ግብፅ

አልጋዎች፣ወንበሮች፣የዙፋን ወንበሮች እና ሳጥኖች በጥንታዊዋ ግብፅ ዋናኞቹ የቤት-ዕቃዎች ዘይቤ ናቸው። ምንም እንኳን ጥቂት እውነተኛ አስፈላጊ የቤት-ዕቃዎች ምሳሌዎች ብቻ ቢተርፉም የድንጋይ ቅርጻቅርጾች፣የግድግዳ ላይ ሥዕሎች እና እንደ አስቂኝ ሥራ የተሠሩ ሞዴሎች ብዙ የሰነድ ማስረጃዎችን ያቀርባሉ፡፡ አልጋው ቀደምት መልክ ያለው ሲሆን ከእንጨት የተሰራ፣ቀለል ያለ ማዕቀፍ ያካተተ እና በአራት እግሮች የተደገፈ ነበር። የሚተኛው ሰው የሚለጠጥ መኝታ የሚሰጠውን ምቾት እንዲያገኝ  ሲባል የተልባ እግር ጉንጉን በማዕቀፉ ዙሪያ ታሰሮበታል። በ18ኛው ሥርወ-መንግሥት አልጋዎች ወደ ግርጌ አዘንብለው፤የተቀባ ወይም የተቀረጸ የእንጨት እግር ሰሌዳ የተኛውን ሰው ከመንሸራተት ይጠብቃል፡፡ በቱታንሃመን መቃብር ውስጥ የተገኙት ታላላቅ አልጋዎች በነሐስ መንጠቆዎች እና ሽቦ አቃፊዎች የተያያዙ ናቸው። ይህም ለማከማቸት አና ለማጓጓዝ  በተፈለገ ጊዜ አካላቸውን ለመለያየት ወይም ለማጣጠፍ እንዲያመች ነበር። በመጠናቸውም ትናንሽ ስለሆኑ ፈርኦኖች ግዛቶቻቸውን በሚጎበኙበት ጊዜ ይዘዋቸው ይንቀሳቀሱ ነበር። በዚያው መቃብር ውስጥ የነሐስ መጋጠሚያዎች ያሉት የሚታጠፍ የእንጨት አልጋ ነበር፡፡

በጨርቅ ትራስ ፋንታ ከእንጨት ወይም ከዝሆን ጥርስ የተሰሩ መንተራሻዎችም ነበሩ። እነዚህ በመሰረታዊነት ግለሰባዊ ነበሩ። በባለቤቱ ልክ ይሰራሉ። የሞተው ሰው ወደ ዘላለም ምድር ሲገባ ይጠቀምበታል ተብሎ ስለሚታሰብ ብዙውን ጊዜ በመቃብሮች ውስጥ ይቀመጣሉ። የሚታጠፉት መንተራሻዎች ምናልባትም ለባሮች ወይም መንገደኞች መጠቀምያ ነበሩ፡፡

ለክብረ-በዓላት አላማእቅድ የተሰሩት የመጀመሪያዎቹ በርጩማዎች አራትማዕዘን ቅርፅ ያላቸው በከፊል የድንጋይ ንጣፎች ነበሩ። ከእንጨት የተሰሩ ሲሆኑ መቀመጫቸው በለስላሳ መከዳ የተሸፈነ ባልጩት ነበር። ከጊዜ በኋላ በርጩማው ጀርባ እና ክንዶች በመጨመር ወደ ወንበር ተለወጠ፡፡ እንደዚህ ያሉ የዙፋን ወንበሮች ታላላቅ ሰዎች እንዲጠቀሙባቸው ተጠብቀዋል፡፡ የእግረኞች መቀመጫዎች ከእንጨት የተሰሩ ነበሩ፡፡ የንጉሱ የእግር መረገጫ በግብፅ ባህላዊ ጠላቶች ምስሎች ተቀርፆ ነበር። ይህም ፈርዖን በምሳሌያዊ መንገድ ጠላቶቹን ከእግሩ በታች እንዲረግጥ ነበር፡፡ ቀጥ ያለ ወንበር ላይ የእንስሳትን እግሮች መቅረጽም የተለመደ ነበር፡፡

ብዙውን ጊዜ በቀለማት ያሸበረቁ ሳጥኖች ወይም ቅርጫቶች ልብሶችን ወይም ሌሎች ዕቃዎችን ለማቆየት ያገለግሉ ነበር፤ጠረጴዛዎች ያልታወቁ ነበሩ ማለት ይቻላል። በሸክላ ዕቃዎች ወይም በእንጨት መቆሚያ የሚደግፍ ጠፍጣፋ የመረብ ትሪ ገበታ ለማቅረብ ያገለግል ነበር። ውሃ ወይንም ወይን የያዙ ማሰሮዎችም በተመመሳሳይ መልኩ ከእንጨት በተሠሩ ማቆሚያዎች ይቀርቡ ነበር።

ግብፃውያን አንድ ላይ የተጣበቁ ቀጫጭን የእንጨት ጣውላዎችን ለሬሳ ሣጥን መስሪያነት ተጠቅመዋል፤ይህም ትልቅ ጥንካሬን ሰጥቷል፡፡የግብፅ የቤትዕቃዎች በአጠቃላይ ክብደታቸው ቀላል እና በቀላሉ የሚጓጓዙ ነበሩ፡፡ ጌጣጌጦቹም ብዙውን ጊዜ ከሃይማኖታዊ ምልክቶች የተገኙ ነበሩ።

ሜሶፖታሚያ

ለሜሶፖታሚያ እና ለመካከለኛው ምስራቅ ጥንታዊ ሥልጣኔዎች አልጋዎች፣ ወንበሮች፣ እና ሳጥኖች እንደ ዋና መገለጫዎች ነበሩ፡፡ በተለይ በእርዳታ የተቀረጹ የሰነድ ማስረጃዎች አሉት።  መገለጫዎቹ ከግብፅ የቤትዕቃዎች ጋር በተመሳሳይ መልኩ የተገነቡ ቢሆኑም አባላቱ ከበድ ያሉ፣ተደጋጋሚ ኩርባዎች በቁጥር ያነሱ እና መገጣጠሚያዎቹም እንግዳ አይነት ነበሩ። ጌጣጌጦቹም የነሀስ፣የተጠረቡ የአጥንት ጉልላቶች እና ጥቃቅን የልብስ ላይ ጌጦች የነበሩ ሲሆን አብዛኞቹ በሙዚየም ውስጥ ተጠብቀው ይገኛሉ፡፡የሜሶፖታሚያ ጥበብ በጥንታዊ የቤት-ዕቃዎች ስልጣኔ የጸኑ የነበሩ ሦስት ባህሪያትን በግሪክ እና ጣሊያን ውስጥ አምጥቷል። ስለሆነም ወደ ሌሎች የምዕራቡ ዓለም ስልጣኔዎች ተላልፈዋል፡፡

መጀመሪያ በክንድ ላይ እንደሚታዩ ብዙ አምባሮች፤የቤት-ዕቃዎች እግሮች ላይ በደንብ የሚታዩ የብረት ቀለበቶች ነበሩ። ከሌላው በላይ ይህ በኋላ ላይ በጣም በተደጋጋሚ የሚዞሩ የእንጨት እግሮች ጌጦችን አመጣ። በሁለተኛ ደረጃ በቤትዕቃዎች ላይ ከባድ ጠርዞችን የመጠቀም መልክ ነበር፣የክፈፍ እና የመከዳ ንድፍን በማደባለቅ አንድ ውጤት ማምጣት፤ይህ በዓይነተኛ ዲዛይን የበለጠ መሰራት ሲችል የበለጠ ደግሞ በኒኦክላሲሲዝም ውስጥ እንደገና ታደሷል፡፡

ግሪክ

የግሪክ ዋና የቤት-ዕቃዎች መገለጫዎች መከዳዎች፣እጅ ማስደገፊያ ያላቸው እና የሌላቸው ወንበሮች፣በርጩማዎች፣ ጠረጴዛዎች፣ባለመሳቢያ ቁም-ሳጥኖች እና ሳጥኖች ነበሩ፡፡ አሁን በአበባ ማስቀመጫዎች ላይ ያሉ የቤትዕቃዎች ምስሎች፣ቅርፃቅርጾች ላይ የተንጠለጠሉ ጌጦች፣ሥነ-ጽሑፋዊ መግለጫዎች ያሉ ብዙ ተጨማሪ ምሳሌዎች ከግብፅ ይልቅ ስለ ግሪክ የቤትዕቃዎች እንደሚገልፁ የታወቀ ነው፡፡በኤጂያን አካባቢ በክኖስሶስ አብሮ የተሰራው የስቱኮ ዙፋን በጣም የቅርብ ነው፤የቅድመ-ሄለኒክ የቤት-እቃዎችንም በውስጥ እንደሚወክል ተደርጎ ይቆጠራል። ጥንታዊ የኤጂያን የሸክላ ዕቃዎች ክብ የመሰሉ የወንበር ቅጾች ምናልባትም ቅርጫትን የሚያመለክቱ ሞዴሎች እና የነሐስ ዘመን ቅርፃቅርፅ ውስብስብ ወንበር ክፈፎች ያሳያል።በጥንታዊ የግሪክ ቤቶች ውስጥ መከዳው ቀን ጋደም ለማለት እና ማታ እንደ አልጋ ለመተኛት ያገለግላል፤ወሳኝ ቦታንም ይይዛል፡፡ የመጀመሪያዎቹ መከዳዎች ምናልባትም በመዋቅር  የግብፅ አልጋዎችን ይመስላሉ፡፡ እግሮችም አልፎአልፎ የእንስሳትን እግር ወይም ኮቴ በመኮረጅ ተሰርተዋል። 

ሮም

የሮም ዋና የቤትዕቃዎች መገለጫዎች ሶፋዎች ፣ እጆች ያሏቸው እና እጆች የሌሏቸው ወንበሮች፣በርጩማዎች፣ ጠረጴዛዎች እና ሳጥኖች ነበሩ፡፡ በግድግዳ ሥዕሎች፣ቅርጻቅርጾች እና ጽሑፋዊ መግለጫዎች ውስጥ እጅግ በጣም ጥሩ ሰነድ ይገኛል።በፖምፔ ላይ የነሐስ ዕቃዎች ሀብት ተገኝቷል። በሄርኩላኑም እንኳ የእንጨት ቁርጥራጮቹ በከፊል ተጠብቀዋል፡፡

እንደ ግሪክ ሁሉ መከዳው ዋናው የቤት-ዕቃ መገለጫ ነበር፡፡ ከነሐስ ክፈፎች ጋር የታነፁት የፖምፔ አልጋዎች የግሪክ ምሳሌዎችን ይመስላሉ፡፡ ያልተለመዱ እንጨቶችን ጨምሮ ወርቅ፣ብር፣የኤሊ ጓንጉል፣አጥንት እና የዝሆን ጥርስ ለማጌጥ ያገለግሉ ነበር።.በኋላም በጣሊያን እና ርቀው በሚገኙ የግዛቱ ክፍሎች ውስጥ የተገኙት መከዳዎች ከፍ ባለ ጀርባ እና ጎኖች ተለይተው ይታወቃሉ። የሮማውያን ወንበሮች በግሪክ ሞዴሎች የተገነቡ ናቸው፡፡ ግሪካዊው የዙፋን ወንበር ቅፅ ጠንካራ ወደ ሆነ አራትማዕዘን ወይም ግማሽክብ ትንሽ ወንበር ተለውጧል። ይህ ወንበር ብዙውን ጊዜ የቀርከሀ፣የእንጨት ወይም የድንጋይ ወንበር ነበር። የግሪክ ኪሊስሞስ ወንበር በሮማውያን  ከባድ መዋቅራዊ አባላት ተሰጡት፤ስሙም ካቴድራ ተባለ፡፡ ሮማውያን ብዙውን ጊዜ ከነሐስ የተሠራ ያጌጠ በርጩማ ይጠቀሙ ነበር፡፡ ይህም በአራት ጠመዝማዛ እግሮች የተደገፈ፣በጥቅልሎች የተጌጠ ነበር፡፡

የአስራዘጠነኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ

የፈረንሳይ አብዮት በናፖሊዮን ዘመነ መንግስት የነበረውን ንድፍ፣በጊዜው የነበሩትን የደች የቤት-ዕቃዎች፣የእንግሊዝ የቤት-ዕቃዎችን፣የሸራተንን ቀጣይ ስራዎች፣የታዋቂውን ፕላን ነዳፊ ጆርጅ ስሚዝን ንድፎች፣የጎቲክ ዳግም መነሳትን፣የሴዶንን የቤት-ዕቃዎች፣የዊሊያም አራተኛ የቤት-ዕቃዎችን እና በቅርብ ጊዜ ነበረው የንግሰት ቪክቶሪያን የግዛት ዘመን፣አህጉራዊ ንድፎችን፣በፈረንሳይ እና በእንግሊዝ የተሰሩ አውደርዕዮችን፣የእንግሊዝ ክበብ ቤቶችን፣የንግድ ልማዶችን፣የጣልያንን የጥርብ ስራዎች፣የቁም-ሳጥን ስራዎችን እና አጠቃላይ የጊዜውን ማስታወሻዎች በተፅዕኖው ስር ለማሳደር የቻለ ነበረ።በ1810 ከሜሪ ሉዊ ጋር ጋብቻ በሚፈፅምበት ጊዜ ያሰራላት ቁም-ሳጥን የናፖሊዮንን ዘመን የቤት-ዕቃ ጥበብ የሚገልፅ ጥሩ ምሳሌ ነው። የተሰራበት እንጨት ከሞላ ጎደል ቀይ-ቡኒ ሲሆን ለነሐስ ቅብ ስራዎችም መንገድ የከፈተ ነው። በወርቅ የተለበጠና በውድ ሀር የተሸፈነም ነበር። የዚህን ቁም-ሳጥን ያህል ባይንቆጠቆጡም ሌሎቹም የዘመኑ ስራዎች በዚሁ መንገድ ተሰርተዋል፤የተለዩ ሆነው የራሳቸውን ዋጋ ይዘውም ቆይተዋል።  

በዚሁ ዘይቤ የተሰራውና ይበልጥ የተለመደው፤ነገርግን እምብዛም ያልተጌጠው የቤት-ዕቃ ጠንካራ፣ደረቅና ምቾትም ያለነበረው ሲሆን የፈረንሳይ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ረብሻ በደስታ መፍነክነክ የሚወደውን ሰው በቤት-ዕቃ ስራው ላይ የነበረውን ጠንቃቃ አሳቢነት ከትኩረቱ ጋር እንደወሰደበት የሚያሳይ ነው። ከጊዜ በኃላ በተለይም በኒውዮርክና በመጠኑም በእንግሊዝ የጨመረውን የቤት-ዕቃ ፍላጎት ተከትሎ የፈረንሳይ ነጋዴዎች ያልተጌጡና ያረጁትን ገዝተው በነሐስ ከለበጡ በኃላ ሚዩብል ደ ሉክስ በሚባለው የፈረንሳይ የቤት-ዕቃዎች ስም ሽጠዋል።በዚያን ጊዜ የደች የቤት-ዕቃ ውስጥ የናፖሊዮንን የቤት-ዕቃ መልክ መባዛት፤የአብዮተኞቹ ጥንታዊ ሮምና ግሪክ መቀጠልን ያሳያል። በትናንሽ የእንጨት ጌጣጌጥ ያጌጡ የፀሀፊ ወንበሮች፣ጠረጴዛዎች፣ወንበሮች እንዲሁም መሰል  እቃዎች እንደ አንበሳ እና ግብፅ ውስጥ ያለውን «ሲፊኒክስ» ተብሎ የሚጠራውን ታዋቂ ሀውልት እንደሚመስል  ባሉ እንስሳት ጭንቅላትና እግር ቅርፅ የወጣላቸው በመሆናችው የዚህ አይነቱ ንድፍ ሌላ ሊቀዳ የሚቻልበት ምንጭ አለመኖሩ በራሱ ምስክርነትን ይሰጣል።

ናፖሊዮንን አምርራ የምትቃወመው እንግሊዝ በዚህ ጊዜ የነበረውን የፈረንሳይ የአነዳደፍ ጥበብ መቀበሏ ልዩ ያደርገዋል። በዚህ አይነት ሸራተን «የቤት-ዕቃዎች መፅሀፍ» በሚለው መፅሀፉ ሲያወሳ «ቺፒንዴል እና ጊዜው» በሚለው ምዕራፉም ሲያብራራ፤ፈረንሳይ በሜሪ አንቶኒዮ ተፅዕኖ ስር በነበረችበት ጊዜ እንደገና ለመድረክ የበቁ ሌሎች ነባር ንድፎች መኖራቸውን የሚገልፁ ማስረጃዎች አሉ። መስመሮች ለቤት-ዕቃ መጥፎ በሚባል ሁኔታ ቀጥ ያሉ ሆነዋል፤ይህም ለውጥ የተደረገው በሸራተን፣ሺረር እና ሌሎች በክፍለዘመኑ በነበሩ የእንግሊዝ ንድፍ አወጪዎች ነበር። የሸራተንን ቀጣይ ንድፎች የምናይ ከሆነ የእንስሳት እግሮችና ጭንቅላት ቅርፆች ተገድበውም ቢሆን ገብተው እናያለን። እነዚህ ፈረንሳይ በቤት-ዕቃው አለም ያሳደረችውን ተፅዕኖ ያለ ምንም ማጠራጠር የሚያሳዩ፣በእንግሊዝና በፈረንሳይ ስራዎች መካከል ያለውን ልዩነት በንፅፅር የፈረንሳይ ግዛት የብረት የቤት-ዕቃዎች ከባድ እና የማያምር ከመሆን ሲድኑ ይህ እይነቱ ስኬት በእንግሊዝ ተፈላጊ ነበር። በነሐስ ስራዎችም ያደጉ ባለመሆናቸው ጌጦችን በነሐስ በተለበጠ ወይም በተቀባ እንጨት ቀርፀው ይጠቀሙ ነበር። ብረትን የሚጠቀሙ ከሆነ ነሐስ እና ክውር ብረት የሚመርጡ የነበረ ሲሆን ቅርጹም በጥርስ ማውጫ በመጠቀም የሚሠራ ግን ከፈረንሳይ አንፃር ሲታይ ገልጃጃ ሊባል የሚችል ነበር። በዚህ ምክንያት በ19ኛው ክፍለዘመን የነበረው የእንግሊዝ የቤት-ዕቃ ደረቅ፣ግዙፍና ከባድ ከጊዜው የፈረንሳይ ዘመናዊነትም ጋር ለንፅፅር ሲቀርብ ግርማሞገስ የሚያስፈልገው መሆኑ የሚያስታውቅ፣ቀዳሚነትንና ግላዊነትንም ለናፖሊዮናዊ የቤት-ዕቃ እንዲቆጠር የሚያደርግ ሆኖ ኖሯል። በአሁኑ ጊዜ በስኪነርስ ኩባንያ ፍርድቤት ውስጥ የፈረስ ጫማ ቅርፅ ያለው የስብሰባ ጠረጼዛ መልክ አንዲመጣ ቅጥያ ተጨምሮላቸው ለኮሚቴ ስብሰባ አገልግሎት እየሰጡ ያሉት በተጨባጭ የሚገኙ ጥሩ ምሳሌዎች ናቸው። 

Pin It on Pinterest

Share This