የቤት እቃዎቻችን ከብዙ ጥሬ አቃዎች በብዙ ዘዴ ላለፉት 30,000 ዓመታት እየተሰሩ ቢመጡም ለብዙ ዘመናት ገበያዉን ተቆጣጥረውት የሚገኙት የእንጨት ምርቶች ናቸው ።

እንጨት ለምን ?

ጠንካራ መሆኑ

በእርግጥ የእንጨት ምርቶች ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ ጠንካራ በመሆናቸው ከቤት መገልገያ ቁሳቁሶች ረጅም ዕድሜን ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው ትክክለኛ ምርጫ ናቸው፡፡ ለምሳሌ በአውስትራሊያ ኦክ  የተባለው የእንጨት አይነት በብዛት በጠንካራነቱና ለብዙ አገልግሎት የሚውል  በመሆኑ እንዲሁም ተፈጥሮአዊ መረጋጋትን የማስፈን አስተማማኝነቱ የተረጋገጠ በመሆኑ በብዛት ጥቅም ላይ ይውላል፡፡

ማርኪ መሆኑ

ቀለል ባሉ ቀለማት የበለፀጉ የእንጨት ውጤቶች ለማንኛውም ክፍል ውበት እና ሞገስን  የመጨመር አቅማቸው ከፍተኛ ስለሆነ በይበልጥ በሙያው በተካነ ባለሙያ በተለያየ የንድፍ ጥበብ መሰራት ቢችሉ እንደ አንድ የቤት መገልገያ ተጨማሪ ውበትና ግልጋሎት በመስጠት ረገድ የማይተካ ሚና ይኖራቸዋል፡፡ከእንጨት የተሠሩ የቤት ዕቃዎች የተፈጥሮአዊውን ዓለም ገፅታ በቤት ውስጥ የማሳየት ትልቅ አቅም አላቸው ለአብነት ያህል በበርካታ አፓርታማዎች የእንጨት ውጤቶች ተመራጭ  የሚሆኑት ይህንን  ተፈጥሮአዊ ውበትና ለማንጸባረቅ ነው፡፡

በተለያዩ አማራጭ መቅረቡ እና ሁለገብነቱ

ከብዙ ሌሎች የተፈጥሮ ፀጋዎች በተለየ እንጨት በማንኛውም ጊዜና ቦታ በገጠርም ሆነ በከተማ  በተለያየ መጠን እና የንድፍ አሰራር ተሰርቶ በብዛት ለአብዛኛው ማህበረሰብ ተደራሽ የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡

ታዳሽ በመሆኑ

በመጀመርያ ደረጃ እንጨት ለአከባቢ ጥበቃ ተስማሚ ነው ይህ ብቻም ሳይሆን የፀሃይ ግለትን በመከላከል፣የካርበን ልቀትን በመቆጣጠር የማይተካ ሚና ይጫወታል።ብዙዎች ዛፍን መቁረጥ ለአካባቢ ጠንቅ እንደሆነ ቢያውቁም በጥናት ላይ ተመስርቶ በመቁረጥ ጥቅም ላይ ማዋል የሚቻል ሲሆን ይህን ማድረግም ለደን ስነምህዳር መጎልበትም ራሱን የቻለ አዎንታዊ ሚና ይጫወታል፡፡ ለምሳሌ በአውሮፓ በዓመት በ 5,000 ካሬ ሜትር ዛፎች በተመነጠሩበት ወቅት አዳዲስ ዛፎች ሊተከሉ ችለዋል፤ ይህ በመሆኑም  እ.ኤ.አ. ከ1990-2005 ብቻ አውሮፓ የግሪክን የቆዳ ስፋት ሊሸፍኑ የሚችሉ ደኖችን አስተዳድራለች፡፡

ከመቼ ጀምሮ ?

በ አርኪዮሎጂ ጥናት እንደተረጋገጠው ለመጀመርያ ግዜ በእንጨት የተሰሩ የቤት እቃዎችን መጠቀም የተጀመረው በጥንታውያን ሜሶፖታማውያን ነው። በነዚህ ግዜያት በነበራቸው ዉበት እና ምቾት በንጉሳውያን ቤተሰቦች ካልሆነ  በስተቀር በሁሉም ቦታ የሚገኙ እንዳልነበረ ታሪክ ያስረዳል።በዚህ መልክ የተጀመረው የእንጨት ስራ የሰው ልጅ የስልጣኔ መለኪያ እና መገለጫ እስኪሆን ድረስ እያደገ አሁን እስካለንበት ዘመን ደርሷል። በተለይ ከ 1900 አጋማሽ በኋላ ከዛ በፊት የነበሩትን አሰራሮችን አና የእንጨት አይነቶችን በመቀየራቸው የእንጨት ስራ ውድ እና ብርቅ እንዲሆን አስችሎታል።በአሁኑ ጊዜ ግን ብዙዎቹ የቤት እቃዎች እየተሰሩ ያሉት ከጥድ፣ከሙጫ ዛፍ ከመሳሰሉት በቀላሉ ሊገኙ ከሚችሉ እና ውድ ካልሆኑ የእንጨት አይነቶች ሲሆን እንደ  ለውዝ እንጨት፣ ማሆንጋይ ያሉ እንጨቶች ለተለዩ እና ለተመረጡ አገልግሎቶች ካልሆኑ በቀር በብዛት አይታዩም።

የእንጨት አይነቶች

ብዙ ጊዜ አንድ እቃ ከምን አይነት እንጨት እንደተሰራ ለማወቅ ከባድ በመሆኑ ብዙዎቻችን በቤታችን ውስጥያሉ የቤት እቃዎች ከምን አይነት እንጨት እንደተሰሩ አለማወቃችን አያስገርምም ምክንያቱም የትኛውም አይነት እንጨት ለቤት እቃ መስሪያነት ሊያገለግል ይችላል ነገር ግን እንጨቶች ባሉዋቸው የተለያየ ዉበት፣የመቆየት እድሜ፣ለመስራት ምቹነት እና እንደ ተጠቃሚ ከኛ ጋር ለአመታት ሊቆዩ የሚችሉ እና የትዝታቻችን አካል ስለሆኑ የምንገዛቸው የቤት ንብረቶቻችን የተሰሩበት እንጨት ፀባይ ማወቅ እና የትኛው እንጨት ለየተኛው መገልገያነት እንደሚውል ማወቅ የእቃዎቻችንን ትክክለኛ ዋጋ እንድናውቅ ይረዳናል። ማን ያውቃል ልንለውጠው የፈለግነው የድሮ ንብረት አሁን ላይ የማይገኝ እና ውድ ከሆነ እንጨት የተሰራ ሊሆን ይችላል ስለዚህ ንብረቶቻችን የተሚሰሩባቸውን እንጨት ጥንካሬ፣ ቀለም፣የመሳሰሉ ባህሪያት ማወቅ ጠቃሚ ነው።

የእንጨት ባህሪያት

እንጨት ጥንካሬ፣ ቀለም ፣ ህዋሳዊ መዋቅር  የተባሉ 3 መሰረታዊ ባህሪያት አሉት። የአንድ እንጨት ቀላሉ መገለጫ ጠንካራ እንጨት(ሃርድውድ) ነው ወይስ ለስላሳ እንጨት(ሶፍትውድ) የሚለው ነው መስፈርት ሲሆን ነገር ግን በዚህ ዘርፍ ባልሰለጠነ ዓይን ይህን መለየት ስህተት ሊሆን ይችላል ምክንያቱም ሁሉም ጠንካራ እንጨቶች ጠንካራ ላይሆኑ ይችላሉ በዚህ ምክንያት ነው ስነ-እፅዋታዊ ባልሆነ መንገድ በማየት ብቻ መለየት አዳጋች የሚሆነው።ባጠቃላይ ጠንካራ እንጨቶች ከአበባማ ተክሎች ሲገኙ ለስላሳ እንጨቶች ደሞ ከኮንፈርን ይገኛሉ።ሌላው በልማዳዊ አገባብ እንጨትን የምንለየው በቀለሙ እና በህዋሳዊ መዋቅሩ ነው። የእንጨቱ ህዋስ(cell) ትልቅ ሲሆን ሻካራ እና ክፍተት የበዛበት ሊሆን ስለሚችል ሻካራዉን የሚያለሰልስ እና ክፍተቱን የሚሞላልን መሳርያ ሊያስፈልገን ይችላል።ህዋሱ ደቃቅ ሲሆን ደሞ እንጨቱ ለስላሳ ይሆናል።የእንጨት ቀለምም ከነጭ እና ቢጫ እስከ ቀይ፣ሃምራዊ እና ጥቁር ተብሎ ሊዘረዘር ይችላል።ይህም እንደ ሌለቹ ባህርያት ሁሉ የእንጨቱን ዋጋ እና ዓይነት ሊወስን ይችላል።

የተለያዩ የእንጨት አይነቶች

የእንጨት አይነቶችን መለየት መጀመርያ ከባድ ቢመስልም በዘርፉ ልምድ እያካበተ ለሄደ ሰው  ነገሩ ቀላል አየሆነ ይሄዳል።የዘርፉ ባለሙያዎች በመዳሰስ፣በማሽተት፣በቀለሙ እና በመዋቅራዊ ቅርፁ በቀላሉ ይለዩታል። የእንጨትን አይነት ለማወቅ ስንፈልግ የእንጨቱን እድሜ፣ ሞድ እና መዋቅራዊ ቅርፁን መመርመር አስፈላጊ ሆኖ የእንጨቱን ሽፋን ማየትም ችላ ሊባል የማይገባ ነገር ነው ነው። በአሁኑ ሰዓት የተለያዩ ቀጫጭን ተለጣፊ የእንጨት ሽፋኖች በብዛት በበርካታ የፈርኒቸር ምርቶች ላይ የሚስተዋሉ ሲሆን ለዚህም ዋነኛው ምክንያት ደረቅ እና ጠንካራ እንጨቶች ውድ እና የማይገኙ በመሆናቸው ነው፡፡ ስለዚህም ይህንን አይነት ሽፋን ያለውን መገልገያ ስንሸምት በቀላሉ ሊሰበር ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ አለብን።በተጨማሪም የምርቶቹን ዋጋ ለመቀነስ ሲባል ሁለትና ከዛ በላይ የሆኑ በጥንካሬ እና በጥራት የሚለያዩ የእንጨት ዝርያዎችን በማጣመር መስራት እየተለመደ መጥቷል ስለሆነም እነዚህ ምርቶችም የጥራት ጉደለት ሊያጋጥማቸው ስለሚችል ጥንቃቄ መውሰድ ያስፈልጋል፡፡ ሁሉም ሰው የየራሱ የሆነ የእጅ ኣሻራ እንዳለው ሁሉ እፅዋትም የየራሳቸው የሆነ ባህርያት እና ምልክት ያላቸው ሲሆን በብዛት ከምንጠቀማቸው የእንጨት አይነቶች ማካከል፡-

ለውዝ(Walnut )

የለውዝ እንጨት ጠንካራ፣ ለረዥም ግዜ ሊቆይ የሚችል፣በጌጥ በተንቆጠቆጡ እና የላቀ ጥበብ ለሚጠቀሙ እቃዎች ተመራጭ የሆነ እና ባለው ዘላቂነት ምክንያትም በአንደኛው የ ዓለም ጦርነት ወቅት ለአውሮፕላን መስሪያነት ያገለገለ እንዲሁም ከትውልድ ወደ ትውልድ በቀላሉ ሊተላለፉ የሚችሉ ቁሳቁሶችን ለመስራት ተመራጭ የሆነ ተፈላጊ የእንጨት አይነት ነው።

ጥቁር እንጨት

ይህ ዘላቂ ጠንካራ እንጨት ሲሆን ብዙ ግዜ ውስብስብ ቅርፃቅርፆችን ለመስራት ይጠቅማል።በተጨማሪም ረጅም ቁመት ያለው በመሆኑ እንደ ምግብ መመገቢያ ጠረጴዛዎች በተጨማሪም ሰሌዳዎችን ለመስራት ተመራጭ ሲሆን ጥሩ እንክብካቤ ከተደረገለት ደግሞ ለብዙ አመታት ሳይበላሽ መቆየት የሚችል እና ግዜ በማይሽረው ገፅታው  ለቤት ውበት ማጎናፀፍ የሚችል ነው።

በሉጥ(Oak)

ለማደግ ብዙ ግዜ የሚፈጅው ይሀ እንጨት ባለው ጠንካራ እፍጋት ምክንያት ጥራት ያለው እና ረዥም ጊዜ ሊቆይ የሚችል  ጣውላ ለመስራት ይጠቅማል።

ሽምበቆ(Bamboo)

ሽምበቆ ከከባቢ አየር ጋር ባለው ተግባቦት እና ውብ በሆነ ፈዛዛ ቢጫ ቀለም የሚታወቅ ነው፤ ከእንጨት ይልቅ ሳር ለመባል የቀረበ እና ከሌሎቹ እንጨቶች አንፃር 10 ግዜ ተሎ የሚያድገው ይህ የእንጨት አይነት ለቤት ውስጣዊ ክፍል ጌማስጌጫነት በብዛት ጥቅም ላይ ይውላል።

ኦልም(Elm)

ኦልም ጥሩ የመተጣጠፍ ባህርይ ያለው ጠንካራ እንጨት ሲሆን ለሁሉም አይነት ቁሳቁሶች መስሪያነት ሊያገለግል የሚችል ቡናማ ቀለም ያለው ሲሆን ውድ እና በቀላሉ የማይገኝ እንጨትም ነው።

የሻይ ዛፍ (Tea)

ይሄ አይነቱ እንጨት በእጅ ጥበብ ለሚሰሩ እቃዎች ተመራጭ ሲሆን ከ ወርቃማ ቢጫ እስከ ጥቁር ቡናማ አይነት ቀለም የሚገኝ በጣም ውድ የእንጨት አይነት ነው።

ሾላ( Sycamore)

በሰፊው ጥቅም ላይ የሚውል ዋጋውም ውድ ያልሆነ የእንጨት ኣይነት ሲሆን  በቀላሉ የማይሰበር በመሆኑ ለልኳንዳ ቤት ጣውላ መስርያነት ተመራጭ የሆነ እና በቀላል የእጅ መሳርያ ጭምርም  ሊሰራ የሚችል ነው።

Rosewood

እንደ ጥቁር እንጨት በጣም ተፈላጊ እና በጣም ውድ የሆነ የ እንጨት ኣይነት ሲሆን በቀላል ማሽኖች ለመስራት የሚያስቸግር በጥካሬም ሻል  ያሉ ማሽኖችን በመጠቀም ደርዝ ሊወጣለት የሚችል የእንጨት አይነት ነው።

Redwood (ቀይ ቅጠላማ ዛፎች)

በርካታ ግልጋሎት የሚሰጡ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለመስራት  የሚያገለግል በቀላሉ ሊለይ የሚችል ለስላሳ የእንጨት አይነት ነው፤በጣም ጠንካራ የማይባለው ይህ የእንጨት አይነት በእጅ ማሽኖችም ጭምር ሊሰራ የሚችል ነው።

ፒካን(Pecan)

ለምግብ ጠረጴዛ እና ለቢሮ እቃዎች መስሪያነት የሚያገለግል ጠንካራ የእንጨት አይነት ነው፤በተጨማሪም በእጅ ማሽኖች ሊሰራ የማይችል እና ዋጋውም ማሃከለኛ የሚባል ነው።

ዝግባ(Cedar)

ለስላሳ እንጨት ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ለቁም ሳጥን መስሪያነት በቀዳሚነት የሚመረጥ ነው፤በተጨማሪም ባለው የተለየ ተፈጥሮአዊ ስጦታ እንጨትን የሚያበላሹ  ነፍሳትን ለመከላከልም ይመረጣል::

Hickory

በጥንካሬው እና ክብደቱ የሚታወቅ ጠንካራ የእንጨት አይነት ሲሆን በመጠንም ተለቅ ያሉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለመያዣነት ተመራጭ የሆነ በዋጋ ደረጃም ያን ያህል ውድ የማይባል የእንጨት አይነት ነው፡፡

Gum

በብዛት ከተለያዩ የእንጨት አይነቶች ጋር በመጣመር  ለእቃ መያዣነት የሚውሉ ቁሳቁሶችን ለመስራት የሚያገለግል ዋጋውም ከሌሎች አንፃር ርካሽ ሊባል የሚችል የእንጨት አይነት ነው።

Cherry

በጣም ማራኪ እና ልዩ  አወቃቀር ያለው ይህ የእንጨት አይነት ለካቢኔቶች መስሪያነት ተመራጭ ሲሆን አገልግሎት ላይ ለማዋል እና ለመስራት ግን አቅም የሚፈትን እና በዋጋ ደረጃም ውድ የሚባል አይነት ነው።

Butternet

ውድ ዋጋ አላቸው ከሚባሉ የእንጨት አይነቶች የሚመደብ ጠንካራ የእንጨት አይነት ሲሆን “White Buterrnet “በመባልም ይታወቃል በክብደትም ቢሆን ቀለል ያለ እና ለመስራትም ምቹ ነው::

BeechWood

በቀላሉ የሚታጠፍ ጠንካራ የእንጨት አይነት ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ በጣም ዉድ ለሆኑ ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች እና ለካቢኔት እና መሰል ቁሳቁሶች መስርያነት የሚያገለግል ሲሆን በባህርዩም በጣም ጠንካራ እና ለመስራት እጅግ አስቸጋሪ የሚባል ዉድ ያልሆነ የእንጨት አይነት ነው።

Pin It on Pinterest

Share This