የመኖሪያ ቦታን ምቹ እና ጽዱ ለማድረግ እንዲሁም ውጤታማነትን ለመጨመር፤ ትክክለኛውን እና ተገቢውን ፈርኒቸር መምረጥ ቁልፉ ነገር ነዉ።ተገቢውን ፈርኒቸር መምረጥ ለጤናዎ የማይተካ ሚና አለው።ምቹ የሆኑ ፈርኒቸሮን  መጠቀም ከሚሰጡን ጠቀሜታዎች መካካል በከፊል ለማየት ያህል፡-

አካላዊ ምቾት

ብዙ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ በሰዎች ምክር ለቤታቸው ወይንም ለመስሪያ ቦታቸው የፈርኒቸር ምርጫ ሲያደርጉ ይታያል።ነገር ግን ለእርሶ ምቾትን የሚጨምሩ እና ለቤቶ ውበት የሚያጎናፅፉ የፈርኒቸር ምርቶችን መጠቀም ይኖርቦታል።በስራ ቦታ ረዘም ያለ ጊዜ ስለምናሳልፍ ኢርጎኖሚክ ዲዛይን ያላቸውን ወንበሮች መጠቀም ለጀርባ፣ለትክሻ እንዲሁም ለአንገት በሽታዎች የመጋለጥ አጋጣሚን ይቀንሳል።በዋናነት የጀርባ በሽታ ካለብዎ ፤ ዜሮ የመሬት ስበት ያላቸው ወይም የማሳጅ ወንበሮችን መጠቀም ምቾት ይመከራል።

የጭንቅላት መደገፊያ ያላቸው ምቹ ወንበሮች የአንገትና የትክሻ ህመምን ይቀንሳሉ፡፡ ረጅም የስብሰባ ጥሪ ካደረጉ ወይም ለረጅም ጊዜ መጽሃፍትን የሚያነቡ ከሆነ የጭንቅላት መደገፊያ ያላቸውን ወንበሮች በመጠቀም ወደኋላ ማዘንበል መቻል እና ለጭንቅላት(ከአንገት በላይ)  ድጋፍ ማግኘት መቻል ከጭንቅላትዎ እና ከአንገትዎ ላይ የተወሰነውን ጫና ይቀንሳል፡፡ እንደዚህ ዓይነት አጭር ዕረፍቶች ሰውነትዎን ለማደስ እና ቀኑን ሙሉ ሥራውን ያለእንከን ለመቀጠል ያግዛሉ፡፡ጠንካራ ወይም ደረቅ ወንበር መጠቀም በወገብዎ ላይ ጫና ሊያስከትል ሰለሚችል በቂ የመቀመጫ ጥልቀት ያላቸውን ወንበሮች መምረጥ ውጥረትን እና ግፊትን ይቀንሳል። በተገቢ ሁኔታ ወንበሩ ከጉልበቶችዎ ጀርባ ሲለካ ከ 2 እስከ 4 ኢንች የመቀመጫ ጥልቀት ሊኖረው ይገባል፡፡

የማስታዎስ አቅምን ለመጨመር

በቂ  እንቅልፍ ማግኘት ለጤና የማይተካ ሚና አለው። ጥሩ የሆነ እንቅልፍ ለማግኘት እና መልካም የሆነ ሌሊት ለማሳለፍ የምኝታ ክፍልን ማስዋብ እንዲሁም ይህንን ተግባር በተገቢው ሁቤታ ለመወጣት የሚያስችሉ የፈርኒቸር ውጤቶችን መጠቀም ቀዳሚዉ ተግባር መሆን ይኖርበታል።

ስሜትን ለማደስ፤ ሃሴት ለመፍጠር

ከረጅም የሥራ ሰአት በኋላ ወደ ቤትዎ ሲመለሱ ፣ ደስታ ሊርቅዎ እና ብስጩ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ በበቂ ሁኔታ በፈርኒቸር ከተዋበ ቤት  በላይ ስሜትዎን ለማደስ ጉልበት ያለው ነገር  አይኖርም፡፡የቤት ዲዛይን፣ የቀለም እና አጠቃላይ የፈርኒቸር ቅንብር ለድካም ፍቱን መድሃኒት ሲሆን ቤቶን በተገቢው የማስጌጫ ቁሳቁስ የማስጌጥ ዋናው ጥቅም የስሜት ህዋሳትን በመሳብ እርካታን መጨመር ነው፡፡ የፈርኒቸር ውበት እና አስፈላጊነት ከሰው ሰው የሚለያይ ቢሆንም የሚፈለገውን ወበትና ጥቅም ለማግኘት ባለሙያ ማማከር ይመረጣል፡፡ከዚህ ጎን ለጎን ደማቅ ቀለማትን መጠቀምም ለቤት ፍካት፣ጭንቀትን ለማስታገስ እና ምርታማነትን ለመጨመር ይረዳል፡፡

ለበሽታዎች የመጋለጥ እድልዎን ለመቀነስ

የስኳር በሽታ ፣ ከመጠን በላይ ውፍረት ፣ ካንሰር እና የልብና የደም ሥር (cardiovascular) በሽታን ተገቢውን የፈርኒቸር ምርት በመጠቀም መቀነስ እንደሚቻል የዘርፉ ባለሙያዎች የሚናገሩ ሲሆን የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት አንድ ግለሰብ በተቀመጠበት የጊዜ ብዛት ምክንያት በተወሰነ የጊዜ ገደብ ውስጥ የመሞቱ ዕድሉ ከፍተኛ እንደሆነ አረጋግጠዋል፡፡ለምሳሌ  የ 2010 የአውስትራሊያ ጥናት ተሳታፊዎች በየቀኑ ለተቀመጡት ተጨማሪ ሰዓታት በጥናቱ ወቅት (በ 7 ዓመት) ውስጥ የመሞታቸው አጠቃላይ ስጋት በ 11 በመቶ ያደገ ሲሆን በ 2012 በአሜሪካ የተደረገ ጥናት ደግሞ አንድ  ሰው ለረዥም ጊዜ የሚቀመጥበትን ሰዓት በቀን በአማካይ ወደ 3 ሰዓት መቀነሰ ከቻለ ዕድሜው በ 2 ዓመት እንደሚጨምር ያመለክታል ፡፡

የጡንቻ መዛባትን ለመቀነስ

ምቹ የሆነ የመስሪያ ስፍራ፤ የአንድን ሰው አቋም ለማሻሻል ይረዳል፡፡ብዙ ባለሙያዎች በየቀኑ ስምንት ወይም ከዚያ በላይ ሰዓታትን በመቀመጥ የሚያሳልፉ ሲሆን በተለይም  ለረዥም ሰዓታት  ባልተስተካከለ ወንበር ላይ የሚቀመጡ ከሆነ በጤና ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖው ክፍ ያለ ይሆናል፡፡ከሥራ ጋር ተያያዥነት ያላቸው የጡንቻ መዛባት (ኤም.ኤስ.ዲ) በጣም በተደጋጋሚ በሥራ ጊዜ  ከሚከሰቱ ጉዳቶች መካከል በዋናነት የሚጠቀስ ሲሆን እ.ኤ.አ. በ 2013 የኤም.ኤስ.ዲ ጉዳቶች  ሰራተኞች ከሚደርስባቸው ጉዳቶች 33% ሸፍነው የነበረ ሲሆን ይህንን ለመቀነስም የተለያዩ  ትላልቅ የግል እና የመንግስት መስሪያ ቤቶች የተስተካከለ  የቢሮ ኢርጎኖሚክስ  በማመቻቸት የሰራተኞቻቸውን ደህንነት ማስጠበቅ ችለዋል፡፡

Pin It on Pinterest

Share This