አዲስ ሶፋ መምረጥ ቀላል የሚባል ስራ አይደለም ፡፡ ምናልባት ቀድሞውኑ እርስዎ የሚወዱት ዘይቤ ይኖርዎታል ነገር ግን ከዚህ በፊት ሶፋ ገዝተው የማያውቁ ከሆነ ወይም መርጠው በገዟቸው ሶፋዎች የሚቆጩ ከሆነ በቀጣይ ለሚገዙት ሶፋ ይረዳዎታል ያልናቸውን መመርያዎች ከታች አቅርበናል ፡፡

አንድ ሶፋ በደንብ የተሰራው የሚያስብለው ምንድን ነው?

 አንድ ሶፋ ለመሥራት ብዙ ቁሳቁሶች ያስፈልጋሉ ከነዚህም ረጅም ዕድሜ በመቆየት ችሎታቸዉ አንዳንዶቹ ከሌሎቹ የተሻሉ ናቸው ። ምናልባት ወፈር ያለ ፍራሽ ያለው ሶፋ ጥሩ ሊመስል ይችላል ነገር ግን ይህ ብቻውን መለኪያው ሊሆን አይችልም።ከፍተኛ ጥራት ያለው ሶፋ የሚከተለው አወቃቀር ይኖረዋል ፡፡

የእንጨት ፍሬም

ይህ በጥሩ ሁኔታ ለተሰራ ሶፋ ቁልፉ ነገር ሲሆን  በጥንካሬው ላይ ተጽዕኖ ሊያሳርፉ የሚችሉ የተለያዩ ምክንያቶችም አሉ።ከእርጥበት ነፃ መሆኑን ያረጋግጡ፦ እርጥበት የሌለው ማለት የእርጥበቱ መጠን(Moisture Content) ከ 7% ያልበለጠ ማለት ሲሆን ለዚህም ደረቅ ያለ  እንጨት ተመራጭ ነው ምክንያቱም በአየር የደረቀ እንጨት የእርጥበት መጠኑ ከሰባት እስከ ስምንት በመቶ ሙሉ ለሙሉ እርጥብ ከሆነ እንጨት ስለሚቀንስ እንጨቱን ለመቀያየር እና ለማጣመም የበለጠ  ተስማሚ ስለሚያደርገው  አነስተኛ የእርጥበት መጠን ያለው የእንጨት አይነት  ለቤት ዕቃ መስርያነት ተመራጭ ነው፡፡

ጠንካራ እንጨት ይምረጡ

ጠንካራ እንጨት ወይም የኢንጂነሪንግ እንጨቶች ሁለቱም ጥሩ አማራጮች ሲሆኑ  ጠንካራ እንጨቶች  በጣም ቀላል እና ጠንካራ የሆነ  ሶፋ ለመስራት ያገለግላሉ ፡፡ ኢንጂነርድ የሆነ እንጨት ማለት አንድ ዛፍ ተወስዶ  ወደ ኢንጂነሪንግ ፓውንድነት የመለወጥ ሂደት ሲሆን  በርካታ ተረፈ ምርትን ከብክነትም ይታደጋል፡፡

ስለ ማገጣጠያው አይርሱ

አንድ ሶፋ  የሚጣመርበት(የሚጋጠምበት) የራሱ የሆነ መንገድ አለው ፡፡ እንጨቶች ብዙውን ጊዜ  የተስተካከሉ ፣ ደርዝ የወጣላቸው የተለጠፉ ሲሆኑ ተጨማሪ ጥንካሬን ለመስጠት  የማዕዘን ማጣበቅያን እንጠቀማለን። ፍሬሞች በሽቦዎች ተጣምረው በአንድ ላይ ይያያዛሉ ፤እነዚህ እንጨቶች በእንጨት ፍሬም ውስጥ በተጣመሩበት ግዜ ሙጫውን ለማቅለጥ በቂ ሙቀት እና ሰበቃን ስለሚፈጥሩ የተሻለ እና ጥንካሬ እንዲፈጠር ያግዛል። ፍሬሞቹ በሁሉም ማዕዘኖች የተያዙ እና ብሬሶቹም በእንጨቱ እርዝማኔ የተሰሩ መሆን አለባቸው። እንጨቶቹ ጥምረታቸው ጠንካራ በሆነ መጠን ሶፋዎ ረዘም ላለ ጊዜ ይቆያል ፡፡

የመዋቅር ስርአት

እያንዳንዱ ሶፋ የተዋቀረበት ስርዓት ሲኖረው ይህም ከሶፋ ጥራት እና ምቾት ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት አለው፡፡ የተለያዩ የመዋቅር ስርአቶች ሲኖሩ ከእነዚህ መካከል ባለ ስምንት እየተባለ የሚጠራው የመዋቅር አይነት ዋና ተጠቃሽ ነው፡፡ይህ የመዋቅር አይነት በብዙ መልኩ ከሌሎቹ የመዋቅር አይነቶች ተመራጭ ያደረገው የክብደቱን ስርጭት እኩል በእኩል በመካፈል ለሶፋው የተሻለ ጥንካሬ ማላበስ መቻሉ ሲሆን ይህም የሆነው ጠንካራ የብረት ሽቦዎች በሶፋው የእጨት ፍሬም ላይ በመታሰር ድጋፍ ስለሚሰጡ ነው፡፡

ምቹ ፍራሽ

 አንድ ሶፋ ትልቅ መሠረት እንዲኖረው ለማድረግ በጥሩ ሁኔታ የተሠራ ፍሬም ያስፈልገዋል ፣ ነገር ግን ሁሉንም ነገር ለማጠናቀቅ የሚያስችለውን ምቹ ፍራሽ ካላካተተ በሶፋው ለይ ማረፍ ምቾትን አይሰጥም፡፡ከቁሳዊ ነገሮች አንፃር በዳክሮን የተጠቀለሉ የፍራሽ ማቀፊያዎች በብዛት የሚገኙ ሲሆን ነገር ግን በጣም ምቹ አይደሉም ፡፡ በሌላ በኩል  በጣም ትልቅ እና ለስላሳ ፍራሽ መጠቀም  አስፈላጊ ሲሆን ነገር ግን ወደ ውስጥ  የመግባት እና የመጎድጎድ አዝማሚያ  ሊታይበት ስለሚችል  አንዳንድ ጊዜ ወደ ቀድሞ ቦታው ለመመለስ  አስቸጋሪ ይሆናል ፤ስለዚህ ጥራት ያላቸውን ምርቶች መምረጡ ላይ ጥንቃቄ መወሰድ ይኖርበታል፡፡በዚህም ረገድ  ለስላሳ እና  አነስተኛ እፍጋት ያላቸውን መጠቀሙ የሚመረጥ ሲሆን  የግል ምርጫችንን ስናስብ ጥራትም ከግምት ማስገባት ይኖርብናል።

ትክክለኛውን ሶፋ ለእርስዎ

ትክክለኛውን ሶፋ ስንገዛ ከተሰራበት ጥሬ እቃ ጎን ለጎን ከግምት ውስጥ መግባት ያለባቸው ሁለት  አንኳር  ነገሮች ሲኖሩ እነሱም የአኗኗር ዘይቤ እና  የቤት ስፋት  ናቸው ፡፡ የተሰራበት ሁኔታ  ስለተወደደ ብቻ አንድን ሶፋ መግዛት ተገቢ ስላልሆነ  ፤ ለመጠቀም ካሰቡት ጋር የሚመች እና በሚገባ ከቤትዎ ጋር የሚስማማ ምርት  ማግኘትዎን እርግጠኛ መሆን ይኖርቦታል፡፡

ለአኗኗር ዘይቤዎ የሚስማሙ ባህሪያትን ይምረጡ

ንድፍ አውጪው አሪል ኦኪን ሶፋ እንዴት መጠቀም እንዳለብዎት እርስዎን በመጠየቅ ይጀምራል ፡፡ “ለአዋቂዎች ክፍል ነው የፈለጉት ወይስ ልጆች የሚጫወቱበት የመጫወቻ ክፍል ውስጥ?”  መልሱ ሊገዙት በሚፈልጉት የሶፋ ዓይነት ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር በመጥቀስ ፡፡ ንድፍ አውጪው ሚካኤል ዌልቸር ደግሞ ‹ብዙ ሰዎች ሶፋ ሲገዙ ልጆቻቸውን እና የቤት እንስሳትን (ውሻ፣ድመት) ከግምት ውስጥ ያስገባሉ ነገር  ግን ሰዎች የሚዘነጉት ነገር ቢኖር የራሳቸውን ፍላጎት አለማወቅ ላይ ነው፡፡ “በሶፋዎ ላይ መተኛት የሚወዱ ሰው ከሆኑ ምናልባት ከማንኛውም ፍራሽ በተሻለ የ ላባ ሶፋ ይሻልዎታል ለምን ቢሉ ሌላ ቢመርጡ በዚያ ሶፋ ላይ ያለማቋረጥ የሚተኙ ከሆነ እነዚያ ፍራሾች ቶሎ የማለቅ እድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡ እንዲሁም ምን ዓይነት ጨርቅ መጠቀም እንደተፈለገም  ማሰብ ተገቢ ነው፡፡ “እርጥበትን እና ዘይታማ ነገሮችን  የማይመጥ እና ቆሻሻ እና አቧራ አጉልቶ የማያሳይ ጠቆር ያለ መምረጡን አንዳንዶች የሚመክሩ ሲሆን ይህ ግን በግል ውሳኔ ላይ የሚመረኮዝ ሲሆን ከሚጠቀምበት ሰው ብዛት አንፃርም ነገሮችን ቃኝቶ የትኛውን እንደሚመርጡ ገዢዎች ማሰብ አለባቸው፡፡

 ወደ ምቾት ስንመጣ ስታይል(ዘይቤ) ጥሬ እቃን ለመምረጥ አንድ ቋሚ መስፈርት ሲሆን  ሶፋዎች በጠባብ መቀመጫ ወይም በተነጠፈ ወንበር (ሰፊ መቀመጫ) ሊሰሩ ይችላሉ ፡፡

ጠባብ ወንበር

ወንበሩ እንደ አንድ ረዥም ትራስ ከሆነ ያ ሶፋ ጠባብ መቀመጫ (bench seat) ይባላል ፡፡ እነዚህ ሶፋዎች እንደ ጠረጴዛዎች ሁሉ  ለመመገቢያነት ጥሩ አማራጭ ናቸው፡፡ ጠባብ መቀመጫዎች እንዲሁ ለመዝናኛ እና ለመወያየት ተመራጭ ሲሆኑ  የበለጠ ቀጥ ተብሎ ለመቀመጥም ያመቻሉ  ፡፡ ዊሊያምስ የተባለ ዲዛይነር ጠንከር ያሉ መቀመጫዎች በጣም ጥሩ አማራጮች መሆናቸውን አፅንኦት የሚሰጥበት ሲሆን  ሽሚዝ የሚባል ባለሙያ ደግሞ እንደዚህ የመሰሉ የወንበር መቀመጫዎች ለዓይን ደስ የሚያሰኙ ቢሆኑም ሰፋፊ በሆነ የጨርቅ ርዝመት ምክንያት የበለጠ ለመጨማደድ እንደሚጋለጡ አስፍሯል ፡፡

ጨርቅ

 የቤት እንስሳት እና ልጆች ከሌሉዎት በእውነቱ በሚመርጡት ጨርቅ ሶፋ ሊኖርዎት ይችላል ፡፡ ነገር ግን  ሶፋዎ ለረዥም አመታት በጥሩ ሁኔታ እንዲቆይ ከፈለጉ ለማፅዳት ቀላል፣ቀለማቸዉም ቶሎ የማይለቁ እና ጠንካራ ጨርቆች መጠቀሙ ይመረጣል፡፡በአሁን ግዜ  “performance fabric” የሚባሉ ጨርቆችን መጠቀሙ ይመከራል ምክንያቱም እነዚህ ጨርቆች  በዘላቂነት ለብዙ ጊዜ መቆየት ስለሚችሉ ነው፡፡ ግራጫ ፣ ክሬም ወይም ነጭ ሶፋ የሚጠቀሙ ሰዎች ይህንን የጨርቅ አይነት ቢጠቀሙ መልካም ነው፡፡በተጨማሪም በቀላሉ ሊታጠቡ የሚችሉ ወጪ እና ገቢ የሆኑ ጨርቆችም ስላሉ እነሱንም ማሰቡ ተገቢ ነው፡፡

ሌዘር

ለማጽዳት ቀላል የሆነ ሶፋ ከፈለጉ ሌዘርን ይምረጡ ምክንያቱም በቀላሉ በመጥረግ ብቻ ሊፀዱ ስለሚችሉ ልጆች እና የቤት እንስሳት ላላቸው ጥሩ ምርጫ ናቸው ፡፡

ዘይቤ(style)

የመረጡት የሶፋ ዘይቤ ከሶፋው እድሜ ጋር ተያያዥነት ላይኖረው ይችላል ነገር ግን  ብዙዎች ለብዙ ዓመታት እንደወደዱት የሚዘልቅ  ምርት ይፈልጋሉ፡፡በተጨማሪም በየጊዜው የመቀየር አቅሙ ለማይኖራቸው ከቤታቸው የቀለማት ውህደት ጋር ሊሄድ የሚችል የሶፋ ምርትን ቢጠቀሙ ተመራጭ ይሆናል፡፡

ትክክለኛ ልኬት ይውሰዱ

በዓለም ውስጥ በጣም የሚያምር ፣ ምቹ  እና በጥሩ ሁኔታ የተሠራ ሶፋ ማግኘት ይችሉ ይሆናል ነገር ግን ከቤትዎ ነባራዊ ሁኔታ ጋር የማይሄድ ከሆነ አስፈላጊነቱ እንብዛም ነው፡፡ባህላዊም ሆነ ዘመናዊ  የሶፋ ምርት ካስፈለጎት  የሶፋው ርዝመት፣ ስፋት፣ ቁመት፣ የሶፋው ሰያፍ መለኪያዎች፣ የሶፋው የጀርባው አንግል፣ የእግሮቹ ርዝመት የቤቶን ስፋት ያማከለ መሆን አለበት፡፡

Pin It on Pinterest

Share This