጋዥ ነው፡፡

ናኖ የሙያ ስልጣኔ ስፋት ያላቸው እንቅስቃሴዎችንና ሌሎች ብዙ ጥቅሞችን ለቤት-ዕቃው ኢንዱስትሪ ያበረክታሉ፡፡ እነዚህ የሙያ ስልጣኔዎች ከሰው ፀጉር አስርሺህ ጊዜ የሚቀጥኑ ቁሳቁስን ያጠቃልላል፡፡ አብዛኞቹ የአውሮፓ አገራት ናኖ ቁሳቁስን ተቀባይነት ሰጥተው ከመጠቀማቸው በፊት ጥናት አድርገዋል፡፡

ከእነዚህ ጥናቶች ውስጥ አንዱ በ2007፤ ሪተር የተባለ ታዋቂ ያጠናው ጥናት አንዱ ሲሆን በዚህ ጥናት ውስጥ ፈጠራ የተሞላባቸው ቁሶች እንደሚከተለው ተመድበዋል፡፡

 • ናኖ ቁሳቁስ
 • ህይወታዊ ቁሳቁስ
 • ህይወታዊ፤ የሚበሰብሱ ቁሳቁስ
 • ቄንጠኛ ቁሳቁስ
 • መልሶ ለመጠቀም የሚቻሉ ቁሳቁስ
 • ድቅል ቁሳቁስ

በመኖሪያ ቤት እንደ ቤት-ዕቃዎች ያሉ ቄንጠኛ ቁሳቁሶች

ቄንጠኛ የቤት-ዕቃዎች በቅዝቃዜ ጊዜ ራሳቸውን ማሞቅ የሚችሉ እና በፀሃይ ብርሃን ውስጥ ቀለማቸውን መቀየር የሚችሉ ሊባሉ ይችላሉ፡፡ የቤት-ዕቃዎች ጥበቃ የሚያስፈልግባቸው ቦታዎች አሉ፡፡ እነዚህም ቢሮዎች፣ሆስፒታሎች ወይም ሌሎች መሰል ቦታዎች ሲሆኑ ለተቋማት የሚያስፈልጉ የቤት-ዕቃዎች ለመኖሪያ ቤቶች ከሚያስፈልጉ የቤት-ዕቃዎች የበለጠ ውድነት አላቸው፡፡

የቤት-ዕቃ ንድፍ በትንሽ የጥሬ-ዕቃ እና የሰው ሀይል ፍጆታ የተሻለ አጠቃቀም እና ምርት መስጠት፤ በዚህ ሂደት ውስጥም ናኖ ቁሶች እነዚህን ሁሉ ፍላጎቶች የሚደርስ እና አነስተኛ ዋጋ የሚያስወጣ ቄንጠኛ የቤት-ዕቃ ማምረት ከአላማዎቹ እንደ አንዱ ሲሆን ናኖ ቁስ ይህን በማሳካት ውስጥ ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡ ናኖ ቁሶች ሙያዊ እና ጥሩ አቅም እንዲኖራቸው ተደርገው ሲሰሩ፤ በስተመጨረሻ ውድ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ከእነዚህ ናኖ ቁሳቁስ አይነቶች የሚጠበቁ ነጥቦች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል

 • ለማፅዳት ቀላል
 • እቃዎችን ከልእለ-ሐምራዊ ጨረር የሚጠብቅ ሽፋን
 • አነስተኛ ፍጆታ
 • ለመቀየር ቀላል
 • ደህንነት
 • እሳትን መቋቋም
 • ይበልጥ ዘላቂ እና ጠንካራ
 • ቀጣይነት ያለው ባህርይ
 • የተሻለ ብዛት ያላቸው ቀለል ያሉ ቁሶች

ቄንጠኛ ቁሶች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል

 • ቅይጥ ቁሶች
 • ባህርይ ቀያሪ ቁሶች
 • የሚታይ ባህርይ
 • ሜካኒካላዊ ባህርይ
 • ኬሚካላዊ ባህርይ
 • ኤሌክትሪካዊ ባህርይ
 • የሙቀት ባህርይ
 • ገፅ ቀያሪ ቁሶች
 • ቀለም ቀያሪ ቁሶች
 • ባለብዙ ጥቅም ቁሶች
 • ብርሃን ለቃቂ ቁሶች

ሌሎች የቄንጠኛ ቁሶች አይነቶች የማይክሮ ካፕሱል ህብር ሲሆኑ 5 ኢቴሊዲን-2 ኖርቦረኒን እና ክፍት ታዲን ሞኖመሮች ከሩቲኒየም ግረብ ጋር የተደባለቁ ናቸው፡፡ እነዚህ ቁሶች በተጎዱ ጊዜ ሜካኒካላዊ ባህሪያቸውን መልሰው የመገንባት ባህርይ አላቸው፡፡ ይህም የተሻለ የእድሜ መጠን እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡ ለዚህ ምሳሌ የሚሆኑት ፖሊመሮች፣ሴራሚኮች እና መሰሎቻው ናቸው፡፡

አብዛኞቹ ናኖ ቁሶች አንድ፣ሁለት ወይም ሶስት ልኬት አላቸው፡፡ አማካይ የንድፍ መጠናቸውም ከ1-100 ናኖ ሜትር

 • የመጀመሪያው ልኬት ቀጭን ለሆነ ግራፊን መሰል ቁስ ነው፡፡ ለዚህ ምሳሌ አንፀባራቂ መስኮት እንደዚህ አይነት ባህርይ አለው፡፡
 • ሁለተኛው ልኬት ጠፍጣፋ የመሆን አቅም አለው፤ ናኖ ዘንግ እና ናኖ ትቦ ወይም ባለ ብዙ ግድግዳ ናኖ ትቦ ሲሆኑ ትቦው ክፍት በመሆኑ ከዘንጉ ይለያል፡፡
 • ሶስተኛው ልኬት ሁሉም የልዩቁስ ቅርፅ ያሉበት ነው፡፡ ቅርፆቹም ሶስት ማዕዘናዊ፣ሉላዊ፣አራት ማዕዘናዊ እና ሞላላዊ ናቸው፡፡

ናኖ ቁስ ለመስሪያ ቁስ እና ለምርት ማሻሻል ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ በሌላ አገላለፅ ልዩ ጨርቃጨርቆች፣ጠንከር ያሉ እንጨቶች እና ለኮንክሪት፡፡ በተጨማሪም ናኖ የሙያ ስልጣኔ በየትኛውም ዕቃ ላይ ለተለያየ አላማ እቅድ እና ጥቅም ውበት ለሚጨምሩ ቅቦች ጥቅም ላይ መዋል ይችላሉ፡፡ ናኖ ቁሶች ቅይጥ፣ኮንክሪት እና ብረት ተብለው ሊገለፁ ይችላሉ፡፡               

Pin It on Pinterest

Share This