የቤት ቀለም ንድፍ ወይም የቀለም ስሌት መፍጠር ለቤትዎ ጥሩ የቀለም ዲዛይን እንዲኖርዎ  ያደርጋል ። እያንዳንዱ ክፍል የቀለም ንድፍ ወይም የቀለም ስሌት ሊኖረው ይገባል፡፡ ለቤት ውስጥ ዲዛይን ፕሮጀክት  ምን ዓይነት የቀለም ንድፍ መጠቀም እንደሚፈልጉ ካወቁ ትክክለኛውን አይነት ቀለም መምረጥ በጣም ቀላል ሂደት ሊሆን ይችላል ፡፡ የተሻለ የቀለም ንድፍ ወይም የቀለም ስሌት  እንዴት እንደሚመርጡ የሚያስችሎት ጠቃሚ ምክሮች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-

ለቤቴ የቀለም ንድፍ እንዴት መንደፍ እችላለሁ? የቀለም ንድፍ ለመምረጥ  ዝግጁ ነዎት? የቀለም ንድፈ ሀሳብ መሰረታዊ ነገሮች :-

የቀለም ንጣፍ(Pallette) መጠቀም

የቀለማት ንድፍን መምረጥ የቀለም ንጣፍ በመፍጠር ላይ የተመሠረተ ነው ፡፡ ለቤት ዲዛይን የሚሆን የቀለም ፓሌት ለአንድ ክፍል ጥሩ ስሜትን የመፍጠር  እና ግርማሞገስን የመስጠት ኃይል አለው፡፡ አንድ ክፍል የበለጠ ድምቀት ወይም ድብርትን ፣ ደስታን ወይም ትካዜ እንዲሰማዎ ሊያደርግ ይችላል። ለፈርኒቸሮች ፣ ለግድግዳዎች ፣ ለመስኮቶች በመረጧቸው ቀለሞች ላይ በመመርኮዝ ተመጣጣኝ እና ተስማሚ  የቀለም ህብረት መፍጠር ይችላሉ ፡፡

ምንዓይነትቀለሞችይማርካሉ?

ክፍሉ የእረፍት እና የመዝናኛ ቦታ እንዲሆን ይፈልጋሉ? ወይስ ለመዝናኛ እና ለማህበራዊ መስተጋብር የበለጠ ጥቅም ላይ  እንዲውል ይፈልጋሉ? ለእርስዎ በጣም ትርጉም ያለው የሳሎን ቀለም ሀሳቦችን ለማቀናጀት እነዚህን ጥያቄዎች እንደ መነሻ ይጠቀሙ ፡፡

ደብዘዛ እና ደማቅ ቀለሞች

በማስጌጥ መርሆች ውስጥ ካሉት የመጀመሪያ ምርጫዎች አንዱ ደማቅ እና ደብዘዛ ቀለሞችን መምረጥ መቻሉ ላይ ነው ፡፡  በደማቅ  እና በደብዘዛ  ቀለሞች ላይ ያለው ክርክር ወደ ግል ምርጫ ጉዳይ ስለሚወርድ ትክክል ወይም ስህተት የሚባል ነገር ሊኖር አይችልም ። ከዚህ በፊት የተሰሩ ፕሮጀክቶች ላይ አንዳንድ መረጃዎች  ማየት ደማቅ  እና ደብዘዛ  ቀለሞች  እንዴት እንደሚጠቀሙ ለማዎቅ ይረዱዎታል ፡፡በቀለም ፅንሰ-ሀሳብ ላይ ከ 1700 ዎቹ ጀምሮ በደማቅ  እና ደብዘዛ  ቀለሞች ላይ እየተደረገ ያለው ውይይት መቋጫ ያላገኘ ሁኗል ፡፡ ሞቃት ቀለሞች ከቢጫ እስከ ቀይ ያሉትን የሚያካትቱ ሲሆን ብዙውን ጊዜም ቡናማ ቀለሞችንም ይጨምራሉ፤በአንፃሩ ደብዘዛ  ቀለሞች ከሰማያዊ-ቫዮሌት እስከ ሰማያዊ-አረንጓዴ የሚያካትቱ ሲሆን ፤ አልፎ አልፎ  ግራጫ ቀለሞችም በዚህ ረድፍ ሲካተቱ ይታያል። በኪነጥበብ እና ዲዛይን ውስጥ ደማቅ  ቀለሞች የበለጠ ሳቢ ሆነው የሚታዩ ሲሆን  በአንጻሩ ደግሞ የደብዛዛ ቀለሞች ምርጫ እንብዛም ነው።

ደማቅ ቀለሞች :- ደማቅ  ቀለሞች ከቀይ ፣ ብርቱካናማ እና ቢጫ የመጀመሪያ ቀለሞች የተገኙ ሲሆኑ እንደ ፀሐይ ያለ የእሳት መሰል ሞቅ ያለ ስሜት ይፈጥራሉ።

ደብዘዛ ቀለሞች ፡- ደብዘዛ ቀለሞች ከእናት ቀለሞች ቫዮሌት ፣ ሰማያዊ እና አረንጓዴ የተገኙ  ሲሆኑ እንደ ውሃ ወይም አረንጓዴ  ያሉ ደብዛዛ  ቀለሞች በአንፃራዊነት የሚያረጋጉ ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡

የቀለምድምቀት

በኬልቪንስ የሚለካው የቀለም ድምቀት ጥናት ዘርፍ ትኩረት የሚሰጠው  የሳይንስ  አንዱ አንኳር የምርምር ዘርፍ ሲሆን ይህ ለቀለም ንድፍ ባለሙያዎች እጅግ ወሳኝ የምርምር ዘርፍን አካቷል፡፡ ደብዘዛ ቀለሞች ሰማያዊነት  ያላቸው እና ከ 5000 ኬልቪንስ በላይ ከፍ ያለ የቀለም ሙቀት ያላቸው ሲሆን ሞቃት ቀለሞች ቢጫነት  እና ከ3000 ኬልቪንስ  ያነሱ ልኬት ያላቸው ናቸው።

ክፍሉ ምን ዓይነት ብርሃን ያገኛል?

ለቤትዎ የቀለም ንድፍ ሲመርጡ ወደ ክፍልዎ ውስጥ የሚገባውን የተፈጥሮ ብርሃን ማሰብ ተገቢ ነው።ክፍሉ ብርሃን በሚያገኝበት አቅጣጫ ተንተርሰን፤ ክፍልዎ የትኛው ቀለም እንደሚስማማው እንመልከት፡-

ሀ-በሰሜን በኩል ያሉት ክፍሎች በጣም ጨለማማ ከሆኑ፣ ቀኑን ሙሉ ተንጸባርቆ የተመለሰውን(Diffused) ብርሃን ይቀበላሉ ፡፡ ይህ ዓይነቱ ብርሃን ደብዛዛ እና ጠቆር ያለ ይሆናል፡፡ ይህ ማለት ደብዛዛ ቀለሞች የበለጠ ፈዘዝ የማለት እድላቸው ከፍተኛ ሲሆን ፣ ነጣ ያሉት ደግሞ  ግራጫማ የመሆን አዝማሚያቸው ከፍ ያለ ነው። ደማቅ ቀለሞች  ከደብዛዛ  ቀለሞች በተሻለ ብርሃንን የማንጸረቅ ሀይላቸው ከፍተኛ ሲሆን  ይህም  ክፍሉን ለማድመቅ እና ለማስዋብ ይረዳል ፡፡

ለ-በምስራቅ በኩል ያሉ ክፍሎች የማለዳ ብርሃንን የሚቀበሉ ሲሆን ይህ ብርሃን ከእኩለ ቀን በፊት ሞቃታማ ቢጫ ወይም ግራጫ የመምሰል እድሉ ከፍተኛ ነው፤ ከዚያም ከእኩለ ቀን በኋላ ወደ ድብዛዛነት ይለወጣል። ክፍሉ ከእኩለ ቀን በኋላ ጥቅም ላይ ከዋለ ሞቃታማ ቀለሞች የብርሃን እጥረትን ሚዛን ለመጠበቅ ይረዳሉ።

ሐ.በስተ  ደቡብ ያሉ ክፍሎች ማለዳ እና ከቀትር በኋላ ብርሃን  እየተቀበሉ ከቀተር በኋላ የሚኖረው የክፍሉን ውበት ይጨምራሉ፡፡

መ.በስተ ምዕራብ ያሉት ክፍሎች ከሰዓት በኋላ ብርሃንን ሙሉ በሙሉ የሚቀበሉ ሲሆን  ማለዳ  ላይ ወደ ምዕራብ የዞሩ ክፍሎች ጥላማ እና ቀዝቃዛ ናቸው ፡፡ የእንደዚህ አይነት ክፍሎችን ሙቀት ለማመጣጠን ብርሃን የሚያንፀባርቁ ቀዝቃዛ ቀለሞችን መጠቀም ወይም ክፍሉ በማለዳ ጥቅም ላይ ከዋለ ደብዛዛ ቀይ ቀለም መጠቀም ይመረጣል።

በመጀመሪያ ምን መምረጥ አለብኝ?

በተወሰነ ቀለም ቤቶን ማቅለም ከጀመሩ በኋላ  የክፍልዎን ዙሪያ ገባ መመልከቱ የትኛውን የቀለም ምርጫ ቢጠቀሙ እንደሚሻል ይጠቁሞታ፤ ይህም ጥሩ የቀለም ህብርን ተግባራዊ ለመድረግ ይረዳዎታል፡፡የ 90/10 የቀለም ደንብንም መተግበሩ ይመከራል ይህም ማለት በክፍልዎ ውስጥ 90 ፐርሰንት ብርሃናማ ቀለም (ወይም የመረጡትን ቀለል ያለ ቀለም) ይጠቀሙ እንዲሁም 10 በመቶ ደግሞ ደማቅ እና ፍካትን የሚጨምሩ ቀለማትን ይጠቀሙ ፡፡

ፀሐይ እንዲገባ ያድርጉ

የጸሃይ ብርሃንን  ለማግኝት ሁላችንም ዕድለኞች ላንሆን እንችላለን ነገር ግን በቻሉት መጠን ክፍሎ የጸሃይ ብርሃንን እንዲያገኝ ቢያደርጉ የሚመረጥ ሲሆን በተጨማሪም በቀለማት ያሸበረቁ የመጽሐፍ መደርደሪያዎች  መጠቀሙም ተጨማሪ ውበት የመፍጠር አቅሙ ከፍተኛ ነው፡፡

Pin It on Pinterest

Share This