የቤትዎን ውበት የማሻሻል እቅድ ካለዎ ምግብ ማብሰያ ቦታን ማዘመን አንዱ እና አስፈላጊው ነገር ነው። ብዙ ጊዜ ምግብ ማብሰያ ቦታን ስናዘምን አይታይም፤ ነገር ግን  ምግብ ለማዘጋጀት፣አልፎ አልፎም ለመመገብ እንዲሁም ተዛማጅ ስራዎችን ለመስራት ብዙ ሰአት ምግብ ማብሰያ ስፍራ ውስጥ መቆየታችን  አይቀሬ ነው።ምግብ ማብሰያ ቦታን ማዘመን ከቻልን ምግብ ከማዘጋጀት በላይ አስደሳች ጊዜ ለማሳለፍ እና ቤታችንን ውብ ለማድረግ ይረዳናል።ምግብ ማብሰያ ስፍራን ማዘመን የሚሰጥውን ጠቀሜታ እንመልከት፦

የተሻለ አገልግሎት

የምግብ ማብሰያ ስፍራን ስናዘምን ከመናገኘው ጥቅም አንዱ ፤ የክፍሉን ግልጋሎት ማሻሻል በዋናነት ይጠቀሳል።በጥንቃቄ የታቀደ ወይም ዲዛይን የተደረገ እና የተዋቀረ የምግብ ማብሰያ ስፍራ ለብዙ አገልግሎት ሊውል ይችላል። በማብስያ ቁሳቁሶች መካከል በቂ ክፍተት መፍጠር ደግሞ ምግብ የማዘጋጀት ሂደቱን  ምቹ እና ቀልጣፋ ያደርገዋል ፡፡ ምግብ የሚዘጋጅባቸው ቦታዎች ምግብ ከማዘጋጀት በተጨማሪ ቤተሰብ፣እንግዶች እና ወዳጆቻችን ብዙ ሰአት የሚቆዩበትን እድል ከመፍጠር ባለፈ ምቾትን እና ደስታን የመስጠት አቅም አላቸው፡

ሃይልን ለመቆጠብ

ምድጃን እና ፍሪጅን አራርቆ ማስቀመጡ ብዙ ሰዎች በአንድ ጊዜ ለመጠቀም እንዲችሉ ያደርጋል ፡፡ ፍሪጅ ከምድጃ ርቆ ሲቀመጥ ምድጃው ሙቀትን በማመጣጠን ከፍተኛ መጠን ያለው ኃይል ለመቆጠብ ያግዛል። ስማርት ትራክ መብራት እና ኤል.ኢ.ዲ አምፖሎች ከመደበኛ አምፖሎች ጋር ሲነጻጸሩ 80% የበለጠ ቀልጣፋ ስለሆኑ እነሱን መጠቀም በተሻለ ሁኔታ የኤሌክትሪክ ሃይልን  ለመቆጠብ ይረዳል ለዚህም በማብሰያ  ስፍራ መካከል በቂ ክፍተት እንዲኖር ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

በቀላሉ ለማጽዳት

የተዝረከረከ የማብሰያ  ስፍራ ፤ በምግብ እና በምግብ መያዣዎች የተሞላ ፍሪጅ ወይም ማቀዝቀዣ ለማፅዳት ከባድ ነው ፡፡ የዘመኑ እና በአግባቡ የተዋቀሩ የማብሰያ  ስፍራዎች  እንዲኖር ማድረግ ከምንጣፍ ጀምሮ የተለያዩ  ቁሳቁሶችን ለማጽዳት አመቺ ያደርገዋል።

የጥገና ወጭ ለመቀነስ

በጥንቃቄ  ዲዛይን የተደረገ እና ለእያንዳንዱ ነገር ትኩረት የተሰጠው የማብሰያ  ስፍራ ሁል ጊዜ የሚያስፈልገው ጥገና አነስተኛ ነው ፡፡ አዲስ እና ልዩ  ቁሳቁሶችን ለመጠቀም እና ለመጨመር ስናስብ ትኩረታች አነስተኛ ጥገና የሚያስፈልጋቸው መሆናቸውን ማረጋገጥ መሆን አለበት ፡፡ ይህ ጊዜን፣ ጉልበትን እና ገንዘብን ይቆጥባል ፡፡የሚጠይቀውን የጥገና ወጪ አነስተኛ ለማድረግ  የወለል ንጣፉ ውሃን ፣ ቆሻሻን እና ጭረትን የሚቋቋም እንዲሁም በጣም ጠንካራ መሆን ይኖርበታል ፤ይህም ለጽዳት የሚጠፋውን ጊዜ ይቀንሳል።

Pin It on Pinterest

Share This