የንድፍ መርሆዎች መደበኛውን አሳብ የሚገልፁ መስፈርቶችን ይሰጣሉ። የወንበር ወይም የጠረጴዛ ዓላማ ለማሟላት በታሰበው ፍላጎት መጠን መነሻው ሲወሰን በብዙ ሂደቶች ውስጥም ይበለፅጋል። በዚህ ሂደት ውስጥ የቤት-ዕቃ ሞዴል አውጪዎች ዐይን እና እጅን አስተሳስሮ ማሰራትን የሚጠይቁ ውስብስብ የሃሳብ እና ድርጊት ስርአት ያጋጥማቸዋል። በዚህ ምዕራፍ የተሸፈኑ የንድፍ መርሆዎች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል።

 • የመዋቅር ሚዛን
 • የዕይታ ሚዛን
 • ቀጣይነት፣አንድነት እና ልዩነት
 • ተዋረድ እና አፅንዖት
 • የተለያየ ይዘት ያላቸውን ጎን ለጎን ማስቀመጥ
 • ምት(ሪትም)
 • ሚዛን እና መመጣጠን

የመዋቅር ሚዛን

የመዋቅር ሚዛን በቤትዕቃዎች ውስጥ ያሉ ኃይሎች ሚዛናዊነታቸውን የጠበቁ መሆን እንዳለባቸው ያመለከታል።ኃይሎች በእኩልነት በማይኖሩበት ጊዜ መደርደሪዎች ሊረግቡ፣የቤት-ዕቃዎች ከቦታቸው ሊነሱ (ሊንጠለጠሉ) ይችላሉ። የቤት-ዕቃዎች ከጎን የሚመጡ፣የሚቀረጥፉ(ትይዩ እና በተቃራኒ አቅጣጫ የሚገፉ ኃይሎችን) እና ዙሪት (መጋጠሚያዎች ላይ የሚያርፉ ሽክርክሪታዊ ግፊቶችን) መቋቋም መቻል አለባቸው።የመዋቅር ኃይሎች የንድፍ ሀሳቦችን ያነሳሳሉ፤እናም በመመስረት ፅንሰ-ሀሳብ ውስጥ ከግምት ውስጥ መግባት ያለባቸው እና እጅግም አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች  ናቸው፡፡ 3/32ኢንች(2.4ሚሜ) ውፍረት ያላቸው የሜፕል ኮምፐንሳቶ ሽፋን በመጠቀም ተገጣጥመው እና በተለያዩ መንገዶች ተቀናበረው የተሰሩት የፍራንክ ኦ.ጌሪ ባለ ጎባጣ እንጨት ወንበሮች በመዋቅራዊ አንፃር ጥሩ ምሳሌ የሚሆኑ   እና በቁሳቁስ ምርመራ የተገኙ ናቸው።

የሚወዛወዙ ወንበሮች በተጠቃሚው ክብደት፣እንቅስቃሴ፣በወንበሩ አይነት፣ በተጠቃሚውና በወንበሩ የመሬት-ስበት ማዕከል በመጠቀም ስራቸውን ያከናውናሉ። ለተጠቃሚውም ወደ ፊት አና ወደ ኃላ እንቅስቃሴ የመቆጣጠር እድል ይሰጣሉ።  በተደጋጋሚ ወደ ኋላ እና ወደፊት መመላለስ ጉልህ ተለዋዋጭ ኃይሎችን ይፈጥራል፤በሚወዛወዘው ወንበር መሰረት እና መገጣጠሚያ ላይም ክብደተ ያለው ግፊት ይፈጥራል። በሚካኤል ቶኔት የተሰራው ዓይነተኛ ባለ ጎባጣ አንጨት ተወዛዋዥ ወንበር ግቡ በተወዛዋዥ ወንበሩ እና በተጠቃሚው መካከል ባለው የመተባበር መስተጋብር አማካኝነት የሚዋልል (ፈሰስ የሚል)እና ሚዛኑን የጠበቀ የሚወዛወዝ እንቅስቃሴ ማግኘት ነው።

የቤትዕቃዎች በማያስተማምን ሁኔታ ረዥም እና ጠባብ በሆኑባቸው ወይም የመሬት-ስበት ማዕከሉ ከጫፍ ነጥቡ ባሻገር በሚውልበት ጊዜ፤የመዋቅር መረጋጋትን ለመጠበቅ ሲባል የቤት እቃዎችን ከወለሉ፣ ግድግዳ ላይ ወይም ከጣሪያ ጋር ማያያዝ አስፈላጊ ይሆናል።እነዚህ መለመጥ እና የሚዛን መዛባት ከመከሰቱ በፊት የመደርደሪያ የአግድም-ስፋት መስፈሪያ ነጥቦች ላይ መጠበቅ ያለባቸው ልኬቶች ናቸው። የመደርደሪያ ስርዓቶች፣ የአልጋ ክፈፎች፣ የሙዚቃ መሳሪያ ማቆሚያዎች፣ የግድግዳ ሰዓቶች፣ የቁም-ሳጥን በሮች እና ለተለያዩ ግልጋሎት የሚውሉ መድረኮች በሙሉ የመዋቅር ሚዛን ለመጠበቅ እና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ይሠሩ ዘንድ በመሰረታዊ የምህንድስና መርሆዎች ላይ ይወሰናሉ።

አንድ ሰው ወንበር ላይ በሚቀመጥበት ጊዜ የመዞሪያ ቦታ በቀጥታ ከወንበሩ እና ከሚቀመጠው ሰው የጋራ የመሬት-ስበት ማዕከል ስር መሆን አለበት፡፡የሚዛናዊነት መርህ ማንኛውንም የሰው አካል ድጋፍ በመንደፍ ውስጥ መታሰብ እና መከናወን ያለበት ነው።

የእይታ ሚዛን

የእይታ ሚዛን የቦታን ክብደት የተመጣጠነ ወይም ያልተመጣጠነ ስብጥር የሚገልፅ ሲሆን ሚዛናዊነት በአንድ ወይም በብዙ የጋራ የተመጣጠነ-ጥበብ፣ በአንድ ምህዋር ላይ ይንፀባረቃል።ከ1890 እስከ መጀመሪያው የዓለም ጦርነት  የነበረው መሳሪያ የጋራ ሚዛናዊነት ያለውና ለቋሚ ዘንጎች አፅንኦት የሚሰጥ በመሆኑ ወደ ላይኛው ጫፍ ጥሩ እይታን ሰጥቷል። የእይታ ሚዛን ሙሉበሙሉ በመመጣጠን ላይ የሚመረኮዝ ባይሆንም ረቂቅ ክብ የቤትእቃዎች በአብዛኛው ከ1930ዎቹ ጀምሮ በደስቲጅል ዕቃዎች፣በጌሪትሪት ቬልድ ቴዎቫን ኢስበርግ ሚዛን የሚገለፁ እየሆኑ የመጡ ሲሆን የተመጣጠኑ ግን አልነበሩም፡፡ ምንም እንኳን ያልተመጣጠነ ሚዛን ማንፀባረቅ ባይችልም ተለዋዋጭነት እና እኩልነት በአንድ ዘንግ በኩል የመታየት እድሉ ከፍለኛ ነው።

የጄሪት ሪትቬልድ የበርሊን ወንበር (1923) እና የቻርለስ እና ሬይ ኤሜስ በፋይበር ግላስ የተጠናከረ ፕላስቲክ ኢሜስ ቻይስ (1948) በእይታ ሚዛናዊ ሲሆን በእንፃሩ ተመጣጣኝ ያልሆነ ስብጥር የሚጠቀም ነበረ።

ቀጣይነት፣አንድነት እና ልዩነት

ስዊድን ስቶክሆልም በሚገኘው ጉናር አስፕልንድ ቤተ-ክርስትያን ዉድላንድ መካነመቃብር ግድግዳ ላይ የተገጠመው ከእንጨት የተሰራው ክፍልፋይ ሳይንሳዊ ገፅታ ያለው፣እንደ አግዳሚ ወንበር ሆኖ የሚያገለግልም ሲሆን ቀጣይነት፣አንድነት እና ልዩነትን ከመግለፅም ባሻገር ክፍልፋዮቹ እኩል በእኩል የተስተካከለ (የሚያጣምር) የከፍታ ማጣቀሻ ናቸው፡፡ ሳይንሳዊ ገፅታ ያለው አግዳሚ ወንበር አራት ማዕዘን ቅርፅ ላላቸው አካላት እና የጠፍጣፋ ዝርግ ወለል ልዩ ልዩ አይነቶች ጥሩ ምሳሌ መሆን የሚችል ሲሆን የታሸገ የተጣበቀ ስስ አንጨት፣ ያልተቋረጠ ጠፍጣፋ ዝርግ ወለል የገፅ ለውጥ እና ቀጣይነትም ማሳይ በመሆን ያገለግላሉ። የግድግዳ እና የቤት-ዕቃዎች ውህደት በውስጥ ቁሳቁስ ስሪት እና ቀጣይነት ላይ ለንድፉ ውበትን ከመስጠት ባሻገር ቀጣይነት ላይ የራሱን አሻራ በማሻረፍ መሰረታዊ መርሆዎችን ያጎላሉ።

የቋሚ ድጋፎች መደበኛነት በቻርልስ እና ሬይ ሲገለፅ ድጋፎቹ እንደገና ሊደገም የማይችል የንድፍ አይነት የሚያቋቁሙ ናቸው፡፡የሙጫማነት ባህርይ ያላቸው የግድግዳ ላይ ማስዋቢያዎች በሚኖራቸው የተሰባጠረ የቀለም አይነት ለንድፉ ውበት የሚሰጡት ሲሆን በተነጣጠሉ አካላት መካከል ባለው የጂኦሜትሪክ ቅደም ተከተል ተለዋዋጭ መስተጋብርም ይፈጥራሉ፡፡

ደረጃ አሰጣጥ እና አፅንዖት

(ደረጃ አሰጣጥ እና አፅንዖት ማለት ነገሮችን በአመክሮ ተመልክቶ ቅድሚያ ለሚሰጠው እንደ ሁኔታው ቅድሚያ መስጠት ማለት ነው።)ይህም በውስጥ ሊሰጠው የሚገባውን ቅድሚያ ይመለከታል።) አፅንዖት በዋናነት የአካባቢን ቀለም፣መጠን፣ልስላሴ፣ ሻካራነቱን እና የቅርፅ ወጥነት  መኖርና አለመኖሩን ያመለክታል፡፡በሌላ በኩል ደረጃ አሰጣጥ የቁሳቁሱን ይዘት፣ ቀለም እንዲሁም የአንደኛ፣ሁለተኛ እና የሦስተኛ ደረጃ አስፈላጊነት ላይ አፅንዖት መስጠት ይችላል።መደበኛ ተዋረድ የተቀመጠውን ሰው ማህበራዊ ደረጃ ሊያጠናክር ይችላል ለምሳሌ የአንድ ረዥም አራት ማዕዘን ቅርፅ ያለው የስብሰባ ጠረጴዛ ማህበራዊ ተዋረድን የሚጠቁሙ የመገለጫ ልዩነቶች አሏቸው።

የተለያየ ይዘት ያላቸውን ጎን ለጎን ማስቀመጥ

የተለያየ ይዘት ያላቸውን ጎን ለጎን ማስቀመጥ በመሰረቱ በስምምነት የሚኖሩትን የሚያቀርብ፣ሁለት  የተለያዩ ነገሮች በአንድ ላይ ተቀምጠው እንዲታዩ ወይም እንዲቀመጡ፤በሌላ መልክ የሚያኖር፣አጠቃቀሙም በተገቢው መንገድ ከሆነ ውጤቱ መልካም ስሜትን የሚቀሰቅስ ነው። ይህ መርህ በአንድ ዘመን የነበረ የቤት-ዕቃ ሌላ ዘመን ላይ በታነፀ ህንፃ ውስጥ ጥቅም ላይ ሲውል አስፈላጊነቱ ጉልህ ሆኖ እንዲታይ ያደርገዋል። የጥንት ቁም-ሳጥን፣አልጋ፣በፈረስ የሚጎተት ሰረገላ ሙሉበሙሉ ከኮንክሪት በታነፀና ዘመናዊ የህንፃ ጥበብ ካረፈበት ግንባታ ጋር በአንድ ላይ ሲታይ አስደሳች ዕይታ እንደሚፈጥር ምንም ጥርጥር የለውም። ዘመናዊ ጥበብን ባህላዊ ከሆነ ቤት ጋር በአንድ ላይ ማስቀመጥ ደግሞ የተገላቢጦሽ ውጤት ይሰጣል። እውነቱ፤የተለያየ መልክ እና ይዘት ያላቸው ዕቃዎች ጥራት ባለው ንድፍ ላይ ጥቅም ላይ መዋል የሚቸሉ ስለሆነ የጥንቱን ከአዲሱ ጋር የመጠቀም ፍላጎት ካለ ያለ ጥርጣሬ ወደ ፊት መሄድ ይቻላል። በዚህ አንድነትና ልዩነትን አጣምሮ በያዘ መልኩ ዘይቤዎችን ቀላቅሎ በመጠቀም ሂደት ውስጥ የሳሳ ሳይሆን ጥብቅ የሆነ የፍላጎት ልዩነት ያስፈልጋል። ልዩነት ያለው ንድፍ ሲዘጋጅ ከግምት ውሰጥ መግባት ያለባቸው ጥንቃቄዎች አሉ። ሁለቱ ዘይቤዎች በተለያየ መንገድ ድንቅ ሊሆኑ ከተፈለገ ቀለም እና ስሪታቸው እርስበርሱ ሊደጋገፍ ግድ ይላል፤ምክንያቱም የቀለም ፅንሰሀሳብ እና ግልፅ ንድፍ ሁለት የተፈጥሮ ልዩነት ያላቸውን ዘይቤዎችን ማጣመር ስለሚችል ነው።

ግሩም ጌጦችን ለመደባለቅ የሚሆኑ መሰረታዊ ሃሳቦች፡-

 • የተለያየ ቅርፅ፣መጠንና አጨራረስ ለስፍራው ግሩም መለያ የሚሰጥ እና እይታን የሚስብ ነው
 • ዘመናዊ ወንበሮችን ከጥንታዊ ጠረጴዛ ጋር አጣምሮ መጠቀም
 • እንጨትና አሉሚኒየምን በዘመናዊ ጌጣጌጥ ማስጌጥ
 • የጥንት ጠረጴዛን ተስተካክሎ በተነጠፈ ዘመናዊ ብረት መለበጥን እንደ አማራጭ መጠቀም
 • ዘመናዊ በሆነ መንገድ የተቀረፁ ነጭ የፕላስቲክ  ወንበሮችና የጥንት ምንጣፎችን አደባልቆ መጠቀም
 • ዘመናዊ ማብሰያ-ቤትን ጥንታዊት ገፅታን ማላበስ
 • ጥንታዊ ቡፌዎችን ከመካከለኛው ክፍለዘመን የቤት-ዕቃዎች ጋር አጣምሮ መጠቀም
 • የእስያ የቤት-ዕቃዎችን ከዘመናዊ የቤት-ዕቃዎች ጋር አጣምሮ መጠቀም 

ሪትም

ምት (ሪትም) የሚለው ቃል የመጣው ከግሪክ ሩዝ-ሞስ ሲሆን ትርጉሙም “መፍሰስ” ነው፡፡ ዳንስ፣ግጥም እና የዲዛይን ምት የሙዚቃ መሠረት ነው፣፡፡ ምት በቦታ ወይም በጊዜ ውስጥ ያሉ ንጥረነገሮች አወቃቀር እና ቅደምተከተል  የሚያሳይ ነው። የፈጠራ ስዕል ውስጥ አግድም እና ቀጥ ያለ አደራደርን ይገልጻል። እርስ በእርስ የሚዛመዱ ንዑስ ክፍሎች የሚፈጥሩት መመሳሰል እና ልዩነት እንዲሁ የሪትም መገለጫ ሲሆን እንደመወለድ እና ሞት ያሉት የሰው ልጅ ህይወታዊ ኡደቶችም የዚህ ሌላ አካል ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡

ሚዛን እና መመጣጠን

ሚዛን የእቃው መጠን ሊቀመጥበት ከታሰበው የቦታመጠን ጋር የሚዛመድ ሲሆን መመጣጠን ደግሞ ዕቃው የተሰራባቸው ተናጠል አካላት ከሙሉ ዕቃው ጋር ያላቸውን ንፅፅር ያመለክታል። ላለው ሰፊ ቦታ፣ንድፍ አውጪው ልኬቱን በአእምሮው ይዞ እስከ ቤት-መጠን ወሰኑ ድረስ የቤትዕቃዎች ሚዛንን መጠበቅ ይኖርበታል፡፡

የአንድ ክፍል ምጣኔ የሚወሰነው በፍላጎት ብቻ አይደለም።የካሬው ስፋት በጣሪያው ቁመት፣ በመስኮት መጠን እና የከፍታ ቁመት እንዲሁም በማንኛውም ክፍት ቦታዎች ይዞታ የሚወሰን ነው፡፡ የክፍሉ የውበት ፍሰት እንዲሁም ሚዛን የሚመጋገብ በመሆኑ እያንዳንዱ ክፍል ላይ ሊኖር የሚገባው የቤት እቃ አይነትና ጥራት ከግምት መግባት አለበት ለምሳሌ የእሳት ምድጃ ያለው አንድ ክፍል ሌሎች ክፍሎች ሊኖሯቸው ከሚገባው ትኩረት አንፃር የተለየ ምጣኔ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን ይህንንም ለመወሰን የሚረዳ ግልጽ የትኩረት ነጥብ መኖር አለበት።የአንድን ክፍል ዓላማ በተገቢው መንገድ ለመጠቀም የቤትዕቃዎቹን ቁልፍ ተግባር ማወቅ የሚያስፈልግ ሲሆን የግድግዳዎቹን ቁመት እና ስፋት መለካት የቤትእቃዎችን የቤት እቃዎችን በአግባቡ ለመጠቀም መነሻ ነጥብ ሊሆን ይገባል፤በተጨማሪም የክፍሉን ዙሪያ እና የግድግዳዎቹን ርዝመት መለካት፣ከተቻለ አንድ የወለል ፕላን ንድፍን ማጠቀም ጥሩ ውጤትን ይሰጣል። 

Pin It on Pinterest

Share This