ቤት ማስዋብ ከወለል ምንጣፍ አመራረጥ ጀምሮ እስከ ፈርኒቸሮች አቀማመጥ ድረስ  ያለውን ጊዜ የሚወስድ እና አድካሚ የሆነ ሂደትን ያጠቃልላል፡፡ ምርጫዎ ምንም ይሁን ምን ቤቶን ምቹ እና ማራኪ  ለማድረግ የተለያዩ የቀለም፣ የፈርኒቸር  እና የቤት እቃዎች አቀማመጥ ዘዴዎችን መጠቀም አማራጭ የሌለው ሆኖ ተገኝቷል፡፡ስለዚህ ‹‹እርስዎ የሚወዱትን የቤት ዲዛይን  እንዴት መፍጠር አለቦት?›› የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ምን አይነት ምልክ እና ገፅታ እንዲኖረው እንደሚፈልጉ በማቀድና በመወሰን መጀመር ይገባል፡፡ተከታዩ ሂደት የታቀደውን ሀሳብ ተግባራዊ ለማድረግ የሚረዶትን  ቁሳቁስ  መምረጥ ይሆናል፡፡ ስስ( ነጣ ያሉ ) ቀለም  የሚጠቀሙ የእንጨት ውጤቶች የመረጋጋት መንፈስ ሲፈጥሩ በአንፃሩ የቀለም ሁኔታቸው ደማቅ የሆኑ የእንጨት ውጤቶች  ዓይንን የመግዛትና ለቤቱ ግዝፈት የመስጠት ጠቀሜታ አላቸው፤በተጨማሪም ጎላ ያለ የወለል ንጣፍም ከመብራት አጠቃቀም ጋር ተደምሮ  የቤቱን ብሩህነትና ማራኪነት ይጨምራል፡፡የተለያዩ የስነ-ጥበብ ውጤቶች ማለትም ሥዕል፣ ቅርፃ ቅርፆች፣ሀገር በቀል የዕደጥበብ ውጤቶች የቤቶን ውበት ለመጨመር ጉልህ ሚና ይጫወታሉ፡፡ለቤቶ ውበት የሚያጎናፅፉ ጌጣጌጦች  የእርሶን ማንነት የመግለጽ አቅም ስላላቸው በአመራረጥ ላይ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡

  የአበባ መስቀመጫ

የእፅዋት ማስቀመጫን ከ5000 ዓመታት በፊት ለመድሀኒት ማስቀመጫነት፤ለዘይትና ለውሀ ማጠራቀሚያነት መጠቀም እንደተጀመረ ጥናቶች ያመለክታሉ፤እጽዋት እና የእፅዋት ማስቀመጫዎች በብልሀት ጥቅም ላይ ከዋሉ ለቤት ልዩ ውበት ያጎናፅፋሉ፡፡ይህንንም ለመጠቀም የተለያዩ እፅዋትን እና የእጽዋት ማስቀመጫ  ቁሳቁሶችን በየጊዜው እየቀያሩ መጠቀም  ቤቱ ሁል ጊዜ አዲስ ገፅታ እንዲኖረው ደርጋል፤ስለዚህ ሁልጊዜ  የተለመደና አንድ አይነት ማስቀመጫዎችን ከመጠቀም ይልቅ በተለያየ አይነት እና ዲዛይን የተሰሩ የእፅዋት ማስቀመጫዎችን በየጊዜው እየቀያየሩ መጠቀም ይመከራል፡፡   

 ሥዕል

ስዕሎች፣ቅርፃ ቅርጾች እንዲሁም  የተለያዩ የእደ ጥበባት ውጤቶች ከተለመዱት እና ሁለገብ ከሆኑት የቤት መገልገያዎች ውስጥ ይመደባሉ፡፡ ስነ-ጥበብን ልዩ ከሚያደርጉት  ነገሮች ዋነኛው በተለያዩ ቀለማትና ጌጣጌጦች ያጌጡ ልዩ መስህብ  ማግኘት መቻሉ እና  ከቤትዎ ገፅታ ጋር የሚስማማ  ውበት መፍጠር መቻላቸው ነው፡፡ስለዚህ የስነ-ጥበብ ውጤቶችን ለቤት ውበት መጠቀም መቻል ትልቅ ብልህነት ነው፡፡

የቤት ውስጥ እጽዋት

የቤት ውስጥ እጽዋት ጥሩ ሆነው የሚታዩ ብቻ ሳይሆኑ ጥሩ የቤት ውስጥ መስጌጫዎች ጭምርም ናቸው፡፡ጥናቶች እንደሚያሳዩት እጽዋት ካርቦን ዳይኦክሳይድን ከአየር ላይ አውጥተው ወደ ኦክስጂን መለወጥ ብቻ ሳይሆን እንደ ፖሊቲኢሌንየስ እና ፎርማለዳይድ የመሳሰሉ ጎጂ ኬሚካሎችን የመቀነስ አቅም አላቸው፡፡እነዚህ ኬሚካሎች በተፈጥሯቸው በቤት ውስጥ ጥቅም ላይ በሚውሉ በርካታ የቤት መገልገያዎች፣ወለል እና ቀለማት ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ከመተንፈሻ አካላትና ከሌሎች ህመሞች ጋር ይያያዛሉ፡፡ጥናቶች እንደሚያሳዩት እፅዋት ውጥረትን ሊቀንሱ ፣ ስሜትን ሊያሻሽሉ እና የበለጠ የፈጠራ ስሜት እንዲሰማን ሊያደርጉን ይችላሉ ፡፡ በቅርቡ በተደረገ ጥናት በቢሮአቸው ውስጥ እፅዋትን የሚጠቀሙ ሰዎች እፅዋት ከማይጠቀሙ በአራት እጥፍ ዝቅ ያለ አማካይ የደም ግፊት ነበራቸው ፡፡ተጨማሪ ጥናትም እንዳመለከተው ሰዎች በተክሎች በተጌጡ አካባቢዎች ሲሰሩ የበለጠ የተሻሉ ሀሳቦችን ማፍለቅ ይችላሉ ስለዚህ እፅዋትን በሚመርጡበት ጊዜ  ከቤቶ አጠቃላይ ገፅታ ጋር የሚጣጣም ቢመርጡ ይመረጣል፡፡

Pin It on Pinterest

Share This