የቤት-ዕቃ የተለያየ አገልግሎትና ልኬት ካላቸው ከተለያዩ አይነቶች ማለትም ከወንበር፣ጠረጴዛ፣አልጋና ከመሳሰሉት የተውጣጣ ሲሆን ዋናው ፅንሰ ሀሳብ በአንድ ላይ አገልግሎት የሚሰጡ የቤት-እቃዎች ንድፋቸውም አንድ ላይ መውጣት አለበት ከሚለው ተለምዷዊ እሳቤ ይለያል። በመሰረቱ የቤት-ዕቃዎችን የሚመለከተው እውቀት በአንፃራዊነት ሲታይ በራሳቸው መቆም ወይም አገልግሎት መስጠት የሚችሉ  ክፍልፋች በመኖራቸው ተመሳሳይ ንድፍ ያላቸውም ቢሆኑ፤የጠረጴዛዎች ፅንሰ ሃሳብ፣የወንበሮች ፅንሰ ሃሳብ፣የአልጋዎች ፅንሰ ሃሳብ እና የመሳሰሉትን አጠራሮች እንድንጠቀም አድርጓል። በቤት-ዕቃዎች ዙሪያ የተደረጉ ጥናቶች ጥንቃቄና ፈሊጣዊነት በአብዛኛው የሚታይባቸው ሲሆን ይህም ማለት አጥኚው የመልከአ ምድርና የጊዜ ርዝመትን በመወሰን በዚህ ወሰን ውስጥ ሆኖ የቤት-ዕቃዎችን ምንጩ ባልተደባለቀ ዋና አገባባቸው ሊረዳቸው ሞክሯል ማለት ነው። የቤት-ዕቃዎች ጥናት በነዚህ ርዕሶች ላይ አጠቃላይ ፅንሰ-ሃሳብን ለመፍጠር ሞክሯል።  እነዚህም ከታች የተዘረዘሩት ናቸው።

 1. የፍብረካ ፅንሰሀሳብ
  1. ቁሳቁስና ሙያዊ ስልጣኔ
  2. ስነ ምህዳርና በአካባቢ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ
  3. ምጣኔ ሀብትና አስተዳደራዊ አመራር
 2. የቤት-ዕቃዎች  ባህሪያት
  1. አገልጋይነት፣ጠቃሚነት፣ቅንተዛምዶ
  2. ውበት፣አድማቂነት
  3. ፍቺ፣መልዕክት
  4. ደህንነት

እነዚህ የቤት-ዕቃዎች ፅንሰሃሳቦችና ባህሪያት በተግባራዊነት ላይ አስፈላጊ ናቸው። አንድ የቤት-ዕቃ ሊያስገኛቸው ከሚገባው አስፈላጊ ግቦች ውስጥም እጅግ አስፈላጊዎቹ እነዚህ ናቸው።የቤት-ዕቃ ንድፎች ግቦች ከሌሎች የዕቃ አይነቶች ግቦች ጋር የሚያመሳስላቸው ነገር አለ። በእርግጥ በቤት-ዕቃዎች ልማት መዳበር አጠቃላይ ግብ ዙሪያ የተሰሩ ብዙ ጥናቶች ያሉ ሲሆን ውጤታቸውም በአጠቃላይ ልዩ ግብን ያማከለ ነው።

የፍብረካ ፅንሰ ሀሳብ

ቁሳቁስና ሙያዊ ስልጣኔ

እስከ 1960ዎቹ የነበሩት ታላላቆቹ የክፍለዘመኑ የቤት-ዕቃ ለውጦች በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ በሙያዊ ስልጣኔ ላይ የተመረኮዙ ናቸው። እነዚህ ቁሶች ንድፍ አውጪዎችን አዳዲስ የቤት-ዕቃ ቅርፆችን እንዲፈጥሩ አነሳስተዋቸዋል።

የቱቦ ቅርፅ ያለው የአረብብረት

ምናልባትም የመጀመሪያው ለቤት-ዕቃነት የዋለ የብረት አይነት ነው። ግቡም የቁሳቁስና የቦታ ቁጠባን ማረጋገጥ ነው። ለዚህ አዲስ ቁስ መነሻ የሚሆኑ ማሽኖች በመጀመሪያ ከመርከብ ግንባታ፣ከአውሮፕላንና መኪና ኢንዱስትሪዎች ተነስተዋል።

የተነባበረ ሳንቃ እንጨት

የመጀመሪያው አገልግሎታቸው የቁም-ሳጥን ጀርባ እና የመሳቢያዎችን ታችኛውን ክፍል መስራት ሲሆን ግን ቀስበቀስ ወደ ሌሎች ዝርግ የቤት-ዕቃዎች ክፍል ተሸጋግረዋል፤ንድፍ አውጪዎችንም ዝርግ ቅርፅን አዘውትረው እንዲጠቀሙ አበረታቷል። በነአልቫር ኣልቶ ፈጠራ ከተገኘው የታጠፈ የተነባበረ ሳንቃ እንጨት በኃላ አዲስና እንግዳ የሆነው አገልግሎቱ ወጥቶ ሊታይ ችሏል።

ከፍቅፋቂ እንጨት የተሰራ ሰሌዳ

ጥብቅነቱ ያለ ክፈፍ ለመስራትና በራስ አዘጋጅቶ ለገበያ ለማቅረብ ቀላል ስለሚያደርገው ተመራጭ ያደርገዋል። የሳጥን ቅርፅ ያለው ንድፍን የሚያበረታታ ሲሆን እንደ ተነባበረ ሳንቃ እንጨት ሁሉ በተለመደ የእንጨት ስራ ማሽን ሊዘጋጅ የሚችል ነው።

ፐላስቲክ

ንፅፅር እንደሚገድፈው፤ባለ ሶስት ወርድና ስፋት ኩርባ ቅፅ መንደፍ በተለይም የቃጫ መስታወት ወይም የኤቢኤስ ሙያዊ ስልጣኔ መጠቀም የተመረጠ ነው። እነዚህ ቁሳቁስና ሙያዊ ስልጣኔዎች በመጀመሪያ ከጀልባ ግንባታ የተገኙ ናቸው። በአየር መነፋት የሚችል ፒቪሲ ፕላስቲክ ወንበሮችን ለመስራት የሚያስችል ሌላ ዘዴ አቅርቧል። ቅርፁን ለመጠበቅ በአየር ግፊት የሚተማመን ሲሆን በዚህም ምክንያት እንደ ትራስ ያሉ ቅፆችን ይጠይቃል።ፖሊዩሬቴን ፍራሽም ከበታች ጠጣር(ደረቅ) ድጋፍ ባይኖር እንኳን ለስስ ማረፊያዎች የሚታይ ቅርፅን በመስጠት መተካት ይችላል።

ወረቀት(በጨርቅ፣በፐላስቲክ ወይም በመሳሰሉተ የተጠናከረ ሊሆን ይችላል)

በመደበኛነትም ባይሆን አዲስ ለመጡ የቤት-ዕቃዎች ዝግጅት ጥቅም ላይ ውሏል።  ምናልባትም ከዘመናዊነትም ያለፈ የኑሮ ዘይቤ፣ማህበራዊ ተንቀሳቃሽነት፣የማሰብና የመመራመር ነፃነት እንዲሁም ከባህላዊ ኑሮን ተከታይ ከሆነው የህብረተሰብ ክፍል ጋር ደግሞ አለመስማማት ይታይበታል።

ከላይ የተዘረዘሩት በሙሉ ፍፁም በቤት-ዕቃዎች ኢንዱስትሪ ውስጥ የተዋወቁ የመጨረሻዎቹ አዳዲስ ቁሳቁስ ናቸው ማለት አይደለም።

የቤት-ዕቃዎች አገልጋይነት ፅንሰሃሳብ

አገልጋይነት በቤት-ዕቃዎች ዙሪያ በተደረጉ ብዙ ገላጭ ጥናቶች ውስጥ የበለጠ ዋጋ ያለው ሲሆን በተለይም በ20ኛው አግማሽ፣አገልጋይነት ለሁሉም ንድፎች መነሻ ነጥብ መሆን እንዳለበት ካወጀው ከተግባራዊ የህንፃ ጥበብ መነሳት በኃላ በበለጠ እየተተገበረ የመጣ ነው። ሞብሊንስቲቱቴት የተባለው የቤተ-ዕቃዎች ጥናት ማዕከል በ1967ዓ.ም የተመሰረተባት ስዊድን በተግባር ለማዋል ፈርቀዳጅ ስትሆን የጥናት ማዕከሉንም በዋናነት በራሷ ፋይናንስ አቋቁማለች። የመጀመሪያዎቹ የስራ-ዕቅዶች የስነምቾትን ሁኔታ እና ልኬት ላይ ትኩረት ያደረጉ ሲሆን በነዚህ ጥናቶች መሰረት ማሳሰቢያዎች(ምክሮች) ተሰጥተዋል፤ በደምብም ተሰራጭተዋል። ከዚህ በታች ያሉት አጠቃላይ ለቢሮ ወንበሮችና መፃፊያ ጠረጴዛዎች የስነ-ምቾት መስፈርቶችን የሚያሳዩ ነጥቦች ናቸው።

 1. የተጠቃሚው ትከሻ ለእንቅስቃሴ ነፃ መሆን ይኖርበታል።
 2. የመደገፊያው ላይኛውና የታችኛው ጠርዝ ምቹ መሆን ይኖርበታል።
 3. ተጠቃሚው ወደፊትና ወደኃላ በሚያዘምበት ጊዜ የጀርባ ድጋፉ ለታችኛው የደረት ክፍል ድጋፍ መስጠት አለበት፤15 እርክን ዝርገት ያህልም ማጋደል ይኖርበታል።
 4. ቀጥ ብሎ ሲቀመጥ ወይም ጥቂት አጋድሎ ሲቀመጥ፤የጀርባ ድጋፉ ለጀርባ አጥንት ድጋፍ መስጠት አለበት።
 5. የጀርባ ድጋፉ እንደ መከዳ በጨርቅና ሰፍነግ መሸፈን አለበት።
 6. የጀርባ ድጋፉ የላይኛውን የዳሌ አጥንት መደገፍ ይኖርበታል። ግን በጀርባ ድጋፍና በመቀመጫው መሀከል ግን ክፍተት መተው ይኖርበታል።
 7. መቀመጫው የሚያዳልጥ መሆን የለበትም። ተመራጩ ዝንባሌ 3 እርክነ ዝርግነት ነው።
 8. መቀመጫው በሰፍነግ መሸፈን አለበት።
 9. የደምስሮችና ጅማቶችን መቆንጠጥ ወይም መቀርጠፍ ለማስቀረት በእግሮቹ መሀከልና በመቀመጫው ፊትለፊት አስር ሳንቲሜትር ያህል ባዶ ቦታ መኖር አለበት።
 10. እግርን እንደልብ ለማንቀሳቀስ የሚያስችል ቦታ መስጠት
 11. ወንበሩ ወደኃላና ወደፊት በመገፋት መንቀሳቀስ የሚችል መሆን አለበት። ነገርግን ተሸከረካሪዎች መወገድ ይኖርባቸዋል።
 12. መቀመጫው ከሰው ዳሌ በጥቂቱ የሰፋ መሆን ይኖርበታል። አቋሙን አስተካክሎ እንዲቀመጥ የሚረዳ መሆን አለበት። ጠፍጣፋ ወይም በጥቂቱ ስርጉድ መሆን አለበት።
 13. በመቀመጫውና በመፃፊያ ጠረጴዛው መሀከል ያለው የከፍታ ልዩነት እንደአስፈላጊነቱ መስተካከል የሚችል መሆን አለበት። ለመፃፊያ ጠረጴዛ ተመራጩ ከፍታ ከ67 እስከ 75ሳንቲሜትር ነው።
 14. ከመፃፊያው ጠረጴዛ በታች 70ሳንቲሜትር ስፋትና ከ60 አስከ 70 ሳንቲሜትር ጥልቀት ያለው እግር ማሳረፊ ያስፈልጋል።

እነዚህ ዝርዝሮች ለቢሮ የቤት-ዕቃዎች ጥቃቅንና ዐቢይ ማሳሰቢያዎች ናቸው። ሌሎች የቤት-ዕቃ አይነቶች በተመሣሣይ መልኩ ተጠንተዋል። ሞቤሊንሰቲቱቴት እና ሌሎች የዘርፉ ባለሙያዎች የጥራት መለኪያና የመመዘኛ ዘዴ አዘጋጅተዋል።

 • የአልጋዎችና ፍራሾች ምቹነት
 • የተዋቀሩ አካላት፣የመደርደሪያዎች እና የመሳሰሉት ጥብቅነት
 • መጫጫርን፣ሙቀትን፣አልኮልንና ሌሎች ፈሳሾችን መቋቋም መቻል
 • የቁሳቁስ ጥራት
 • ከመታጠፍና ከመገልበጥ ስጋት ነፃ መሆን

አሁን በብዙ አገራት ለብዙ አመታት የተደረገው የስነምቾት ጥናት ለተለያዩ የቤት-ዕቃዎች ንድፍ እንደ መስፈርት ብቻ ሳይሆን እነደ መምሪያ መፅሀፍ ታትሞ ተቀምጧል።በአገልጋይነት ጥናቱ ውስጥ ያሉ እሳቤዎች፣ቅጂዎችና ዘዴዎች በሌሎች ተነፃፃሪ ቁስ ውጤቶች ካሉት የተለየ እሳቤዎች፣ቅጂዎችና ዘዴዎች ያሉት አይደለም። እነዚህ በአለምአቀፍ ደረጃ ሊሰራ የሚችል የጥናት መሳሪያዎች በምርቶች አገልጋይነት ላይ በተለየ ገፅ ተመርምረዋል።

የቤት-ዕቃዎች መልዕክት ፅንሰሃሳብ

የቤት-ዕቃዎች እንደልብስ፣መኪና እና ቤት ሁሉ ለሰዎች እንደ ዋና መገልገያ ከሚውሉት ጎራ ይመደባሉ። የቤት-ዕቃ ከተጠቃሚው ጋር በቅርብ የሚጎዳኝ ሲሆን የቤት-ዕቃን በመምረጥ ውስጥ ተጠቃሚው ሌሎች በምናባቸው ስለእርሱ የሚኖራቸውን ስዕል መበየን ይችላል።የምዕራባዊው አለም ከተሜ በህብረተሰብ ውሰጥ ጠንካራ የደረጃ አቀማመጥ ላይ ይገኛሉ። ብዙ ሰዎችወደ ከፍተኛ የህብረተሰብ መደብ ስርአት ከፍ ለማለት ወይም የተፋጠነ ቅፅበታዊ ምጥቀት ሊሳካየማይችል ቢሆንም ቢያንስ ለዚህ አይነቱ ከፍታ የተዘጋጁና በቂ መሆናቸውን ማሳየት ይፈልጋሉ።የቤት-ዕቃና ጨርቃጨርቆች ማህበረሰባዊ ሁኔታንና በዚያ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን ሁኔታ ከማሳየት በተጨማሪ  የባለቤቱን ማህበረሰባዊ ተወዳዳሪነት ይጨምራሉ። ለዚያም ነው ነባር የታችኛው የህብረተሰብ ክፍል የምዕራባዊ መሳፍንትን ለማስመሰል የሚፈልገው(የሚያስመስለው)። ይህም የማስመሰል ነገር የቤት-ዕቃዎች ዘይቤ በህብረተሰቡ ውስጥ ምንያህል ሊሰራጭ እንደሚችልና አዳዲስ ዘይቤዎች በተደጋጋሚ መፈጠር እንደሚችሉ ያሳያል።     

የቤት-ዕቃዎች ስነውበት

የቤት-ዕቃዎች እንደልብስ፣መኪና እና ቤት ሁሉ ለሰዎች እንደ ዋና መገልገያ ከሚውሉት ጎራ ይመደባሉ። የቤት-ዕቃ ከተጠቃሚው ጋር በቅርብ የሚጎዳኝ ሲሆን የቤት-ዕቃን በመምረጥ ውስጥ ተጠቃሚው ሌሎች በምናባቸው ስለእርሱ የሚኖራቸውን ስዕል መበየን ይችላል።የምዕራባዊው አለም ከተሜ በህብረተሰብ ውሰጥ ጠንካራ የደረጃ አቀማመጥ ላይ ይገኛሉ። ብዙ ሰዎች ወደ ከፍተኛ የህብረተሰብ መደብ ስርአት ከፍ ለማለት ወይም የተፋጠነ ቅፅበታዊ ምጥቀት ሊሳካ የማይችል ቢሆንም ቢያንስ ለዚህ አይነቱ ከፍታ የተዘጋጁና በቂ መሆናቸውን ማሳየት ይፈልጋሉ።የቤት-ዕቃና ጨርቃጨርቆች ማህበረሰባዊ ሁኔታንና በዚያ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን ሁኔታ ከማሳየት በተጨማሪ  የባለቤቱንማህበረሰባዊ ተወዳዳሪነት ይጨምራሉ። ለዚያም ነው ነባር የታችኛው የህብረተሰብ ክፍል የምዕራባዊመሳፍንትን ለማስመሰል የሚፈልገው(የሚያስመስለው)። ይህም የማስመሰል ነገር የቤት-ዕቃዎች ዘይቤበህብረተሰቡ ውስጥ ምንያህል ሊሰራጭ እንደሚችልና አዳዲስ ዘይቤዎች በተደጋጋሚ መፈጠር እንደሚችሉ ያሳያል።   የቤት-ዕቃዎች ስነውበትውበት ያላቸው እቃዎችን በአካባቢያችን ዙሪያ መመልከት ጥሩ ስሜት እንደሚሰጥና አንዳንድ የቤት-ዕቃዎች ከሌላው የተሻለ ውበት እንዳላቸው እሙን ቢሆንም ለምርጫ እና በእርሱ ዙሪያ ውይይትለማድረግ ከባድ ይሆናል። ከዚህ በመነሳት ውበት ያለው የቤት-ዕቃ ንድፍን ማዘጋጀት ምንያህል ፈታኝነት ያለው ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም። በዚህ ሁኔታ ውስጥ የስነውበት ጥናትሃሳብን ነዳፊዎች፣አምራቾችና ህዝቡ በውበት ጥያቄ ላይ ሲወያዩ፣ግቦችን ሲያስቀምጡና እነዚህንምአዲስ በሚመጡ የቤት-ዕቃዎች ላይ በተግባር ለማዋል ቀላል መንገዶችን የሚያሳይና የሚከፍትይሆናል።በቀስታ የሚሄድ የማስተዋል ችሎታ መላምት ውስጥ አንድ ሰው በአንዳች ሳቢነት ባለው የጥበብስራ ውስጥ የሚያገኘው የሚያስደስት የስነውበት ስሜት ነው። ይህ ግኝት “ኢዩሬካ” ተብሎ የሚጠራየሚያስመሰግን ስሜት ሲሆን ይህ ሀይለኛ የጋለ ስሜት ቀድማ ለሚመጣ ለትንሽ ሰከንዶች በሚቆይ ግራመጋባት ሊታጀብ ይችላል። እንደ ንፅፅርም ምስጢራዊ የሆኑና አንዳች ጥቅም የሚሰጡ የጥበብ ስራዎች ከሌሉበት የውበት ስሜቱ የማያንፀባርቅ ይሆናል። ምንም እንኳን አንድ ስራ በውበት መገኘትውስጥ አስፈላጊውን የአሰራር ሁኔታ ቢያሟላም፤የስራው የውበት ዋጋ የላቀ ቢሆንም የሰው ልጅ የመገንዘብ አቅም በአንድ ዕይታ ውስጥ ትልቅ የሚባል የመረጃ መጠንን የመቀበል አቅም የለውም።በዚህ ምክንያት አይነተኛ የሆነ ታላቅ ስራ የብዙ ንብርብሮች ይዘት ሆኗል። ለመጀመር ያህል ስሜትን የሚያጓጓ  ቀለል ያለ ይዘት ወይም ማስጌጫ ሊኖረው ያስፈልጋል፤ካልሆነ ግን ህዝቡ አየት አድርጎ ከማለፍ የዘለለ ትኩረት ለስራው ሊሰጠው አይችልም። ቀስበቀስ እንዲሰተዋልና ተወዳዳሪነቱእንዲጨምር ጥልቀት ያለው ይዘት ሊኖረውም ያስፈልጋል። ይህ ጥልቀት ያለው ይዘት  የኢዩሬካስሜትን በአንድ ደረጃ ይጨምራል።

Pin It on Pinterest

Share This