ለክፍለዘመናት የቤት-ዕቃዎች ለተመሳሳይ ጥቅም ተሰርተዋል፡፡ መፃፈያ ጠረጴዛዎች፣ ጠረጴዛዎች፣የስራ አግዳሚ ወንበሮች ለስራና ለመመገበቢያነት የሚሆን ስፍራን ሰጥተዋል፡፡ ሰንዱቆችን፣ቁምሳጥኖችና ሳጥኖች ለማከማቻነት የተሰሩ ናቸው፡፡ መከዳዎች፣ወንበሮችና አልጋዎች ለማረፊያነት እንዲሆኑ ተሰርተዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ከፍ ካለ የህፃናት ወንበር እስከ በብረት የተሰራ የስራቦታ መፃፊያ ጠረጴዛ፤ለእያንዳንዱ ሃሳብ ለወለደው ሁኔታ የሚሆን የቤት-ዕቃ ማግኘት ይቻላል፡፡ ስስና ምቾት በሚሰጥ ነገር የተጠቀጠቁ ትራስ ከሚመስሉ መከዳዎች እስከ በብረትና በመስታወት የተሰሩ አንፀባራቂ ጠረጴዛዎች ይደርሳሉ፡፡ የቤት-ዕቃ ሰዎች ቀላል እና ምቾት በሚሰጥ አለም ውስጥ እንዲኖሩ ታስቦ የተሰራ ነገር ነው፡፡ የቤት-ዕቃ ኢንዱስትሪው በተለያዩ ሰፊ ቡድኖች ከፍሎ ያያቸዋል፡፡ የቤት-ዕቃዎችን የማቧደን አንደኛው መስፈርት ጥቅም ላይ እንደሚውሉበት ቦታ እና ሁኔታ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ባሉ የቤት-ዕቃ ውጤቶች ውስጥ ቦታ ቆጣቢ የሆኑ የቤትዕቃዎች ታጥፈው ጥቅም ላይ መዋል የሚችሉት በስፋት ይገኛሉ፡፡በቤት ውስጥ የምንጠቀምባቸው የቤት-ዕቃዎች በራሳቸው ሌላ ትልቅ ቡድን ይፈጥራሉ፡፡ በዘይቤያቸውም የመተኛ፣የመደገፊያና የግልጋሎት ተብለው ይከፋፈላሉ፡፡ የመከዳ አልጋ ከቦታ ቆጣቢ የቤት-ዕቃዎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ይህ አስደናቂ ልምጥምጥነታቸው በትናንሽ አፓርታማ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ትልቅ እገዛ ያደርጋል፡፡ በተለይም እንግዳንም ጥሩ በሆነ አያያዝ ለማስተናገድ ይጠቅማሉ፡፡ ተጣጣፊ በመሆናቸው እና ለአያያዝም ምቹ በመሆናቸው ለማደራጀት አይከብዱም፡፡

ቦታ ቆጣቢ ጠረጴዛ

ጠረጴዛዎች ልዩ ልዩ አይነት ጠቀሜታ አላቸው፡፡ ምንም እንኳን አንዳንዴ ጠረጴዛዎች ተጨማሪ እንግዶችን ለማዝናናት የሚያንሱ ወይም ለአነስተኛ ቤተሰብ ወይም በትንሽ አፓርታማ ውስጥ እጅግ ሰፊ ቦታን የሚይዙ ቢሆንም፤አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ከመመገቢያ ክፍላቸው ጋር የሚመጣጠኑ ጠረጴዛዎችን ይመርጣሉ፡፡ ቦታ ቆጣቢ ጠረጴዛዎች በተለዋዋጭ ባህሪቸው ይህንን ችግር መፍታት ይችላሉ፡፡

ቦታ ቆጣቢ አልጋዎች

ቦታ ቆጣቢ አልጋዎች ቋሚነት ያለውና ተንቀሳቃሽ በተባሉ ሁለት መደቦች ሊከፈሉ ይችላሉ፡፡ ቋሚ ቦታ ቆጣቢ አልጋ መፅሀፍ መደርደሪያ፣መፃፊያ ጠረጴዛ ወይም ሁለቱን ያጣመረ፤ማለትም መፃፊያ ጠረጴዛው ወደ አልጋ መለወጥ የሚችል ሊሆን ይችላል፡፡ የአልጋው መጠን እንደ ተጠቃሚው ፍላጎት ልዩነት ሊኖረው ይችላል፡፡ የእነዚህ ዋነኛው ጥቅም የተለመዱት የቤት-ዕቃዎች የማይሰጡትን የቦታ ነፃነት ማስገኘታቸው ነው፡፡ አነስተኛ የእንግዳ ማረፊያዎች በልዩነት ይመርጧቸዋል፡፡ተንቀሳቃሽ ቦታ ቆጣቢ አልጋዎች በዋነኝነት ለትምህርት ቤቶች ማደሪያ ክፍሎች ወይም ብዙ ልጆች ባሉበት ቤተሰብ እንዲሆን ተደርጎ የተነደፈ ነው፡፡ የዚህ አይነቱ ቦታ ቆጣቢ አልጋ በአብዛኛው ከሁለት ነጠላ አልጋዎች እና ከመሰላል የተሰራ ነው፡፡ ሁለቱም አልጋዎች በክፈፍ ሊታቀፉ ይችላሉ፡፡ ይህም ህፃናት በውስጡ ለመጫወትና ለሌሎች ተግባራት እንዲጠቀሙባቸው ያግዛል፡፡ አልጋውን ወደ ክፈፉ በምናጥፍበት ጊዜም መሰላሉ በቀላሉ በመተጣጠፍ በአልጋው ላይኛው ክፍል ላይ መቀመጥ ይችላል፡፡ ልጆች በፈለጉት ጊዜ እንዲጠቀሙበት ሲባል አልጋው ለመከፋፈት በጣም ቀላል ነው፡፡ ይህ የአልጋ ንድፍ በትንሽ አፓርታማ ውስጥ ልጆች ለእያንዳንዳቸው የራሳቸው ክፍል ሳይኖራቸው ለሚኖር ቤተሰብ ጥሩ የሚባል ምርጫ ነው፡፡

ቦታ የመቆጠብ የአሰራር ዘዴ

የአልጋ ክፈፍንና የመፅሀፍ መደርደሪያን ማገናኘት፡ የዚህ አይነቱ ዘዴ በአልጋዎች ክፈፍ ላይ የሚገጠም ነው፡፡ ይህም ሁለቱን የቤት-ዕቃዎች ለማገናኘት ያግዛል፡፡ ይህን ዘዴ በልዩነት ተመራጭ የሚያደርገው መደርደሪያው ከፍ እና ዝቅ በሚልበትም ጊዜ እንኳን በመደርደሪው ላይ ያሉ ዕቃዎች በቦታቸው ላይ እንዳሉ መቀመጣቸው ነው፡፡ አልጋ ሆኖ በሚያገለግልበት ጊዜ መደርደሪያው እንደ እግር ሆኖ ማገልገል ይችላል፡፡  

ትግበራና የወደፊት እድገት

የቤት-ዕቃው በበቂ ሁኔታ ከአፓርታማው አቀማመጥ ጋር እንዲገጥምና ተጨማሪ ትርፍ ቦታን እንዲያስገኝ ሲባል የህንፃ ንድፍ አውጪዎች ከቦታ ቆጣቢ የቤት-ዕቃ ንድፍ አውጪዎች ጋር ተባብረው እንዲሰሩም ይመከራል፡፡ በዚህ ትብብር ውስጥ የሚገኘው አዲስ ንድፍ የቤቱን አቅም መጨመር ብቻ ሳይሆን ለመጠቀም ይከብዳሉ ተብለው የሚታሰቡን ቦታዎች ሳይቀር ሁሉንም ቦታ በአግባቡ ለመጠቀም ያስችላል፡፡ለመለዋወጥ የሚቻል ቦታ ቆጣቢ የቤት-ዕቃ የቤት-ንድፍን የማይቃወም በመሆኑም ተመራጭነት አለው፡፡ ተንቀሳቃሽ ግድግዳዎችና ተለዋዋጭ አልጋዎች፣መከዳዎችና የመመገቢያ ክፍል ጠረጴዛዎች በተጨማሪም የተደበቁ ቴሌቪዥኖችና የማብሰያ ቁሶች የቤቱን አጠቃላይ ቦታ እና የቤት-ዕቃውን ሁለት አይነት ጥቅም እንዲሰጥ ምክንያት የሆኑ ናቸው፡፡የዚህ ንደፍ ዋነኛ ጥቅሙ ሀይልን ያማከለ ፈጠራ ማስተዋወቅ ነው፡፡ ምንም እንኳን ተለዋዋጭ ቦታ ቆጣቢ የቤት-ዕቃዎች በዚህ ሀይል በሚቆጥብ ቤት ውስጥ ትልቅ ሚና ቢኖራቸውም ከቤቱ ንደፍ ጋር ተያያዥነት ሲኖራቸው ውጤታቸው ይበልጥ እጅግ ያማረና አርኪ ይሆናል፡፡ እነዚህ የቤት-ዕቃዎች ሊነደፍ የሚችለውን የመጨረሻ ትንሽ የቤት-ንድፍ እና ግንባታ ለማከናወን ማስተማመኛ ይሰጣሉ፡፡ በተለይም ተንቀሳቃሽ ግድግዳውና ቦታ ቆጣቢው አልጋና ጠረጴዛ ሁለት ክፍሎች ወደ አንድ ወጥ ክፍልነት በቀላሉ ለመቀየር የሚችሉበት ቁልፍ መንገዶች ናቸው፡፡ ይህም ዋናውን የመነሻ ወጪ እና የህንፃውን ሀይልና ቦታ ያድናል፡፡ ይህ የቤት-ዕቃዎች ንድፍ በትላልቅ ከተሞች ላሉ ጠባብ የወለል ስፋት ላላቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶችም እጅግ ተመራጭ ነው፡፡

በአጠቃላይ በአሁኑ ጊዜ ሰዎች ለተሻለ የስራ እድልና የተሻለ የኑሮ ሁኔታ ሲሉ ሰፊ እንቅስቃሴ ወዳለባቸው ትላልቅ ከተሞች ይጓዛሉ፡፡ ይህ ወደ ከተሜነት የመለወጥ ዝንባሌ ከተሞች ባዶ ቦታ እንዳይኖራቸው፤የንብረቶች ዋጋም እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ በትላልቅ ከተሞች የሚኖሩ ሰዎች ትናንሽ አፓርታማና የጋራ መኖሪያ ቤት ብቻ የመግዛት አቅም አላቸው፡፡ ይህም ለተለዋዋጭ የቤት-ዕቃዎች መበልፀግ ጥሩ እድል ይሰጣል፡፡ የተለዋዋጭ የቤት-ዕቃዎችን የወደፊት ጊዜ የተሻለ ለማድረግ ንደፍ አውጪዎቹ ይበልጥ ፈጠራ የተሞላባቸው ሀሳቦችን መፍጠር እና ከስነ ህንፃ ምሁራንና ከመሀንዲሶች ጋር በመተባባር መስራት ስኬት ላይ ለመደረስ የሚስችላቸው ሌላኛው መንገድ ይሆናል፡፡ አጠቃላይ ወጪዎችንና የቤት-ዕቃ ዋጋዎችን መቀነስ ሌላው ከግምት ውስጥ መግባት ያለበት ዋና ነገር ነው፡፡    

በባለብዙ ጥቅም የቤት-ዕቃዎች ውስጥ ስብጥርን መፍጠር

በነዚህ የቤት-ዕቃዎች ውስጥ ስብጥርን መፍጠር፤የሚመስለውን ያህል ከባድ አይደለም፡፡ እንደ ሌሎቹ ሁሉ በመጀመሪያ ሊከናወን የሚገባው የትኩረት አቅጣጫን መስጠት ነው፡፡ የትኩረት አቅጣጫ ማለት አንድ ሰው ወደ ክፍሉ እንደገባ አይኑን ሊስብ ወይም አይኑ ሊያርፍበት የሚችልበት ቦታ እንደማለት ነው፡፡ ከነዚህ የቤት-ዕቃዎች ተግባር አንፃር የቤቱ ተግባር ተለዋዋጭ ስለሆነ በእያንዳንዱ አቀማመጥ ውስጥ ሥብጥር የሚፈጥር አቀማመጥ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ለምሳሌ በመኝታ ቤት ውስጥ ዋነኛው የትኩረት ነጥብ መሆን ያለበት አልጋው በመሆኑ መካከለኛውን ክፍል ይዞ እንዲቀመጥ ያስፈልጋል፡፡

በቀጣይ መደረግ ያለበት ደግሞ ሚዛኑን መጠበቅ ነው፡፡ በመኝታቤትም ሆነ፤በአልጋው ሌላ ክፍል የትኩረት ነጥብ ተደርጎ በተመረጠው የቤት-ዕቃ ሁለቱም ጎኖች አጠገብ የቤት-ዕቃዎችን ማስቀመጥ፡፡ በሁለቱም ጎን የተቀመጠው የቤት-ዕቃ ሚዛናዊነትን የጠበቀ ሊሆን ይገባል፡፡  ብዙውን ጊዜ ሰዎች የተመጣጠኑ የአልጋ ጎን ጠረጴዛና የጎን መብራትን መጠቀም ያዘወትራሉ፡፡እነዚህ ከጎን የሚቀመጡ የቤት-ዕቃዎች በእኩል ርቀት ላይ መቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡ስብጥርን በምናይበት የመጠን ልዩነትም የተሰባጠረ ውበትን የሚያመጣ መሆኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡   

ባለብዙ ጥቅም የቤት-ዕቃዎችን የማሳመር ወርቃማ ህጎች (በጥቂቱ)

ለጭውውት የሚሆን ቦታን መፍጠር

ሰዎች አንገታቸውን ሳያጣምሙ ወይም ከክፍል ክፍል ከፍተኛ የጩኸት ድምፅ ማውጣት ሳያስፈልጋቸው መነጋገር መቻል አለባቸው፡፡ ሰዎች ድምፃቸውን ከፍ ሳያደርጉ መነጋገር ይችሉ ዘንድ መከዳዎችና ወንበሮችን በቀጥታም ባይሆን እንኳን አቀማመጣቸው ፊትለፊት መሆን ይገባዋል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እነዚህን ቦታ ቆጣቢ የቤት-ዕቃዎች የምንጠቀመው በጠባብ ቦታ ውስጥ ስለሆነ ይህን ሁኔታ ማሟላት ፈታኝነት አይኖረውም፡፡

ትክክለኛ መጠን ያላቸውን ምንጣፎች መጠቀም

ለአያያዝ የማንቸገር ከሆነ ምንጣፎች ከቤት-ዕቃዎች ስር ድረስ ቢነጠፉ ይመረጣል፡፡ በሚታዩበት ስፍራ ጠርዛቸውን ከግድግዳ ትንሽ ማራቅና ወለሉን ለእይታ ማውጣት ውበትን ለመጨመር ያግዛል፡፡

በቂ የቤት-ውስጥ ብርሀን እንዲኖር ማድረግ

የቤት-ውስጥ ብርሀን በየትኛውም ክፍል ውስጥ እጅግ መሰረታዊ የሆነ ቢሆንም አብዛኛውን ጊዜ በቸልታ ሲታለፍ ይስተዋላል፡፡ ተንጠልጣይ መብራትን፣የመሬት ላምባና የጠረጴዛ ላምባ፣ከተቻለ ደግሞ በግድግዳ ላይ የሚሰቀሉ ሻማ መያዣ መሰሉ ብርሀን ሰጪዎችን ከከፍተኛ ጥንቃቄ ጋር መጠቀም ለቤት ውበት እጅግ ተመራጭ ነው፡፡ ዋናው ፍሬ ሃሳብ ግን ከክፍሉ ስፋት ጋር ተመጣጣኝ ብርሀንን መጠቀም ነው፡፡

Pin It on Pinterest

Share This