በ 1900 ዎች መጀመሪያ ላይ በባውሃውስ ዲዛይን ትምህርት ቤት የተጀመረው የዘመናዊ ፈርኒቸር እንቅስቃሴ አንድን የተወሰነ ዘይቤ (ስታይል) ያመለክታል ፡፡ እነዚህ ዲዛይኖች ከእነርሱ ቀድመው ከነበሩ የፈርኒቸር ዲዛይኖች አንፃር  ሲታዩ  በእጅጉ የተራቀቁ ነበሩ፡፡ዘመናዊ ዲዛይን ስንል የሚያመለክተው ከ 19 ኛው መቶ ክፍለዘመን  ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በዘመናዊነት ወይም በጊዜው ባለው ተጽዕኖ የተሰሩ  እና እየተሰሩ ያሉ የቤት ዕቃዎችን ነው ፡፡ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በዲዛይን ውስጥ ከመጠን በላይ  የመለዋወጥ እና የክህሎት ተግባራዊነት  እሳቤዎች የቤት እቃዎች ውበት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳደሩ ሲሆን ከዚያ ቀደም  በሁሉም የቤት ዕቃዎች ላይ የዲዛይን ማሻሻል መደረግ እንዳለበት በእጅጉ  የሚወተውቱ ሁኔታዎች በርካቶች ነበሩ፡፡ የቤት ዕቃዎች  ከዕይታ ክቡድነት  ወደ ምስላዊ ብርሃንነት ተሻሽለዋል ፡፡ ይህ ከጌጣጌጥ ወደ አነስተኛ የዲዛይን መርሆዎች መሸጋገር አዲስ ቴክኖሎጂን በማስተዋወቅ ፣ በፍልስፍና ለውጦች እና በሥነ-ሕንጻ መርሆዎች ተጽዕኖዎች የመጣ ሊሆን ይችላል ፡፡ በዘመናዊ ሥነ ጥበብ ሙዚየም የሕንፃና ዲዛይን መምሪያ መስራች <ፊሊፕ ጆንሰን> እንደሚናገሩት፤

ዛሬ የኢንዱስትሪ ዲዛይን በተግባር ተነሳሽነት ያለው እና እንደ ዘመናዊ ሥነ-ህንፃ ተመሳሳይ መርሆዎችን የሚከተል ነው። የማሽን ቀላልነት ፣ የመስመሮች ልስላሴ ፣ በጌጣጌጥ መራቀቅ  ምናልባት በሁለቱ ዲዛይን ማለትም በባህላዊ እና በዘመናዊ  ዲዛይኖች  መካከል እጅግ መሠረታዊው ንፅፅር ሊሆን ይችላል ፡፡ዘመናዊ የፈርኒቸር ዲዛይን የፋብሪካ ሞጁሎችን ለማስተዋወቅ ቀላል ሲሆን ይህም የወቅቱን የጊዜ አጠቃቀም እንዲሁም ለቀልጣፋ እሳቤዎች አፅንዖት ሰጥቷል ፡፡ የዘመናዊነት ንድፍ ጊዜን ፣ ገንዘብን ፣ ቁሳቁሶችን እና ጉልበትን በመቆጠብ በፈርኒቸር ንድፍ ላይ ማተኮር የቻለ ሲሆን  የዘመናዊ ዲዛይን ዋናው ግብ  ትክክለኛ እና ጊዜ የማይሽረውን ውበት መስጠት ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።

የዘመናዊ  ፈርኒቸር ዲዛይን ተወዳጅነት የተጀመረው በመካከለኛው ምዕተ ዓመት አጋማሽ ሲሆን  ውበት ያላቸው እና ጠቀሜታቸዉ የጎላ ፈርኒቸሮችን  ለመስራት  ከእደ ጥበብ ባለሙያዎች ጋር አብረው በሚሰሩ ሰራተኞች ሀሳብ ሊመሰረት ችሏል፡፡ አዳዲስ ቁሳቁሶችን የመጠቀም ችሎታን መሞከር ፤ ለዘመናዊ ፈርኒቸር ዲዛይን መሠረት ጥሏል፡፡ዋና ዋና ዘመናዊ የፈርኒቸር ዲዛይን ፅንሰ-ሀሳቦችን ፡-

ግልጽ የሆኑ መስመሮች እና የጂኦሜትሪክ ቅርጾች

ዘመናዊው ዘይቤ በተቻለ መልኩ ግልፅ እይታዎችን መፍጠር ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሲሆን ዘመናዊ የፈርኒቸር ዲዛይን ትኩረቱን በይበልጥ በንጹህ መስመሮች ፣ ጂኦሜትሪክ ቅርጾች እና ማዕዘኖች ላይ ያደረገ  ነው ፡፡ ስለሆነም ቀጥታ መስመሮች እና ጠርዞች ከዋናዎቹ ዘመናዊ የንድፍ ጽንሰ ሃሳቦች መካከል  በዋናነት የሚካተቱ ሲሆን ለአብነት ያህል  አራት ማዕዘን ቅርጽ ያላቸው ባለ አራት ማእዘን ሶፋዎች  እና ወንበሮች ለዚህ አይነተኛ ምሳሌ ተደርገው የሚቀርቡ ሲሆን  አንድን ዘመናዊ ክፍል  ውብ እና ማራኪ ገፅታን በመስጠት በኩል ጉልህ ሚና ይጫወታሉ ፡፡

ዘመናዊ የፈርኒቸር ዲዛይን ጠመዝማዛ(curved )ሊሆኑ አይችሉም ማለት ነው?

ምንም እንኳን ኩርባዎች ከግማሽ ምእተ አመት በፊት የነበሩ የዲዛይን አይነቶች ቢሆኑም ፤ በአሁኑ ጊዜ ዘመናዊ ኩርባዎች(curvatures) እንደ አዲስ እየዘመኑ  ጥቅም ላይ እየዋሉ እንደሆነ እንደሆኑ ማስተዋሉ ተገቢ ነው።

ብረቶችን መጠቀም

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የቤት ዕቃዎችን(ፈርኒቸሮችን)  ከብረት ጋር አጣምሮ  የመሥራት አዝማሚያ እየታየ ሲሆን የዘርፉ ባለሙያዎች እንደ አሉሚኒየም ፣ ኒኬል እንዲሁም የማይዝግ ብረት ሲጠቀሙ ይስተዋላል፡፡ የዘመናዊ ዲዛይን ዘይቤ በተጨማሪነት በተለያዩ ቀለሞች ያጌጡ እና በአብዛኛው ከነሀስ ስ እና ጥቁር ብረቶች  የተሠሩ መብራቶችንም ያጠቃልላል ፡፡

ተፈጥሮአዊ ቁሳቁሶች

በዘመናዊ ዘይቤ ፣ሸካራ ቁሳቁሶችን መጠቀም ወቅታዊ እሳቤ ሲሆን ተፈጥሯዊ እንጨቶችን እና ድንጋዮችን መጠቀም በክፍሉ ውስጥ ተጨማሪ ውበትን  እና የመንፈስ መነቃቃትን  ለመጨመር ይረዳል ፡፡

መጠን እና ተግባራዊነት

ከዘመናዊ የቤት መገልገያ  ጽንሰ-ሐሳቦች መካከል አንዱ ተግባራዊነት እና ዘርፈብዙ አጠቃቀሙ ነው፡፡ ለምሳሌ ፣ የማብሰያ ክፍሎች  በርከት ያሉ ቁሳቁሶችን ለማስቀመጥ  ምቹ ሊሆኑ የሚችሉ ሲሆን በአንፃሩ ደግሞ በአልጋዎች ራስጌ  መደርደሪያ ማስቀመጥም  ከላይ የተቀመጠውን ሀሳብ የሚደግፍ ሆኖ ይቀርባል ፡፡

ክፍት ቦታ

ዘመናዊ የዲዛይን ዘይቤ የአነስተኛ ቦታ አጠቃቀም አስተሳሰብን ያበረታታል ። በዚህ ዘይቤ ውስጥ የውስጥ ዲዛይነሮች(Interior Designers) የበለጠ የክፍት ቦታዎችን አጠቃቀም የሚተገብሩ ሲሆን  ይህንን ቦታ  በተገቢው መንገድ ጥቅም ላይ ማዋል የሚኖረውን ጥቅም አፅንኦት ይሰጡበታል፡፡ ስለሆነም እያንዳንዱ ግለሰብ ይህንን ተግባራዊ እንደሚያደርግ የሚጠበቅ ሲሆን  በክፍት ቦታው  ላይ የሚያካትተውን  እያንዳንዱ ነገር  ቀድሞ ከግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል ፡፡

ቀላልእና ገለልተኛ ቀለሞች

ቀለል ያሉ ነገሮችን መጠቀም የዘመናዊ ፈርኒቸር ዘይቤ ጉልህ ሀሳብ ሲሆን  የተለያየ አይነት ቀለም እና የግድግዳ ምስሎችን መጠቀም የዚህ አንዱ ማሳያ  ነው።

መለዋወጫዎች

በአሁኑ ጊዜ በእጅ የተሰሩ መለዋወጫዎችን እየጨመሩ የመጠቀም አዝማሚያ ያለ ፡፡ ንድፍ አውጪዎች እ.ኤ.አ. በ 1925 በፓሪስ ውስጥ በተካሄደ ዐውደ ርዕይ  ላይ (ኤክስፖዚሽን ኢንተርናሽናል ዴ አርትስ ዲኮራቲትስ  ኢንዱስትሪያል)  የዚህን እሳቤ ተግባራዊነት  አፅንኦት የሰጡበት ሲሆን እጅግ  አስፈላጊ ነው ብለውም  ያምናሉ።በዚህም የተነሳ አዳዲስ መለዋወጫዎችን ሲጨምሩ የቦታዎን ስፋት ከግምት ውስጥ ማስገባቱ ተገቢ  ሲሆን ከተገቢው በላይ በአንድ ቦታ ላይ ብዙ መለዋወጫዎችን ማድረግ አይመከርም ፡፡ ለክፍልዎ ልዩ ውበት ለመስጠት የተንጠለጠለ  ብርሃንን መጠቀምን   ዐውደ ርዕይ  አርት-ዲኮ አሳይቷል።

በዛ ያሉ(Maximalist)ንድፎች እና ቀለል ያሉ (Minimalist)ንድፎች

ለዓመታት አነስተኛ ንድፍን ከቀላል ቀለሞች ጋር በማዋሃድ ቀለል ያለ ንድፍ ያለው ዲዛይኖች እየተሰሩ መሆኑን እናውቃለን ፡፡ በቅርቡ ንድፍ አውጪዎች በዛ ያሉ ንድፎችን መጨመር ጀምረዋል ፡፡ ጊዜ እያለፈ ሲሄድ ይህ ሁለቱንም አቅጣጫዎች በአንድ ላይ የማቀላቀል አዝማሚያ እንደገና እየተለመደ መጥቷል፡፡ በተጨማሪም የቀለም አፍቃሪዎች የተለያዩ ቀለሞችን አንድ ላይ በማዋሃድ  አስደሳች ልዩ መንፈስን ለማከል ሲጠሩ ይታያል ፡፡እንዚህ የዘመናዊ ዲዛይን መርሆች እ.ኤ.አ. ከ1950 ዎቹ እና ከ 1960 ዎቹ አጋማሽ ምዕተ ዓመት ጀምሮ ተወዳጅ ሁነው ቀጥለዋል ፡፡ዘመናዊው ዲዛይን ለቤትዎ ትክክለኛ ምርጫ ከሆነ እና በቤትዎ ውስጥ ማካተት ተገቢ ሆኖ ካገኙት ከዲዛይን ባለሙያ ጋር  መነጋገር ጥሩ ይሆናል፡፡

የሽግግር ፈርኒቸሮች

በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ  የሚመረቱት ሁሉም የቤት ዕቃዎች ዘመናዊ አይደሉም ፣ ምክንያቱም ዛሬም ገበያው ላይ በርከት ያሉ የባህላዊ ንድፍ ውጤቶች አሁንም አሉ። በእርግጥ  በሁለቱ መካከል ያለ፤ ሁሉን ያማከለ  አጠቃላይ የንድፍ ዘይቤ አለ ይህም የሽግግር ፈርኒቸር የምንለው ነው ። እንደ መሸጋገሪያ ዲዛይን  ዘመናዊም ባህላዊም የሆኑ በርካታ ዘይቤዎችን አካቶ የያዘ ነው፡፡

Pin It on Pinterest

Share This