ተጠቃሚዎች ከቤት-ዕቃ የሚፈልጓቸው ነገሮች

ተግባር

የቤት-ዕቃን በመምረጥ ውስጥ አብዛኛው ተጠቃሚ ተግባራዊነትን በመጀመሪያ ደረጃ ላይ እንደሚያስቀምጠው ይገልፃል፡፡ ጥሩ የሚባል የቤት-ዕቃ አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች እቃዎችን በማስቀመጥ የሚገጥማቸውን ተግዳሮት የሚያስቀር የቤት-ዕቃ ነው፡፡ ለምሳሌ ብዙ ሰዎች እቃቸውን በፈርጅ ማስቀመጥ ይፈልጋሉ፡፡ ስለዚህም ሳጥን ወይም ኪስ መሰል ውቅር ያለውን የቤት-ዕቃ ይመርጣሉ፡፡

የማከማቻ ዘይቤ

ከተግባር በመቀጠል ተጠቃሚዎች ለቤት-ዕቃው ገፅታ ዋጋ ይሰጣሉ፡፡ ማከማቻ ሁሉንም ነገር ለማደራጀትና ለማሳየት ጥሩ መንገድ መሆኑን ያምናሉ፡፡ ማከማቻ ሰዎች ንብረታቸውን ከፊትለፊታቸው ቀርቦ ለማየት እና ለጓደኞቻቸውና ለቤተሰባቸው ለማሳየት ይረዳቸዋል፡፡

ተለጣጭነት

አንዳንድ ሰዎች በኑሮ ሁኔታቸው ምክንያት ከአንድ ቦታ ወደ ሌላው ይዘዋወራሉ፡፡ በዚህም ጉዟቸው ወስጥ የሚኖሩበት ቤት ስፋት መለዋወጡም የማይቀር በመሆኑ ሰፊ የመኖሪያ ክፍል ሲኖራቸው የሚለጠጥ ጠባብ የመኖሪያ ክፍል ሲኖራቸው ደግሞ መጠኑ የሚቀንስ የቤት-ዕቃ ይፈልጋሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አዲስ እቃዎችን መግዛታቸው አይቀርም፡፡ ስለዚህ የሚያስቀምጡት የእቃ መጠንም አብሮ እንደሚጨምርና ለዚህም መፍትሄ የሚሆን ተለጣጭ የቤት-ዕቃ እንደሚያስፈልጋቸው መገመት ይቻላል፡፡

ቅለት

ለመገጣጠም ከባድ የሆነ የቤት-ዕቃ አላማውን ያላሳካ ከመሆኑም በተጨማሪ ተጠቃሚዎች አይናቸውን ሊጥሉበት አይጋብዝም፡፡ ቅለት ማለት ተጠቃሚዎች ትእዛዝ ማንበብ ሳያስፈልጋቸውና ጊዜያቸውን በዚያ ላይ ሳያጠፉ በቀላሉ ተረድተው እንዲጠቀሙ ማመቻቸት ማለት ነው፡፡ 

ጄምስ ሄነሲ ቪክቶተር ፓፓኔክ የዘላን የቤት-ዕቃ በሚለው መፅሀፋቸው እንደፃፉት የዘላን የበት-ዕቃ ማለት ለመስራት ቀላል፣ክብደቱ ቀላል ሆኖ መተጣጠፍ የሚችል፣ለመገጣጠም እና መልሶ ለማፍረስ የሚቻል፣በተፈለገው መንገድ ለማዋቀር የሚቻል የቤት-ዕቃ ነው፡፡ የተፈጥሮን ስነ-ምህዳር የመንከባከብ መወገድ ወይም መልሶ ለመጠቀም የሚቻልም ነው፡፡

አብዛኛው በህይወታችን ውስጥ ያለው የቤት-ዕቃ ግዙፍ፣ከባድ፣ተሰባሪና በሌሎች ምክንያቶች ለማንቀሳቀስ የሚከብድ ነው፡፡ ምንም እንኳን የዘላን የቤት-ዕቃ እሳቤ ተቃራኒ ቢሆንም አዘውትረው እየተንቀሳቀሱ ለሚኖሩ ሰዎች ጥቅም ለመስጠት፤ እንዳንድ የስነ እንቅስቃሴ ሀይሎችን፣ቁሳቁስ ምርጫ እና ቀላል የሆኑ የማምረት ቴክኖሎጂ ይጠቀማል፡፡ በዚህም ሰዎቹ በጥቂት ክፍያ ብዙ ብዙ ጥቅም እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡

እነዚህ የቤት-ዕቃዎች ጥቅም ላይ በሚውሉበት ጊዜ በቀላሉ የሚገጣጠሙ እና ዘላቂነት ያላቸው ናቸው፡፡ በተምኔታዊ እይታ በተለያየ አካባቢ ለመጠቀም የሚያስችል ተጣጣፊነት አላቸው፤ ማለትም እንደየ ስፍራው ሁኔታ የሚስተካከል ነው፡፡ ጥቅም ላይ በማይውሉበት ጊዜ በቀላሉ መፍረስ የሚችሉ፤ በሚቀመጡበትም ጊዜ ብዙ ቦታ የማይወስዱ መሆን አለባቸው፡፡ በሚጓጓዙበትም ጊዜ ቢሆን ቀላል እና በቀላሉ መሸከም የሚቻሉ መሆን አለባቸው፡፡

የዘላን የቤት-ዕቃዎች እሳቤ በሺህ የሚቆጠሩ አመታትን ያስቆጠረ ነው፡፡ በቅርብ አመታት ይህ ሃሳብ ከዓለም እርምጃ በሚፈጥበት እና ሰዎች በተደጋጋሚ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላው እየቀያየሩ በሚኖሩበት ጊዜ መልሶ መላልሶ መወለድን(መመስረትን) ልምምዱ አድርጓል፡፡

ዘላን የቤት-ዕቃ ንድፍን ለመስራት የሚያስችሉ የተለመዱ መዋቅሮች

በመቶ የሚቆጠሩ ዘላን የቤት-ዕቃዎችን በማጥናት፤ ንድፍ አውጪው አምራቾች ዘላን የቤት-ዕቃዎችን ለመስራት የሚጠቀሟቸው ብዛት ያላቸው መዋቅሮች መኖራቸውን ሊረዳ ችሏል፡፡ እነዚህም ከዚህ በታች ተብራርተዋል፡፡

ሰያፍ ንብርብርነት ያላቸው መዋቅሮች

ይህ መዋቅር ብዙውን ጊዜ በታጣፊ የቤት-ዕቃዎች ንድፍ ውስጥ ይታያል፡፡ ሁለት ጠቀሜታዎች አሉት፡፡ አንዱ ጥቅሙ በእንቅስቃሴ ወይም በማስቀመጥ ጊዜ ለማጠፍ ቀላል መሆኑ፤ ሌላኛው ደግሞ ሰያፍ ንብርብርነት ያለው መዋቅር ጫናን ሲቋቋም የማይነቃነቅ በመሆኑ የቤት-ዕቃውን ለመጠቀም የደህንነት ጉዳይ የማያሳስብ መሆኑ ነው፡፡ ንድፍ አውጪዎችና አምራቾች ለስነውበት መሳካት ግብ ወይም ለሌላ ጉዳይ ሲሉ ጥቂት ለውጦችን ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ለዚህም ጥቂት ኩርባዎችን ሊጨምሩ ወይም ብዛት ያለው ሰያፍ ንብርብር ለማግኘት ሶስት ወይም ከዚያ በላይ እንጨቶችን በአንድ ቦታ ላይ አስተሳስረው ይጠቀማሉ፡፡ መተጣጠፍና ፀንቶ መቆምን ለማከል አንድ ምርት ከአንድ በላይ ሰያፍ ንብርብር መዋቅር ሊኖረው ይችላል፡፡ ሰንሰለት ወይም ጠፍርም ሰያፍ ንብርብሩን ለማስተሳሰር እና ቋሚነቱ የተረጋገጠ እንዲሆን ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፡፡

ኦሪጋሚ መዋቅር

ወረቀትን ነገሮችን በሚወክል ቅርፅ የማጣጠፍ ጥበብ ሲሆን ከአገረ ጃፓን ወደ መላው አለም የተስፋፋ ጥበብ ነው፡፡ኦሪጋሚ አንድ ወይም ከዛ በላይ የወረቀት ቁርጥራጭን ያለምንም ማጣበቂያ ቆራርጦ ወይም አጣጥፎ በማዘጋጀት ብቻ ባለሶስት ገፅ ቅርፅን የሚያስገኝ መዋቅር ነው፡፡ ባለ ሁለት ገፅ ዕቃን ወደ ባለ ሶስት ገፅ ዕቃ ለመለወጥ የሚሆኑ ብዙ መንገዶችን ያሳያል፡፡ስለዚህም ንድፍ አውጪዎች አንዳንድ ጊዜ ተጣጣፊ ወይም በቀላሉ የሚገጣጠሙ መዋቅሮችን በሚያዘጋጁበት ጊዜ በኦርጋሚ መዋቅር ሊሳቡ ይችላሉ፡፡ ንድፍ አውጪዎችና አምራቾች እቃዎችን እንደ ወረቀት በማጣጠፍ እንዲሰሩም ያግዛል፡፡

በየወገኑ መነጣጠል የሚችል መዋቅር

ተጣጣፊነት ቀለል ያሉ መነጣጣል የሚችሉ አካላትን በመጠቀም በቀላሉ መከናወን ይችላል፡፡ በቀላሉ መነጣጠል የሚችሉ አካላትን በመጠቀም የቤት-ዕቃው ለተለያዩ ሁኔታዎች በሚገጥም መልኩ መጠኑን ማስተካከል ይቻላል፡፡

መሞላት የሚችሉ መዋቅሮች

አብዛኛውን ጊዜ ተጠቃሚዎች መሞላት የሚችል መዋቅር ያለውን የቤት-ዕቃ ግዢ በሚፈፅሙበት ጊዜ መጀመሪያ የሚገዙት መሰረታዊ መሸፈኛውን ይሆናል፡፡ ከዚያም በፍላጎታቸው መሰረት በአንድ የተወሰነ ቁስ ይሞሉታል፡፡ ይበልጥ ታዋቂዎቹ መሙያ ቁሶች አየር፣ውሃ እና ፎም ናቸው፡፡

የጋሪ መዋቅሮች

የጋሪ መዋቅሮች ተሸከርካሪን ከእቃው በታች ያኖራሉ፡፡ ይህም ማንቀሳቀስን ቀላል ለማድረግ ነው፡፡ በአብዛኛው ሁለት ወይም አራት ተሸከርካሪዎች ይጨመራሉ፡፡ አራት ተሸከርካሪ ያላቸው የቤት-ዕቃዎች ሁልጊዜም በአንድ ክፍል ውስጥ ለማጓጓዝ ይሆናሉ፤ ሁለት ተሸከርካሪ ያላቸው ግን ተረጋግተው ለመቆም እንዲያግዟቸው ሁለት መቆሚያ እግሮች ይደረግላቸዋል፡፡ እነዚህ እቃዎች መንቀሳቀስ በሚያስፈልጋቸው ጊዜ ሚዛናቸውን ወደ ጎማው በማጋደል መግፋት ይቻላል፡፡

መከመር የሚችሉ መዋቅሮች

በንድፍ፤ አንዳንድ ቅርፅ ያላቸው እቃዎች አንዱ በአንዱ ላይ መከመር(መደራረብ) ይችላሉ፡፡ የነዚህ መዋቅሮች ጥቅም፤ በሚከማቹበት ጊዜ ስፋት ያለውን ቦታ ይቆጥባሉ፡፡ እንደ መዋቅራቸው ልዩነት፤ የሚከማቹበትም መንገድ ይለያያል፡፡ አንዳንዶቹ እኩል ቅርፅ ኖሯቸው እርስ በእርስ ይደራረባሉ፡፡ ሌሎቹ እንደ ራሺያ የልጆች መጫወቻ ጎጆ፤የተለያየ ቅርፅ ኖሯቸው አንዱ በአንዱ ውስጥ ይገባል፡፡

ስስ ሽፋን ያለው መዋቅር

አንዳንድ ጊዜ የቤት-ዕቃዎች ስስ ከሆነ ሽፋን ጋር ይቀርባሉ፡፡ የታጣፊ ወይም ፈራሽ ዕቃዎች ሽፋን ሁልጊዜም እንደ ጨርቅ ወይም መረብ ካሉ ስስ ቁሶች ይዘጋጃሉ፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ስስ ሽፋኖች ታጣፊነታቸውን ወይም ተለጣጭነታቸው ላይ ተፅዕኖ ማሳደር የማይችሉ በመሆናቸው ነው፡፡ በተጨማሪም እነዚህ ቁሶች ቀላል ክብደት ያላቸው በመሆኑ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ እነዚህ ሽፋኖች ሙሉለሙሉ ሊባል በሚችል ሁኔታ የቤት-ዕቃውን አብዛኛውን ክፍል ይሸፍናሉ፡፡

የመደርደሪያ ሳጥን

ብዙ የሳጥን ቅርፅ ያላቸው ማከማቻዎችን በዕለትተዕለት ኑሯችን ውስጥ እንጠቀማለን፡፡ የማከማቻዎችን ንድፍ ማዘጋጀት ሳጥኖችን ማዘጋጀት እና ከክፍሉ ጋር በሚጣጣም ሁኔታ ማደራጀት ነው፡፡ በብዙ አጋጣሚዎች ንድፍ አውጪዎች መሰረታዊ ሳጥን ያዘጋጁና ሌላውን በተመሳሳይ ቅጂ ይጨርሳሉ፡፡ ተጠቃሚዎችም የፈለጉትን ያህል መጠን ገዝተው በራሳቸው መንገድ ማደራጀት ይችላሉ፡፡ ሳጥኑ አብዛኛውን ጊዜ በኩብ ወይም ኢ-መደበኛ በሆነ ቅርፅ ይዘጋጃል፡፡ ልዩ በሆነ የመገጣጠም ስልት በእያንዳንዱ የመገጣጠሚያ ቦታ ላይ የታያል፡፡

ዘላን እሳቤዎችን በስራ ላይ በማዋል ሁለት ችግሮች ይፈታሉ፡፡ የመጀመረያው ችግር ክብደት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ጠባብ የመኖሪያ ስፍራ ነው፡፡

Pin It on Pinterest

Share This