ሽፋን ያላቸውን የቤት-ዕቃዎች ማዘጋጀት በስፋት ሲታይ ትርጓሜው ቤትን ምቾት በሚሰጡ ጨርቆች፣መከዳዎችን ምቾት በሚሰጥ ስፖንጅ ወይም ጨርቅ፣በመጋረጃ፣በአልጋልብስ መሸፈን እና ሰረገላ መሰል መገልገያዎችንና መኪኖችን ሽፋን አበጅቶ መሸፈንን ያጠቃልላል፡፡ በቀደመው ጊዜ ግብፃውያን ሽፋን እና ምቾት ሰጪ ዕቃ የተጨመረላቸው መከዳዎችን፣ ወንበሮችንና እግር ማስደገፊያዎችን ይጠቀሙ እንደነበር ጥናቶች አረጋግጠዋል፡፡

ጊዜው የዘይቤ፣የምቾት እና የቅንጦት ነው፡፡ እነዚህ ሽፋን እና ምቾት ሰጪ ዕቃ የተጨመረላቸው የቤት-ዕቃዎች ከዚህ የጊዜው ሁኔታ በመነሳት ተፈላጊ ሆነዋል፡፡ እነዚህ የቤት-እቃዎች ትራስና የተለያየ የስፖንጅ አይነት ያላቸው ሲሆኑ በጨርቅ ወይም በቆዳ የተሸፈኑም ሆነው ከላያቸው ላይ ስፖንጅ ከመጣበቁ በፊት የሚገጠምባቸው የብረት ወይም የእንጨት መቃን አላቸው፡፡

የተለያዩ አይነት ሽፋን እና ምቾት ሰጪ ዕቃ የተጨመረላቸው የቤት-ዕቃዎች አሉ፡፡ እነዚህም ነጠላ መከዳዎች፣ባለ ጥምር መቀመጫ መከዳዎች፣ባለ ሶስት መቀመጫ መከዳዎች፣የእንግዳ መቀበያ ቤት መንበሮች፣የመመገቢያ-ቤት ወንበሮች እና ሌሎችም ናቸው፡፡ የቤት-ዕቃዎቹ ባላቸው ጥሩ አጨራረስና የቀለሞች ድብልቅ፣ንድፍና የሞዴሎች ብዛት ብዙ ተጠቃሚዎች ሽፋን እና ምቾት ሰጪ ዕቃ የተጨመረላቸው የቤት-ዕቃዎችን ይመርጧቸዋል፡፡

እነዚህ አነስተኛ እድሳት የሚበቃቸው የቤት-ዕቃዎች ለረጅም ጊዜ መቆየት የሚችሉና ጥራት ያላቸው የቤት-ዕቃዎች ናቸው፡፡ ይህ ማለት በየሳምንቱ በሚገባ የአየር ፅዳት በመስጠት የእንግዳ መቀበያንና የቴሌቪዥን ቤትን ንፁህ ማድረግ ይቻላል ማለት ነው፡፡

ዘላቂነት ያላቸው የቤት-ዕቃዎች ሲሆኑ እጅግ ከፍ ያለ ወጪን በማይጠይቅ የገንዘብ መጠን መገዛት የሚችሉም ናቸው፡፡የቤት-እቃዎቹን መስራት ችሎታ የሚጠይቅ በመሆኑ በቆዳ፣በጨርቅ፣በእንጨት መቃኖች ስራ የተካኑ ባለሙያዎችን በተለይም አናጢዎች ስራ እንዲሰሩ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ ብዙ የእነዚህ አይነት የቤት-ዕቃዎች በመኖራቸው ተጠቃሚው እንደየአጠቃቀም ልማዱ አማርጦ መጠቀም እንዲችል እድል ሰጥቶታል፡፡ ለምሳሌ በስራ ቦታ ወይም በመኖሪያ ቤት ውስጥ ቋሚ እንግዳ የሚኖር ከሆነና የቤት-ዕቃው ጥቅም ላይ የሚውል ከሆነ ረጅም እድሜ ያለውን ከብረት ወይም ከእንጨት መቃን የተሰራ የቤት-ዕቃ መጠቀም የተሻለ ይሆናል፡፡

በተመሳሳይ ጨርቁን በመምረጥ ውስጥ ጥጥ፣ሱፍ፣ፖሊስተር ጨርቅ ወይም የናይሎን ጨርቅን የቤቱ የውስጥ ሁኔታ በሚመጥነው ያህል መምረጥ ይቻላል፡፡ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተጠቃሚ ባለበት ቆሻሻ የሚችሉ ጨርቆችን መጠቀም ተመራጭነት አለው፡፡ ለቤተሰብ መኖሪያ ቤትም ቆዳና የቀላል ጥጥ ጨርቅ ረጅም ጊዜ መቆየት የሚችሉና በቂ ምቾትም ያላቸው በመሆናቸው ይመከራሉ፡፡

ሽፋን እና ምቾት ሰጪነት የተጨመረለት የቤት-ዕቃ ምቾት ከመስጠቱም በተጨማሪ የሰዎችን የኑሮ ሁኔታ ያንፀባርቃል፡፡ ባህላዊው አሰራር የተጠቀለለ ሽቦ፣የእንስሳትን ፀጉር፣ሰንበሌጥና የተለያዩ እቃ ማሸጊያዎችን ይጠቀማል፡፡ አዳዲስ ዕቃዎች በጥቅም ላይ ቢውሉም የቀድሞው የአተገባበር ዘዴዎች እንዲቆዩ ተደርገዋል፡፡ ርካሽ የሚባሉት ምቾት ሰጪ የቤት-ዕቃዎች ሙሉበሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ ዘመናዊነትን የተላበሱ ሲሆኑ አንፀባራቂና ተጣጣፊ ፐላስቲኮችንና ይጠቀማሉ፡፡

ለማዘጋጀት የምንጠቀማቸው መሳሪያዎችና ቁሳቁስ

መሳሪያዎች፦ የሚያስፈልጉት ቁሳቁሶች አነስተኛ መዶሻ፣መቀሶች፣ቀጥ ያሉና የታጠፉ መርፌዎችና ሚዛን ማስተካከያ ናቸው፡፡

ሚዛን ማስተካከያው መደላደልን ለማረጋገጥ ሲባል የሚዘጋጅ ሲሆን የሚጠቀጠቀውን ምቾት ሰጪ ነገር አሰተካክሎ ለመሰደር የሚጠቅም ከስስ የጥጥ ክር የሚሰራ ነው፡፡ በአንዱ ጫፍ  ቀለበት የመሰለ ከባድ ጥቅል ሲኖረው በሌላኛው ጫፍ ደግሞ የተወጠረ ይሆናል፡፡ መቀሶች ስምንት ኢንች ወይም ከዛ በላይ ርዝማኔ እንዲኖራቸው ያስፈልጋል፡፡

እያንዳንዳቸው አስራሁለት ኢንች ርዝመት ያላቸው ባለሁለት ሹል ጫፍና ስድስት ኢንች ርዝመት ያለው ጎባጣ ባለአንድ ሹል ጫፍ ሁለት መርፌዎች ያስፈልጋሉ፡፡ ከነዚህም ሌሎች የሚኖሩ ከሆነ ስራውን ያቃልላሉ፡፡ ስድስት ኢንች ርዝመት ኖሮት ቀጥ ያለው ባለሁለት ሹል ጫፍ መርፌ  ከማያያዣው ጋር ለማገናኘት፤ባለ ሶስት ጎን ሹል መርፌዎች ደግሞ ቆዳን ለመስፋት ያገለግላሉ፡፡

ቁሳቁስ፦ማጣበቂያ የቁሳቁስን ነገረ ጉዳይ በሚታይበት ጊዜ የመጀመሪያው ከግምት ውስጥ የሚገባ ነው፡፡ እጅግ ጥሩ የሚባሉት ኤል ኤም ሲ እና ቢ ኤፍ ኤም ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ከቀጣዩ  በተሻለ የተቀራረበ መሰካካትና ጥራት አለው፡፡ የላስቲክነት ባህርዩን ከማጣቱ በፊትም ከፍተኛ ውጥረትን የመቋቋም አቅም አለው፡፡

ቃጫ

ቃጫ በርካታ ቁሶችን ለማያያዣነት ተመራጭ ነው፡፡ እንደአብዛኞቹ ጨርቆች አይቦጫጨቅም ወይም አይቀደድም፡፡ ቃጫ በሶስት ክብደቶች ይገኛል፡፡ እነዚህም ቀላል(ስምንት ኦዝ)፣መካከለኛ(አስር ኦዝ) እና ከባድ(አስራሁለት ኦዝ) ናቸው፡፡ እነዚህን የቤት-ዕቃዎች ለማዘጋጀት ባለመካከለኛ ክብደቶቹ ተመራጭ ናቸው፡፡የቤት-ዕቃዎቹን ውስጠኛ ክፍል ለመጠቅጠቅ የተለያዩ ቁሳቁሶችን መጠቀም ይቻላል፡፡ ተመራጩ ግን የተጠቀለለ የፈረስ ፀጉር ነው፡፡ በዋጋ ግን ውድ ሊባል የሚችል ነው፡፡በወንበር ላይ የሚታዩ የጨርቅ ላይ ጥልፍ ንድፎች ጥሩ ንድፍ የሚሰጠውን ስሜት  ሊሰጡ ይገባል፡፡ ለተመራጭነታቸውም እንደ ዋነኛ መስፈርት የሚታይ መሆን አለበት፡፡ ይህም ቀለም፣ቅርፅ፣አቀማመጥና ከነባሩ አካባቢ ጋር ሊለማመድ የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡

ስጋጃ

ስጋጃ ቀለም ባላቸው ክሮች የታተሙ ጨርቆች የሚል ፍቺ ሊሰጠው ይችላል፡፡ የተሳካ ውጤት የሚሰጡት ስጋጃዎች በቋሚ የሽመና ዕቃ ላይ የሚዘጋጁ ናቸው፡፡በቀለሞች የተዋበ ረቂቅ ጉንጉን፣ያማረ የጥጥ ጨርቅ፣በአግድሞሽ መስመሮች የተሸመነ ኩታ ሌሎች የቤት-ዕቃውን ለማዘጋጀት የሚያገለግሉ የጨርቅ አይነቶች ናቸው፡፡ በአግድሞሽ የተሸመነ ኩታ በቃጫ የሚሰሩ እንጨቶችን የሚተካ ነው፡፡

አይነቶቻቸው

ባህላዊ

ባህላዊ የቤት-ዕቃዎች አሸፋፈን የስፌት ማሽኖች፣በሰዎች እጅግ መሻሻል የተደረገባቸው ጨርቆችና የላስቲክ ፍራሾች ከመምጣታቸው በፊት ለክፍለ ዘመናት ወንበሮችንና መከዳዎችን ለማሸግና ለመሸፈን ጥቅም ላይ ይውሉ የነበሩ ናቸው፡፡ ድፍን እንጨት ወይም የተወሳሰበ ስርአትን በመጠቀም፣ማሰሪያዎች፣የእንስሳት ፀጉር፣ሙጃና ከዘንባባ ሽልቃቂ የሚገኝ ቃጫ፣ሱፍና ሌሎችም እቃዎች ጥምረትን በማምጣት በእጅ የሚዘጋጁ ናቸው፡፡

ዘመናዊ

ዘመናዊ የቤት-ዕቃ አብዛኛውን ጊዜ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ከሴሉላር ፖሊዩሬቴን የሚዘጋጅ ነው፡፡ ይህም ጥሩ መዋቅርን፣ከሸክም ተፅዕኖ ማገገምንና ከሁሉም በላይ ደግሞ ቀላል ክብደትን ይሰጣል፡፡ ውበት ሰጪ በሆነ ጨርቅ ይሸፈናል፡፡ ምክንያታዊ በሆነ ጊዜ ውስጥ ሰው ሰራሽ ፖሊመርም በጊዜ ብዛት ያረጅና ብቃቱን ያጣል፡፡ ከባህላዊ አሞላሎች አንፃር ትርጉም ባለው መልኩ ቀላልነት አለው፡፡ በዚህ አግባብ ፍራሽ በአንድ ኪዩቢክ ሜትር ላይ ባለው ክብደት ደረጃ ይሰጠዋል፡፡ አምሳ ኪሎግራም በአንድ ኪዩቢክ ሜትር ወይም አምስት ፐርሰንት ክብደት የተለመደ ነው፡፡ የቤት-ዕቃ ከመዝናናትም ጋር ያለውን የቀስበቀስ እድገት ማካተት አግባብነት ያለው ነው፡፡

አውቶሞቢል

የአውቶሞቢል መቀመጫዎችን መሸፈኛ ለማዘጋጀት ከፍተኛ ጥበብን ሲጠይቁ በተጨማሪም ከምንጣፍ ጋር ለማገልገል ይችላሉ፡፡

ለንግድ

እነዚህ ለንግድ ስራ የቀረቡ ምቾት ያላቸው የቤት-ዕቃ አይነቶች ናቸው፡፡ እንደ ምሳሌ በምግብ ቤቶች ውስጥ ያለው ለሁለት ሰዎች የሚሆን አንድ መደገፊያ ያለው መቀመጫ፣የመመገቢያ ክፍል ወንበሮች፣የመጠጥ ቤት በርጩማዎች፣የጥርስና ሌሎችም ህክምና መስጫ ጠረጴዛዎች ወዘተ…መጥቀስ ይቻላል፡፡ ሌላው የዚህ አይነት የቤት-ዕቃ ተጠቃሚዎች በእንግዳ መቀበያ፣በህንፃዎችና በመስሪያ ቤቶች ውስጥ ያለው የመጠበቂያ ስፍራ መቀመጫዎች ናቸው፡፡በአንዳንድ የችርቻሮ ንግድ ህንፃዎች ውስጥ ምቾት ያላቸው ግድግዳዎች ይገኛሉ፡፡

የባህር(የመርከበኞች)

እነዚህ ከሌሎቹ በተለየ እርጥበትን፣የፀሀይ ብርሀንን እና ከባድ የሆነ አጠቃቀምን ከግምት ውስጥ ያስገባሉ፡፡ በባህር ሀይል ደረጃ ለሚዘጋጁ ተጣጣፊ ፕላስቲኮች የተለያዩ መነሻ ምንጮች እንደ ስፓርድሊንግና ሞርበርን ያሉ ሲሆን በመቶዎች በሚቆጠሩ ቀለሞችና ዘይቤዎች ይገኛሉ፡፡እንዳንዱ በባህር ሀይል ደረጃ በቀዝቃዛ ንቃቃት፣መፈግፈግና መፈተግን በመቋቋም እና መሻገትን በመቋቋም አቅማቸው መጠን ይመዘናሉ፡፡ በባህር ሀይል ስራዎች ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉት አዳዲሶቹ የተጣጣፊ ፕላስቲኮች ማያያዣዎች ቴናራ ክርና ሞኔል ሽቦ ናቸው፡፡ በዚህ ውስጥ እንጨት ለአገልግሎት የሚገባ ከሆነ ከባህር ላይ አገልግሎት ጋር የሚሄድ ጥራት እንዳለው ከተረጋገጠ በኃላ መሆን አለበት፡፡በከፍተኛ ደረጃ የላስቲክነት ወሰኑን የማያልፍና በመጋጠሚያዎቹ መሀል ውሀ እንዳይገባ ለማስቀረት በሚጠቅም ቀጭን የላስቲክ ሰፈፍ የተሸፈነ ከፍተኛ እፍጋት ያለው የፕላስቲክ ፍራሽን መጠቀም የተለመደና የሚመከር ነው፡፡

Pin It on Pinterest

Share This