በመኖሪያ ቤት ውስጥ እያንዳንዱ ክፍል የራሱ የሆነ ዓላማ አለው። ስለአንድ ክፍል ተግባር በውስጡ በሞሉት የቤት-ዕቃዎች ውስጥ ብዙ ማለት ይቻላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ የቤት-ዕቃዎች በተለያዩ ክፍሎች መካከል ሊሻገሩ ሲችሉ፤አንዱ ከሌላው በተሻለ ሁኔታ ይገጥማል። ለምሳሌ የተጣራ-ኦክ የመመገቢያ ጠረጴዛ እና ወንበሮች በመኝታ ክፍል ወይም በእንግዳ መቀበያ ክፍል ውስጥ ያለቦታቸው ይመስላሉ። የአንድ መኖሪያ ቤት የቤትዕቃዎች በሚሟሉበት ጊዜ ወጥነት እና ሞቅ ያለ ዕይታ ያለው እንዲሆን  በአንድ ጊዜ አንድ የክፍል አቀማመጥ መቀየስ ይመከራል።

የቤት-ዕቃዎች ዓይነቶች ለመኖሪያ ቤት

መኖሪያ-ቤትን ለማስጌጥ ምን ያህል የቤትዕቃ አይነቶች መጠቀም ይቻላል? በእርግጥ ተራው የመከዳ እና የቡና ጠረጴዛ አማራጭ አለ፤ ግን ወደ ተራው ለመሄድ የማይፈለግ ከሆነስ? እርስዎ ቢሆኑስ በእንግዳ መቀበያ ክፍልዎ ያልተለመደ ወይም ሌላ የተለየ እንዲሆን ይፈልጋሉ? እርግጠኛ ለመሆን፤መከዳዎች እና የቡና ጠረጴዛዎች የክፍል ምሰሶዎች ናቸው። ሆኖም ሌሎች የመኖሪያቤት ዕቃዎች ዓይነቶች አሉ።

የእንግዳ መቀበያ ክፍል መከዳ

በእርግጥ የእንግዳ መቀበያ ክፍል የቤትዕቃዎች አይነቶች ዝርዝር ያለ መከዳ የተሟላ አይሆንም። በእውነቱ አንድ  የእንግዳ መቀበያ ክፍል የተሠራው በመከዳ ነው ማለት ይችላል። አንድ መከዳ የሳሎን

ቤት የመነሻውን ስሜት ይወስናል፤ድባብንም እንዲሁ። በእንግዳ መቀበያ ክፍልዎ ንድፍ ላይ ማሰላሰል የመጀመሪያ ነገር መሆን አለበት፡፡

የቡናጠረጴዛ

ከመከዳዎ ስብስብ ጎን ለጎን ሌላው የእንግዳ መቀበያ ክፍል ዋና ዝግጅት በእርግጥ የቡናጠረጴዛ ነው። ለመጠጥ እና መጽሔቶች ለቡናም ቢሆን በቡና ጠረጴዛው አለም ምቹ መድረክ ለማቅረብ ታሰቦ የተዘጋጀ የቤት-ዕቃ ነው፡፡ ቀለም ላይ ከሚያተኩሩት ከመከዳዎች በተለየ የቡናጠረጴዛዎች ብዙውን ጊዜ በሸካራነት ላይ የበለጠ አፅንዖት ይሰጣሉ፡፡ የቡና ጠረጴዛ በሚመርጡበት ጊዜ ቁሳዊ ውበትን ከግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ ነው።

የወንበር የጎን ጠረጴዛ

ነገሮች መዝናናት የሚጀምሩበት ቦታ እዚህ አለ፡፡ በመደበኛ የጎን ጠረጴዛ እና በወንበር ጎን ጠረጴዛ መካከል ያለው ልዩነት ምንድንነው? በጣም ግልፅ የሆነው ልዩነት መደበኛ የጎን ጠረጴዛ አራት ማዕዘን ቅርፅ ያለው ሲሆን በሁለት ሶፋዎች መካከል እንዲቀመጥ የታሰበ ወይም ለባለብዙ መቀመጫ የመከዳ ዝግጅት እንደ መገጣጠሚያ እንዲያገለግል መዘጋጀቱ ነው፡፡ ምንም እንኳን ለተወሰነ ጊዜ ሊሠራ ቢችልም መደበኛ የጎን ጠረጴዛ ተደግፎ መፃፊያ ወንበሮች፣ክንፍ ወንበሮች እና ተለጣጭ መደገፊያ ያላቸው መፃፊያ ወንበሮች የሚሰሩትን ስራ የሚመዝን ግን አይሆንም።  

አክሰንት ወንበር

በተለምዶ ለመኖሪያ ክፍል የመቀመጫ ዝግጅቶች ሲመረጡ ሶስት መሰረታዊ አማራጮች አሉ፡፡ እነዚህ ሶስት መሰረታዊ አማራጮችም መከዳ፣ተደግፎ መፃፊያ ወንበሮች፣ክንፍ ወንበሮች እና ተለጣጭ ተደግፎ መፃፊያ ወንበሮች ናቸው፡፡በተጨማሪም ሦስቱ ምርጫዎች ብዙውን ጊዜ በሁለት መለኪያዎች ላይ የተካተቱ ናቸው፤ዲዛይን እና ምቾት፡፡ በእርግጥ ከሁለቱም ዓላማዎች በጣም ጥሩው ሁልጊዜ ተመራጭ ነው። ግን ብዙውን ጊዜ አንዱን ከሌላው መምረጥ ግድ ይላል፡፡ የክንፍ ወንበር የበለጠ ንድፍ-ተኮር መሆን አለበት ወይስ የበለጠ ምቾት-ተኮር? በተራ ትዕይንት አንድ መከዳ በሁለቱም ዓለማት ውስጥ እግር ሊኖረው ይገባል፡፡ አንድ መከዳ የመኖሪያ ቤትዎን መሰረታዊ ንድፍ ይወስናል። ይህን ስንል ግን በጣም ብዙ ምቾት ወጪ ማድረግ የለበትም።ተደግፎ መፃፊያ ወንበር ለምቾት የተሰራ ሲሆን ብልህ የውስጥ ዲዛይነሮች አንድ ማረፊያ ወንበር ሲመርጡ ይህንን ተግባራዊ በማድረግ መጽናናትን በማግኘት ዲዛይንን ለምቾት መስዋዕት ያደርጉታል። አክሰንት ወንበሮች የሚያምር ቀለም   መግለጫ ሲሆኑ የተቀመጡትን ህጎች በመከተል የሳሎንን ድባብ የበለጠ ከፍ የሚያደርጉ ናቸው፡፡

አክሰንት ቁም-ሳጥን

የመኝታ ክፍልን ዲዛይን በምናንሰላስልበት ጊዜ የቁሳቁስ ውበት፣ሸካራነትንና ቀለምን መወሰን በጣም አስፈላጊ ከሆኑ ነገሮች ውስጥ ሲሆኑ ልስላሴ አና ሸካራነት ከቀለሞች በተለየ ረቂቅ ናቸው፤ለማዛመድ የሚደረጉ ሙከራዎችም ከፍተኛ ችግር ሲገጥማቸው ይታያል። ነጭ፣ጥቁር፣ቀይ እና ሰማያዊ የቀለሞች መሰረት፤ቀርከሃ እና የእንስሳት ቆዳ የተለያዩ የእንጨት ባህሪያት መሰረት ናቸው። መኖሪያ አካባቢን የሚያጎሉ መደበኛ ያልሆኑ ቁምሳጥኖችን መጠቀም አስደናቂ ውጤቶችን ያመጣል።

የመጽሐፍ መደርደሪያ

ለመጽሃፍ እና ለመጽሔት አፍቃሪዎች አንድ በእርግጠኝነት ሊታሰብበት የሚቻለው የቤት-ዕቃዎች አይነት የመጽሐፍ መደርደሪያ ነው፡፡ በጣም ብዙ የተለያየ አይነት ዝርያዎች ያላቸው ናቸው። አስደሳች የመጽሐፍ መደርደሪያ አስደሳች የመኖሪያ ክፍልን ያሳያል። ፍፁም የመፅሀፍ ይዞታ ያላቸው የመፅሀፍ መደርደሪያዎች  ለንድፍ አውጪ የውስጣዊውን ክፍል ሁለገብ ብዝሃነትን ያቀርባሉ።

አግዳሚ ወንበር

በእርግጥ የሳሎን ክፍል የቤት-ዕቃዎች ዝርዝር ያለ አግዳሚ ወንበር ሙሉ አይሆንም። ብዙውን ጊዜ አግዳሚ ወንበሩ በመኝታ ክፍል ውስጥ በተለይም በእራሱ በአልጋው መጨረሻ ላይ ይሠራል። በጣም ጥሩ በሆነው በእንግዳ መቀበያ ክፍል መቀመጫዎች ውስጥም ያገለግላል፡፡ የአንድን የክንፍ ወንበር ወይም አክሰንት ወንበር ንድፍ-ተኮር ሚና የሚያሟላ ሲሆን በተመሳሳይ ጊዜ ለእንግዶች ተጨማሪ ቦታ መስጠትም ይችላል፡፡ አንድ አግዳሚ ወንበር ከምቾት ይልቅ የንድፍ ጥበብን ያሳያል።

የመኝታቤት ዕቃዎች ዓይነቶች

አልጋ

አልጋ በመኝታ ክፍል በጣም አስፈላጊ ከሆኑት የቤትዕቃዎች ውስጥ አንዱና ዋነኛው ነው። ምክንያቱም የመተኛ ቦታ ስለሆነ ብቻ አይደለም፡፡ የሚመረጠው የአልጋ ዓይነት የሙሉ ክፍሉን ድባብ ይለውጣል፤ተጨማሪ የቤትዕቃዎች አማራጮችን የመጠቀም ሁኔታንም ይወስናል።ከባህላዊ ዘይቤ ውስጥ ወይም የበለጠ ዘመናዊ ከሆነ ዘይቤ ውስጥ የአልጋን አይነት መምረጥ ይቻላል። ነገርግን የአልጋን ክፈፍ መምረጥ ላይ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ማለትም ከፍተኛ ጥራት ያለው እና ዘላቂ ክፈፍ መጠቀም የግድ ነው።

የጭንቅላት ሰሌዳ

በአልጋ ክፈፍ አናት ላይ የሚጫን የግድግዳ ላይ ማስዋቢያ፤የጭንቅላት ሰሌዳ ምናልባትም በጣም የሚታየው የአልጋ ክፍል ነው፡፡ የጭንቅላት ሰሌዳ አጭር ወይም ረዥም ፣አራት ማዕዘን ወይም የተቆረጠ፣ እና ባዶ ወይም የታጣፈ ሊሆን ይችላል።  በተለይም የአልጋው ክፈፍ በግልፅ የሚታይ ከሆነ የጭንቅላት ሰሌዳው ከአልጋው ክፋፍ ጋር አብሮ የሚሄድ መሆን ይኖርበታል። ከዚህ ባለፈ የጭንቅላት ሰሌዳ ምርጫ አንደ ተጠቃሚው ተፈላጊ ምቾት ይወሰናል።

መስቀያ

እንደ የዓይን መነፅር ወይም የእንቅልፍ ጭምብሎች ያሉ በእጅዎ ላይ የሚፈልጓቸውን ዕቃዎች በመሳቢያዎቹ ውስጥ ለማስቀመጥ ይቻላል። ብዙውን ጊዜ የሚጣጣሙ ሁለት የሌሊት መቆምያዎች አያንዳንዳቸው ጥግ ይዘው እንዲቆሙ ይፈለጋል። ለዕይታ አመላካችነት እና ለአጠቃቀም ቀላል እንዲሆኑ ሲባል የምሽት መቀመጫዎች ከሞላ ጎደል እና ከፍራሽ የላይኛው ክፍል ወለል ጋር እኩል መሆን አለባቸው። እነዚህ ከአለባበስ እና ከአልጋ ጋር ሲተባበሩ ወጥ የሆነ ህይወትን ለመምራት መንገድ ይከፍታሉ ፡፡

የመኝታ ክፍል ስብስብ

የመኝታቤት ዕቃዎችን ውህደት ለማረጋገጥ አስተማማኙ መንገድ የመኝታ ስብስሰብ መጠቀም ነው፡፡ የመኝታ ክፍል ስብስቦች መሰረታዊ የመኝታ ቤት ዕቃዎች እሽጎች ናቸው፡፡ እነሱ በተለምዶ ቢያንስ ሦስት ዕቃዎችን ይዘው ይመጣሉ። እነዚህም የአልጋ ክፈፍ፣የጭንቅላት ሰሌዳ እና የሌሊት ወንበሮች ናቸው፡፡ ከፈለጉ መኝታ ክፍሉን በማስጌጥ ከተወሰደ ልምድ በመነሳት ወደጥቅሞቹ ወደሚያዘነብሉት ምርቶች መሸጋገር ይችላሉ፡፡

አርሞየር

አርሞየር ልብሶችን ለማከማቸት የሚጠቅም ቁም-ሳጥን መሰል የቤትእቃ ነው። በተጨማሪም የልብስ ማስቀመጫዎች ተብለው የሚጠሩ ሲሆን  እነዚህ የመኝታ ክፍል የቤትዕቃዎች በመጠን ይለያያሉ፣ግን ልብሶችን ለመስቀል እንዲጠቅም በተለምዶ ቢያንስ አንድ ቁም-ሳጥን አላቸው። የታጠፉ ልብሶችን ለማስቀመጥ የሚሆኑ ጥቂት መሳቢያዎችም አሉት። አርሞየሮች በተለይ በጣም ጠባብ ወይም ምንም ቦታ በሌላቸው የመኝታ ክፍሎች ውስጥ ጠቃሚነታቸው የጎላ ነው።

የመመገቢያ ክፍል የቤትዕቃዎች ዓይነቶች

የመመገቢያ ጠረጴዛ

የመመገቢያ ጠረጴዛ በመመገቢያ ቤት ውስጥ የትኩረት ነጥብ ሊሆን የሚችል ሲሆን አራትማዕዘን፣ክብ፣ወይም ሞላላ ቅርፅ ሊኖረው ይችላል። የመመገቢያ ጠረጴዛ ቅርፅ በመመገቢያ ክፍሉ ውስጥ ሊገኝ በሚችለው የቦታ ስፋት ልክ፣በቋሚነት ቤት ውስጥ በሚመገቡ ሰዎች ቁጥር ልክ እና በግል ምርጫ ላይ የሚመሰረት ነው። ቅጠል-ጣል ጠረጴዛ ቅጠል ተብሎ የሚጠራ የሚወጣ የሚገባ ተንቀሳቃሽ ክፍል ስላለው የጠረጴዛን መጠን ለመቀያየር ያስችላል፡፡የተመረጠው ምንም ይሁን ምን፤ ምርጫ በሚደረግበት ጊዜ ወንበሮች ወደ ውስጥ እና ወደ ውጭ እንዲንቀሳቀሱ በቂ ቦታ መስጠት ላይ ትኩረት ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡

የመመገቢያ ወንበሮች

በቤት ውስጥ አዘውትረው የሚመገቡ ወይም ትናንሽ ልጆች ያሉዋቸው ሰዎች ከመመገቢያ ወንበሮቻቸው ብዙ ጥቅም እንደሚያገኙ ይጠበቃል፡፡ ለዚያም ነው ዘላቂ የመመገቢያ ወንበሮችን መጠቀም አስፈላጊ የሚሆነው፡፡ እንደ እንጨት፣ብረት፣ፕላስቲክ እና የመሳሰሉትን በመጠቀም የተሰሩ አስተማማኝ የመመገቢያ ወንበሮችን ማግኘትም ከጊዜ ወደ ጊዜ ቀላል እየሆነ ይገኛል። እንዲሁም ማን እንደሚጠቀምበት ግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል። ለምሳሌ፦ትናንሽ ልጆች በቤት ውስጥ ካሉ ጥሬ እንጨት እና በጨርቅ የተሸፈኑ ወንበሮችን መጠቀም  ለማጽዳት አስቸጋሪ ሁኔታ ይፈጥራል። የመመገቢያ አግዳሚ ወንበር የተሻለ አማራጭ ሲሆን ይታያል።           

ቡፌ                  

ቡፌ ራሱን የቻለ፣የማብሰያ እና የመመገቢያ ቦታን የማከማቸት አቅም የሚያሰፋ በተለይም ሰፋ ያለ ወገብ እና መጠነኛ ቁመት ያለው ቁም-ሳጥን ነው፡፡ ቡፌዎች አነስተኛ ማእድ ቤት ወይም አብሮ የተገነቡ ካቢኔቶች እጥረት ላላቸው ቤቶች ፍጹም መፍትሄዎች ናቸው። ቡፌዎን ትርፍ ሳህኖች እና ዕቃዎችን ለማሰቀመጥ መጠቀም ትርፍ ናቸው የሚባሉ ቦታዎችን በመመገቢያ ቤት ጌጦች አስጊጦ አዲስ ገፅታን ለመፍጠር፤ከዚያም አለፍ ሲል ጥሩ የግል ባህርይን ለማበልፀግ ይረዳል። ጠረጴዛ እና ወንበሮች በአቀማመጥ ስርአቱ ላይ ጣልቃ መግባት ስለማይኖርባቸው ቡፌን መጠቀም ሲታሰብ ለተመረጠው ቡፌ የሚሆን በቂ ቦታ በመመገቢያ ቤት ውስጥ መኖሩን ማረጋገጥ ያሰፈልጋል።  

የመመገቢያ የቤትዕቃዎች ጥቅል

ለተሟላ እና ለተቀናጀ የመመገቢያ ቤት፤የመመገቢያ የቤትዕቃዎች ጥቅልን መጠቀም የተሻለ ውጤት ይሰጣል። እነዚህ ጥቅሎች ማንኛውንም የመመገቢያ ክፍል ነፋስ ለመስጠት እና ከመጭበርበርም ለመዳን ያግዛሉ።   ብዙ ጊዜ በጥቅሉ ውስጥ ያሉት ዕቃዎች በቁጥር አ17ምስት ናቸው ። እነዚህም ጠረጴዛ እና አራት ተመሳሳይነት ያላቸው ወንበሮች ናቸው።

የመጠጥ ቤት በርጩማዎች

የመጠጥቤት በርጩማዎች ባር ወይም የተራዘመ ባንኮኒ ላላቸው ማብሰያ ቤቶች ጥሩ የመቀመጫ መፍትሄዎች ናቸው።  የመጠጥቤት መቀመጫዎች እና የባር ወንበሮች ከመደበኛ የመመገቢያ ወንበሮች የበለጠ በጣም ከፍ ያደርግዎታል። አብሮ የተገነባ ባር ከሌለ የመጠጥ ቤት ጠረጴዛ የመጠጥ ቤት በርጩማዎችን ወደ መመገቢያ ቦታ አምጥቶ ለመጠቀም የሚያግዝ አንድ ትልቅ አማራጭ ነው።

                                                                          

Pin It on Pinterest

Share This