ከመሠረታዊ የቤት ዕቃዎች አንዱ የሆነው ወንበር ለመቀመጫነት የምንመርጠው የቤት እቃችን ነው፡፡የወንበር ዋና ዋና ገጽታዎች ሁለት  ክፍሎች  ናቸው፤ጀርባ እና መቀመጫ፤ ሁለቱም በ 900 ወይም በትንሹ ከፍ ባለ አንግል እርስ በርሳቸው የተያያዙ ሲሆኑ ብዙውን ጊዜ አግድም መቀመጫው አራት ማዕዘኖች በተራ አራት እግሮች ወይም ከሶስት እግሮች ጋር ተያይዞ ወይም ባለ አራት ክንድ መዞሪያዎች በሚዞሩበት ዘንግ ላይ ተጣብቆ መቀመጫው ላይ የተቀመጠ ሰው ክብደትን ለመደገፍ ጠንካራ ሆኖ ይሰራል ፡፡ የወንበር እግሮች በተለምዶ ለተቀመጠው ሰው ጭኖች እና ጉልበቶች 90 ° ወይም ከዚያ በታች የሆነ አንግል ለመፍጠር በቂ ናቸው ፡፡በቤት ውስጥ ባሉ በርካታ ክፍሎች ውስጥ (ለምሳሌ በመኝታ ክፍሎች ፣ በመመገቢያ ክፍሎች እና በመኝታ ክፍሎች ውስጥ) ፣ በትምህርት ቤቶች እና በቢሮዎች(ከጠረጴዛዎች ጋር) እንዲሁም በተለያዩ ሌሎች የስራ ቦታዎች ወንበሮች ከእንጨት ፣ ከብረት ወይም ከሰው ሰራሽ ቁሳቁሶች ተሰርተው እና መቀመጫቸው ብቻውን ወይም መላው ወንበሩ በተለያዩ ቀለሞች እና ጨርቆች  ተሸፍኖ ይቀመጣል።

ከ 20 ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የወንበር ቴክኖሎጂ በጣም እያደገ እንደ ብረት ማጠፊያ ወንበሮች ፣ የብረት እግር ወንበሮች ፣ ተንሸራታች ወንበሮች ፣ የተለያየ ቅርፅ ያላቸው የፕላስቲክ ወንበሮች እና ኢርጎኖሚክስ ወንበሮች የመሳሰሉ የወንበሮች አይነቶችን አካቶ  እና ጠቃሚነቱን ጨምሮ ብቅ ያለ ሲሆን በይበልጥም ከ ራዲዮ እና ቴሌቪዥን መስፋፋት ጋር ተያይዞ የወንበር ተወዳጅነት እና ተፈላጊነት ጨምሯል።

የ 1960ዎቹ ዘመናዊ እንቅስቃሴ ደግሞ ይበልጥ አዳዲስ ወንበሮች እንዲፈለሰፉ ያደረገ ሲሆን ለምሳሌ ያህል“ የቢራቢሮ ወንበር ” (የሃርድዮ ወንበር ተብሎ ይጠራ የነበረ) እና  የእንቁላል ቅርፅ ያለው የፖድ ወንበሮች ተጠቃሽ ሲሆኑ እ.ኤ.አ. በ 1966 ደግሞ የፕላስቲክ ወንበሮች በስፋት ተመርተዋል፤ቆየት ብሎም የፓምፕ እና ከቆዳ ወይም ፖሊመሮች የተሠሩ ወንበሮች የተከተሉ ሲሆን ወንበሩ ውስጥ የተካተተ ሜካኒካል ቴክኖሎጂ ለእንቅስቃሴ ምቹ የሆኑ ወንበሮችን በይበልጥም ለቢሮ አገልግሎት እንዲውል አስችሏል ፡፡

ጥንታዊ ተወዳጅወንበሮች

ጥንታዊ እቃዎችን ለመጠቀም ስናስብ ሁሌም ከዘመኑ ጋር ይሄዳሉ ወይ ብለን እንጠይቃለን ፡፡ ለዘመናዊ የቤት ዕቃዎች ዲዛይን መነሻ የሆኑ እና ከመጀመሪያው ፅንሰ ሀሳባቸው ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በተወዳጅነት እና ጊዜ በማይሽረው ዲዛይን ዘመን ሳይሽራቸው ተወዳጅ ሆነው የዘለቁ የመካከለኛው ምዕተ-ዓመት ስራዎች አሉ ፡፡ እነዚህ በነ ጆርጅ ኔልሰን ፣ ኤድዋርድ ወርምሌይ ፣ ኢሮ ሳሪንየን ፣ ሃሪ በርቶያ ፣ ቻርለስ ኤሜስ እና ጄንስ ሪሶም በ 1961 እ.ኤ.አ. በ “Playboy” መጽሔት ላይ ተለይተው የቀረቡት  ጥንታዊ ዲዛይን ወንበሮች አንድ ተራ ክፍልን ወደ አስደናቂ  ነገር ለመለወጥ ግሩም የሆነ ቅንብር ነበራቸው ፤ሆኖም ከእነዚህ ውስጥ የትኛው ለተወሰነ ቦታ ጥሩ እንደሚሆን መወሰን ትንሽ ግራ ሚያጋባ ሊሆን ይችላል ፡፡ በዚህ ላይ እርስዎን ለማገዝ እነዚህን ወንበሮች በተለያዩ ዘመናዊ መንገድ ለመጠቀም  ሀሳቦችን የሚሰጥ መመሪያ አዘጋጅተናል ፤በተጨማሪም የእያንዳንዱ ወንበር ታሪክ አጭር ማጠቃለያዎች ተካተዋል።

የእንቁላል ወንበር

ታሪክ- በአርኔ ጃኮብሰን የተነደፈው ጥንታዊው የእንቁላል ወንበር በ 1958 በጀርመን ለሚገኘው የራዲሰን ብሉ ሮያል ሆቴል ውስጣዊ ዲዛይን የተሠራ ነበር ፡፡

የእንቁላል ወንበር ጥቅም፦ ይህ ወንበር እንደ ሰገነት ወይም ቤተ-መጽሐፍት ባሉ ከፍ ያሉ እና ትልቅ ጣርያ ባላቸው ዘመናዊ ቦታዎች ላይ በጥሩ ሁኔታ ያገለግላል፡፡የእንቁላል ወንበር ዋጋ በእውቅ ዲዛይነር ከተሰራ እስከ 5500 ዶላር ያህል የሚያወጣ ሲሆን ትክክለኛ ጥራት ያላቸው ቅጂዎች ወደ 850 ዶላር ያህል ያስወጣሉ ።

የስዋን ወንበር

 ታሪክ: ስዋን ወንበር ከእንቁላል ወንበር ጋር በትንሹ ተመሳሳይ  ሲሆን በተመሳሳይ ጊዜ ለዚሁ ሆቴል ኮሚሽን በ 1958 የተሰራ ነው። ስዋን ወንበር እንከን-አልባ በሆነ ጠመዝማዛ  ቅርፁ በጊዜው በጣም ተጽዕኖ ያሳደረ ሲሆን ይህ የአሰራር ዘይቤ እስከ ዛሬ ድረስም ተወዳጅ ሆኗል ፡፡

 የስዋን ወንበር ጥቅም፦ደማቅ ቀለም ያለው የስዋን ወንበር ሰፋ ያሉ ክንዶች እና ዝቅ ያለ ጀርባ ያለው ሲሆን ልክ እንደ ላውንጅ ወንበር ሆኖ ይቀመጣል ፡፡ የስዋን ወንበር በዲዛይነር አንቱ በተባሉ ባለሙያዎች ከተሰራ 3100 ዶላር የሚያስወጣ ሲሆን የትክክለኛ የጥራት ቅጂዎች ዋጋ ወደ 280 ዶላር ያህል ነው።

የአልማዝ ወንበር

  ታሪክ: – በ 1950 ዎቹ የተሠራው አልማዝ ወንበር በዲዛይነር ሃሪ በርቶያ ብረትን በመበየድ እና የተለያዩ ቅርጾችን በማያያዝ በብልህነት የተሰራ ምርት ነው።

የአልማዝ ወንበር ጥቅም፦ የአልማዝ ወንበር ክብደት የሌለው እና ጠንካራ ሲሆን ከጥንታዊ ቤቶች እና ከለምለም የአትክልት ግቢ ጀምሮ  እስከ ትንሹ የንባብ ጎጆ በማንኛውንም ቦታ ቢቀመጥ የተለየ ዉበት ያለው ወንበር ነው ፡፡ የአልማዝ ወንበር 970 ዶላር ያህል የሚያስወጣ ሲሆን ትክክለኛ ጥራት ያላቸው ቅጂዎች ዋጋ ወደ 160 ዶላር ይደርሳል።

ላውንጅ ወንበር

 ታሪክ: – በቻርልስ እና በራይ ኢሜስ የተነደፈው ላውንጅ ወንበር የዚህ የመካከለኛው ምዕተ-ዓመት ዘመናዊ ወንበሮች ዉበት ግሩም ማሳያ ነው ፡፡ በ 1956 በተጣራ  ጣውላ  እና በቆዳ  ተገንብቶ የነበረ ሲሆን አሁን ግን  በመረጡት ቀለም ፣ የቆዳ ደረጃ እና የመሠረት ስታይል ሊያሰሩት ይችላሉ።

የላውንጅ ወንበር ጥቅም ፦ይህ ወንበር በተለምዶ ከኦቶማኖች  ጋር የተቆራኘ ሲሆን እጅግ በጣም የሚያምር የሳሎን ምንጣፍ ላይ ሲታይ ድንቅ ነው ፡፡ ላውንጅ ወንበር 3900 ዶላር የሚገመት ሲሆን ትክክለኛ ጥራት ያላቸው ቅጂዎች ዋጋም  ወደ 650 ዶላር ይደርሳል።

ኢይፍልቤዝ ሼል ወንበር  

ታሪክ: – የኢፍል ቤዝ ሼል ወንበር የኢፍል ታወርን የሚያንፀባርቁ መሰረታዊ እግሮች እና መቀመጫው የኤሊ ሼል በሚመስል መልኩ የተሰራ ነው። እ.ኤ.አ. በ 1948 በቻርልስ እና በሬ ኢሜስ የተቀየሰ ቀላል የጎን ወንበር ከጅምሩ ጀምሮ ተወዳጅ እየሆነ የመጣ እና ዛሬ በቀላሉ እንደ የጎን ወንበር የምንጠቀምበት ቀላል የጎን ወንበር ነው ፡፡

አይፍል ሼል ወንበር ጥቅም፦ይህ ክላሲክ ወንበር በመመገቢያ ክፍል ውስጥ ሊቀመጥ የሚችል እና ለክፍሉም ልዩ ውበት ሊያጎናፅፈው የሚያስችል አቅም አለው፡፡የአይፍል ሼል ወንበር ዋጋ ወደ 250 ዶላር የሚደርስ ሲሆን ትክክለኛ ጥራት ያላቸው ቅጂዎች ዋጋም ወደ 45 ዶላር ያህል ነው ፡፡

ላቻይስ ወንበር

ታሪክ: – በ 1948 እ.ኤ.አ በኤኤምስ የተነደፈው ላ ቻይስ ወንበር ለዝቅተኛ ወጭ የቤት ዕቃዎች ዲዛይን ወደ ዘመናዊ የሥነ ጥበብ ዓለም አቀፍ ውድድር ውስጥ ገባ ፡፡ የሰውን ቅርፅ ለማቀፍ ታስቦ የተሰራው ይህ ወንበር ከፋይበር ግላስ ተመሳስሎ መቀረጹ የእድገቱ ምስጢር ነው ፡፡

የላ ቻይስ ወንበር ጥቅም: -ይህ ተወዳጅ እና አስገራሚ የ ወንበር አይነት በየትኛዉም የ ቤታችን ክፍል ቢቀመጥ ዉበት በመፍጠር ረገድ አይጠረጠርም። ላ ቻይስ ወንበር ወደ 9,500 ዶላር የሚገመት ሲሆን ትክክለኛ ጥራት ያላቸው ቅጂዎች ዋጋም ወደ 800 ዶላር ይደርሳል ።

ሼልሮከር ወንበር

 ታሪክ፡- የ ፋይበር ግላስ ሮከር እጅግ በጣም ምቹ በሆነ ቅርፅ እና ውበት ባለው  አሠራር ውብ ሆኖ የተሰራ ሲሆን ወንበሮቹ  እ.ኤ.አ. በ 1948 ለመጀመርያ ግዜ ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ አሁንም ቢሆን ከዘመናዊ የሕፃናት ክፍል እስከ አንጋፋው ሳሎን ድረስ  በሚያምር ሁኔታ የሚያገለግሉ ጊዜ የማይሽራቸው ወንበሮች ናቸው ፡፡ የሼል ሮከር ወንበር ዋጋ 500 ዶላር ሲሆን ትክክለኛ ጥራት ያላቸው ቅጂዎች ወደ 54 ዶላር ያህል ዋጋ ተቆርጦላቸዋል ።

የኳስ ወንበር

ታሪክ፡-ይህ ዘመናዊ የኳስ ወንበር ወይም የግሎብ ወንበር ተብሎ የሚጠራው የወንበር አይነት እ.ኤ.አ. በ 1963 የተነደፈ ሲሆን ያሁኖቹን ዲዛይኖች የሚያስንቅ ወንበር ነው። አዲስ የፋይበርግላስ መቀመጫን የጀመረው ኢዮአርናርዮ በዘመኑ እጅግ ያልተለመደ ወንበር በማስተዋወቅ ከሱ በኋላ ለመጡትም ምሳሌ የሆነ ነው ፡፡ በመጀመሪያ ወንበሩ ወደ ኢንዱስትሪያዊ ዲዛይን ያተኮረ ሲሆን ዛሬ ላይ ግን እነዚህ ወንበሮች በዓለም ዙሪያ ተወዳጅነታቸው ጨምሮ በብዙ የዓለም ክፍል ጥቅም ላይ ውለው ይገኛሉ፡፡

 የኳስ ወንበር አጠቃቀም፡-ወንበሩ በጨዋታ ዘና ያለ መንፈስ ለመፍጠር በማንኛውም ክፍት የመኖሪያ ቦታ ወይም ላውንጅ ውስጥ ይጠቅማል ፡፡ የኳስ ወንበር ዋጋ 6,500 ዶላር ሲገመት ትክክለኛ ጥራት ያላቸው ቅጂዎች ዋጋ ወደ 650 ዶላር ይጠጋል።

በብል ወንበር

ታሪክ፡-የ ኳስ ወንበር ከተፈበረከ ከ አምስት አመት በኋላ አርንዮ የ በብል ወንበርን ሰራ  ፡፡ ይህ ወንበር ክብደት የሌለው ሲሆን  ብርሃንም ከሁሉም አቅጣጫዎች እንዲገባ ለማድረግ ግልፅ ፋይበር ግላስን ተጠቅሟል ፡፡

የበብል ወንበር አጠቃቀም፡-ይህ ወንበር የስነ-ጥበብ ውጠቶች እና የመሳሰሉ ነገሮች በሚገኙበት ቦታ ሲቀመጥ ካለው ብርሃን ጋር በመዋሀድ የተለየ ዉበት እና ዘመናዊ ገፅታ የማምጣት አቅም አለው ። የበብል ወንበር 4200 ዶላር ያወጣል ተብሎ ሲገመት ትክክለኛ ጥራት ያላቸው ቅጂዎች ዋጋም ወደ 650 ዶላር ያህል ይደርሳል።

የመመገቢያ ወንበር

 ታሪክ፡-እጅግ በጣም ምቹ እና ቀላል በሆነ የግንባታ ስራው የታወቀ ሲሆን ይህ የመመገቢያ ወንበር በኤሮ ሳሪነን በ 1957 የተቀየሰ እና ለ የፋይበር ግላስ ሼል ወንበሮችም  መንገድ የጠረገ ነው ፡፡

የሳሪንየን የመመገቢያ  ወንበር አጠቃቀም፡-እነዚህ ወንበሮች በተለመደው የጠረጴዛ አቀማመጥ በመመገቢያ ክፍል ውስጥ ከዘመናዊ የቤት እቃዎች ጋር ሲቀመጡ የበለጠ ዉበት ይኖራቸዋል ፡፡ የሳሪነን የመመገቢያ ወንበሮች 1800 ዶላር ያህል የሚያስከፍሉ ሲሆን ትክክለኛ ጥራት ያላቸው ቅጂዎችም ዋጋ ወደ 400 ዶላር ይደርሳል።

የቱሊፕ ወንበር

 ታሪክ-ይህ ያማረ የቱሊፕ ወንበር እ.ኤ.አ. በ 1956 ዓ.ም በነበረው ተፈላጊነት ዝናን አትርፏል፡፡ይህ የወንበር አይነት የዘመናዊነት ንፁህ መገልጫ ሲሆን በወቅቱም እንደ ዛሬው ሁሉ ተወዳጅ ነበር ።

የቱሊፕ ወንበር አጠቃቀም፦ የቱሊፕ ወንበር በመመገቢያ ክፍል ውስጥ በመመገቢያ  ጠረጴዛ ዙሪያ ሰዎች ተሰብስበው እንዲጫወቱ የሚጋብዝ እና ለጨወታ ምቾትን የሚሰጥ የወንበር አይነት ነው፡፡የቱሊፕ ወንበር 1290 ዶላር ያህል የሚያወጣ ሲሆን ትክክለኛ ጥራት ያላቸው ቅጂዎችም ወደ 110 ዶላር ያህል ይገመታሉ።

ዎምብ ወንበር

 ታሪክ፡-ዎምብ ወንበር ምናልባት በታሪክ ውስጥ በጣም ምቹ ከሆኑት የሳሪነን ወንበሮች አንዱ ነው ፡፡ በ 1948 በፍሎረንስ ኖል ጥያቄ የቀረበ ሲሆን ወንበሩ ለእርሷ ብቻ የተመረተ ነበር!

 የዎምብ ወንበር አጠቃቀም፦ተዝናንቶ ለመቀመጥ ፣ የዎምብ ወንበሮች በዘመናዊ ሳሎን ቤት ጥግ ላይ አንድ ሰው ብቻውን ተዝናንቶ ሊቀመጥ ቢፈልግ ተመራጭ የ ወንበር አይነት ሲሆኑ ወንበሮቹ  3000 ዶላር ሲገመቱ ትክክለኛ ጥራት ያላቸው ቅጂዎች ደግሞ ወደ 200 ዶላር ያህል ያወጣሉ።

ሪዞም ላውንጅ ወንበር

ታሪክ: በ 1941 በጄንስ ሪሶም የተነደፈው የሪሶም ላውንጅ ወንበር በወቅቱ እጅግ በጣም ያልተለመደ የወንበር አይነት ነበር። የጥጥ ድር ከእንጨት ጣውላ ጋር በማጣመር የተሰራው ይህ ዲዛይን ከዘመናዊ ኑሮ ጋርም ተስማሚ ነው፡፡

ሪዞም ላውንጅ ወንበር ጥቅም : ይህ ላውንጅ ወንበር ሁለገብ በመሆኑ ከማንኛውም ግላዊ ኑሮ ጋር አብሮ ሊጓዝ ይችላል፡፡በሳሎን እና በቤተመፃህፍት ክፍል ውስጥ ሊቀመጥ የሚችለው ይህ ወንበር ወደ 1600 ዶላር የሚያወጣ ሲሆን ትክክለኛ ጥራት ያላቸው ቅጂዎችም ወደ 800 ዶላር ይጠጋሉ።

LC4 ላውንጅ ወንበር

ታሪክ-‹ማረፊያ ማሽን› በመባልም የሚታወቀው የ LC4 ላውንጅ ወንበር በድካም የዛለ ሰውነትን ለማሳረፍ አይነተኛ ምርጫ ሲሆን በኒው ዮርክ ከተማ ውስጥ ባለው ዘመናዊ የሥነ ጥበብ ሙዚየም ውስጥ እንደቅርስነት የተቀመጠው ይህ ወንበር እጅግ በጣም ክፍተት ላለው ዘመናዊ ቦታ ተስማሚ ሲሆን በቢሮ ወስጥም ጥቅም ላይ ቢውል የበለጠ ዉበትን የሚያጎናፅፍ ይሆናል፡፡የዚህ ወንበር ዋጋ ከታዋቂ ባላሙያዎች ስም ጋር ገቢያ ላይ ከወጣ እስ 2970 ዶላር ያህል የሚያስከፍል ሲሆን ትክክለኛ ጥራት ያላቸው ቅጂዎች ዋጋም ወደ 600 ዶላር ሊያሻቅብ ይችላል።

Pin It on Pinterest

Share This