የቤት-ዕቃዎች የየዕለት ኑሯችን አካል ናቸው፡፡ እንደ መመገቢያ ጠረጴዛ ያሉት ተፈላጊ ተግባርን የሚያከናውኑ ሲሆኑ የጥንት ቅርፃቅርፅና ጥርብን የሚያሳዩት ደግሞ ስነውበትን አጉልቶ ማሳየትን የሚከውኑ ናቸው፡፡ ለዓመታት በቤተሰብ ውስጥ የቆየ ባለመሳቢያ ቁምሳጥን የስሜታዊና የምልክትነት ዋጋ ያለው ነው፡፡ የቤት-ዕቃዎች የዚህን ያህል ጥቅም የሚሰጡን ከሆነ ልንሰጣቸው የሚገባውን ያህል እንክብካቤ ማግኘት አለባቸው፡፡ በሀላፊነት የሚረከባቸው ሰው የመረዳት ደረጃና የማድረግ አቅም መጨመር በቤት-ዕቃ ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት ውስጥ መተኪያ የሌለውና መሰረታዊው ነገር ነው፡፡

ለመከላከል የሚቻል ጉዳት

በቤት-ዕቃዎች ላይ የሚደርስ ጉዳትና ጥፋት ብዙ መንገድ ያለው ነው፡፡ በሀላፊነት የሚረከባቸው ሰው ተፅዕኖ ሊያሳድር የሚችልባቸውን ሁኔታዎችና ድርጊቶችን ለመከላከል የሚቻሉ ጉዳቶች ብለን እንጠራቸዋለን፡፡ አብዛኞቹ የበለጠ ተፅዕኖ ያላቸው በቤት-ዕቃዎች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች ተጠቃሚያቸውና በሃላፊነት የተረከባቸው ሰው ደካማ ምርጫና ተፈጥሯቸውን በተሳሳተ ሁኔታ መረዳቱ የሚያመጣቸው ናቸው፡፡ለመከላከል የሚቻል ጉዳቶች ዋነኛ ምክንያቶች

  • ደካማ የሆነ አካባቢያዊ ሁኔታን የመቆጣጠር ሁኔታ
  • ግድየለሽነት የተሞላበት አጠቃቀም
  • በቂ ባልሆነ የመረከብ ጥቅል ውስጥ ማንቀሳቀስ

ሁሉም የቤት-ዕቃ አይነቶች ከደረጃቸው ዝቅ የሚሉ ቢሆንም ሂደቱን የእንክብካቤና የጥገና መስፈርቶችን፤የእንጨቱን ወይም የተሰራበት ጥሬ-ዕቃ አይነትን በመረዳት መቀነስ ወይም ማለዘብ ይቻላል፡፡

አካባቢ

በዚህ እሳቤ ውስጥ አካባቢ ማለት ዕቃው የሚገኝበት ሁኔታ እንደማለት ነው፡፡ በሀላፊነት የወሰዳቸው ሰው ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮችና ገንዘብና ንብረት ለቤት-ዕቃዎች ተመራጭ አካባቢን ለመፍጠር አስፈላጊ ናቸው፡፡ አብዛኛውንም ጊዜ የሁለቱ ምጥጥን ድርጊት ነው፡፡ ለመበላሸት ወይም ከብልሽት ለመጠበቅ የሚሆን ምቹ የሆነ ሁኔታ እንጂ ለየትኛውም ነገር ፍፁም አካባቢ የለውም፡፡ ለቤት-ዕቃዎች ምቹ የሚባለው አካባቢ በግምት ወደ አምሳ ፐርሰንት ከሚሆን አንፃራዊ እርጥበት፣አርባ ዲግሪ ፋራናይት የሆነ የሙቀት መጠን፣የበዛ ብርሀን የሌለበት፣በተጨማሪም ከንክኪ ነፃ የሆነ አካባቢ ነው፡፡ እነዚህን ሁኔታዎች በሚያሟላ ፉካ ውስጥ ማስቀመጥ ከብልሀትም ሆነ ከፋይናንስ አንፃር ሊሳካ የሚችል ቢሆንም እንኳን ለመጠቀም ግን እጅግ ከባድ ያደርገዋል፡፡ ስለዚህ ቢያንስ የብርሀንን፣የተለዋዋጭ የሙቀትና የእርጥበት መጠን  ተፅዕኖ እና ከብዙ አገልግሎት በኃላም ቢሆን ጉዳትን የመቋቋም አቅም በመረዳት ከመጠቀምም ሆነ ከማቆየት አንፃር ያለውን ሁኔታ መረዳት ተጠቃሚው ከፍላጎቱ ጋር የተጣጣመ የቤት-ዕቃን ማግኘት እንዲችል ያግዘዋል፡፡

ብርሀን

ምናልባትም ለመረዳትም ሆነ በቀላሉ መፍትሄ ለመስጠት የሚሆነው የአካባቢያዊ ጉዳይ በብርሀን የሚደርስ ጉዳት ነው፡፡ ብርሀን ብለን የምንጠራው ከኤሌክትሪክ መግነጢሳዊ ፍንጠቃ ውስጥ ከአይናችን ጋር የሚስማማው ጠባቡን ክፍል ነው፡፡በቀላሉ ሲቀመጥ፤ብርሀን የሀይል ምንጭ ነው፡፡ ብርሀን ባረፈበት ነገር ላይ ሁሉ ተፅዕኖ ያሳድራል፤እናም ብርሀን በቀጥታ ወደ ቤት-ዕቃዎች ጉዳት ሊተረጎም ይችላል፡፡ የሚያደርሰው የጉዳት ደረጃ በድምቀቱና በቀለሙ ይወሰናል፡፡ ደማቅ ብርሀን ከደብዛዛ ብርሀን የበለጠ ጉዳት ያደርሳል፣ሰማያዊ ቀለምም ከቀይ ቀለም የበለጠ ጉዳት ያደርሳል፡፡

በአብዛኛው፤የብርሀን ጉዳት ቀለም ማበላሸት ሲሆን ማንጣት ዋነኛው የጉዳቱ አይነት ነው፡፡ ብርሀን አስተላላፊም ሆኑ ዥጉርጉር ቅቦችን፣የቤት-ዕቃው የተሰራበት እንጨት በተለይም ስጋጃና የመሳሰሉት ዋነኛ ተጠቂዎቹ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ የብርሀን ጉዳት እሳት ወለድና ቋሚ ሊባል የሚችል ነው፡፡ለብርሀን ጉዳት መልስ መስጠት በአንፃራዊነት ቀላል ሲሆን የማያቋረጥ ቢሆን የተሻለ ውጤት ይሰጣል፡፡ የቤት-ዕቃው አገልግሎት በማይሰጥበት ጊዜ ደብዛዛ ብርሀን ባለበት ክፍል ውስጥ እንዲቀመጥ ይመከራል፡፡ አገልግሎት የሚሰጥም ከሆነና ለብርሀን የሚጋለጥ ከሆነ ጉዳቱን እንደ የመስኮት ጥላ፣መጋረጃና ፀሀይን መከላከል የሚችሉ መስታወቶችንና ከፍታ ያለው የብርሀን መስገቢያ ያሉ ቁሶችና ዘዴዎች በመጠቀም በተለመደ መልኩ መቀነስ ይቻላል፡፡ ይበልጥ ጎጂ የሆነ የቀለም ድግግሞሽ የሚያሳስብ ከሆነ ልእለ-ሐምራዊ አጣሪ መጠቀም ይመረጣል፡፡ ለምሳሌ ያህል ፋናዊ አምፑልን እና ከፀሀይ ብርሀን ቀጥታ የሚመጣ ልእለሐምራዊ ጨረርን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ለረጅም ጊዜ የማንጠቀመው ከሆነ ደግሞ በውስጡ አሳልፎ የሚያሳይ አቧራ መከላከያ መጠቀም ይመከራል፡፡በአእምሮ መያዝ ያለበት ዋነኛው ነገር በብርሀንና በቤት-ዕቃዎች ላይ የሚደርሰው ጉዳት ነው፡፡ ብርሀን እስካለ ድረስ እንደ ድምቀቱና እንደሚጋለጥበት የጊዜ ርዝማኔ ጉዳት የሚደርስበት ይሆናል፡፡ ነገርግን ቀላል የሆኑ እርምጃዎችን መተግበር ጉዳትን በመቀነስ ረጅም መንገድን ማስኬድ ይችላሉ፡፡

አንፃራዊ እርጥበት

በቤት ዕቃዎች ላይ የሚደርሰው ትልቁ አካባቢያዊ ጉዳት በአንፃራዊ እርጥበት ከፍተኛ ልዩነት ምክንያት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በተለይም ከእንጨት የተሰራ የቤት-ዕቃ አንፃራዊ እርጥበት ከፍ ሲል እርጥበት ይስባል፤ዝቅ ሲል እርጥበት ይለቃል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ማበጥ እና መሟሸሽን ያሳያል፡፡ ሁኔታውን የበለጠ አስጊ የሚያደርገው ደግሞ እኩል ባልሆነ ሁኔታ በተለይም የቅንጣቶቹ አቅጣጫዎች መለጠጥ እና መኮማተርን ያመጣል፡፡ ይህ ሂደት አዲስ ጥርብም ሆነ  በጥንት መቃብር ውሰጥ ያለ የቤት-ዕቃ፤ከእንጨጥ የተሰራ ከሆነ የማይቀርና የእንጨት የቤት-ዕቃ አስካለ ድረስ የሚኖር ነው፡፡እርጥበት ሲቀየር በእንጨት የተሰሩ የቤት-ዕቃዎች አካላት እርስበርስ መገፋፋት ወይም መሳሳባቸው የማይቀር ነው፡፡ በተለይም እርስበርሳቸው በደምብ ያልተጋጠሙና በውስጣቸው ባለ ውጥረት ምክንያት መጣመም ወይም መሰበር የጀመሩ የቤት-ዕቃዎች ላይ ጎልቶ ይታያል፡፡

በአንፃራዊ እርጥበት መለዋወጥ ምክንያት ጉዳት የሚደርስበት የቤት-ዕቃ ከእንጨት የተሰራው የቤት-ዕቃ ክፍል ብቻ አይደለም፡፡ እድሜያቸው በገፋና እየተበላሹ በሄዱ ቁጥር ቅባቸው ይበልጥ አልተጣጠፍ ይላል፡፡ እንጨቱ ከእርጥበት ልዩነት ጋር እየተለዋወጠና ቅቡም በከፍተኛ ደረጃ ተሰባሪ እየሆነ ስለሚሄድ የአንፃራዊ እርጥበት መለዋወጥ የቅቦችን መሰነጣጠቅና መሰባበር ያፈጥናል፤ከታችኛውም አካል ጋር እንዲለያዩ ያደርጋል፡፡ ይህ ችግር በተለይም ቅቦቹ ከመጀመሪያም መለጠጥ የማይችሉ ሲሆኑ ይበልጥ ጥብቅ ይሆናል፡፡ በተለይም የተቀቡ ወይም የተለበዱ የጀሶ ገፆች ላይ ይበልጥ ይስተዋላል፡፡ለአንፃራዊ እርጥበት የሚሰጠው ምላሽ በአካባቢው ላይ ያለን አመታዊ አማካይ አንፃራዊ እርጥበት ከማወቅ ይጀምራል፡፡ በመቀጠልም በቦታው ላይ ያለውን አንፃራዊ እርጥበት ለቤት-ዕቃው ወደሚቀርበው እንፃራዊ እርጥበት በተቻለ መጠን ማቀራረብ፤በአጠቃላይ በአስር ፐርሰንት ከፍ ወይም ዝቅ ማድረግ፡፡ ይህ ምጣኔ በክረምት ጊዜ እርጥበትን በማስገባትና በበጋ ጊዜ እርጥበትን በማስወጣት ሊደረግ የሚችል ነው፡፡

የሙቀት መጨመር እርጥበትን ይቀንሳል፡፡ የሙቀት መቀነስ ደግሞ በተቃራኒው እርጥበትን ይጨምራል፡፡ በዚህ ምክንያት በክረምት ጊዜ ውስጣዊ እርጥበትን የሚቀንስ ዘመናዊ የማሞቂያ መሳሪያ ሊቀየር የማይችል እክል በቤት-ዕቃው ላይ ያመጣል፡፡ ይህንን ውጤት ለመከላከል በበጋው ጊዜ የቤት-ዕቃው ያለበትን ስፍራ ቀዝቀዝ ማድረግ ይቻላል፡፡ እርጥበትን የሚያመጣጥነው መሳሪያ የተረጋጋ አንፃራዊ እርጥበትን ደግፎ ያቆያል፡፡

የነዋሪዎች አጥፊነት

ሶስተኛውና ትኩረት ሊሰጠው እየተገባው ያልተሰጠው አካባቢያዊ እክል የነዋሪዎች አጥፊነትነው፡፡ እንጨት ነፍሳትን፣አይጦች እና ፈንገስን ጨምሮ ለእንስሳትም ሆነ ለደቂቅ አካሎች ጥቃት የተጋለጠ ነው፡፡ ከነዋሪዎች አጥፊነት ለመጠበቅ የሚሆነው ጥሩው መንገድ የቤት-ዕቃውን በመደበኛነት መቆጣጠር እና ምግብን ከቤት-ዕቃው አርቆ ማስቀመጥ፤ካልተቻለም ቢያንስ በታሸገ መያዣ ማስቀመጥ ነው፡፡

በነፍሳት መወረር

የቤት-ዕቃዎች ስብስብ በተለይም በነፍሳት ሲወረር በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊወድም ይችላል፡፡ ምስጥ፣አናጢ ንቦችና ጉንዳኖች፣የጢንዚዛ ዕጭ እና ሌሎች ነፍሳት ከገፁ በታች ያለውን ክፍል በመብላት የቤት-ዕቃውን አጥብቀው ይጎዱታል፡፡ዕጮቹ የኑሮ ዑደት ጊዜያቸው ደርሶ ብቅ የሚሉበት ጊዜ አስኪደርስ በእንጨቱ ውስጥ መተላለፊያ ዋሻ መሰል ቀዳዳ ያበጃሉ፡፡ በዚህ መውጫ ቀዳዳ ነፍሳቱ በሚወጡበት ጊዜ የታኘከውና የተብላላው እንጨት ተገፍቶ ይወጣል፡፡ እነዚህ የቤት-ዕቃውን እንዳይጎዳ ለመቆጣጠር የሚረዱ ፍንጮች ናቸው፡፡ነፍሳት የወጡበት ቀዳዳ አዲስ የተቆረጠ እንጨት የሚሳየውን ቀለም ያሳያል፡፡

የነፍሳት ኩስና የእንጨት አቧራ ክምር ከቤት-ዕቃ ላይ ወይም በታች መታየት የነፍሳት ወረራን የሚያሳይ ሲሆን በዚህ ጊዜም ማጠን አስፈላጊ ነው፡፡ አንዴ ከተከሰተ ሌሎች የመወረር እድላቸው ከፍ ያለ ስለሚሆን ከተወረረው የቤት-ዕቃ አካባቢ ያሉ የቤት-ዕቃዎችንም መፈተሸ አስፈላጊ ነው፡፡

አይጦች

አይጦች አባዛኛውን ጊዜ እንጨትን እራሱን ለምግብነት ሲሉ አይመገቡትም ይልቁንም በሌላ ጎን ያለ ምግብ ጋር ለመድረስ ይበሉታል፡፡ አይጥ አስተኔዎችን ለማራቅ ተመራጩ መንገድ ምግቦችና ቅመሞችን በቤት-ዕቃው ውስጥና በአካባቢው አለማስቀመጥ ነው፡፡ በተጨማሪም ነፍሳትን የሚስብ በመሆኑ አፅንኦት ሊሰጠው ይገባል፡፡የአይጥ አስተኔዎች በአንድ የቤት-ዕቃ ውስጥ ካሉ የሆነ የጉዳት ምልክት መታየቱ የማይቀር ነው፡፡

ሽበት፣ሻጋታ እና ፈንገስ

ሽበት፣ሻጋታ እና ፈንገስ በየግድግዳው፣ቤት-ዕቃ እና በአየር ውስጥም ሊገኙ ይችላሉ፡፡ በፈንገስ ወረራ የሚደርሱ ጉዳቶች ግን ከውጪ በሚመጣ እርጥበት ካለ ወይም የድርህዋሶቹ አንፃራዊ እርጥበት ከመቶ መቶ ሲሞላ ብቻ የሚደርሱ ናቸው፡፡ አየርና ከፍያለ ሙቀትም የነዚን ኣካላት ፈጣን እድገት ያፋጥናሉ፡፡ የሻጋታ በእንጨት በተሰሩ የቤት-ዕቃዎች ላይ መብቀል የቤት-ዕቃዎቹን ገፅታ ለብልሽት ይዳርጋል፡፡ ሌሎች ፈንገሶች ደግሞ ሙሉበሙሉ ሊያወድሙ ይችላሉ፡፡

ሻጋታና ፈንገስን መቆጣጠር እጅግ ቀላል ነው፡፡ አንፃራዊ እርጥበቱን ከሰባ በመቶ አለማስበለጥ ይመከራል፡፡ ይህም ብልሽቱ ማቆም ባይቻልም እንኳ የሻጋታና ፈንገሶቹ ዘር እንዲዋልግ ያደርጋል፡፡ በተመሳሳይ ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ የፈንገስን የእድገት ፍጥነት ይቀንሳል፡፡ ከፍተኛ ጫናን፣ሊደርስ የሚችል መጠቅለልና መሰንጠቅን ለመከላከል ሲባል እርጥበት አዘል በሆነ አካባቢ አንፃራዊ እርጥበትን የመቀነስ ሂደቱ ቀስበቀስ እንዲከናወን ይመከራል፡፡

ክፍሉ ሰባ በመቶ ከሆነ አንፃራዊ እርጥበት በታች እስከሚሆን ከደረቀ በኃላ የሻጋታ አባባሾች ከቤት-ዕቃው ገፅ ላይ በቆሻሻ መሳቢያ በጥንቃቄ ተስበው መውጣት ይችላሉ፡፡ ይህ በሚሰራበት ጊዜ አቧራውን ላለመተንፈስና ላለመበታተን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ስራው ከተጠናቀቀም በኃላ ማፅጃውን ማጽዳት ያስፈልጋል፡፡ከመጠን በላይ የሆነን እርጥበት ምንጭ ማወቅ እና ለማስወገድ መወሰድ ያለበትን እርምጃ ማጤን አስፈላጊ ነው፡፡ ከመሬት በታች ያሉ ግድግዳዎች በሽፋን መታሸግ እና እንፋሎትን የማያሳልፉ መደረግ አለባቸው፡፡ በጣሪያና ግድግዳ ላይ ያሉ የሚያፈሱ ቀዳዶች ወይም እዣቶች መጠገን አለባቸው፡፡በፈንገስ የሚመጡ ጉዳቶች ወይም መበስበስ ከፍተኛ እርጥበትና ተመጣጣኝ ሙቀት ባለበት ቦታ ብቻ ይከሰታሉ፡፡ የቤት-ዕቃው ካልረጠበና እርጥብ ሆኖ ካልቆየ ይህ አይነቱ ጉዳት መጥፎ ወይም ሀይለኛ አይባልም፡፡ ምንም እንኳን እነዚህ ሁኔታዎች ጠባቂ ሊባሉ የሚችሉ ቢሆኑም የቤት-እቃው እንደ ምድር-ቤት ወይም ከጣራ በታች ያለ ትንሽ ክፍል ባለ የውሀ ግፊት የተለመደ በሆነበት አካባቢ ከተቀመጠ ዝናብ በጣለ ቁጠር አካባበውን መቃኘት ያስፈልጋል፡፡  

የቤት-ዕቃ አጠቃቀምና እንክብካቤ

ግድየለሽ እና መረጃ የሌለው የቤት-ዕቃዎች እንክብካቤ ሁለተኛው ለመከላከል የሚቻል የቤት-እቃዎች ጉዳት መንስኤ ነው፡፡ የቤት-ዕቀዎች ጉዳት ሲደርስ ሊታይ የሚችል ነው፡፡ በሃላፊነት የወሰዳቸው ሰው ሊቆጣረው በማይችለው ደረጃ ደካማ በሆነ ስሪት ወይም ትክክል ባልሆነ አጠቃቀም እና እንክብካቤ ምክንያት ሊከሰትም ይችላል፡፡ የቤት-ዕቃን በአግባቡ ለመያዝ ምሁር ወይም ልዩ ሙያተኛ መሆን አያስፈልገውም፡፡ ተፈጥሯዊ እውቀትን ጨምሮ የዕንጨት ዕቃዎች ተፈጥሮን፣ምንነት እና ማከናወን የሚጠበቅባቸውን ነገሮች ማወቅን ብቻ የሚጠይቅ ነው፡፡እነዚህ አንዳንድ ተፈጥሯዊ ዕውቀትን ማመልከቻ የሚሆኑ ናቸው

  • ገፃቸውን ከእሳትና መጠን ካለፈ ሙቀት መጠበቅ
  • ንድፋቸው ለመቀመጥ አገልግሎት በተዘጋጀ የቤት-ዕቃዎች ላይ ብቻ መቀመጥ
  • በቤት-ዕቃው ላይ የምናስቀምጠውን ነገር እጅግ መጠንቀቅ

እንደብረት፣የቡና መጠጫ ትልቅ ኩባያ እና ከእርሳስ የተሰራ የሾርባ ሳህን ያሉ ክፍያለ ሙቀት የያዙ እቃዎች ቅቦችን የማንሳት አቅም አላቸው፡፡ ሞልቶ የፈሰሰ ውሀ፣ከአበባ ማስቀማጫዎችና ከቀዝቃዛ መጠጦች ጠርሙስ የሚመጣው “ፍካት” ተብሎ የሚጠራ ብርሃን አሳላፊ ቅቦችን ነጭ ቀለም እንዲይዙ የሚያደርግ ጎጂ ውጤትን ያደርሳል፡፡ እንደ ቀለም ወይም ሻይና ቡና ፈሳሹ በገፁ ላይ ሲንጠባጠብ እና ሽፋኑን በሚዘልቅበት ጊዜ ጉዳቱ እጅግ ከፍ ይላል፡፡ካርቦናማ አሟሚዎች ማለትም የጥፍርቀለም እና የጥፍርቀለም ማስለቀቂያ፣ሽቶዎች እና የአልኮል መጠጦች እንደ ቀለም አይነት ተግባር ሊፈፅሙና በተለያዩ ሽፋኖች ላይ ቫርኒሽ ሊያስለቅቁ ይችላሉ፡፡ለእነዚህን ችግሮች መድረስ በእጅጉ ቀላል የሚባል ነው፡፡ ትኩስ እና ቀዝቃዛ ማስቀመጫዎችን፣መጠናቸው ትልቅ የሆነ መተኮሻዎችንና መፃፊያ ጥራዞችን መጠቀም እውናዊ የጉዳቱን አቅም አስከማጥፋት ድረስ ይጠቅማል፡፡

Pin It on Pinterest

Share This