ጅማሮ፦ የታሪክ ባለሙያዎች ፈርኒቸር በእድሜ የታሪክ እኩያ ነው ይሉናል፡፡ የመጀመሪያው አልጋ ጢሻ ፣የመጀመሪያው ወንበር ግንዱ የተቆረጠ የዛፍ ጉቶ እንዱሁም የመጀመሪያው ጠረጴዛ ጠፍጠፍ ብሎ የተገኘ ድንጋይ ናቸው የሚል ሃሳብ ያቀርባሉ፡፡ በንድፈ ሃሳብ መቅረጽ ከተጀመረ ደግሞ 30,000(ሰላሳ ሺህ አመት) ገደማ ሞልቶታል ይሉናል የቅርስ ባለሙያዎች፡፡ ለዚህም እንደማስረጃነት የሚጠቀሰው ’ቬነስ ፉጉሪን (venus figurin)’ የተሰኘው በሩሲያ ዉስጥ የተገኘው ቅርጽ ሲሆን በቅርጹ ወንበር ሊይ የተቀመጠች ሴት ጣኦት (goddess) ትታያለች በላይኛው ፓል ኦቲክ ዘመን 30,000 ሰላሳ ሺህ ዓ.ዓ(አመተ ዓለም) እንደተሰራ በምርምር የተረጋገጠው ይህ ቅርጽ ከ28,000 እስከ 32,000 አመት እድሜ አስቆጥሯል፡፡የቬነስ ፉጉሪን ቅርጾች የተለያየ መጠን ያላቸው ቢሆኑም በቅርጾቹ በዛን ዘመን የነበረ እውነታን በጥበብ ለመግለፅ  የተደረገ ሙከራ በመሆኑ በላይኛው ፓልኦቲክ ዘመን የፈርኒቸር ንድፍ አውጪ እና ቀራጺያን ነበሩ ወደሚል ድምዳሜ ያስጉዘናል፡፡ ምንም እንኳን ቅርጾቹን ለመስራት ጥቅም ሊይ የዋለውን  ጥሬ ቁስ ለማወቅ አዲጋች ቢሆንም፡፡

ቀጣዩ መዲረሻችን በኦርከኒይ ስኮትላንድ ጥንታዊ መንደር ይሆናል፤ በዚህ ከ3200-2500ዓ.ዓ አካባቢ የታነጸ ጥንታዊ መንደር ውስጥ ስሪታቸው ከድንጋይ የሆኑ ቁም ሳጥን፣ ኮመዲኖ እና አልጋዎች የተገኙ ሲሆን በጠጨማሪም  የፈርኒቸሮቹን ቁስ አካል ማግኘት ተችሏል፡፡እዚህ ቅርጹን ብዙም ሳይለውጥ ተጠብቆ የቆየ ጥንታዊ መንደር ውስጥ ሰባት ትውልዶች እንደኖሩበት በቅርቡ የተደረገ ጥናት ያስረዳል፡፡ ለፈርኒቸር መስሪያነት ከድንጋይ የተሻለ ቁስ እንዳለ የተረዱ ሀዝቦችም አልጠፉም፤ በጥንታዊ ግብፅ የመጀመሪያው ስርወ መንግስት 3200ዓ.ዓ(ዓመተ ዓለም) ወዲህ ከእንጨት የተሰሩ የቤት ውስጥ እቃዎች በግብጻውያኑ መቃብር ውስጥ የተገኙ ሲሆን ጥንታዊያን ግብፆች እንጨትን ከቆዳ፣ ወርቅ፣ ብር፣ ኢቦኒይ ከተባለጥቁር እንጨት እንዱሁም ከዝሆን ጥርስ በማጣመር ወንበር እና አልጋ የመሳሰለትን መገልገያዎች በግሩም ሁኔታ ቀርጸው ይጠቀሙ እንደነበር ከእነዚህ ቅርጾች ለመረዳት ተችሏል፡፡ትውልድ እንዲማርበት እና ለምርምር እንዲጠቀምበትም በሙዚየም ውስጥ ለእይታ ክፍት ተደርገው ተቀምጠዋል፡፡እንዲህ እያለ ውልደቱን ያገኘው የፈርኒቸር ጥበብ በጥንታውያን ሮማውያን እና ጥንታዊያን ግሪኮች ትኩረቱ ከውበት ወደ ምቾትአዙሮ ይሰራ ነበር፡፡ኩሩል ሲት በጥንታዊ ሮም ውስጥ የተሰራ የእንግለዘኛዋን ኤክስ (x)ቅርጽ የመሰለ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ምልክት የሆነ መቀመጫ ሲሆን ታስቦበት ረጅም ሰአት ለመቀመጥ እንዲይመች ተደርጎ ለተሿሚዎች የተሰራ ወንበር እናገኛለን፡፡ ለምን?

   የመጀመሪያው ተሿሚው ብዙ ጊዜውን ወንበር ሊይ ተቀምጦ በስንፍና እያሳለፈ ስራ እና ህዝቡን እንዳይበድል ሲሆን ሌላኛው  ምክንያት ስልጣኑ ጊዜያዊ እንደሆነ እና ባለው ጊዜ አቅሙን አውጥቶ እንዲሰራ ለማስገንዘብ ነው፡፡

ከአዝጋሚ ለውጥ በሗላ በተለይ በ 15ኛው እና 16ኛው ክፍለ ዘመን የጣሊያን ህዳሴ ዘመን በባለጸጋው የማሕበረሰብ ክፍል እያደገ የመጣው የጥበብ ፍቅር የፈርኒቸር ጥበብ እንደ አዲስ እንዲያንሰራራ ምክንያት ሆኖታል:: በተለይ የዚህ ዘመን ንድፍ አውጪዎች (architects) እንጨትን በጋለ ብረት ወይም በጋለ አሸዋ በመለብለብ እና ፈሳሽ ዘይት በመቀባት የሚሰሩትን “ኢንትራሽያ (intracia)” እና “ፕይትራ-ደራ (pietra-dura)” የተሰኙ የማስዋቢያ ዘዴ ይጠቀሙ ነበር፡፡ፈርኒቸርን ካነሳን የቀደሙትን የ12ኛው ክፍለ ዘመን የፈርኒቸር አሰራር ዘይቤን በዘመኑ ከደረሱበት ዘይቤ በማጣመር ለፈርኒቸር እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረከቱትን የ 19ኛው ክፍለ ዘመን ንድፍ አውጪዎችን አለማመስገን ከባድ ነው፡፡

በሃገራችን:- በሃገራችን ኢትዮጵያ የፈርኒቸር ታሪክ በአክሱም ስልጣኔ ዘመን እንደተጀመረ ሳምያ አህመዴ የተባለች ግለሰብ “Material usage in the history of furniture design in Ethiopia” በሚለው ጥናታዊ ጽሁፏ አስፍራለች ፡፡ ሃገራችን ብዙ-ብሔረሰብ ያላት በመሆኑ እነዚህ የተለያየ የአኗኗር ዘይቤ ያላቸው የማሕበረሰብ ክፍሎች የሚጠቀሟቸው የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶች የዛኑ ያህል የተለያዩ ናቸው፡፡ ይህንን ጥበብ በትምህርት በእና ቴክኖሎጂ በመደገፍ እንዲሁም  ፈጠራን በማከል ትልቅ አቅም መፍጠር ይቻላል፡፡

በ 20ኛው ክፍለ ዘመን የቴክኖሎጂ ማንሰራራትን ተከትሎ የፈርኒቸር ንድፈ ሃሳብ በኮምፒውተር በመታገዝ መሰራት የጀመረበት ጊዜ ነው ምርቶቹም እቃን እና ሰውን ከማስቀመጥ የዘለለ አገልግሎት መስጠት እንደሚችሉ የተረዳንበት ወቅትም ነው፤ ለአብነት ያህል አልጋ ከመኝታነት ወንበርም ከመቀመጫነት አልፈው የተለያዩ ምርምሮች እየተደረጉ ምቹ እና ለጤና ተስማሚ ለማድረግ ሲሞከር ነበር፡፡ እንዱሁም ቁም ሳጥን እና ኮመዲኖም ከቁሳቁስ ማስቀመጫነት ልቀው የቴክኖሎጂ ጥግ ማሳያ ሲሆኑ ተመልክተናል፡፡

አሁን:- አሁን አሁን ፈርኒቸር ሲባል ቀድሞ አእምሯችን ሊይ የሚመጣው ነገር ቦታ ነው፡፡ የሰው ቁጥር መብዛት እና የኢኮኖሚ ውስንነት ያመጣው ተጠጋግቶ የመኖር ባህል የቦታ መጣበብን እያስከተለ ነው፡፡ ባለሙያዎች ለዚህም ቢሆን መፍትሔ አላጡለትም ውበትን፤ ጥራትን፣ እድሜን እና ቦታ ቆጣቢነትን አጣምረው የያዙ የፈርኒቸር ምርቶችን በዘመናችን እየተመለከትን እንገኛለን ፤ለዚህም ተጠቃሽ የሚሆነው በርእሳችን ላይ የሰፈረው ግድግዳ ላይ ተለጣፊውን  አልጋ ማንሳት ይቻላል፡፡ ይህ አልጋ እንደማንኛውም አልጋ ሲሆን ለየት የሚያደርገው ግን ቦታችንን ሰፋ ማድረግ  በምንፈልግበት ጊዜ ከመሬት አንስትን ግድግዳ ላይ በተዘጋጀው ማስቀመጫ ዉስጥ ማስቀመጥ ስለሚያስችለን ነው፡፡ አንዳንዶቹ ተለጣፊ አልጋዎች ሁለት ገጽታ አላቸው ለምሳሌ መጽሀፍ መደርደሪያ ሆኖ ጀርባው ሲታጠፈ አልጋ የሚሆነውን ምርት ማንሳት ይቻላል፡፡

አሳሳቢ እየሆነ ከመጣው የቦታ ውስንነት እና እያደገ ከመጣው ቴክኖሎጂን የመጠቀም ባህላችን አንጻር ወደፊት የሚሰሩትት የ ፈርኒቸር ንድፈ ሀሳቦች ብዙውን በአንዴ እና ከሰው ሃይል ውጪ የሚንቀሳቀሱ ይሆናሉ የሚል ግምት አለ፡፡ እነዚህ ስራዎች ጅማሮ ላይ ናቸው ብንልም ስሕተት አይሆንም ለአብነት ያህሌ ታጣፊ አልጋ፣ ቡፌን እና ወንበርን በአንድ ላይ አጣምሮ የያዘውን ምርት እና በሪሞት መቆጣጠሪያ መጠኑን  ማሳደግ እና መቀነስ የሚቻለውን ጠረጴዛን መጥቀስ ይቻላል፡፡

ነገር ግን እነዚህ ምርቶች በዋጋቸው ውድነት ምክንያት ለሰፊው ማህበረሰብ መድረስ አልተቻለም፤ ለምሳሌ አንድ ባለ ሪሞቱን ታጣፉ አልጋ ለመግዛት ካሻዎት ከ100,000-150,000ISK ወይንም የኢትዮጵያ (26,250- 35,000)ብር መክፈል ይጠበቅቦታል ዋጋው አቅም ላለው የሚቻል ቢሆንም ምርቶቹ እጅጉን የሚያስፈልጉት በዝቅተኛ ኑሮ ላለ ማህበረሰብ ከመሆኑ አንጻር ግቡን መቷል ለማለት ያዳግታል፡፡

ስጋት:-እንደሚታወቀው ፈርኒቸርን ለመስራት በብዛት አገልግሎት ላይ የሚውለው እንጨት ሲሆን ይህም በቀጥታ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ለአብነት  ያህል በአመት 15.3 ቢሊየን ዛፍች እንደሚቆረጡ በቅርቡ የተደረገው የሞግቤይ ጥናት ያሳያል ምን::ያህለ ለፈርኒቸር እንደዋለ ትክክለኛ ቁጥር ማግኘት አዲጋች ቢሆንም 10 ፕርሰንት ብለን የግሌ ግምት ብንወስድ እንኳን በአመት 1.53 ቢሊዮን ለፈርኒቸር ይውላል ማለት ነው፡፡

ማጠቃለያ:- ለመሰረታዊ አገልግሎት ሲውል የነበረው የፈርኒቸር ስራ አሁን ላይ ከኑሮዋችን ጋር በእጅጉ ተቆራኝቶ ለችግሮቻችን መፍትሄ ይዞ እስከ መምጣት እና አኗኗራችንን እስከመቅረጽ ደርሧል፡፡ ሳሎን፣ጓዳ፣ ካፌ፣ የስራ ቦታ፣ መኪና፣ አውሮፕላን፣ ሙዚየም፣ ጥበብ ማሳያ (art gallery )፣ ሆስፒታል ወዘተርፈ የፈርኒቸር ምርቶች በእያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን ከአካባቢያችን አይታጡም፡፡ ታዲያ ይህ የጥንቱን ሰው ከዘመናዊው ሰው ያስተሳሰረው የጥበብ ድልድይ የ ብዝሀ-ህይወት ጉዳትና የአካባቢ መራቆትን እንዳያስከትል ሁሉም ሰው እፅዋትን በየጊዜው መትከል እና መንከባከብን ይኖርበታል፡፡

Pin It on Pinterest

Share This