ከአንድ ምርት የሚጠበቀው ተግባር በቅፁ እና በሚገነባባቸው ውህዶች ላይ መሰረታዊ ተፀዕኖ የሚያሳድር ሲሆን  እያንዳንዱ የቤት-ዕቃ ጥቅም ላይ ሲውል የሚያስፈልገውን ዘዴ፣ባህርይ እና ቦታ በተሟላ መልኩ የሚያሳካ የተወሰነ ተግባር ማከናወን ይኖርበታል። ብዙውን ጊዜ የአንድ የቤት-ዕቃ ምርት ተግባር አዳዲስ ቅርፅ እና ጥበብ የተሞላበት አገላለፅ ማሳየት ሲሆን ምርቱንም ለመጠቀም መነሳሳትን የሚፈጥረው ይኸው ጠባዩ ነው። ለብዙ ሺህ አመታት የሰው ልጅ የቤት-ዕቃ የሚሰጠውን ጥቅም አሻሽሏል፤የቤት-ዕቃው መዋቅራዊ ቅፅና የአመራረቱ ሙያዊ ስልጣኔም ላይ ብዙ ለውጦች አምጥቷል። በአሁኑ ጊዜ የወንበሮች መቀመጫ ስሪት የተቀየረ በመሆኑ ቀድመው የነበሩ ልምዶችን በሚያስንቅ መልኩ ተጠቃሚው በወንበሩ ላይ ጡንቻዎችን አላልቶ መቀመጥ ይችላል። ከወለል በላይ ያለው ርቀትና በመቀመጫውና መደገፊያው መሀከል ያለው ማዕዘን ልኬትም እንዲሁ ተለውጧል። በዚሁ ውስጥ የልኬት ምጣኔ፣የትክልና ተንቀሳቃሽ የቤት-ዕቃ ክፍሎች ድልድልና ለጥቅም የሚውሉባቸው ቦታዎችም የተቀየሩ ሲሆን በጥሩ ንድፍና ብልሃት የተሰሩት በሰዎች ሃሳብ ውስጥ ለመቆየት ችለዋል።

ባለብዙ ጥቅም (ተግባር) የቤት-ዕቃዎች ከሰዎች የአኗኗር ሁኔታዎች መበላሸትና የመኖሪያ ቦታን ጥቅም ማሳደግ የግድ አስፈላጊ በመሆኑ የመጡ ናቸው። የቤት-ዕቃዎች ከተወሰኑ የስሪት አባሎቻቸው መሻሻል በኃላ እነዚህ ምርቶች ለስራ፣ለመመገቢያ፣ለዕቃ ማከማቻ፣ለመኝታና ለእረፍት መውሰጃነት የሚሆኑ ቦታዎችን መስጠት ቻሉ። ባለ ብዙ ጥቅም የቤተ-ዕቃዎች እንደ ልምድም ቀለል ባለ ቅፅና ባልተወሳሰበ ዘይቤ፣በሙያዊ ስልጣኔ የበላይነት ስር ሆነው የተጠቃሚውን ብዛት ያለው ፍላጎት በማሟላት ይለያሉ። ምንም እንኳን ብዙ የቤት-ዕቃ አይነቶችና ተግባራቸውን አጠቃሎ በያዘ አንድ የቤት-ዕቃ ውስጥ ለተጠቃሚው ምቾት መስጠት ባይቻልም አባሎቻቸው ተግባሮቻቸውን ለማከናወን በሚጥሩበት ጊዜ እርስበርስ ገደብ እንደሚሆኑ ከግምት ማስገባት ያስፈልጋል። 

የሰው ልጆች አብዛኛው የቤት-ዕቃ ተጠቃሚና በዕለትተዕለት እንቅስቃሴያቸው ውስጥ የቤት-ዕቃ ቢኖርም በኑሯቸው ውስጥ እያበረከተ ያለውን ቁምነገር ግን ልብ የሚሉ ቁጥራቸው እጅግ አነስተኛ ነው። የቤት-ዕቃዎች ጠቀሜታ በቁጥር እጅግ የበዛ እና ዘርፈብዙ ነው። ከዚህ በታች ያለው ፅሁፍ የቤት-ዕቃዎችን ጠቀሜታ ከብዙ በጥቂቱ ለመዘርዘርና ለመግለፅ ይሞክራል።

የግል ዘይቤን እንደመግለጫ መንገድ

በአሁኑ ጊዜ በመኖሪያ ቤቶች ውስጥ የተዘበራረቀ መልክ ካላቸው ይልቅ ከባለቤቱ ማንነት ጋር ተስማሚ የሆኑ የቤት-ዕቃዎችን መመልከት እየተለመደ መጥቷል።

እንደ መሰባሰቢያ ስፍራነት

በተለይ በበዓላት ጊዜ የቤት-ዕቃዎች መሰባሰቢያነታቸው ጎልቶ ይወጣል። ሞቅ ባለና ደስታን በሚሰጠው የቤት-ዕቃ ዙሪያ በመሰባሰብ ቤተሰብና ጓደኛ ይስተናገድበታል፤ቆይታውንም የተሟላ ያደርጋል። በተለይ ስሪቱ ከእንጨት ወይም ብረት ከሆነ በሻካራነቱ ወይም በልስላሴው ውስጥ ተፈጥሮ የምትሰጠውን የተረጋጋ ስሜት ይሰጣል፤በተጨማሪም የጥንት ጊዜን የማስታወስ አቅምም አለው።

በአንድ ክፍል ውስጥ የትኩረት ነጥብ መስጠት

አንዳንድ ጊዜ አንድን ክፍል ከጥሩ ወደ ላቀ፤ከተራ ወደ ዘይቤያዊ ለማሸጋገር አንድ የቤት-ዕቃ ለብቻው በቂ ሆኖ ይገኛል። ሰዎች ወደ ቤት በሚጋበዙበት ጊዜ አይናቸው በአንድ ውብና ትኩረት በሚስብ ግን ቀለል ባለ የቤት-ዕቃ ላይ ሲያርፍ የእንግድነት ስሜታቸው ተወግዶ ከጋባዡ ጋር ጥሩ ጊዜን እንዲያሳልፉ ይረዳል።

ከላይ በምስሉ ላይ እንደሚታየው በዓይነተኛው መፅሀፍ መደርደሪያና መከዳ ከቤት-ዕቃው ተግባራት አንዱም እንኳን በበቂ ሁኔታ አልተረጋገጠም። ለመደርደሪያነት የታሰቡት ቦታዎች በፍራሹ ልኬትና አቀማመጥ ተወስኗል፤ለዚህም ወደላይ(በቁመቱ) ታጥፏል። የፍራሹም አሰራር ቢሆን በመደርደሪያው ጥልቀት ይወሰናል። ይህም የሚለጠጡ ተደራራቢ ንብርብሮችን ቁጥር ማለትም የመኝታና የማረፊያ ምቾትን ያቃውሳል። አብዛኛውን ጊዜ የመከዳውን  ታችኛውን አካል መያዣ ከፍ በማድረግ የሚገኙት ለስራ መስሪያነት የሚያገለግሉት መደቦችም ቢሆኑ ከመከዳው ፍራሽ ልኬት እኩል መሆናቸው አይቀሬ ነው። በግንባታና በሙያዊ ስልጣኔ መፍትሄዎች የተለያዩ የቤት-ዕቃ ተግባራትን መዋሃድ የሚያረጋግጡ፤ሁሉንም በአንድ አጣምረው የሚይዙ መሆናቸው ለመጠቀም የሚያነሳሳ ሆኖ ሳለ የነዚህ ባለብዙ ተግባር የቤት-ዕቃዎች ተጠቃሚ ምቹ ማረፊያ፣ሳቢ የስራ ጠረጴዛና ወደ ዕቃዎች ክምችት ቀላል መድረሻ ለማግኘት መተማመን አይችልም።  

የእነዚህ የቤት-ዕቃዎች ብዙ ተግባር መፈፀም በእርግጥ ጠቃሚነትም አለው። ንድፍ አውጪዎችና ገንቢዎች የተያያዘ እና እርስበርስ የሚደጋገፍ ቅፅን በቤት-ዕቃ ስራዎች ላይ ያኖራሉ። የእነዚህ አይነት የቤት-ዕቃዎች ማከማቻ ያላቸው፣የራሳቸው ብርሀን መስጫ ያላቸውና የተቀመጡትን ምርቶች ቁጥርና አይነት የሚያስታውሱ ሲሆኑ የማብሰያ ቤት የቤት-ዕቃዎች ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ይሆናሉ። ሌላው እንደ ምሳሌ የሚጠቀሰው ማጣጠፍን በማስቀረት ለእግር ማሳረፍያነት የሚሆኑ ቅጥያዎች ያሉት፣የመታሻ አገልግሎት የሚሰጥ፣ማሞቂያ ያለው፣ለመቀመጥና ለመነሳት የሚረዳው የቤት-ዕቃ ነው። የአገልግሎት ሁኔታው እንደሚያሳየው የሌሎችንም ሆነ የራሱን ተግባሮች የሚገታ አይደለም። በቅፅና ተግባራቸው ስምምነት ያላቸው፣ፈጠራ የተሞላባቸው የንድፍ ውህዶች፣ዘመናዊ የሙያ ስልጣኔና የተለየ ምህዳር ያላቸው መስሪያ ቁሶች ሲሆኑ በዚህ መልኩ የተነደፈ የቤት-ዕቃ ውጤቱ ከፍተኛ ጥራት ያለው ይሆናል። በዚህ ውስጥ የቤት-ዕቃዎቹ የበዛ ጥቅም መስጠትና ከተጠቃሚው የበዛ ፍላጎት ጋር መጣጣም ትልቁ ብልጫቸው ነው። ይህም የቤት-ዕቃዎች ዘመናዊነት ሀሳብ አዲስ ትርጓሜና አይነት አስገኝቷል። ብዙውን ጊዜ ተግባራዊነቱ ከኤሌክትሮኒክና ራስ ሰርነት፣ጥራትን ማሻሻል፣ምቾትና የአጠቃቀም ጥንቃቄን በንድፎቹ ውስጥም ዘመናዊ አከፋፈልና የንድፍ መስመሮች ያካትታል። በነዚህ ምክንያቶች ባለብዙ ተግባራዊነት ከበፊት ጊዜያት ጋር ሲነፃፀር የበለጠ ጥራት ያላቸውን የቅንጦት የቤት-ዕቃዎች የበለጠ እያጀበ አየመጣ የቤት-ዕቃን ጥቅምም ይበልጥ እንዲጨምር እያገዘ መሆኑን ማስተዋል ይቻላል።

እየተዋወቁ ያሉ ፈጠራ የተሞላባቸው የግንባታ ፍቺዎች የተቀላጠፉ፣እምነት የሚጣልባቸውና ደህንነታቸው የተጠበቀ ሊሆኑ ይገባል። በኢንዱስትሪ ንድፍ ውስጥ ከምርቱ አገልግሎት አስፈላጊነት በተጨማሪ የተጠቃሚውን አካላዊና ስነልቦናዊ መስፈርቶች ያሚያሟሉ እንዲሆኑ ስለሚጠበቅ በዚያ ላይ  የበለጠ ትኩረጥ ይሰጣል። የቤት-ዕቃ አገልግሎት ከተጠቃሚው አካል ጋር ባለው ቀጥተኛ ንክኪ ውስጥ ይታወቃል። የአገልግሎቱ እውነተኛ ገለፃ በልኬት፣በቅርፅ እና በተግባራዊነት ጥራት አንዳንዴም በተሰራበት ቁስ ውስጥ ይታያል።

የቤት ዕቃዎች በትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚሰጡት ጥቅም

የቤትዕቃዎች በትምህርት ተቋማት ውስጥ ለምን አጅግ አስፈላጊ ሆኑ?

ትምህርት እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው። በሰዎች የወደ ፊት ኑሮ ላይም የራሱ የሆነ ተፅዕኖ ያሳድራል።  አንድ ሰው በመማሪያ ክፍል ውስጥ በሚገባበት ጊዜ መልኩንና መዋቅሩን ያስተውላል። ብዙ አስፈላጊ መስሎ ባይታይም በተማሪዎች የመማር ሂደት ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። የቤት-ዕቃዎች አደረጃጀት የተማሪዎችን ባህርይና የስራ ስነምግባር የመቀስቀስም ሆነ የማጥፋት አቅም አላቸው። ውጤታማው የመማሪያ ክፍል አደራጃጀት የሁለት ወይም የሶስት ጠረጴዛዎች ስብስብ፣የመምህር ጠረጴዛ የክፍሉን ጥግ ይዞ፣በአጠቃላይ በክፍሉ ውስጥ ጉልህ ልዩነት የሚፈጥር አቀማመጥ ያስፈልጋል። የጠረጴዞቹ ስብስብ ለተማሪዎች የግል ስራቸውን ሳያቋርጡ ለመምህሩም ትኩረት እየሰጡ እርስበርስ የመወያየት እድል በመስጠታቸው ግባቸውን በቂ በሚባል ሁኔታ መትተዋል ሊባል ይችላል።

የቤት ዕቃዎች በህክምና ተቋማት ውስጥ የሚሰጡት ጥቅም

ሆስፒታሎች፣በአጠቃላይ ቀዶጥገና እና በአእምሮ ህክምና ማዕከላት ተግባራዊነቱ የተረጋገጠ አስደሳችና የተዘጋጀበትን አላማ የሚያሳካ የስራ አካባቢ አስፈላጊ መሆኑ ይታወቃል። በቁጥር ብዛት ያላቸው ህመምተኞች በነዚህ ተቋማት ውስጥ ለረጅም ጊዜ በሚቆዩበት ጊዜ በአካልም ሆነ በሀሳብ እንደግለሰብ የመዝናናትና ከፍያለ ግምት የማግኘት ስሜትን ሊያገኙና ምቾት ሊሰማቸው ይገባል። ንድፍ አውጪዎችና ፕላን ነዳፊዎች ውበትንና በተለየ መልኩ በልክ ተሰርቶ የሚገጠም የሆስፒታል የቤት-ዕቃን ምርጫና ለአገልግሎት ተግባር ማዋልን ቀዳሚ ግባቸው ያደርጋሉ።

የሚያስደስትና አዎንታዊ አካባቢን መፍጠር

የእንግዳ መቀበያ የተረጋጋና ዘና የሚያደርግ ሊሆን ይገባል። በአግባቡ የተገጠመ የመፃፊያ ጠረጴዛ፣ የመደርደሪያ አሃድና ምቾት ያለው መቀመጫ ይህን ለማሳካት አስፈላጊ ናቸው።

ብዛት ያለው ለመጠቀም የሚሆን ቦታን መፍጠር

በቋሚነት የተገጠሙ የቤት-እቃዎች ከማከማቻ ስፍራዎች በተጨማሪ በጠባብ ቦታዎችም መደርደሪያዎችን በመጠቀም የተሻለ የመጋዘንነት አገልግሎት ይሰጣሉ። ተንቀሳቃሽ ጠረጴዛዎችና የማከማቻ መሳቢያዎች በማከሚያ ስፍራዎች ያሉትን የሙያ ተግባራት በአግባቡና በቀላሉ ለማከናወን ይረዳሉ። በተለይም የተለያየ ህክምና በአንድ ላይ ለሚሰጥባቸው የህክምና ተቋማት እጅግ ጠቃሚነት አላቸው።

ሙያዊ መልክ መስጠት

የተገጠሙ የቤት-ዕቃዎችን መጠቀም ሰላማዊና ሙያዊ መልክን ለመግለፅ የሚያግዝ ሲሆን የቀለም ምርጫው ከባድ ሳይሆን ቀለል ያለና ንፁህ የሆነ ዕይታን የሚፈጥር ነው።

ለህክምና ተቋማት የቤት ዕቃዎችን ለመምረጥ ማሟላት ያለባቸው የጥራት መስፈርቶች:-

ዘላቂነትና ንፅህናቸው የተጠበቀ መሆን     

የወንበሮችና ጠረጴዛዎች ገፅ ለቫይረሶች፣ለባክቴሪያና ለሻጋታ ምቹ የመራቢያ ቦታ የመሆን እድል አላቸው። ለህክምና መስጫ የሚሆኑ የቤት-ዕቃዎች ምርጫ በሚደረግበት ጊዜ ገፃቸው ጀርሞች የሚያደፍጡባቸው አይነቶች ፤ማለትም መጋጠሚያ ያላቸውና የተጨማደዱ መሆናቸውን እንደ ዋና አሉታዊ ባህርይ ማየት ያስፈልጋል። ፀረ-ረቂቅ የበሽታ አምጭ ተህዋሲያን መጠቀም እና በጨርቅ መሸፈን የህመምና የበሽታ አምጪ ተዋሲያንን አጋልጦ በማውጣት ለማጥፋት መተኪያ የሌላቸው መንገዶች ናቸው።ይህንን ተግባር ለማከናወን የሚችሉ ትልቅ ብቃት ያላቸው ጨርቆችና ዝገት መቋቋም የሚችሉ ቅቦች በስፋት ይገኛሉ። ለማፅዳት ቀላልና ፀረ-ባክቴሪያ ሆነው በሽታ አስተላላፊ የሆኑትን መመከትና ማጥፋት የሚችሉ ማፅጃ ቁሶችን መጠቀምም አስፈላጊ ነው። ይህንን የማይቋረጥ ኬሚካላዊ እጥበት መቋቋም የሚችል ፅናት ያላቸው የቤት-ዕቃ አይነቶችን መጠቀም አስፈላጊ መሆኑ ግለፅ የሆነ ነው።

ምቾትና ደህንነት

በሁሉም የእድሜ ደረጃ፣ቅርፅና መጠን ላይ የሚገኙ ሰዎች ሆስፒታልና ክሊኒኮችን ይጎበኛሉ። በመሆኑም በሆስፒታሎችና ክሊኒኮች ያሉ የቤት-ዕቃዎች በየትኛውም የእድሜ ደረጃ፣የአካል መጠን ወይም የአካል ጉድለት ውስጥ ላሉ ሰዎች ምቹና ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት ሊሰጡ ይገባል። እንደ ምሳሌ ለመጥቀስ ያህል ጥንካሬ፣መጠነኛ ከፍታና አስተማማኝ የእጅ ማስደገፊያ ያላቸው የቤት-ዕቃዎች ጥሩ አማራጮች ናቸው። ለስለስ ያለ ጠርዝ ያላቸውን የቤት-እቃዎችን መጠቀምም አደጋ በሚደርስበት ጊዜ ጉዳቱን ለመቀነስ ይረዳል። እጅግ ተቀጣጣይ የሆኑና ስለታማ ወይም መነቃቀል የሚችሉ የቤት-ዕቃዎችንም አለመጠቀም በራስ ወይም በሌሎች ሰዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ይጠብቃል።

ግላዊነት እና ብቃት

ስለህክምና ተቋማት ስናስብ ሃሳባችን ከወንበርና ጠረጴዛ ያለፈ ሊሆን ይገባል። ግላዊነትንም ያካተተ የቤት-ዕቃ ሀኪሞችም ሆኑ ረዳቶቻቸው ስራቸውን ያለ መረበሽ እንዲከናውኑ ይረዳል። ለታካሚም ቢሆን ሀኪሙ ሙሉ ትኩረት እንደሰጠው ስለሚያስብ የእንክብካቤና የደህንነትስሜትን እንዲያገኝ ያደርጋል።

ለቤተሰብ መሰባሰብ

ሰዎች ወደ ህክምና ተቋማት በሚሄዱበት ጊዜ ለብቻቸው የመሄድ አዝማሚያቸው እጅግ አነስተኛ ነው። ስለዚህ ብዙ ወገን ያለውን ቤተሰብ ማስተናገድ የሚችል ውቅር ያለው የቤ-ዕቃን መጠቀም አስፈላጊ ነው።

Pin It on Pinterest

Share This