ወንበሮች ረዘም ላለ ጊዜ በቤታችን፣በስራ ቦታ እንዲሁም በተለያዩ  ቦታዎች ዘወትር የምንጠቀምባቸው መገልገያዎች በመሆናቸው ከጤና አንጻር ተስማሚውን የወንበር አይነት መምረጥ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡  የኮርኔል ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ባደረጉት ጥናት መሠረት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ሠራተኞች በጀርባ ወይም ከወንበር ጋር በተያያዘ ህመም  ይሰቃያሉ፡፡በሌሎች ኢንዱስትሪዎች ወይም ዘርፎች ከሚሰሩ ሰራተኞች ይልቅ ቢሮ ውስጥ ለረዥም ጊዜ በመቀመጥ ስራቸውን በሚያከናውኑ ሰራተኞች  ላይ የጀርባ ህመም በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚታይ ጥናቱ ይጠቁማል ፡፡ በቀን ውስጥ እስከ ስምንት ሰዓት መቀመጥ ለጀርባ ህመም ሊያጋልጥ የሚችል ሲሆን ይህም የሆነበት ምክንያት ለረዥም ጊዜ መቀመጥ በ 300% እንተርስቴብራል ዲስኮች ላይ ጫና ስለሚጨምር ነው ፡፡ውጤታማነትን ለመጨመር እና የጀርባ ህመምን ለመቀነስ ፤ ኢርጎኖሚካል የስራ ቦታ መፍጠር እንዲሁም ከፍተኛ ጥራት ያለው የቢሮ ወንበር ላይ ኢንቬስት ማድረግ ተገቢ ነው ፡፡ ለዛሬው ስለ ሂፕ(ከፍታ ያላቸው) ወንበሮች ልንነግራችሁ ወደድን :-

ሂፕ ወንበሮች

የሰው እድሜ እየጨመረ በሄደ ቁጥር መገጣጠሚያዎች እና የተወሰኑ የሰውነት ክፍሎች መደበኛ የሆነውን እና የተለመደውን አገልግሎት መስጠት ስለማይችሉ፤ የዕለት ተዕለት ኑሯችንን ለመቀጠል አዳጋች ይሆናል ግፋ ሲልም የሂፕ ቀዶ ጥገናዎች አስፈላጊ ሊሆኑ ይችላሉ።በማገገሚያ ወቅት በሂፕ ህመም ላይ ለሚሰቃዩ ሰዎች ሂፕ ወንበሮችን መጠቀም ህመም ለመቀነሰ ይመከራሉ፡፡በአሰራር ደረጃ ከፍ ብለው የሚሰሩት  እነዚህ ወንበሮች አካል ጉዳተኞች በነጻነት ተቀምጠው ከሌሎች ወዳጆቻቸው ጋር ጊዜ የሚያሳልፉበትን ምቾት የሚሰጡ ሲሆን በህመሙ የሚሰቃዩ ሰዎችን ያካተቱ  መደበኛ ዲዛይን ያላቸው ሂፕ ወንበሮች  በሆስፒታሎች ፣ በክሊኒኮች፣በመዝናኛ ስፍራዎች ፣ በምግብ ቤቶች፣በትምህርት ቤቶች እንዲሁም በመኖሪያ ስፍራ መኖራቸው አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ፡፡

በሂፕ ወንበሮች የሚጠቀሙት እነማን ናቸው ?

የሂፕ ወንበሮች በተለይ ሂፕቲካል ቀዶ ጥገና ለተደረገላቸው ሰዎች በቶሎ ለማገገም የተሰሩ ወንበሮች ናቸው ፡፡ የሂፕ ወንበሮች ከተለምዷዊው ወንበር ከፍ ያሉ ሲሆኑ ይህም የሆነበት ምክንያት፤በማገገም ላይ ያሉ ሰዎች በቀላሉ መነሳት እና መቀመጥ እንዲችሉ ለማስቻል ነው፡፡ ከፍ ያለ(ሂፕ) ወንበር የሰውነትን ክብደት ከጉልበት ላይ በማስወገድ ምቾት ይፈጥራል ፡፡ለመቀመጥ ወይም ለመቆም አስቸጋሪ የሆኑ የሂፕ እና የጉልበት አርትራይተስ ወይም ሌሎች የጤና እክሎች ላለባቸው ሰዎች  ሂፕ(ከፍ ያሉ)  ወንበሮች ቀዳሚ ምርጫቸው እንዲሆኑ ይመከራሉ፡፡ መታጠቢያ ቤትን ጨምሮ የሂፕ ወንበሮች ለተለያየ ዕለታዊ አገልግሎት እንዲውሉ ተደርገው የተሰሩ በመሆናቸው ለአረጋውያን ሂፕ ወንበሮች ከሌሎች ወንበሮች በተሻለ ሁኔታ ብዙ ጥቅሞችን ያስገኛሉ ፡፡ በቀላሉ መርዘም እና ማጠር  እንዲችሉ ተደርገው የተሰሩት እነዚህ ወንበሮች ሰዎች በቀላል በሚፈልጉት ሁኔታ እንዲገለገሉባቸው የሚያስችሉ ሲሆን በተለይም  በመታጠቢያ ቤት ውስጥ የሂፕ(ከፍታ ያለው) ወንበሮችን መጠቀም አረጋውያንን ተንከባካበው ለማጠብ ወይም ብዙ ሳይደክሙ ራሳቸውን ችለው እንዲገለገሉ ይረዳሉ ፡፡

የሂፕ ወንበሮች ሽንጣቸውን፣ዳሌያቸውን እንዲሁም ወገባቸውን ለተጎዱ ወይም ለረጅም ጊዜ በጉልበት ህመም ለሚሰቃዩ ሰዎች ለመርዳት ሲባል የተሰሩ ሲሆኑ ያለምንም አጋዥ ቁጭ ብለው በቀላሉ መነሳት እንዲችሉ ያግዛሉ፡፡ ለምሳሌ፤ የሂፕ ወንበሮች የሂፕ ቀዶጥገና ለተደረገለት  ሰው የጭን ጡንቻዎቹን ከመጠን በላይ እንዲጠቀሙ አይጠይቅም  ምክንያቱም ከፍታ ያለውን ወንበር እራሳቸው በመግፋት መነሳትና መቀመት ይችላሉ፡፡ አዛውንቶች፣በሂፕ ህመም የሚሠቃዩ  እንዲሁም ተመሳሳይ ችግር ያለባቸው ሰዎች በሂፕ ወንበር ላይ ቢቀመጡ የተሻለ አገልግሎት ያገኛሉ፡፡ብዙ የሂፕ ወንበሮች ተንቀሳቃሽ  በመሆናቸው  ከወዳጅዎ ጋር  ለመመገብ እና ለመሰል አገልግሎት  ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ ሲሆን በምቾት  መቆየት ጊዜዎን በደስታ እንዲያሳልፉ እና ከሌሎች ወዳጅዎ ጋር አዎንታዊ ግንኙነቶችን እንዲያስቀጥሉ ያስችልዎታል።

ሂፕ ወንበሮች በሕክምና ክፍሎች

የህክምና ባለሙያዎች ከቀዶ ጥገና በኋላ መልሶ የማገገምን ሂደት ለማቀላጠፍ ተገቢውን መሳሪያዎች መጠቀም የሚመክሩ ሲሆን በቶሎ መፈወስ የሚቻልበት  አንደኛው መንገድ  የሂፕ ወንበሮችን መጠቀም እንደሆነ አፅንኦት ይሰጡበታል፡፡ ስለሆነም እነዚህን ቁሳቁሶች በሀኪም ቤት ወይም በፊዚካል ቴራፒ ቢሮዎች ውስጥ ማካተት ተገልጋዮች ምቾት እንዲሰማቸው እና ለስራ ቅልጥፍና ያግዛሉ፡፡ለምሳሌ በተለያዩ ቢሮዎች ውስጥ ታካሚዎች ለብዙ ሰአታት ቁጭ ብለው ይቆያሉ፤እንዲሁም ቅጾችን ለመሙላት ወይም በአካል ምርመራዎች ለማካሄድ በተደጋጋሚ ከወንበሮች መነሳት ይኖርባቸው ይሆናል፤ስለዚህ በሕክምና ክፍሎውስጥ የሂፕ ወንበሮችን ማካተት ለታካሚዎች በየደረጃው ስለሚሰጡት የአገልግሎት ጥራት እንደሚጨነቁ ከማሳየት በተጨማሪ እነዚህን ወንበሮች በህክም ክፍልዎ  ውስጥ ማኖሩ ስራዎን በአግባቡ እንዲዎጡ ያግዝዎታል፤እንዲሁም የተገልጋዩን  ምቾትና እና ደህንነቱ የተጠበቀ እንደሚሆን ያደርጋል፡፡የሠውነት ክብደት በሰውነት ውስጥ በእኩል መሰጨት በአንገት፣በትከሻ እንዲሁም በጀርባ ላይ ያለው ክብደት መጣጠን የጤናማ ሰውነት ሂደት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ስለዚህም በጀርባ ላይ የሚኖርን የአከርካሪ መጨፍለቅን ለመከላከል የሂፕ ወንበሮችን መጠቀም ይመረጣል፡፡

በቢሮዎች ውስጥ

በተደጋጋሚ ወይም አልፎ አልፎ በሚከሰት የሆድ ህመም የሚሠቃዩ ሰዎች ከፍ ባለ(ሂፕ) ወንበር ላይ እንዲቀመጡ ይመከራል ፡፡በስራ ቦታ ለብዙ ሰዓታት በመቀመጥ የእለት ተእለት ተግባርን ማከናወን የተለመደ ሂደት ሲሆን  ይህም ህመሙ ያለበትን ሰው ለበለጠ ጉዳት ይዳርጋል፡፡ስለሆነም ይህንን ሁኔታ ለመቀነስ እነዚህን ወንበሮች በስራ ቦታ መጠቀም ምርታማነትን ይጨምራል፡፡

በሌሎች ስፍራዎች

ከሥራ ቦታ በተጨማሪ የሂፕ ወንበሮች እንደ ምግብ ቤቶች እና መኖሪያ ቤቶች ባሉ ቦታዎች መጠቀም  ጥሩ አማራጭ ሲሆን በምግብ ቤቶች አከባቢ ለደንበኞች ምቾት ሲባል መጠቀሙ ይመከራል፤ የተለያዩ የሂፕ ችግር ላለባቸው ተጠቃሚዎችም እነዚህን ወንበሮችን ማዘጋጀት ተገቢ ነው ፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በውበት ሳሎን ውስጥ  ለደንበኞች  የሂፕ ወንበሮችን ማዘጋጀት ለስራዎ ቀልጣፋነት ይረዳል ፡፡አሁን በሂፕ ወንበሮች ላይ ኢንቬስት የማድረግ ጥቅሞችን ካወቁ ፤ በተለያየ ስፍራ የሚጠቀሙባቸውን የወንበርዎን ምርጫ ይመልከቱ፤በወንበር ላይ ሲወስኑ ፍላጎቶችዎን ያስቡ፡፡ ለዕለት ተዕለት አገልግሎት እነዚ ወንበሮች ያስፈልጎታል? በአርትራይተስ ህመም ይሰቃያሉ? ከቀዶ ጥገና ህክም በቶሎ ለማገገም  እና ለሌሎች ስፍራዎችም እንዲረዶት እነዚህን ወንበሮች ይጠቀሙ፡፡

Pin It on Pinterest

Share This