የፀሐይ ብርሀን የቤትን ገፅታ ብሩህ ለማድረግ ትልቅ ሚና ይጫወታል ነገር ግን የፀሐይ ብርሀን ቤትን ብሩህ ለማድረግ የግዴታ  አስፈላጊ ላይሆን ይችላል፡፡ቤቶ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ክፍሎችን ብሩህ  ለማድረግ የተለያዩ መንገዶች ሲኖሩ ከነዚህ መካከል የተወሰኑት

በነጭ ቀለም ያጌጡ ቁሳቁሶችን መጠቀም

ነጭ ቀለም በተፈጥሮው ነገሮችን ቀላል እና ብሩህ አድርጎ የማሳየት አቅም አለው፡፡ይህንን የተፈጥሮ ስጦታ እንደመጠቀም ቀላል እና አመቺ ነገር ፈልጎ ማግኘት ከባድ ሊሆን ይችላል፡፡አብዛኛውን ጊዜ የቤት ውስጥ ቀለሞች ነጭ እንዲሆኑ የሚፈለጉትም በዚህ ምክንያት ነው፡፡የመፅሀፍ መደርደሪያዎች ፣ጠረጴዛዎች ፣መጋረጃዎች እንዲሁም ሌሎች የቤት ውበትን እና ብሩህነትን ሊጨምሩ የሚችሉ ቁሳቁሶች ነጭ ቀለም ቢኖራቸው ይመረጣል ምክንያቱም ከነጭ ቀለም ወጣ ያሉት አብዛኛዎቹ የቀለም አይነቶች ለዓይን የመክበድ ባህሪ ስላላቸው ነው፡፡

ረዣዥም እቃዎችን ከመስኮት አከባቢ ማራቅ

በቤት ውስጥ የምንገለገልባቸው ነገር ግን ወደ ቤት ውስጥ የሚገባውን የተፈጥሮ ብርሀን ሊያግዱ የሚችሉ ቁሳቁሶችን መቀነስ ካልተቻለም ቦታ መቀየር አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው ለምሳሌ የተለያዩ እጽዋት፣ የመጽሀፍት መደርደሪያዎች ለመስኮት ቅርብ ባይሆኑ ይመረጣል፡፡ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች ብርሀንን በመቀነስ ቤቱ ደብዛዛ እንዲሆን የማድረግ አቅም አላቸው፡፡

መስታወት መጠቀም

መስታወት መጠቀም አንድን ክፍል  የበለጠ ትልቅ እንዲመስል እንዲሁም ወደ ቤት ውስጥ የሚገባውን ብርሀን በማንጸባረቅ እና ተጨማሪ ውበት በማጎናጸፍ አይነተኛ ሚና ይጫወታል፡፡

የቀለም ምርጫን ማስተካከል

የቤት ቀለም የአንድን ቤት ነባራዊ ሁኔታ ሙሉ ለሙሉ የመለወጥ አቅም አለው፡፡ ስለሆነም የቤትን ውበትና ብሩህነት ለመጨመር የቀለም ምርጫ በደንብ ሊታሰብበት ይገባል፡፡ከዚህ በተጨማሪ የተለያዩ እጽዋትን መጠቀምም የቤትን ፍካት ይጨምራል፡፡

Pin It on Pinterest

Share This