የቤት ውስጥ ክፍሎችን ዲዛይን ሲያደርጉ ጊዜ የሚወስደው እና ትልቁ ተግዳሮት ሊሆን የሚችለው የተለያዩ ቀለማትን እንዲሁም ቁሳቁሶችን በማጣመር  ተገቢውን  የዲዛይን ውበት እንዴት ማምጣት እንደሚቻል ማሰብ ላይ ነው፡፡ቤት ሲያስጌጡ አስፈላጊ ነው የሚሉትን ዘይቤ ለመምረጥ እንዲሁም ለእያንዳንዱ ክፍል ልዩ ገፅታ ለመፍጠር ማሰብ አልፎ ተርፎም ባለሙያ ማማከር ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ይህም በይበልጥ ለትናንሽ ክፍሎች ሲሆን አስፋላጊነቱ የጎላ ይሆናል፡፡

ክፍሎችዎን ዲዛይን ከማድረጎ በፊት ከግምት ማስገባት ያለቦት ነጥቦች

ባለሙያ ማማከር

እያንዳንዱ ክፍል ከክፍሉ ጋር ተስማሚ ከሆኑት ቁሳቁሶች ጋር  በጥሩ ሁኔታ ተጣምሮ መታየት ይኖርበታል ይህ እንዲሆን ጎልቶ እንዲታይ የታሰበው የየክፍሉ  ዲዛይን  ከቤቱ አጠቃላይ  የንድፍ አሰራር ጋር ተመሳሳይ ወይም አብሮ የሚሄድ እና የሌሎቹን ክፍሎች ውበት የማያደበዝዝ መሆን አለበት፡፡ሁሉንም ቁሳቁሶች(ጌጣጌጦች፣የተለያዩ የፈርኒቸር ውጤቶች፣መብራቶች) በአንድ ክፍል ከማስቀመጥ ይልቅ እያንዳንዱ ክፍል እንዲኖረው የሚፈለገው መልክ(ሥዕል) ቀድሞ መታሰብ እና መጤን አለበት፡፡ይህም አስፈላጊ እና ክክፍሉ መዋቅር ጋር አብሮ የሚሄዱት ቁሳቁሶች፣ቀለማት፣ጌጣጌጦች ብቻ ተመርጠው እንዲለዩ ያደርጋል፡፡ የክፍሎቹ አገልግሎት እንደዚሁ የየክፍሎቹን ንድፍ ይወስናል፡፡ከባለሙያ ጋር አብሮ መስራት እያንዳንዱ ዝርዝር ሁኔታ በጥልቀት የታሰበበት እንዲሆን እና የታሰበው እቅድ ከግብ እንዲደርስ ያደርጋል፡፡

ለአነስተኛ ክፍሎችን ልዩ ትኩረት ማድረግ

አነስተኛ ክፍሎችን ዲዛይን ማድረግ የተለየ ፈታኝ ሁኔታን ይዞ መምጣቱ አይቀርም ምክንያቱም ክፍሉ አስፈላጊ እና መቅረት የለባቸውም የምንላቸውን ቁሳቁሶች ማካተት ሊኖርበት ስለሚችል ነው፡፡ስለዚህ በባለሙያ በመታገዝ  ክፍሉ ጥሩ ሆኖ እንዲታይ  ማድረግ ይቻላል፡፡የቦታ አጠቃቀም ክህሎትም አነስተኛ ክፍሎችን ለማስዋብ አይነተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ለክፍሉ ልዩ ውበት የሚያላብሱ ከክፍሉ ስፋት ጋር ሊሄዱ የሚችሉ(ቢቻል በትእዛዝ የሚሰሩ የፈርኒቸር ውጤቶች ቢሆኑ ይመረጣል) የፈርኒቸር ውጤቶችን መጠቀም ቢቻል  ያለውን ቦታ በተገቢው ከመጠቀም አልፎ  ልዩ ውበት ሊያጎናፅፈው ይችላል፡፡በዚህ ረገድ ሀሮት ፈርኒቸር የእርሶን ፍላጎት ያማከሉ የፈርኒቸር ውጤቶቸን በተማጣጣኝ ዋጋ አቅርቦላችኋል፡፡

የቀለም ምርጫን ማስተካከል

የምንመርጠው የቀለም አይነት  ቢቻል ከቤቱ አጠቃላይ ገፅታ ጋር ቢመሳሰል ይመረጣል በአነስተኛ ክፍሎች ውስጥ ቀለል ያሉ የቀለም አይነቶችን(ደብዘዝ ያላለ) መጠቀም ቢቻል ጥሩ ነው፡፡ ትክክለኛውን ቀለም በሚመርጡበት ጊዜ ክፍሉ የሚውልበትን አላማም ከግምት ማስገባት  እንዲሁ ትልቅ  ሚና ይጫወታል፡፡

Pin It on Pinterest

Share This