ስለ መጸዳጃ ቤት መስታወቶች ብዙ የሚወደዱ ነገሮች አሉ መስታወቶች ሰውነት ላይ ያለውን ማንኛውንም ነገር ከማሳየት ባለፈ አሁን አሁን ደግሞ ለፎቶ ተመራጭ ቁስ እየሆኑ መጥተዋል፡፡በእርግጥ ትክክለኛው መስታወት የቤቱን ውበት በማጉላ አንድ አይነተኛ ሚና ይጫወታል፤ የተፈጥሮ ብርሃንንም ያጎላል፡፡በመሆኑም ይህንን ቁስ በመጠቀም የሚፈለገው ውበት ለመስጠት እንዲቻል የሚረዱ የተለያ የመስታወት አይነቶችን እንዘረዝራለን፡፡

ፉል ብሊድድ መስታወት

እንደ ጡብ እና ድንጋይ ያሉ ቁሳቁሶች በ አነስተኛ መታጠብያ ቤት ውስጥ ብዙ እይታን ይጨምራሉ። በመሆኑም በትንሽ መታጠቢያ ቤት ውስጥ ግድግዳዎን በመጠቀም ለማሳመር በእግጉ ተፈላጊ ናቸው። ከወለል እስከ ጣሪያ ባለው ግድግዳ ላይ በመጠቀምም መስታወት የሕንፃ ክፍሎቹን ውበት በእጥፍ መጨመር ይቻላል።ይህ አይነቱ የመታጠብያ ቤት መስታዎት በጡብ ወይም በድንጋይ የተሰራ መታጠብያ ቤት ላላቸው  ቤቶች ተመራጭ ነው።

የታጠፈው የማዕዘን መስታወት

የመስታወት ከክፍሉ የቀለም ንድፍ ላይ መጣጣም በዲዛይን ሂደት ውስጥ ነገሮችን በጣም ቀላል ያደርጋቸዋል። ብዙ ግዜ አንድ ክፍል ሙሉ ለሙሉ በአንድ አይነት ቀለም የሚቀለም ከሆነ አሰልቺ የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው።የክፍሉን ጥግ ላይ የታጠፈ መስታዎት በማድረግ  ወደ አስደናቂ ሰፍራነት መለወጥ ይቻላል፡፡

ድርብ እጅ መታጠብያ እና ነጠላ መስታወት

ድርብ ማጠቢያዎች ስላሉዎት ድርብ መስተዋቶች ያስፈልጉዎታል ማለት አይደለም ፡፡ አንድን መስታዎት ሁለት ቦታ በመክፈል ከጫፍ እስከ ጫፍ ይዘርጉት፡፡ አንድ ትልቅ መስታወት ያለበትን ስፍራ በእጥፍ ስለሚጨምር ከመስታዋት በስተጀርባ የተደበቀ ካቢኔት ሊያደርጉም ይችላሉ ፡፡ በአረንት እና ፒኬ በተባሉ ዲዛይነሮች በተዘጋጀው በዚህ ንድፍ በመታገዝ  የመታጠቢያ ክፍል ውስጥ ባሉት መስታወቶች አማካኝነት የክፍሉን ውበት በመጨመር ረገድ ቀለል ያሉት የነሐሱ ክፈፍች ሌሎቹን አንፀባራቂ ዝርዝሮች በጠቅላላ ጎላ አድርጎ በማሳየት አይነተኛ ሚና የሚጫወቱ ሲሆን በተጨማሪም ጥቁር ግራጫነት ባላቸው መሳቢያዎች እና በጥቁር ስዕሎች ላይ የበለጠ ጎልተው ይታያሉ፡፡

የመስተዋት ካቢኔት

 በመታጠቢያ ቤት ውስጥ ያለው ስፍራ ጠባብ በሚሆንበት ጊዜ ከመታጠቢያ ገንዳው በላይ መስታወት ያለው ካቢኔት ማድረግ ምንም ችግር የለውም ፡፡ በተለይ ባህላዊ ቃና ባለው ቤት እና የሚያምር የመታጠቢያ ክፍል ውስጥ የተንሰራፋው የመስታወት ካቢኔት ያለ ምንም እንከን የመጣጣም እድሉ ከፍተኛ ነው።

የማዕዘን ድርብ መስታወቶች

ድርብ ማጠቢያዎች ከድርብ መስተዋቶችን ጋር ሲሆኑ ዉበታቸው የበለጠ ጎልቶ ይወጣል ፡፡ይህ በግድግዳ መስታወት ውጭ በሁለቱ መስታወቶች መካከል ያለው ክፍት ቦታ ለተጨማሪ የግድግዳ መብራት ቦታን የሚሰጥ ሲሆን፤ክፍት እና በብርሀን የተሞላ መፀዳጃቤት ምርጫዎ ከሆነ ይህን የመታጠቢያ ቤት መስታወት ምርጫዎ እንዲያደርጉ ይመከራል፡፡

ባለ ቅርጽ መስታወት

ትንሽ ለየት ያለ ነገር የሚመቾት ከሆነ ወይም አራት ማዕዘን እና ክብ መስተዋቶች ማየት ከሰለቾት ሳቢነት ያለው በተለያ ቅርፅ የተሰራ የመስታወት አይነት መሞከሩ መልካም ነው። ለምሳሌ የታጠፈው መስታወት  የመታጠቢያ ገንዳውን ጠመዝማዛ  መልክ በመስጠትየሚያሳምረው ሲሆን  ባለቀለም ሐምራዊ አምፖል ሲጨመርበት ደግሞ ሳቢነቱ የበለጠ ይጨምራል።

ተንጠልጣይ መስታወቶች

የተንጠለጠሉ መስተዋቶች በዲዛይን ዓለም ውስጥ አጭር  እድሜ ያለቸው ተወደጅ ዲዛይኖች ናቸው ፡፡ ለእይታ አስደሳች የሆነ  ቅንጡ ዘመናዊ  መስታዎቶች ናቸው ፡፡

ቀጥ ያለ መስታወት

ተናንሽ የመታጠብያ ክፍልን ዲዛይን ሲያደርጉ እና በምርጫዎ ላይ የፈጠራ ነገር እንዲኖርዎት የሚፈልጉ ከሆነ ይህንን መስታዎት ምርጫዎን ያድርጉ ፡፡የመታጠቢያ ገንዳውን በጠርዝ ጎን ለጎን አድርጎ በመስኮቱ እና በማእዘኑ መካከል በቀጭኑ ቦታ ላይ በትክክል እንዲስማማ ጠባብ ቀጥ ያለ መስታወት በማከል ውብ የሆነ ከባቢን መፍጠር ይቻላል ፡፡

ዘንበል ያለው ባለ ሙሉ ርዝመት መስታወት

 ይህ እስካሁን ካሉ የመታጠብያ መስታወት ዲዛይኖች በጣም ቀላሉ የመታጠቢያ መስታወት ሀሳብ ሲሆን ለመስራት ማድረግ ያለብዎት ነገር ቢኖር ክፍሉ ውስጥ መግባት ግድግዳው ላይ ዘንበል ማድረግ ነው ሲሆን ይህ ቅንብር የበለጠ ውጤታማ የሚሆነው ግን  የእብነ በረድ ወለሎች እና ለስላሳ ቀለሞች ሲታከሉበት ነው፡፡በመሆኑም በእንደዚህ አይነት ይህንን የመስታወት አይነት በመጠቀም በማድረግ አስደናቂ ዉበትን መፍጠር ይቻላል፡፡

ኦቫል ድርብ መታጠብያ ሳህኖች

ቀደም ሲል እንደተገለጸው  ሁለት መታጠቢያዎች እና ሁለት መስታወቶች ሲኖረው ልዩነቱ መስታዎቱ ሞላላ መሆኑ ላይ ነው፡፡ ይህን ዘይቤን በመጠቀም እና መስታዎቶቹን ጎን ለጎን በማጣበቅ አዲስ ውበት መፃዳጃ ቤትዎ ላይ ይጨምሩ ፡፡

የመልበሻ ክፍል መስታወት

የመታጠቢያ ክፍልዎ በጣም ሰፊ ከሆነ ፣ ባለ ሶስት አቅጣጫዊ መስታወት በመጠቀም የተሟላ የመልበሻ ክፍል ማግኘት ይችላሉ፡፡ ይህም በጠዋት ተነስተው ለመዘገጃጀት ሂደቱን በጣም ቀላል ያደርግሎታል።

የተሸለመው መስታወት

በተለያዩ ቀለማት እና የዲዛይን አይነቶች ያጌጡ የተለያዩ የመስታወት አይነቶችን የሚመለከት ረድፍ ሲሆን በተለያዩ የመታጠቢያ ክፍሎች ውስጥ የመስታወቱ ሰማያዊ የቆዳ ውጫዊ ሽፋን ከእብነበረድ እና ከጥቁር ግድግዳ ጋር የሚፈጥረው ውህደት አስገራሚ ነው፡፡

Pin It on Pinterest

Share This