የተባበሩት መንግስታት የአካባቢ እና ልማት ኮሚሽን ቀጣይነት ያለውን ንድፍ በአሁን ጊዜ ካለው ትውልድ ጋር የሚጣጣም እና የቀጣዩን ትውልድ ፍላጎቱን የማሟላት አቅም የማይገድብ ብሎ ይገልፀዋል፡፡ በመሆኑም ቀጣይነት ሶስት መስፈሪያ አሉት፡፡ እነዚህም ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊ እና አካባቢያዊ ናቸው፡፡ የፅሁፉ የትኩረት ነጥብ አካባቢያዊ ቀጣይነት ነው፡፡
በቅርብ ጊዜያት ኩባንያዎች እና ድርጅቶች ምርቶቻቸው የሚያሳድሩትን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመቀነስ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ይህን ለማድረግም የተለያዩ ዘዴዎች ተለይተዋል፡፡ የምርት ቀጣይነት የምርቱ ዕድሜ ርዝማኔ በአካባቢ ላይ የሚያመጣውን ተፅዕኖ ለመቀነስ ሲባል ከግምት ወስጥ መግባት አለበት፡፡
የአካባቢ እና የእድሜ ዑደት ንድፍ መሳሪያዎች ምርቱ በአካባቢ ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ እና ምርትን መልሶ የመጠቀም እና/ወይም የመፈታታት ለማነፃፀር ያግዛሉ፡፡ በንድፍ ሂደት ውስጥ በአካባቢ ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ማነፃፀር እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ብራስ(1997) ባሳተመው መፅሀፉ ውስጥ የቤት-ዕቃ አምራቾች የሚከተሉትን ጥያቄዎች ከግምት እንዲያስገቡ አሳስቧል፡፡
- ንድፍ አውጪዎች የዑደት ህይወት ላይ አፅንኦት እንዲኖራቸው የሚያግዙ አይነት አዲስ መሳሪያዎች
- እነዚህ ዘዴዎች እንዴት ከነባር እና በአግባቡ ከተመሰረተ የንድፍ ስርአት፣መሳሪያ እና ልምምድ ጋር ሊዋሃዱ ይችላሉ
- መደራረብን እንዴት መቀነስ እንደሚቻል እና መረጃን በመሰብሰብና በማደራጀት እንዴት ቅልጥፍናን መጨመር ይቻላል
ኩባንያዎቹ የአካባቢ እና የኑሮ ዑደት ለማስተካከል የሚሆን ንድፍን ስራ ላይ ከማዋላቸው በፊት ለዚህ የሚሆን አደረጃጀት እና መሰረተልማት ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ሳይሆን ወደ ተግባር መግባት አሉታዊ መዘዝ ይኖረዋል፡፡ በመሆኑም እነዚህ መሳሪያዎች የንድፎቹን አካባቢያዊ ተፅዕኖ መቀነስ ብቻ ሳይሆን የምርት ስርአቱንም ማሻሻል ይኖርባቸዋል (ብራስ 1997 እ.አ.አ)፡፡ እንደ ውጤት፤ ኩባንያዎች ቀጣይነት ያለው ንድፍን የማሳካት ግብን እውን ለማድረግ የሚከተሉትን መመሪያዎች መከተል ይኖርባቸዋል፡፡ በስያሜ እንደተቀመጡትም
- ቀላል – ለመጠቀም የሚቀል
- በቀላሉ የሚገኝ – ምክንያታዊ የሆነ ዋጋ
- በትክክል ተበያኝ – አጠቃቀሙ ግልፅ የሆነ
- በገሃድ የሚታይ – ተመሳሳይ ውጤቶች መገኘት ይኖርባቸዋል
- ተገቢ – በትክክል የተለካ፣የታሰበውን ነገር የሚጠቅስ እና የሚተነብይ
- ጠንካራና ጤናማ – ብዙ ምላሽ በትግበራ ውስጥ ለሚመጡ ለውጦች አለመስጠት
- ግንዛቤንና ትንበያን መጨመር
የመስሪያ ቁሳቁስ ምርጫ
ባለፉት አስርት አመታት አካባቢ ላይ ትኩረት ያደረጉ የህዝብ ፍላጎት እና ደንቦች በዓለምአቀፍ ገበያ ላይ ብዙ ለውጦች እንዲመጡ አድርገዋል፡፡ እነዚህ ፍላጎቶች እና ደንቦች አምራቾች የአመራረት መንገዳቸውንና ለአካባቢ ሃላፊነት በሚሰማው መንገድ እነዲሆን አድርጓል፡፡ የመሳሪያ ቁሳቁስ ምርጫ ወሳኝ ነው በመሆኑም ንድፍ አውጪዎች ቀዳሚ የምርቶች ንድፍን ከመጀመራቸው በፊት ቀሶቹ በአካባቢ ላይ የሚያደርሱትን ተፅዕኖ እንዲያጤኑ ያደርጋል፡፡
በአሁኑ ጊዜ አምራች ኩባንያዎች መስሪያ ቁሳቁስን ለመምረጥ የአካላዊ፣ኬሚካላዊ እና ስነ-ውበት እንዲሁም ዋጋ እና የመገኘት አዝማሚያን መሰረቱ ያደረገውን የተለመደውን ባህላዊ መስፈርት መገለጫ ሳይሆን አካታች ሀይል፣የካርበን ዱካ እና የተፈጥሮ ሀብት መሟጠጥን የሚያካትቱ አዳዲስ ግብአቶችን ይጠቀማሉ፡፡
እነዚህ ግብአቶች አዲስ እና የበለጠ ቀጣይነት ያለው የቁስ አጠቃቀም እና መልሶ አጠቃቀም አካባቢን የሚጎዳ ውጤትን ለመቀነስ ይረዳሉ፡፡ የሚከተለው አጠቃላይ ቁስ በአካባቢ ላይ ያለውን ተፅዕኖ ለማጤን የሚረዳ መግለጫ ነው፡፡
የቁስ ባህርይ | አነስተኛ አካባቢያዊ ተፅዕኖ | ከፍተኛ አካባቢያዊ ተፅዕኖ |
የጥሬ ዕቃ መገኘት አዝማሚያ | መልሶ ለመጠቀም የሚቻል እና/ወይም እንደልብ የሚገኝ | መልሶ ለመጠቀም የማይቻል እና/ወይም ብርቅ |
ከምንጩ ያለው ርቀት | ቅርብ | ሩቅ |
አካታች ሀይል | ዝቅተኛ | ከፍተኛ |
ድግመ ዑደት በመቶኛ ሲገለፅ | ከፍተኛ | ዝቅተኛ |
የልቀት ምረታ | ዜሮ/ዝቅተኛ | ከፍተኛ |
የቆሻሻ ምረታ | ዜሮ/ዝቅተኛ | ከፍተኛ |
የመርዘኛ እና ጠንቀኛ ነገሮች ምረታ | ዜሮ/ዝቅተኛ | ከፍተኛ |
የተረፈ-ምርቶች ወደ ምርትነት ቅያሬ | ከፍተኛ | ዝቅተኛ |
መልሶ ጥቅም መስጠት | ከፍተኛ | ዝቅተኛ |
የአገልግሎት ዘመኑን የጨረሰ ተረፈ ምርት | ዜሮ/ዝቅተኛ | ከፍተኛ |
መልሶ ለመጠቀም ያለው ቅለት | ከፍተኛ | ዝቅተኛ |
የቁስ ባሕሪያት
በአንድ ቁስ የህይወት ሂደት ውስጥ የተካተተው የሀይል መጠን የቁሱን አካባቢያዊ ደረጃ በመመዘን ውስጥ ቁልፍ ማስረጃ ነው፡፡ ሁሉም ቁሶች ከፀሀይ ተወስዶ በምድረ ዕብን ውስጥ የተያዘ ሀይልን ይወክላሉ፡፡ አንዳንድ ቁሶች ለማምረት ከሌሎቹ በበለጠ ሀይልን ይጠይቃሉ፡፡ ከእነዚህ ቁሶች ውስጥ አሉሚኒየም እንደ ምሳሌ መጠቀስ ይችላል፡፡ እነዚህ ቁሶች በከፍተኛ ደረጃ ሀይሉን አካተው የያዙ ናቸው፡፡
አብዛኞቹ ሰውሰራሽ እቃዎች ከአነስተኛ እስከ መካከለኛ ሀይልን ይይዛሉ፡፡ ከዚህ በታች ያለው አንዳንድ ቁሶች በውስጣቸው ያለውን የተካተተ የሀይል መጠን ይገልፃል፡፡
የቁስ አይነት | መደበኛ የተካተተ ሀይል (በእያንዳንዱ ኪሎግራም ውስጥ ያለ የማክሮ ጁል መጠን) |
በህይወተ ክበብ እና በምድረ ዕብን የሚገኙ ቁሶች | |
የሴራሚክ ቁሶች | 2-4 |
እንጨት፣ቀርከሃ፣ቡሽ | 2-8 |
የተፈጥሮ ጎማ | 5-6 |
ጥጥ፣ቃጫ፣ሀር፣ሱፍ | 4-10 |
የእንጨት ቅይጦች | 6-12 |
ከፍተኛ እፍጋት ያለው አሉሚኒየም | 300-350 |
ቀላል የአሉሚኒየም ቅይጦች | 235-335 |
ሜላሚን | 120-150 |
ኢፖክሲ | 100-150 |
ናይሎን | 170-180 |
ወርቅ | 5600-6000 |
ፖሊኢታሊን | 85-120 |
ፖሊፕሮፓሊን | 90-115 |
ክውር ብረት | 34-66 |
ከፍተኛ ሀይል ያካተቱ የማምረቻ ቁሶች በምርት ሂደቱ ውስጥ አካባቢ የሚበክሉ፤ ከምርት በኃላ ደግሞ ቀጣይነት ያላቸው ናቸው፡፡