የጥሬ-ዕቃዎች፣በከፊል ተሰርተው ያለቁ እቃዎች፣ማሽነሪዎችና ጉልበትን በመጠቀም ቁሳዊ ውጤቶችንና አገልግሎቶችን በለውጥ ውስጥ እንዲገኙ ማድረግ ምረታ ይባላል፡፡ ፍብረካ ለሸቀጣሸቀጥ ንግድ የሚሆኑና በአሁኑ ተወዳዳሪነት በበዛበት በዚህ ጊዜ ለኢኮኖሚያዊ ማዕረግ ዕድገት ወሳኝ የሆኑ ምርቶችን ማምረት ነው፡፡ በመሰረታዊነትም ከቴክኖሎጂያዊ ዕድገትም ጋር እየተለወጠ ይገኛል፡፡ በተለመደው አመራረት በጣቢያዎች መካከል ዕቃዎች ይንቀሳቀሳሉ በተጨማሪም በመቆረጥ፣በመበሳት፣በመገጣጠም ምክንያት በራሳቸው ዘውግ ላይ ይሽከረከራሉ፡፡ ይህም ብክነትንና ክፍት ቦታን ያስከትላል፡፡ በድምረታዊ ፍብረካ ግን የመስሪያ ጣቢያዎች ቁጥር ስለሚቀንስ ከሞላጎደል ብክነት እና ክፍተት የለውም ለማለት ያስችላል፡፡የተለመደውን አይነት የቤት-ዕቃ ለማምረት ባያስችልም፤በአሁኑ ጊዜ ለቤት-ዕቃዎች አመራረት ድምረታዊ ፍብረካን መጠቀም ተስፋፍቷል፤እየተስፋፋም ይገኛል፡፡ ምክንያቱም የገፅ አጨራረስ እና ጥራት፣ብዛት ያለው ምርትን የማምረት አቅም፣ከብረት የተሰሩ እቃዎችን መግጠም፣ ሜካኒካላዊ ፀባይ ወዘት…ናቸው፡፡

በቤት-ዕቃዎች ምርት ውስጥ ድምረታዊ ፍብረካን በመጠቀም የተሰሩ ምርጥ ተግባራዊ ምሳሌዎች

በፍጥነት ከተሰሩ ትላልቅ የቤት-ዕቃዎች ውስጥ ትራቤኩላ አንዱ ሲሆን ሁለት ሜትር ያህል ርዝመት ያለው አግዳሚ ወንበር ነው፡፡ የተመረተውም መስታወት በተሞላ ፖሊያሚድ እቃ ሲሆን እየመረጠ ሳይቀልጥ ነገርግን በሙቀት ብቻ በመጋገር የተሰራ ነው፡፡ የተፈጩ ፖሊያሚድ ቅንጣቶች በጨረር ሀይል በቅርፅ ማውጫው ውስጥ ይጋገራሉ፡፡ አንድ ቀን ከግማሽ ከሚወስደው ከዚህ የመጋገር ሂደት በኃላ ቅርፅ ማውጫው ከአስራ ሁለት እስከ አስራ አምስት ሰዓት መቀዝቀዝ አለበት፡፡

ይህ አንድ ነጠላ መከዳ ስቴሪዮሊቶግራፊ ዘዴን በመጠቀም የተሰራና ለብርሀን አፀፋ ምላሽ የሚሰጡ ማጣበቂያዎች በአልትራቫዮሌት የጨረር ምንጭ የተጠመዘዙበትም ነው፡፡ እያንዳንዳቸው 0.0099 ሳንቲሜትር ውፍረት ያላቸው ስድስት ሺህ ድርብርቦች ያሉት መከዳ ነው፡፡ መዳብና ለቅብ አገልግሎት በሚውል የክሮሚየም ውህድ የተለበጠ አጨራረስ ያለውና ሁለት ነጥብ አምስት ኪሎ የመስሪያ ቁሳቁስን ብቻ በመጠቀም የተፈበረከ ነው፡፡

የቤት-ዕቃ ኢንዱስትሪው ባለ ሶስት-ገ ህትመትን እየተጠቀመ ያለባቸው እጅግ ሳቢ መንገዶች

ባለ ሶስት ገፅ ህትመት በአንፃራዊነት እንደ ውስን ብልሀት(ዘዴ) የሚታይ የነበረ ሲሆን ምሳሌና ክፍለ አካሎችን ማዘጋጃ ለማዘጋጀት ብቻ ያገለግል ነበር፡፡ ነገርግን በመጠን፣በፍጥነት እና በጥራት ባሳየው በሰፊ መሻሻሎቹ እንደ የቤት-ዕቃ ኢንዱስትሪ ማምረት ያሉ ዘርፎች የባለ ሶስት ገፅ ህትመትን አዲስና አስደሳች ጥቅም እያገኙ ናቸው፡፡አጠቃላይ ምክንያቶቹ አነስተኛ ዋጋ፣በምርት ሂደቱ ውስጥ ጥቂት ደረጃዎችን ማለፍ ብቻ በቂ መሆኑ እና ለውጦችን በቀላሉ በተግባር ላይ ለማዋል ማስቻሉ ሲሆን ባለሶስት-ገፅ ህትመትን በመጠቀም የተሰሩ የቤት-ዕቃዎችን ለመጠቀም ሁለት አጥጋቢ ምክንያቶች አሉ፡፡ እነዚህም ንድፍ እና ቀላል ክብደት ናቸው፡፡

ንድፍ

የመጀመሪያውና ግንባር ቀደሙ ባለሶስት ገፅ ህትመትን በመጠቀም የተሰሩ የቤት-ዕቃዎችን  መርጦ የመጠቀም ምክንያት ልዩነት ያላቸው የባለሶስት ገፅ ህትመት አባሎችን በአንድ አዋህዶ ለመጠቀም ማስቻሉ ነው፡፡ የእቃው ንድፍም ዋነኛ ሊታይ የሚገባው የጥራት መስፈርት ነው፡፡ የተለመደው አመራረት ውስብስብ ጂኦሜትሪዎችን፣የዕቃውን ንድፍ አይነቶችን፣ልዩ ቅርፆችንና የማበጀት አማራጮችን ለማዋሃድ አያስችልም፤ወይም ከሚገባው በላይ ወጪን ይጨምራል፡፡

ቀላል ክብደት

ባለሶስት ገፅ ህትመትን በመጠቀም የተሰሩ የቤት-ዕቃዎችን የመጠቀም ሌላኛው ምክንያት ክብደታቸው በአንፃዊነት ቀላል መሆኑ ነው፡፡ ክብደትን ማቅለል ባለሶስት ገፅ የቤት-ዕቃዎችን በማምረት ውስጥ እጣ-ፈንታቸውን የመቀየር ያህል ይቆጠራል፡፡ ይህም ባለሶስት ገፅ የቤት-ዕቃዎችን የሚያዘጋጅ የኮምፒዩተር ፕሮግራም እና ማተሚያ በመኖሩ ለማድረግ ቀላል የሆነ ሲሆን ጥቂት ክብደቶችን በመቀነስ የቤት-ዕቃውን ክብደት እጅግ ቀላል የማድረግ እድል መስጠቱ እንደ ምክንያት መታየት የሚችል ነው፡፡ ይህ የክብደት መቅለል የቤት-ዕቃውን በማጓጓዝ ውስጥ ለአምራቹም ሆነ ለተጠቃሚው የተሻለ ጥቅም ያስገኛል፡፡

ባለሶስት ገጥ ህትመትን በመጠቀም የተሰሩ የእንግዳ መቀበያ ክፍል የቤት-ዕቃዎች ምሳሌዎች

በስካንዲኒቪያ ዘይቤ የተሰራ ጠረጴዛ

በአውቶካድ እና የሶስት ገጥ ሶፍትዌርን በመጠቀም ጆን ክርስቲ ጊዜ የማይገድበው፣ቀጥታ መስመሮች ያሉት፣ለስላሳና አንፀባራቂ ንድፍና በፈካ ቀለሙ የሚታወቀውን የቤት-ዕቃ ሰርቷል፡፡ የዚህ ወፍራም ጠረጴዛ የላይኛው ክፍል የለውዝ አይነት እንጨትን በመጠቀም የተሰራ ሲሆን መጋጠሚያዎቹ ደግሞ በፖሊያሚድ ቁስ የተሰሩ ናቸው፡፡ ይህም ባለሶስት ገፅ ህትመትን ለመጠቀም የሚያስችሉት ቴክኖሎጂዎችና ማምረቻዎች በእንጨት የተሰሩ የቤት-ዕቃዎችን ጭምር ለመስራት እንደሚያስችሉ ያሳያል፡፡ በባለሶስት ገፅ ህትመት የተሰራው ወንበርና ጠረጴዛ በትንሽ ወጪ እንደ ተጠቃሚው የእንጨት አይነትና የቀለም ምርጫ መዘጋጀት የሚችል ነው፡፡

የአይኪያ ባለመደገፊያ ወንበር

በአይኪያ የሚፈበረኩ የቤት-ዕቃዎች ቀለል በማለታቸውና በብዛት ስዊድናዊ ንድፍን በመከተላቸው ይታወቃሉ፡፡ የመጀመሪያው ባለሶስት ገፅ ህትመትን በመጠቀም የተሰራው የአይኪያ ባለመደገፊያ ወንበር በሁለት ቀለሞች የተጌጠና በተለያዩ መጠኖች መዘጋጀት የሚችል ነው፡፡ ጥልፍልፍነት ያለው ወንበር በመሆኑ ይህ በከፊል በውስጡ የሚያሳይ ንደፍ በሚታተምበት ጊዜ የሚኖሩ እነቃሪዎችን ለማስወገድም ይጠቅማል፡፡ አይኪያ ኩባንያ በመደበኛው የአመራረት ዘዴ ከሚመረቱት ወንበሮች ይልቅ በባለሶስት ገፅና በድምረታዊ ፍብረካ የሚሰሩ የቤት ዕቃዎች ዘላቂነት እናዳላቸው መስክሯል፡፡ቬንቹሪ የተባለ በፈረንሳይ የሚገኝ የቤት-ዕቃዎች አምራች ኩባንያ የፐርሺያ ውበት ያላቸው ወንበሮችም በባለሶስት ገፅ ህትመት ሊሰሩ እንደሚችሉ አረጋግጧል፡፡ የኤፊል ማማን የሚመስሉ፤ስያሜያቸውም ኤፊል ወንበር የተባሉ ወንበሮችን አምርቷል፡፡ በተለያዩ ቁሳቁሶች የተሰሩ ቢሆኑም ያላቸው ተመሳሳይ መልክና መዳብ መሰል ቀለማቸው እና ተመሳሳይነት ያለው ውስብስብ ንድፋቸው እውነተኛነትን ያሳያል፡፡ አነስተኛ መጠን ስላላቸው በአነስተኛ ገንዘብ ለማግኘት የሚቻሉ ናቸው፡፡

በቤት-ዕቃዎች ዓለም ውስጥ ከባለሶስት ገፅ ህትመት ምን መጠበቅ ይቻላል?

ትላልቅ ኩባንያዎች ባለሶስት ገፅ ህትመትን በሞዴሎቻቸው ውስጥ ማስገባት ጀምረዋል፡፡ ይህም እንደ ውጤት በከፍተኛ ደረጃ ንድፍ የወጣላቸው ተስማሚነት ካለው ተጠቃሚ ጋር መነጋገር የሚችሉ ወንበሮችና ጠረጴዛዎችን አስገኝቷል፡፡ ባለሶስት ገፅ ህትመት ለአንዳንድ የቤት-ዕቃ አይነቶች አጠቃላይ ጅምላ ህትመት ውድ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገርግን ለማራኪና አስደሳች ንድፍ ድምረታዊ ንድፍ ተመራጩ መንገድ ነው፡፡ የቤት-ዕቃዎች በአመታት ውስጥ ከሚለዋወጡት ከጥበብ እና ባህል ጋር እጅለእጅ ተያይዘው የሚሄዱ ናቸው፡፡ ይህ የቤት-ዕቃዎች ይበልጥ ውስብስብ ንድፍ እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡ በዚህ ምክንያት ባለሶስት ገፅ ህትመት መደበኛ የአመራረት ዘይቤ እንደሚሆን እና በውስጡ ያለው ውጤት ብዙም ውድ ያልሆነ እና የቤት-ዕቃን ለማምረት የሚስማማ መንገድ እንደሚሰጥ ተስፋ ይሰጣል፡፡

በባለ-ሰስት ገጥ ህትመት የተዘጋጀ የቤት-ዕቃ የወደፊት ጊዜ ከጨረር የአቆራረጥ ዘዴ ጋር ተያይዞ የሚሄድ ነው፡፡ በማያቋርጠው የቴክኖሎጂ መሻሻል ውስጥ የባለ-ሶስት ገጥ ህትመትም መሻሻልን ማሳየቱ የማይቀር ነው፡፡ በመጪዎቹ ጊዜዎች ባለሶስት ገጥ ህትመት አሁን ያለውን የማምረት ሂደት መተካቱ የማይቀር ነው፡፡ የጨረር አቆራረጥ ዘዴዎችን ከባለሶስት ገጥ ህትመት ጋር በአንድላይ በመጠቀም የቤት-ዕቃ ሞዴሎች በፍጥነትና በቀላሉ በትክክኛው ወርድና ስፋት መለካትና መቆረጥ ይችላሉ፡፡ አንዴ ከተቆረጠም በኃላ በጨረር በመቅረፅ መበጀት ይችላሉ፡፡

Pin It on Pinterest

Share This