አነስተኛ አፓርታማዎች ፣ የህዝብ ብዛት መጨመር እና የከተማ መኖሪያ ቤቶች እድገት ውጤት ናቸው። የገበያው ዋጋ እና የከተማ መስፋፋት ሰዎችን ወደ ጠባብ መኖሪያ ስፍራ ይገፋቸዋል። የሰዎች ፍላጎት ይበልጥ እየናረ ይገኛል። የቦታ መጥበብ በዚያ የሚኖሩ ሰዎችን እንዴት ይጎዳል?

የተለያዩ ፅሁፎች ከቤቶች ልማት ጋር ተያይዞ ሊመጣ የሚችለውን የጤና እክል እየተወያዩበትና እያሰመሩበት ይገኛሉ።የቤት ዕቃዎች ቅንጦት ሳይሆኑ ለኑሮ የግድ አስፈላጊ በመሆናቸው ለሁሉም ሰው ያስፈልጋሉ ምክንያቱም  ከመደበኛ የወለል ስፋት 50% የሚሆነውን ይሸፍናሉና። በመሆኑም በጠባብ ስፍራ ለመኖር ጥሩ እና ቦታ የማይፈጁ የቤት እቃዎችን መጠቀም ደህንነቱ የተጠበቀ ኑሮንም ማስቀጠል ላይ ትኩረት ያስደርጋል። ይህ ፅሁፍ በቤት-ዕቃዎች፣ትናንሽ አፓርታማዎችና ደህንነቱ በተጠበቀ የሰው ኑሮ መካከል ያለውን ዝምድና ለማጥናት ይሞክራል። እንደ የከተማ ቤቶች ልማት፣የህዝብ ቁጥር መጨመር፣የቤት-ዕቃዎች እና መሰረታዊ የሰው ፍላጎቶች ተጠንተዋል። በመሃላቸው ያለው ግንኙነትም የሚብራራ ይሆናል።

መግቢያ

ህብረተሰቡ እያደገ ባለው ከተሜነት እና የህዝብ ቁጥር መጨመር እየተጎዳ ነው። (ተ.መ.ድ 2014) ይህም በከተሞች አካባቢ የቤቶች ፍላጎት እንዲጨምር ያደረገ ሲሆን በመጠን ትንሽ ለሆኑ አፓርታማዎችና ከፍ ላለ የገበያ ዋጋ መምጣትም አስተዋፅኦ አድርጓል።አነስተኛ አፓርታማ ስንል የሚፈጥረው ምስል ሙሉበሙሉ ተለውጧል። ከ 30 አመታት በፊት ገደማ አነስተኛ አፓርታማዎች 55 ስኼር ሜትር የወለል ስፋት ያቀርቡ ነበር። ዛሬ ግን ከ10 እስከ 15 ስኼር ሜትር የሚሆኑ አፓርታማዎች እየተሸጡ ነው። የቤት-ዕቃዎች እና የግል ንብረቶች በፊት የሚወስዱትን ቦታ አሁንም ይወስዳሉ። የከተማ ቤቶች ልማት ዜጎች ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ የሚገኝ ሲሆን በአነስተኛ ቦታዎች እንዲኖሩም አስገድዷል። በዙሪያችን ያለው ቦታ ለመኖሪያ ቦታ ያለን እሳቤ ላይ ተፅዕኖ ያደርጋል። የቤቶች ልማት እንዴት የሰዎችን ደህንነት ያቃውሳል?

የሰዎች ፍላጎት እንደ በፊቱ ወይም ከዚያም በላይ ሁኗል። የሰዎችን ደህንነት ለመፍጠር ብዙ መስተዳደር እና መሟላት ያለባቸው መሰረታዊ ፍላጎቶች አሉ። 

 የከተማ ቤቶች ልማት

በጠባብ ቦታ መኖር አዲስ ክስተት አይደለም። ለረጅም አመታት ሰዎች በአነስተኛ አፓርታማዎች ኖረዋል። ለዚህ ዋና ምክንያት በትላልቅ ከተሞች ያለው የህዝብ እፍጋት ነው። እንደ ተ.መ.ድ የ2014 ገለፃ በትላልቅ ከተሞች የሚኖረው ህዝብ ብዛት በ2050 በ66% የጨምራል።የከተማ ህዝብ ብዛት መጨመር ለአነስተኛ መኖሪያ ቦታዎች ምክንያት ሲሆን ይህንን ተከትሎም ከፍተኛ የአፓርታማዎች ፍላጎት ይከሰታል። ይህ በተለይም በምዕራቡ አለም ትልቅ ጉዳይ ሲሆን መፍትሄ የሚሉትም አነስተኛ አፓርታማዎችን መጠቀም ነው።

አነስተኛ አፓርትመንቶች

የባለ አንድ መኝታ አፓርታማዎች ስፋት ከ7-10 ስኼር ሜትር የገመታል። በዚህ የአፓርታማ ፍላጎት መጨመር ምክንያት አብዛኞቹ አነስተኛ አፓርታማዎች 1 ወይም 2 ክፍሎች አላቸው። የሲንቴፍ ጥናት እንደሚገልፀው ከሆነ ትናንሽ አፓርታማዎች የጥራት ጉድለት አለባቸው። እነዚህም ፡-

  • መግቢያ በሮች አይኖሩም ወይም በጣም ትንሽ ይሆናሉ
  • በጣም ትንሽ የመጋዘን ስፍራ
  • በጣም ትንሽ የማብሰያ ቦታ
  • መደበኛ ቦታ የሌለው መኝታቤት
  • ለአካል ጉዳተኞች በቀላሉ ተደራሽ አለመሆን

ለግንባታ የሚጠይቀው ጥሬ-ዕቃ ብዛት አነስተኛ መሆኑ ብቸኛ የአነስተኛ አፓርትመንቶች ጥሩ ጎን ሆኖ ከአካባቢ ጥበቃ አንጻር ሊታይ ይችላል።

የቤት-ዕቃዎች

እንደ እንጨት ሳይንስ ፕሮፌሰሩ ካርል ኢክልማን የቤት-ዕቃ ከሰው ውድ ንብረቶች መካከል አንዱ ነው።”ይቀመጥበታል፣ይተኛበታል፣የመገብበታል፣ ምናልባትም በጣም ዋጋ የሚሰጠውን ንብረቱን በውስጡ ሊያስቀምጥ ይችላል”።የቤት-ዕቃ በተለያየ ቅርጽ እና መጠን እንደ ጥቅም እና አገልግሎቱ ሊገኝ ይችላል።

የቤት ዕቃዎች በአፓርታማ ውስጥ

የቤት-ዕቃ(ፈርኒቸሮች) የአንድ አፓርታማ በጣም አስፈላጊ አካል ነው። ቶገርሰን በ2017 ያጠናው ጥናት የትኛው የፈርኒቸር ውጤቶች በሰዎች መኖሪያ በተለይም በባለአንድ-መኝታ አፓርታማ ውስጥ የተለመደ እንደሆነ ያሳያል። አልጋ፣ቁምሳጥን፣ጠረጴዛ፣መፅሀፍ መደርደሪያ፣ወንበር፣ኮመዲኖ፣ሶፋ እንደ ቅደም ተከተላቸው ዋና የተለመዱ የቤት-ዕቃዎች ናቸው።በአነስተኛ አፓርትመንቶች ልማት ምክንያት መሰረታዊ የቤት-ዕቃዎችን በመኖሪያ ስፍራ ለማስቀመጥ አስቸጋሪ ሆኗል። በመሆኑም የጥሩ እና ቦታ ቆጣቢ የቤት-ዕቃዎች ፍላጎት ጨምሯል። የቤት-ዕቃዎችን ዕድገት ከሚያሳዩ ምሳሌዎች መካከል የአልጋ ስፋት አንዱ ነው። እ.አ.አ በዘጠናዎቹ የተለመደ የአልጋ ርዝመት 200ሳ.ሜ ሲሆን ዛሬ ግን 210-220ሳ.ሜ ሆኗል። እነዚህ በአንድ ላይ ከከተማ ቤቶች ልማት ጋር ጥሩ መገጣጠም አይፈጥሩም ምክንያቱም አፓርታማዎች በመጠን እያነሱ የቤት-ዕቃዎች ግን እየጨመሩ ይገኛሉና ።

የጊዜው መፍትሄዎች

ጥናቶች እንደሚያሳዩት የቦታ ጥበት ችግርን ለመፍታት መንገዶች አሉ። ቢሆንም ትናንሽ መኖሪያ ስፍራዎችን ከመጠነኛ የፈርኒቸር ውጤቶችጋር ያካተቱ አዳዲስ አሳቦች ያስፈልጋሉ። ብዙ አገልግሎት የሚሰጡ፣ተገጣጣሚ እና በልዩ ንድፍ የሚሰሩ ፍርኒቸሮች  ጥቅም ላይ እየዋሉ ሲሆን ሁሉም መፍትሄዎች ቦታን በመቆጠብና ቦታ አጠቃቀምን በማሻሻል ላይ ያተኩራሉ። 

ብዙ አገልግሎት የሚሰጡ የቤት-ዕቃዎች

ከስያሜያቸው እንደምንረዳው የእነዚህ የቤት-ዕቃዎች ዋና አሳብ ከአንድ በላይ አገልግሎት መስጠት ነው። በገበያ ላይ የተለያየ ስሪት ያላቸው  የቤት-ዕቃዎች ያሉ ሲሆን ለምሳሌ ያህል እንደ መፅሀፍ መደርደሪያ፣ ዕቃ ማስቀመጫ፣ ጠረጴዛና ወንበር ሆኖ ማገልገል የሚችለውን ምርት መጥቀስ ይችላል።

Pin It on Pinterest

Share This