ለየትኛውንም መኖሪያ ቤት ውበትን ከሚያጎናፅፉ ነገሮች መካከል የቤት ውስጥ ወንበሮች፣ሶፋዎች፣ጠረጴዎች ከአመራረጣቸው ጀምሮ እስከ አቀማመጣቸው ድረስ ትልቅ ተፅእኖ አላቸው፡፡በ 2013 ዓ.ም በቤትዎ ውስጥ ያሉ የተለያዩ ክፍሎችን ለማሳመር እና ለማዘመን እቅዱ ካሎት ቤቶን ለማስዋብ የቤት ማስዋቢያ ቁሳቁሶች፣ፈርኒቸሮች ትልቅ ጠቀሜታ አላቸው፡፡ እነዚህን ቁሳቁሶች እና ፈርኒቸሮች መምረጥ ጥንቃቄ እና ብልሀት የሚፈልግ ሲሆን የሚፈልጉትን አይነት ውበት ቤትዎ እንዲኖረው ከፈለጉ ከታች የቀረቡትን ጠቃሚ ምክሮች ቢተገብሩ መልካም ነው፡፡


   የክፍሎችን ስፋት ከግምት ያስገቡ

የቤት ውስጥ ዲዛይንን ለማስዋብ የመጀመሪያው ነጥብ እቅድ ማውጣት ነው፡፡እያንዳንዱ ቤት ውስጥ የሉት የተለያዩ ክፍሎች የየራሳቸው ተግባር አላቸው ስለዚህ የሚመርጧቸው የፈርኒቸር  አይነቶች  የየክፍሉን አገልግሎት ባማከለ መልኩ ቢሆን የቤቶን ውበት ለመጨመር አይነተኛ ጥቅም ይሰጣል፡፡ ቤቱ ሊኖረው የተፈለገው ውበት ምን አይነት ነው፣የወንበሮቹ አቀማመጥ እንዴት መሆን አለበት፣ የምንጠቀማቸው የቤት ውስጥ ቀለማት ምን አይነት መሆን አለባቸው፣የተለያዩ ጌጣጌጦች የት ቦታ መቀመጥ አለባቸው የሚለው ቀድሞ ቅድመ ዝግጅት መደረግ አለበት፡፡ስለዚህ ይህ የመጀመሪያው የእቅድ አወጣጥ ሂደት የክፍሉን ስፋት ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚመርጣቸው ፈርኒቸሮች መጠን ከክፍሉ ስፋት ጋር አብሮ መዛመድ አለበት፡ አለበለዚያ ክፍሉ የተጨናነቀ እንዲሆን ወይም ብዙ ሰፊ ቦታ እንዲተርፍ እና የቦታ ብክነት እንዲፈጠር ሊያደርግ ይችላል፡፡ ስለዚህ ለእያንዳንዱ ክፍል የሚያስፈልገው የፈርኒቸር መጠን የየክፍሉን ስፋት ከግምት ውስጥ በማስገባት ያሎትን ቦታ በብቃት ለመጠቀም ይረዳዎታል፡፡ ይህም ቀድሞ መጠናት አለበት፡፡

  አንድ ገጽታ ይምረጡ

የቤቶን ውበት ከሚጨምሩ ዓበይት ነገሮች በሁለተኛው ደረጃ ላይ ሊቀመጥ የሚገባው ቤቶ ሊኖረው የሚገባውን ወይም የሚፈለገውን ገፅታ መለየት መቻል ነው፡፡ የመረጡትን የቤት ገፅታ ሊያጎናፅፉ የሚችሉ በተለየያ አይነት እና ቅርፅ የተሰሩ የቤት ውስጥ ቁሳቁሶች አልፎ ተርፎም የተለያዩ ጌጣጌጦች ይኖራሉ፡፡ ለምሳሌ ቤቶ ዘመናዊ ገፅታ እንዲላበስ ከፈለጉ ዘመናዊ ቁሳቁሶችን፣ወንበሮችን፣ እንዲሁም ለቤቶ አይነተኛ ውበት የሚያጎናፅፉ የተለያዩ ቀለማትን ቢጠቀሙ ይመረጣል፡፡

በተቃራኒው ወደ ባህለዊ ነገሮች የሚያዘነብሉ እና ቤቶ ባህለዊ ገፅታ ያስፈልገዋል ብለው ካሰቡ ባህላዊ ቁሳቁሶችን፣ ጌጣጌጦችን፣ ባህላዊ ወንበሮችን (በይበልጥ በአንዳንድ ማህበረሰብ ውስጥ ጥቀም ላይ የሚውሉ ከተለያዩ እፅዋት የሚሰሩ ልዩ ባህላዊ ቁሳቁሶች እና የቤት ውስጥ መገልገያዎች የቤትን ወበት ለመጨመር ትልቅ ዋጋ ይኖራቸዋል ለዚህ አይነተኛ  ምሳሌ ቀርከሀ አንዱ ነው) እና ተፈጥሮአዊ ቀለማትን ቢጠቀሙ የበለጠ ውጤታማ ይሆናሉ፡፡ከፍላጎቶዎ ጋር የሚስማማ እና የእርስዎን ዘይቤ የሚያንፀባርቅ ትክክለኛ የቤት ቁሳቁሶችን፤ እንዲሁም የተለያዩ ጌጣጌጦችን መምረጥ እንዲችሉ ቤቶ እንዲኖረው የሚፈልጉትን ገፅታ ቀድሞ መምረጥ ትኩረቶን በአንድ ነገር ብቻ ላይ እንዲያሳርፉ ይረዳዎታል፡፡

 ተገቢዉን ቁሳቁስ ይግዙ

ቤቶ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ክፍሎችን ስፋት ካወቁ እንዲሁም ቤቶ እንዲኖረው የሚፈልጉትን ገፅታ ከለዩ በኋላ ቀጣዩ እርምጃዎ ለቤቶ ውበት ሊጨምር የሚችል ትክክለኛውን ቁሳቁስ መግዛት ይሆናል፡፡የሚፈልትን ቁሳቁስ ግብይት ፍለጋ ከመጀመሮ በፊት የአኗኗር ዘይቤዎን ከግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርቦታል እንዲሁም የሚገበዩበት ድርጅት የሚያመርታቸውን ምርቶች ጥራት ቀድመው ማወቅ ቢችሉ ጥሩ ነው፤ይህን ማድረጎ ከአላስፈላጊ ወጪ ይታደጎታል፡፡

የእያንዳንዱ ሰው የቤት ውስጥ ቁሳቁሶች ምርጫ ሊለያይ ስለሚችል ወደ ሀሮት ፈርኒቸር ጎራ ቢሉ የእርሶን ፍላጎት ከግንዛቤ ውስጥ ያስገቡ የመመገቢያ ጠረጴዛዎችን፤ ዘመኑ የሚጠይቀውን ጥራት ያሟሉ ሶፋዎችን እንዲሁም ሌሎች ተጨማሪ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ፡፡

Pin It on Pinterest